Paulos Fekadu
Paulos Fekadu
  • 103
  • 499 461
እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 35)
ክርስቶስ በገዛ ደሙ ወደ መቅደስ በመግባቱ ክርስቶስና ደሙ የተነጣጠሉ አድርገን ማሰብ ግን የለብንም። ክርስቶስ ሊቀ ካህንም መሥዋዕትም ነውና። ይህም ከብሉይ ኪዳኑ ጥላ በእጅጉ ይልቃል። ምክንያቱም የብሉይ ኪዳን ጥላዎች ሊቀ ካህናቱ ስለ ሕዝቡ መሥዋዕት ማቅረቡን እንጂ ሊቀ ካህናቱ ራሱን በመሥዋዕትነት ማቅረቡን አይናገሩም። በብሉይ ኪዳን የኀጢአት መሥዋዕት ሲቀርብ፣ ኀጢአተኛውን የሚወክለውና በኀጢአተኛው ምትክ የሚቀርበው የታረደው በግ ወይም ፍየል እንጂ መሥዋዕት አቅራቢው ካህን አይደለም። መሥዋዕቱ ያለ ካህኑ ኀጢአተኛውን ሊወክል በቂ ነው።
ታዲያ የካህኑ ሥራ ምንድን ነው? በብሉይ ኪዳን በስርየት ቀን መሥዋዕት የሚያቀርበው ሊቀ ካህናቱ ነው። መሥዋዕቱ ኀጢአተኛውን ሊወክል በቂ ቢሆንም፣ ካህኑ በሌለበት በጉ ወይም ፍየሉ በመሥዋዕትነት ወደ እግዚአብሔር አይቀርብም። መሥዋዕቱ ራሱን በመሥዋዕትነት ለመሥዋዕት ተቀባዩ ለማቅረብ አይቻለውምና። ሊቀ ካህናቱ መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜም የመሥዋዕቱን ደም በመሠዊያው ላይ በመርጨት ሕዝቡንና ቤተ መቅደሱን (የመገናኛ ድንኳኑን) ከርኩሰት ያነጻል (ዘሌ. 16፥15-19)። በዚህም እግዚአብሔር በኪዳኑ መሠረት ከሕዝቡ ጋር እንዲኖር ለማመቻቸት መሠዊያውን ያበጃጃል። ስለዚህ መሥዋዕቱ ራሱን በራሱ ለእግዚአብሔር ሊያቀርብ አይቻለውም። ያለ ካህን መሥዋዕት የለም።
ይህን በልቡናችን ስንጨብጥ ነው በትእምርቶችና በተምሳሌቶች የታጨቀውን የዕብራውያን መልእክት ጭብጥ የምናስተውለው። በኀጢአተኞች ምትክ መሥዋዕት ሆኖ የቀረበው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እግዚአብሔር አስቀድሞ በመሠዊያው ላይ እንዲደረግ የፈለገው ሁሉ በመስቀሉ ላይ ሆኗል። የኢየሱስ መሥዋዕትነት ለሁሉ ይበቃል። ነገር ግን ይህ መሥዋዕት ለእግዚአብሔር መቅረብ አለበት። እናም በሰማያዊ ስፍራ ይህን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ያቀረበው፣ ደሙን ይዞ ወደ ሰማያዊቱ መቅደስ የገባውም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው (ዕብ. 9፥12)። እንከን የለሹ ካህን፣ እንከን የለሹን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቀረበ። ቅዱሱ ካህን የገዛ ደሙን ይዞ ወደ ቅድስት ገባ። ከሁሉ የሚሻለው ካህን፣ ከሁሉ የተሻለውን መሥዋዕት፣ በምትሻለው መቅደስ ውስጥ አቀረበ። ሊቀ ካህናቱ ኢየሱስ፣ መሥዋዕቱም ኢየሱስ። ምንኛ ድንቅ ነው!
zhlédnutí: 652

