የእግዚአብሔር ልጅ - መለኮት (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 29)

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 19. 03. 2024
  • ሐዋርያው ዮሐንስ፣ “ከቶውንም እግዚአብሔርን ያየ ማንም የለም፤ ነገር ግን በአብ ዕቅፍ ያለው አንድያ ልጁ የሆነው አምላክ እርሱ ተረከው” ሲል በወንጌሉ መግቢያ ላይ ጽፏል (1፥18፤ አመት)። በዚህ ክፍል “አንድያ ልጅ” ተብሎ የተተረጐመው፣ በግሪክኛው መጽሐፍ ቅዱስ “ሞኖገኔስ ሁዮስ (μονογενὴς υιος)” የተባለው ነው። “ሁዮስ” ልጅ ነው። “ሞኖስ” (μόνος) ማለት “አንድ፣ ብቻ” ማለት ሲሆን፣ “ጌኖስ” (γένος) ደግሞ “ዐይነት፣ መደብ” የሚል ትርጕም አለው። ስለዚህ ከሁለቱ ቃላት ጥምረት የተገኘው “ሞኖገኔስ” የሚለው ቃል “በዐይነቱ የተለየው፣ የተለየ መደብ ያለው፣ ልዩ የሆነው፣ መሳይ የሌለው” (“pertaining to being the only one of its kind within a specific relationship” and “pertaining to being the only one of its kind or class, unique (in kind)”) ማለት ነው።
    ቅዱስ ዮሐንስ በአምስት ስፍራዎች የተጠቀመው ይህ ቃል (ዮሐ. 1፥14፤ 1፥18፤ 3፥16፡18፤ 1ዮሐ. 4፥9) በዐይነቱ ቀዳሚም ተከታይም የሌለው ልጅነትን ወይም ልዩትነትን (uniqueness) ያመለክታል። አብርሃም “አንድ ልጁን” ይስሓቅን ለመሥዋዕት ስለ ማቅረቡ የዕብራውያን ጸሓፊ የተናገረው በዚሁ ቃል ነው (11፥17)። ይስሓቅ የአብርሃም ብቸኛ ልጅ አልነበረም፤ ነገር ግን ይስሓቅ ከሣራ በመወለዱም ሆነ የተስፋ ቃል ልጅ በመሆኑ የተለየ ልጅ ነው፤ መሳይ የለውም። ወንጌላዊው ሉቃስም ብቸኛ ልጅነትን (one-and-only) የሚያመለክተው በዚሁ ቃል ነው (7፥12፤ 8፥42፤ 9፥38)።

Komentáře • 13

  • @surafeleyob5914
    @surafeleyob5914 Před 4 měsíci +1

    ተባረክ ዘመንህ ይለምልም እውነትም የዘመኑ ጳውሎስ🥰😍🥰😍🥰🤩😍🥰

  • @masartmissoo1160
    @masartmissoo1160 Před 4 měsíci +1

    Amasagnalohgn yegeta lij

  • @Kidist_
    @Kidist_ Před 2 měsíci

    Many blessings Paulos! Very interesting.

  • @upright4363
    @upright4363 Před 4 měsíci +1

    ወንድሜ ጌታ እጅግ አድርጎ ይባርክ የዘምኑን ጨለማ ጌታ በአንተ ውስጥ ስለበራው ጌታን አመሰግናለሃ፣
    ጌታ ዘምንህን አበዝቶ ይባርክ በርታ

  • @almazsibihat1051
    @almazsibihat1051 Před 4 měsíci +1

    ወንድሜ ጳውሎስ ጌታ እየሱስ አብዝቶ አብዝቶ ይባርክህ በዚህ ዘመን ስለ እየሱስ የተዘበራረቀ የሀሰት ትምህርት ባለበት ጌዜ ላይ አንተ ግን እውነተኛውን ትምህርት እያስተማርክ ህለሆነ ወንድሜ በርታ ተባረክ::

  • @user-gj6pt6dq5k
    @user-gj6pt6dq5k Před 4 měsíci +1

    tsega yibzalk know days gize sagegh teregagche misemaw new...bizu awqo endi meregagat des ylal....tnsh bcha yedmtse tirat ystekakel..bergit i'm okay wz it

  • @masartmissoo1160
    @masartmissoo1160 Před 4 měsíci +1

    Amasagnalohgn yegeta lij