Video

ሊቀ ካህናቱ ኢየሱስ (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 34)
zhlédnutí 785Před měsícem
ክህነት፣ ንግሥና እና ነቢይነት በብሉይ ኪዳኗ እስራኤል ውስጥ በኪዳን ሰጪው እግዚአብሔርና በኪዳኑ ሕዝብ መካከል ያለውን ግንኙነት ሲያበጃጁ ኖረዋል። በዚህም ግንኙነት ውስጥ ሊቀ ካህናቱ፣ ንጉሡ እና ነቢዩ የየራሳቸው ተደጋጋፊ ሚና አላቸው። ከእነዚህ ሦስት አገልግሎቶች መካከል የክህነት አገልግሎትን የተለየ ጉልህ ስፍራ እንዲወስድ የሚያደርገው ሁናቴ ግን ተከስቷል። ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ586 ዓመታት ጀምሮ ንጉሣዊው ሥርዐት ከእስራኤል ተመንግሎ ቀረ። ከክርስቶስ ልደት ከ400 ዓመታት አስቀድሞ ደግሞ የነቢያት አገልግሎት እየሟሸሸ መጣ። ከዚያ በኋላ የተጻፉ ሃይማኖታዊ ጽሑፎችም በቅዱሳት መጻሕፍት ዝርዝር ውስጥ አልተካተቱም። ...
የጌታ ኢየሱስ ባሪያዎች (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 33)
zhlédnutí 462Před měsícem
ጌታ ኢየሱስ በደሙ ዋጅቶናልና በዋጋም ገዝቶናልና ባሪያዎቹ ነን። እንዲያውም ድነትን ያገኘነው ጌታ ኢየሱስን በመታዘዝ ነው፤ መጽሐፍ፣ “እርሱን ለሚታዘዙ ሁሉ የዘላለም ድነት ምክንያት ሆነላቸው” ብሏልና (ዕብ. 5፥9፤ አመት)። እዚህ ላይ ሐዋርያትንና ነቢያትን ጨምሮ አማኞች ሁሉ የእግዚአብሔር ባሪያዎች መሆናቸውን ማስታወስ የተገባ ነው። የጌታ መልአክ ሐዋርያው ዮሐንስን፣ “ከአንተ ጋር … ከወንድሞችህም ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ” በማለት ሁላቸውም የእግዚአብሔር ባርያ ስለ መሆናቸው ተናግሯል (ራእ. 19፥10)። መጽሐፍ ቅዱስ በብዙ ቦታዎች ይህን ደጋግሞ ያወሳል። የእግዚአብሔር ልጅ መሆን የእግዚአብሔር ባሪያ ከመሆን ጋር ተቃር የ...
ምን ዐይነት ልጅነት? የልጅነታችን ግብ? (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 32)
zhlédnutí 779Před měsícem
የወልድ የእግዚአብሔር ልጅነት በእርሱና በአብ መካከል ያለውን ልዩ ዐይነት ግንኙነት ያሳያል። በዚህ ዐይነቱ ልጅነት እግዚአብሔር አብ ከኢየሱስ በቀር ሌላ ልጅ የለውም። አንድ አብ ብቻ እንዳለ ሁሉ፣ አንድ ወልድ ብቻ አለ። በዚህ ዐይነቱ አባትነትም እግዚአብሔር ለማንም አባት አይደለም፤ ሌላ ወልድ የለምና። አማኞች የእግዚአብሔር የጸጋ ልጆች ናቸው። . . . ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው፤ እኛም የእግዚአብሔር ልጆች ነን። እርሱና እኛ አንድ ወገን፣ አንድ ቤተ ሰብ ነን። “ሰዎችን የሚቀድሰውና የሚቀደሱት ሰዎች ከአንድ ቤተ ሰብ ናቸው፤ ስለዚህ ኢየሱስ ወንድሞች ብሎ ሊጠራቸው ዐያፍርም” (ዕብ. 2፥11፤ አመት)። ይህ ማለት ግ...
የእግዚአብሔር ልጆች (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 31)
zhlédnutí 781Před 2 měsíci
እግዚአብሔር የሰዎች ሁሉ ፈጣሪ፣ ደጋፊና አኗሪ መሆኑ እውነት ነው። ነገር ግን በክርስቶስ ውስጥ ያልሆነ ሰው እግዚአብሔርን አባቱ አድርጎ መጥራት አይችልም። “የእግዚአብሔር ልጅነት በተፈጥሮአዊ ልደት ወደዚህ ምድር ለገባ ሁሉ የሚበረከት ሁሉን አቀፍ ሹመት አይደለም፤ ሰው ኢየሱስ ክርስቶስን በመከተል የሚቀበለው ልዕለ ተፈጥሮአዊ ስጦታ እንጂ። … የእግዚአብሔርን ልጅነት ያገኘነው ሰው ሆ በመወለድ ሳይሆን፣ ዳግመኛ በመወለድ ነው።” በልጁ በጌታ በኢየሱስ ሞት ከእርሱ ጋር ታርቀው አዲስ ልደትን ላገኙና የመንፈሱ ማደሪያ ለሆኑ ብቻ እንጂ እግዚአብሔር ለሰዎች ሁሉ አባት አይደለም። ሰዎች የእግዚአብሔር ልጅነትን ሥልጣን የሚያገኙት በ...
የእግዚአብሔር ልጅ - መለኮት ማጠቃለያ (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 30)
zhlédnutí 698Před 3 měsíci
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅነት የተለያዩ ገጽታዎች የሚናገርባቸው በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች አሉ። ከእነዚህ መካከል አንዳንዶቹን ነጥለን እያወጣን ስንመረምር ቈይተናል። እነዚህም፣ 1) ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅነቱ ከዘላለምም የሆነ አምላክ፣ 2) ከዳዊት ዘር የመጣ መሲሓዊ ንጉሥ፣ 3) እውነተኛ እስራኤል መሆኑን ያስረዳሉ። የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባባቱ አንዳንዴ በአንዱ ገጽታ ላይ አጽንዖት ያደርጋሉ፤በሌላ ጊዜ ደግሞ ሌሎቹን ገጽታዎች አጣምረው በአንድነት ሲያቀርቡና አንዱን ገጽታ በሌላው ጥላ ሥር ሲያውሉት ይስተዋላልና ሚዛን እንዳንስት ጥንቃቄ ያስፈልጋል። የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሓፊዎቹ መልእክታቸውን በመ...
የእግዚአብሔር ልጅ - መለኮት (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 29)
zhlédnutí 607Před 3 měsíci
ሐዋርያው ዮሐንስ፣ “ከቶውንም እግዚአብሔርን ያየ ማንም የለም፤ ነገር ግን በአብ ዕቅፍ ያለው አንድያ ልጁ የሆነው አምላክ እርሱ ተረከው” ሲል በወንጌሉ መግቢያ ላይ ጽፏል (1፥18፤ አመት)። በዚህ ክፍል “አንድያ ልጅ” ተብሎ የተተረጐመው፣ በግሪክኛው መጽሐፍ ቅዱስ “ሞኖገኔስ ሁዮስ (μονογενὴς υιος)” የተባለው ነው። “ሁዮስ” ልጅ ነው። “ሞኖስ” (μόνος) ማለት “አንድ፣ ብቻ” ማለት ሲሆን፣ “ጌኖስ” (γένος) ደግሞ “ዐይነት፣ መደብ” የሚል ትርጕም አለው። ስለዚህ ከሁለቱ ቃላት ጥምረት የተገኘው “ሞኖገኔስ” የሚለው ቃል “በዐይነቱ የተለየው፣ የተለየ መደብ ያለው፣ ልዩ የሆነው፣ መሳይ የሌለው” (“pertai...
ንጉሥ (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 28)
zhlédnutí 638Před 4 měsíci
ከትንሣኤው በፊት ውጫዊ ገጽታው ሲታይ ተራ ሰው፣ ቤት የለሽ፣ ጓደኛ አልባ፣ ተጽዕ የሚያደርግበት ኀይል የሌለው ምስኪን ይመስላል። ያኔ የእግዚአብሔር ልጅነቱ በውርደትና በዝቅታ የሚታይ ነበር፤ አሁን በትንሣኤው ግን የእግዚአብሔር ልጅነቱ በኀይል ተገለጠ። ስለዚህ ትንሣኤው የእግዚአብሔር ልጅነቱ በኀይል የታወቀበት ወይም በኀይል የእግዚአብሔር ልጅነቱ የተገለጠበት እንጂ ጌታ ኢየሱስ ለመጀመሪያ ጊዜ የእግዚአብሔር ልጅ የሆነበት አይደለም። አሁን ከትንሣኤው በኋላ ጌታችን የሚላገጥበትና የሚፌዝበት ንጉሥ አይደለም። በአህያ ላይ የሚቀመጥ ንጉሥም አይደለም፤ በድል አድራጊ የጦር መሪነት በፈረስ ላይ የሚታይ እንጂ (ራእይ 19፥11)።
እውነተኛ እስራኤል (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 27)
zhlédnutí 904Před 4 měsíci
ኢየሱስ ክርስቶስ በእውነተኛ እስራኤልነቱ የእስራኤልን የእግዚአብሔር ልጅነት ወክሏል። ከዚህም የተነሣ ለእስራኤል የተነገሩ ብዙ ትንቢቶች የተፈጸሙት በእርሱ ሕይወት ነው። የሐዋርያው ማቴዎስም ጥረት፣ የጌታ ኢየሱስ ሕይወት ከቅዱሳት መጻሕፍት ጋር የሚጋጭ ሳይሆን፣ ለእስራኤል የተገቡት ተስፋዎች ሁሉ ፍጻሜ መሆኑን እስራኤላውያኑ ተደራስያን እንዲገነዘቡ ነው። ለእስራኤል የተሰጠው ተስፋና ኪዳን በኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተፈጸሙ እንጂ እንዳልተሻሩ የምናምነው ለዚህ ነው። እነዚህ ክፍሎች እንደሚያስተምሩን፣ “ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው” ማለት “ኢየሱስ እውነተኛ እስራኤል ነው” ማለት ነው። ጌታ ኢየሱስ በእስራኤል ቦታ ገብቶ እርሷ...
የእግዚአብሔር ልጅ ምን ማለት ነው? (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 26)
zhlédnutí 1,2KPřed 5 měsíci
መላእክት የእግዚአብሔር ልጆች ተብለው ተጠርተዋል (ኢዮብ 1፥6፤ 2፥1፤ 38፥7)። የዕብራውያን ጸሓፊ ግን ከመላእክት መካከል እግዚአብሔር ማንንም ልጄ በማለት እንዳልጠራና አባትም ሊሆናቸው ቃል እንዳልገባ ይናገራል (1፥5-6)። ስለዚህ መላእክት የእግዚአብሔር ልጆች የሆኑበትና ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ የተባለበት ልጅነት አንድ ዐይነት አይደሉም ማለት ነው። በአንድ በኩል፣ “እስራኤል የበኵር ልጄ ነው” በማለት ስለ ተጻፈ የእስራኤልን የበኵር ልጅነት እናውቃለን (ዘፀ. 4፥22፤ ኤር. 31፥9)። ነገር ግን መላእክት የተፈጠሩት ከእስራኤል መመረጥ በፊት ነው። ታዲያ መላእክት ቀድመው ተፈጥረው፣ እንዴት እስራኤል የበኵር ልጅ ...
አምላክ-ሰው (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 25)
zhlédnutí 1,3KPřed 6 měsíci
ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ አንድ አካል እንጂ የተለያዩ የሰው-ነትና የመለኮትነት አካላት የሉትም። ከመጀመሪያውም የመለኮትነት አካሉ የሰው-ነትን ባሕርይ በመውሰድ ብቻ ነው ሰው የሆነው። ከፅንሰቱ እስከ ውልደቱ፣ ከውልደቱ እስከ ዕድገቱ፣ ከዕድገቱ እስከ መስቀል ሞቱ፣ ከሞቱ እስከ ትንሣኤውና ዕርገቱ ሕይወቱን ብናጠና የምንገናኘው አንዱን ኢየሱስ ነው። አምላክም ሰውም የሆነው አንዱና ያው ክርስቶስ!
"በእግዚአብሔር መልክ፣ የባሪያ መልክ" (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 24)
zhlédnutí 1,2KPřed 7 měsíci
እግዚአብሔር ሰው በመሆኑ ከምልከታችን ቢከለል እንጂ ማንነቱ አልተቀየረም። እርሱ ሰው የሆነበት እውነታ እግዚአብሔር ምን መምሰል እንዳለበት ያለንን ረቂቅ ግንዛቤ ከመንገድ ገፍቶ አስወጥቶታል። መለኮታዊው ድንቅ ብርሃን በጨለማማው የሰው መስታዎት ክብሩን ከልሎ መጣ። የዓለማቱ ፈጣሪ ግርማዊው አምላክ በግርማዊ ውርደት በመካከላችን ተገኘ። ቅዱስ ፍቅር የሆነው እውነተኛ አምላክ በውሱን ሰው-ነት ታየ። በእኛ ውሱንነት ልክ መኖርን መረጠ። ሰዎች መለኮታዊ ግልጠትንና ይቅርታን መቀበል እንዲቻላቸው ራሱን አዋርዶ ሰው ሆ ተጠጋቸው፤ የባሪያን መልክ ይዞ ቀረባቸው። በዚህም የእግዚአብሔር ፍቅር ለሰዎች ተገለጠ። ትሑት ፍቅሩ ሁሌም የግምት ...
የስሙ ጉልበትና ከነቢያት መብለጡ (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 23)
zhlédnutí 888Před 7 měsíci
በኢየሱስ ስም አጋንንትን ማስወጣትና በኢየሱስ ስም ጸሎት ማድረስ ትርጓሜው ጥልቅ ነው። አጋንንት በማንም ስም አይወጡም፤ በኢየሱስ ስም እንጂ። ጸሎትም በተወዳጅ ሐዋርያ ወይም በመልአክ ስም አይደረግም፤ በኢየሱስ ስም እንጂ። አብም መንፈስ ቅዱስን የሚልከው በኢየሱስ ስም ነው (ዮሐ. 14፥26)። ስለዚህ የክርስቶስ ኢየሱስ መለኮትነት ከሥላሴ ማንነት ጋር ተጋምዷል። ይህም መለኮትነቱን ያመለክታል። ሌሎች በእርሱ ስም አጋንንትን ሲያስወጡ፣ ጌታ ኢየሱስ ግን አጋንንትን ለማስወጣት የተጠቀመው ልዩ ዘዴ አልነበረም። ለዚህ ሲል ወደ እግዚአብሔር ጸሎት አላደረገም። ከራሱ የሚበልጥን ሌላ ኀያል ስምም አልጠራም። አጋንንቱን፣ “በእግዚአብሔ...
ስግደት ለኢየሱስ (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 22)
zhlédnutí 836Před 8 měsíci
መጽሐፍ ቅዱስ ለእግዚአብሔር ስለሚቀርብ ስግደት ወይም አምልኮ በተለያዩ መንገዶችና አገላለጾች ያስተምረናል። ታዛዥነትን ለመግለጽ በአምላክ ፊት ወይም በእግሩ ሥር በመደፋት ወይም በመንበርከክ የሚደረግ አምልኮ ከእነዚህ ዋነኛው ነው። ይህን የሚገልጠው የግሪክ ቃል “ፕሮስኩኒዎ” (προσκυνέω) ሲሆን፣ ቃሉ በግሪክኛው ብሉይ ኪዳንም ሆነ በአዲስ ኪዳን በስፋት በጥቅም ላይ ውሏል። መላእክት እንኳ እንዲሰግዱለት የተገለጠው ይህንኑ የግሪክ ቃል በመጠቀም መሆኑ ለጌታ ኢየሱስ የቀረበለት ስግደት ለእግዚአብሔር ብቻ የሚቀርብ አምልኮ ስለ መሆኑ ያጸናል። “ፕሮስኩኒዎ” ስግደትን ብቻ ሳይሆን፣ አምልኮንም እንደሚጨምር የኮይኔ ግሪክ መዝገ...
በማዕበሉ ላይ ጌታ - ኢየሱስ (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 21)
zhlédnutí 870Před 9 měsíci
በመዝሙር 107፥23-30 እንደ ተገለጸው ማዕበሉን ጸጥ ባሰኘው አምላከ እስራኤልና ጌታ ኢየሱስ ማዕበሉን ጸጥ በማሰኘቱ መካከል (ማር. 4፥35-41) የሚታየው ተመሳሳይነት እጅግ ትኵረት ይስባል። ያህዌ በባሕሩ ረብሻ ላይ ሥርዐት በማስፈን ሕዝቡን ከውሃ ማዕበል እንደሚታደግ ሁሉ፣ ኢየሱስም በደቀ መዛሙርቱ ሕይወት ተመሳሳይ ኀይሉን ገልጧል። እግዚአብሔር በመርከበኞቹ ላይ የገለጠውን፣ ኢየሱስም በገሊላ ባሕር በደቀ መዛሙርቱ ላይ አድርጓል። ብሉይ ኪዳን ለእግዚአብሔር ብቻ የሰጠው ይህ ኀይል የናዝሬቱ ኢየሱስም እንዴት ሊኖረው ይችላል? አሳማኙ ምላሽ፣ ኢየሱስ በሥጋ የተገለጠ የእስራኤል አምላክ መሆኑ ነው።
ኢየሱስ "እኔ ነኝ" ነው (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 20)
zhlédnutí 1,1KPřed 9 měsíci
ኢየሱስ "እኔ ነኝ" ነው (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 20)
ኢየሱስ ኀጢአትን ይቅር ይላል (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 19)
zhlédnutí 906Před 10 měsíci
ኢየሱስ ኀጢአትን ይቅር ይላል (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 19)
ኢየሱስ አዳኝ፣ ከሕግ በላይ (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 18)
zhlédnutí 926Před 10 měsíci
ኢየሱስ አዳኝ፣ ከሕግ በላይ (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 18)
ኢየሱስ ሁሌም ጌታ ነው (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 17)
zhlédnutí 1,1KPřed 11 měsíci
ኢየሱስ ሁሌም ጌታ ነው (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 17)
ኢየሱስ ከኀጢአት ስለ ማዳኑ (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 16)
zhlédnutí 1KPřed 11 měsíci
ኢየሱስ ከኀጢአት ስለ ማዳኑ (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 16)
ኢየሱስ እግዚአብሔርን መግለጡ (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 15)
zhlédnutí 1,1KPřed rokem
ኢየሱስ እግዚአብሔርን መግለጡ (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 15)
በሥጋ የተገለጠ አምላክ (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 14)
zhlédnutí 1,2KPřed rokem
በሥጋ የተገለጠ አምላክ (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 14)
የጌታ ኢየሱስ የትውልድ ሐረግ (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 13)
zhlédnutí 1,2KPřed rokem
የጌታ ኢየሱስ የትውልድ ሐረግ (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 13)
ሰው የሆነ አምላክ (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 12)
zhlédnutí 1,2KPřed rokem
ሰው የሆነ አምላክ (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 12)
አምላክ ምን ዐይነት ሰው ሆነ? (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 11)
zhlédnutí 1,5KPřed rokem
አምላክ ምን ዐይነት ሰው ሆነ? (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 11)
አምላክ ሰው ሆነ (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 10)
zhlédnutí 1,5KPřed rokem
አምላክ ሰው ሆነ (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 10)
ኢየሱስ - የእግዚአብሔር አገልጋይ (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 9)
zhlédnutí 1,1KPřed rokem
ኢየሱስ - የእግዚአብሔር አገልጋይ (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 9)
ወልድ በብሉይ ኪዳን (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 8)
zhlédnutí 1,7KPřed rokem
ወልድ በብሉይ ኪዳን (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 8)
ሦስት አካላት፤ አንድ አምላክ (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 7)
zhlédnutí 1,8KPřed rokem
ሦስት አካላት፤ አንድ አምላክ (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 7)
አንድ አምላክ፤ ሦስት አካላት (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 6)
zhlédnutí 2KPřed rokem
አንድ አምላክ፤ ሦስት አካላት (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 6)

Komentáře

  • @KirubelAtnafu-dq1vm
    @KirubelAtnafu-dq1vm Před 2 hodinami

    ወደ አጉል ፍልስፍና ገብቼ ነበር ይሄ ትምህርት ነፃ አወጣኝ❤ Thank you paul God bless

  • @AdaneMathewos
    @AdaneMathewos Před dnem

    Tebarekilin ♥️

  • @kassahunzewdie7057
    @kassahunzewdie7057 Před 2 dny

    ከሞላ ጎደል ጥሩ ተንትነሐል።አሁንም ያላሥተዋልከውን ልጠቁምህ።አንተ እንዳልከው የዘፍጥረት ምዕራፍ አንድ ጠቅላላውን ሢሆን የዘፍጥረት ምዕራፍ ሁለት ሠውንና መኖሪያው የሆነችውን ምድር በመነጠል መልሶ በመፈጠራቸው ጊዜ የሆነውን ይተርካል።ያላሥተዋልከው ግን በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሠውን በመልኩና እንደምሳሌው ፈጠረው ሢል ከምንም ወደአንድ ነገር አመጣው ነው የሚለው።እግዚአብሔር መንፈስ ነው።የፈጠረውም መንፈሱን ብቻ እንደነበረ አትጠራጠር የእግዚአብሔር መልክ(አይነት)መንፈስ እንጂ አፈር እንዳልሆነ አስተውል እናም በዚያኑ መንፈስ አድርጎ በፈጠረው ጊዜ አስቀድማ ከተፈጠረችው ምድር አፈር ወስዶ የውጭውን አካሉን አበጅቶለታል።ለምን??መንፈሱ መንፈሳዊውን አለም የሚረዳበት ሢሆን መንፈሳዊ በሆነችውና በምድር ላይ በተተከለችለት ዙፋን *የምድር ሉአላዊ ግዛት የገዥነት መንበር*(ገነት) ሆኖ እግዚአበሔርም የሚገናኝበትና የሚጎበኘው በዚህችው እንደቤተመንግስት በሆነችው ገነት እንደሆነ ልብ ይሏል።የውጭው አካሉ ደግሞ የተገኘበትን ግዑዙን አለም የሚረዳበት ማለትም በውጭው አካሉ ላይ ባሉት የሥሜት ህዋሣቱ(ማየት መሥማት መዳሠሥ ማሽተት መቅመሥ) ግዑዙን አለም የሚረዳበት አካል ነበረው ማለት ነው።ሥለዚህ አስቀድሞ ሠውን በመልኩ ፈጠረው ሢል እግዚአብሔር አንድ እንደሆነው ሁሉ ሠውም አንድ ብቻ እንደነበረ ለማሥተዋል ሞክር ወረድ ብሎ አሁንም በመንፈስ ወንድና ሤት(male &female) አድርጎ ፈጠራቸው የሚለው በፍጥረት በመንፈስ አንዱ አካል የሁለቱ የወንድና የሤት ጥምረት** ሁለት በአንድ**እንደሆነ ነው የገለፀልህ የኤፌሶኑ ወንድና ሤት አንድ አካል እንጂ ሁለት አይደሉም ካለህ በህዋላ ይህ ታላቅ ሚሥጢር ነው ብሎሀልና እባክህ የሠውን አፈጣጠር ከሌሎች የምድር ፍጥረታት ጋር ለማነፃፀር ባትሞክር የተሻለ ነው።ቢያንስ ሌሎች ፍጥረታት ምድር ታውጣቸው ተብለው ወደመታየት የመጡ ከአፈር የተገኙ እንደሆኑና ሠው ግን ምድሮ ታውጣው ያልተባለና ይልቅስ እግዚአበሔር **ሠውን(የፈጠረውን)**ከምድር አፈር(አስቀድማ ከተፈጠረችው ምድር በተወሠደ አፈር አበጀው**እንደሚል አስተውል።ይህንን መንፈስ የሆነውንና ሢፈጠር በመልኩ የፈጠረውን አንዱን አዳም(በመንፈስ ሁለት በአንድ የሆነውን) ከምድር አፈር የውጪውን አካሉን ከሠራለት በህዋላ አስቀድሞ ወንድና ሴት የሆነውን በሥጋ ሢለየው ከዋናው ሥጋ ላይ ሤቷን አወጣት እንጂ ከምድር አፈር ለብቻዋ እንዳልሠራት አስተውልና አሁን በግዑዙ አካል ሢለያዪ የተለያዩ የወንዴና የሤቴ የመራቢያ አካላት ያላቸው ሆኑ።ይህ ማለት አስቀድሞ በመንፈስ(ሁለት በአንድ) ሆነው ሣሉ በእንግሊዝኛው male & female የተባሉት የፆታ መለያ እንዳልሆኑና በሥጋ ከተበጀ በህዋላ ሢነጣጠሉ MAN & WOUMB MAN ሠውና የማህፀን ሠው በመባል የመራቢያ አካላት ልዩነት በሥጋ እንደተገለፀ አስተውል።እናም ሠው አምላኩን የሚመሥልበት ማንነት (መንፈስ) ያለውና ከምድር አፈር ከሆነው አካሉ ደግሞ እንደማንኛውም ህይወት ያለው ፍጡር ነፍስንና ሥጋን እንደተካፈለ(የኢየሡስን የውጭ አካል ልብ ይሏል) ወንድሞቹ በስጋ እንደሚካፈሉ ያለህ ይህንን ነው።የሠው ነፍስ ከተገኘችበት ከምድር ፍጥረታት ነፍስ የምትለይበት ከእግዚአብሔር እስትንፋስ የተገኘ ህይወት(ዘለአለማዊነት) ያገኘች መሆንዋ ነው።እንስሳት ነፍሳቸው ከሌለች የሉም።መንፈስ የላቸውምና ጊዜያዊ ናቸው።ሠውን ከእንስሳት አፈጣጠር ጋር ፈፅሞ አታነፃፅረው።ለማንኛውም ሠው በመንፈስ ሁለት በአንድ የሆነ ፍጥረት መሆኑን ለመረዳት በመልኩና #በአምሳያው# የፈጠረው መሆኑንና በዘፍ 5 ላይ ሥማቸውንም በፈጠረበት ቀን **አዳም**ብሎ በአንድነት እንጂ በሁለትነት እንዳልጠራቸው እንዲሁም እንደሌላው ፍጥረት በመንጋ እንዳልተፈጠረ አንድ ብቻ ሆኖ ከተለያየ በህዋላም ሁለቱ አንድ አካል እንጂ ሁለት አይደሉም የሚለው የዘፍጥረቱና የኤፌሶኑ ሚስጢር ትስስር ያረጋግጥልሀል።እናም ሠው የሚታየውና ከምድር የተገኘው አካሉ ከምድር የተበጀው አካሉ ከምድር እንደተገኙት ሌሎች ፍጡራን ጊዜያዊ(የሚታየው ጊዜያዋ ነው) ሢሆን በመልኩ የተፈጠረውና የማይታየው መንፈሱ ግን የማይጠፋና ዘለአለማዊ እንደሆነ አስተውል።የተፈጠረው ማንነቱ መንፈሱ ነው የተበጀው ደግሞ ስጋው ነው።ዘፍጥረት 1 እና ሁለትን ቀላቅልና ተረዳው።ሠው ከእንስሳት የሚለየው በመንፈሱና የህይወት እስትንፋስ በተሠጣት ነፍሱ ነው።አሁንም በመንፈሳዊው አለም በገነት የሚኖሩት ፃድቃን ያለፆታ አስቀድሞ በተፈጠሩበት መንፈስ እንዳሉና አምሳያ የሆኑበትንሥላሤነት(መንፈስ ነፍስ ሥጋ) የሚታየውን ከምድር አፈር የተበጀለትን ጊዜያዊውን መኖሪያ በሠማያዊ መኖሪያ አካል በመለወጥ እንደሚጠናቀቅ አስተውልና መንፈሳዊውን ዕውነት በአእምሮ የታሪክ ምርምር ሣይሆን ዳግመኛ በመወለድ ከመንፈስ በመማር ብቻ ልትረዳው እንደምትችል 1ኛ ዮሐ 2:26-27 ከራሤ ልምድ አካፈልኩህ ተባረክ።

    • @PaulosFekadu
      @PaulosFekadu Před 13 hodinami

      "ከራስህ ልምድ" ስላካፈልከኝ አመሰግናለሁ። በዚህ ስፍራ ግን የራሴን ልምድ እያቀረብሁ አልነበረም።

  • @kassahunzewdie7057
    @kassahunzewdie7057 Před 3 dny

    ወንድሜ ሆይ አሁንም ያላሥተዋልከውን ልጠቁምህ።ወልድ በብሉይ ኪዳን በማለት የጠቀስካቸው ጥቅሶች በሙሉ የእግዚአብሔር መልአክ የሚሉ ናቸው።ቃሉ በአዲስ ኪዳን በዕብ 1:1-3 ተመልከተው እግዚአብሔር አብ ነው በልዩ ልዩ ሁኔታ በነቢያትም በኩል እየተገለፀ ይናገር የነበረው።ወልድ ደግሞ በሠው አካል የተገለፀው በአዲሡ ኪዳን እንደሆነ አሁን በዚህ ዘመን ደግሞ በልጁ በኩል ለእኛ ተናገረን ነው የሚልህ።ሥለዚህ **የእግዚአብሔር መልአክ**ተብሎ የተጠራው በእርግጥም የእግዚአብሔር መልአክ እንጂ ራሡ ወልድ አይደለም።ምክንያቱም እግዚአብሔር(ወልድንም ጨምሮ)ውስንነት የሌለው አምላክ ስለሆነ ራሡን በውስን ቦታና በውስን አካል ለመግለፅ ሢል የሚጠቀምባቸው የራሡ የሆኑ ልዩ ቅርቡ የሆኑ መላእክት አሉት በራዕይ አራቱ እንስሳት የሚባሉት በአቀማመጥ ከእግዚአብሔር በመቀፀል እንደሆኑ አስተውል።እናም ወልድም ቢሆን በብሉይ ውስን አካል ያለው መንፈስ እንዳልሆነ አስተውል።ሥለዚህ ወልድም እራሡን በውስን ቦታና በውስን አካል ለመግለፅ ሢፈልግ የሚጠቀምባቸው የእራሡ መላእክት አሉት።ለምሳሌ በራዕይ 1: ላይ እግዚአብሔር ለኢየሡስ ክርስቶስ ኢየሡስ ክርስቶስ ደግሞ በመልአኩ ልኮ ለዮሐንስ እንደነገረው ይገልፃል እናም ኢየሡሥ ራሡ ሣይሆን የኢየሡስ መልአክ ነው ኢየሡስን ወክሎ ሞቼም ነበርኩ ለዘላለም ህያው ነኝ እያለ ይናገር የነበረው።በብሉይም የእግዚአብሔር መልአክ የሚባሉት ልዩ መገለጫው የሆኑ መላእክት ሆነው ሙሉ በሙሉ እግዚአብሔርን ወክለው በእኔነት የሚናገሩ ናቸው።ለምሳሌ ለአብርሀም በመምሬ አድባር ሥር ከተገለፁት መላእክቶች አንደኛው የእግዚአብሔር መልአክ ሢሆን ሁለቱ ግን ተራ መላእክት(ምናልባትምየመልአኩ መላእክት) ናቸው።እነዚህ ሶስቱ መላእክት ደግሞ በሠው አካል ተገለፁ ማለት ነው።እንጂ አብም ሆነ ወልድ በብሉይ በቀጥታ በውስን አካል መገለጥ አይችሉም ውስን መንፈስ አይደሉምና መገለጫ መላእክት አሉአቸው።ሌላ ልጨምርልህ ኢየሡስ ካረገ በህዋላ ለጳውሎስ በውስን ቦታ የተገለፀለት የኢየሡሰ መልአክ ነው እንጂ ራሡ ኢየሡስ ከከበረ በህዋላ በአለም ሁሉ የሚገኝበትን መለኮታዊ ክብሩን መልሶ የያዘ ስለነበረ ከራሡ 7 መላእክት በአንዱ ነው የተገለፀው ማለት ነው።እናም ወንድሜ ሆይ ስህተትህን በአድናቂዎችህ ፊት አምኖ ለመቀበል ቢከብድህ እንኳን በሥውር መርምረህ ብትቀበለው መልካም ነው እላለሁ።እኔ የሐይማኖት ቡድን ደጋፊ አይደለሁምና ስለዶክትሪን አትጨነቅ ይልቅስ በቀጥታ ከእግዚአብሔር መማርም እንዳለ ተረዳ 1ኛ ዮሐ 2:26-27

  • @user-rg2bi5rb6h
    @user-rg2bi5rb6h Před 5 dny

    Wow Geta abezito tebarekeh beralig🙏🙌🙌🙏💚💚

  • @obsaurgessa766
    @obsaurgessa766 Před 6 dny

    ኢየሱስ ከሞተ ቦሃላ ለ3ቀን የቆየው ዬት ነው 1. መስቀል ላይ ሆኖ ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር ሆነ ይላል ያ ወንበዴ አብሮት የሄደው ወደ ገነት ነዉ 2. ወደ ሲኦል እንደወረደም መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል የእነዚህ ሁለት ትርጉሞች እስካልገባን ድረስ በወይኒ ያሉት የሚለው አይገባንም

  • @sirakhailemariam6057

    ቁጥር አስራ ስምንት አንተ የቀመርከውን ቀመር ያፈርሰዋል። ዩሀ• 6÷44 በራሱ የተመረጡትና በመንፈስቅዱስ አማካኝነት የድንጋይ ልቦቻቸው የተቀየሩት ብቻ ወደ ክርስቶስ እንደሚመጡ በግልፅ ይናገራል። የተመረጡ ሰዎች ካልተመረጡት የተሻሉ በመሆናቸው ሳይሆን በእግዚአብሄር ቸርነትና ምህረት ብቻ መመረጣቸውን መጠራታቸውን መፅደቃቸውን መፅሀፍቅዱስ በግልፅ ይናገራል።

  • @jonathanmulugeta5108

    God bless you 🙏🙏

  • @AsinuUgebo
    @AsinuUgebo Před 7 dny

    ❤❤❤❤❤❤geta yibarikihi

  • @mulutsega-dk9dy
    @mulutsega-dk9dy Před 7 dny

    antenim yichemiral wondime mastewalin yistih.

  • @AsinuUgebo
    @AsinuUgebo Před 7 dny

    wow ba geta mini ayinati megelat newu yibizaliki tsaga abate tabaraki kahine iyesus simiki yibaraki

  • @kassahunzewdie7057
    @kassahunzewdie7057 Před 8 dny

    ንስጥሮስ ምናምን እየተባሉ የሚጠሩት የሐይማኖት መሪዎችና መምህራን እንደፖለቲካ ሢነታረኩ በጉባኤ ሢወስኑ የነበሩበት ዘመናት በሙሉ ሥጋዊው ሐይማኖታዊው ሥርአት እንጂ በፍፁም እደግመዋለሁ በፍፁም መንፈሳውያን የነበሩበት ማለትም መንፈስ ቅዱሥ የሚሠራበትና የሚወስንበት የቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ስርአት ጠፍቶ የነበረበት ዘመን እንደነበረ ማሥተዋል ይገባል።ይሠበሠባሉ ይከራከራሉ በድምፅ ብሎጫ አሸናፊው ወገን የብዙሀኑ ድምፅ ይሆናል የተሸነፈው አርዮስ ደግሞ **እርኩሥ ከመአርዮስ** ይባላል ኪኪኪኪኪኪኪ በጣም አስቂኝ ሥጋዊና የህፃናት ጨዋታ የሚመሥል ሁኔታ ነበረ።።እውነታው ግን ማንም ሊያሥተባብለው የማይችለው **ኢየሡስ ክርስቶስ**የነበረ፣ትን መለኮታዊ ክብር በመተው እራሡን ባዶ በማድረግ ፍፁም ሠው ብቻ ሆኖ በምድር የተመላለሠ ማለትም በፊልጵ 2:6-8 እንደተገለፀው*ከእግዚአብሔር መልክ(መለኮታዊ ክብር) ወደሠው መልክ(የባርያ መልክ) እራሡን አዋርዶ በሥጋ የተገለፀ **ፍፁም ሠው**ብቻ ሆኖ እስከ30 አመቱ እንደማንኛውም ሠው ኖረ በሠላሣ አመቱ መንፈስ ቅዱሥ ተሞላ(ሠው እንጂ አምላክ መንፈሰ ቅዱሥ እንደማይገደል እንደማይሠቃይ እንደማይሞት አስተውሉ።ወደነበረበት መለኮታዊ ክብሩ የተመለሠው ከትንሣኤ በህዋላ በፊልጵ 2:9 ጀምሮ በተገለፀው መሠረት ነው።በዮሐ 1:10በአለም ነበረ የተባለው መለኮትነቱ ሢሆን ወደገዛወገኖቹ መጣ ሥጋ ሆነ የተባለበት ግን ፈፁም ሠው ብቻ የሆነበት ነው።አስተውሉ??አምላክን አምላክ የሚያሠኘው በአለም ሁሉ በአንድ ጊዜ መገኘት መቻሉ ነው።በእስራኤል በውስን ቦታ በውስን አካል የተገለፀው ኢየሡስ ግን ሠው ብቻ ነበረ።

  • @hannates
    @hannates Před 12 dny

    በሚገባ ግልጽ ሆነልኝ። እግዚአብሔር ይባርክህ!

  • @AshenafiAdisu-dg8sl
    @AshenafiAdisu-dg8sl Před 12 dny

    ስላንተ ገታ ይመስገን ግን ክፍል 14 ን እንደት ማግኘት እችላለሁ?

  • @AshenafiAdisu-dg8sl
    @AshenafiAdisu-dg8sl Před 13 dny

    Thank you,But why not episode 14

  • @Capcut3255
    @Capcut3255 Před 13 dny

    ጌታ ይባርክህ ጥሩ ትምህርት ነው ፡መሀከል ላይ ድምጹ ይቃረጣል ።

  • @henokhenok
    @henokhenok Před 13 dny

    ተባረክልንንን ተባረክልንንንን

  • @God_Is_Love1111
    @God_Is_Love1111 Před 13 dny

    ❤❤❤

  • @surafelgelagle31
    @surafelgelagle31 Před 15 dny

    Be blessed

  • @masetewalyenuren4078
    @masetewalyenuren4078 Před 16 dny

    Tebarek bebzu 👍🏼👍🏼🙏🏼🙏🏼🙏🏼🙌🏼🙌🏼🙌🏼

  • @KeepsakeSelamu
    @KeepsakeSelamu Před 18 dny

    tsega yibzalih paul gin ene bicha negn part 14n maggnet yalchalkut ?

    • @PaulosFekadu
      @PaulosFekadu Před 17 dny

      czcams.com/video/-LuPMlMNp-U/video.html

  • @shimelisabate8953
    @shimelisabate8953 Před 18 dny

    ሰላም ወንድሜ ጳውሎስ ድምጽ አይሰማም እንደገና ኢዲት ይደረግ

    • @PaulosFekadu
      @PaulosFekadu Před 13 dny

      ድምፁ በደንብ ይሰማል። ምናልባት ችግሩ ያለው ከምትሰማበት ዲቫይስ ሊሆን ይችላል

    • @henokghebremeskel1243
      @henokghebremeskel1243 Před 8 dny

      ይሰማል

  • @YonasTesfay-jp7jz
    @YonasTesfay-jp7jz Před 18 dny

    bless you pawos

  • @wegene2056
    @wegene2056 Před 18 dny

    ቃለ ህይወት ያሰማልን መንግስተ ሰማያትን ያውርስልን፡፡

  • @PerfectGRACEMinistries-2023

    Blessed paul❤❤❤

  • @meralenaaida2316
    @meralenaaida2316 Před 21 dnem

    እግዚአብሔር ይመስገን ስላንተ

  • @meralenaaida2316
    @meralenaaida2316 Před 21 dnem

    ተባረክ

  • @meralenaaida2316
    @meralenaaida2316 Před 23 dny

    ተባረክ እርድቶኝ መጽሀፉን ከትምህርቱ ጋር አብሬ እያነበብኩ ነው :

  • @user-fk8wq9vv4x
    @user-fk8wq9vv4x Před 25 dny

    ተባረክ

  • @kimaster9170
    @kimaster9170 Před 29 dny

    Amen🙏 የኔ ዘመን ጳውሎሴ🥰🙏🙏

  • @abidantheleader5169
    @abidantheleader5169 Před 29 dny

    ተባረክ ወንድሜ እባክህ ወንጌል ማቴዎስ ምእራፍ 2 የመጨረሻ ጥቅስ ስለ ናዝራዊው ብታብራራልን

  • @genetdaniel
    @genetdaniel Před měsícem

    በእውነት ስለአንታ ጌታ አመሰግናለሁ በጣም ቡዙ ነገር አዉቅሃሎ ፀጋ ይብዛል😍😍😍

  • @genetdaniel
    @genetdaniel Před měsícem

    በእውነት በጣም በጣም ደስ ቢሎኝል ሚክነቱም እንዴት አይነት ሰው ማውቅ እንዴት አይነት ትምህርት ሚሚር በእውነት ፀጋ ይብዛልክ ❤

  • @genetdaniel
    @genetdaniel Před měsícem

    በእውነት ፀጋ ይብዛልክ❤🎉

  • @masartmissoo1160
    @masartmissoo1160 Před měsícem

    Yegeta lij p/s geta tsagawun yechamerlik

  • @henokhenok
    @henokhenok Před měsícem

    well come...የተወደድክ መምህር ❤

  • @mastwalasmare3049
    @mastwalasmare3049 Před měsícem

    እንኳን ደና መጣህ ፓዬ😊

  • @alazargosa8915
    @alazargosa8915 Před měsícem

    ❤❤❤❤❤❤❤❤ፀጋው ይጨምርልክ

  • @alazargosa8915
    @alazargosa8915 Před měsícem

    ተባረክ❤❤❤❤ፀጋውን ያብዛልክ

  • @meralenaaida2316
    @meralenaaida2316 Před měsícem

    ❤❤❤

  • @alazargosa8915
    @alazargosa8915 Před měsícem

    መንፈሳዊ አይኖቼ ባንተ ትምርት በርቶልኛል ስላንተ ጌታ ይመስገን

  • @meralenaaida2316
    @meralenaaida2316 Před měsícem

    ♥️♥️♥️

  • @meralenaaida2316
    @meralenaaida2316 Před měsícem

    ♥️♥️

  • @asmeromtesfai5107
    @asmeromtesfai5107 Před měsícem

    prefetencial or favoring isue for specific service or mission

  • @samuelabera9510
    @samuelabera9510 Před měsícem

    ፓውል ተባረክ

  • @meralenaaida2316
    @meralenaaida2316 Před měsícem

    ❤❤

  • @meralenaaida2316
    @meralenaaida2316 Před měsícem

  • @meralenaaida2316
    @meralenaaida2316 Před měsícem

    ♥️

  • @tizitaaersulo2106
    @tizitaaersulo2106 Před měsícem

    God bless you 🙏

  • @PerfectGRACEMinistries-2023

    THANKS PAUL❤❤❤❤❤❤❤❤