ኢየሱስ አዳኝ፣ ከሕግ በላይ (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 18)

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 17. 08. 2023
  • ኢየሱስ የሚለው ስም የተሰየሙ ሰዎች ከዚያን ወቅት በፊት፣ በዚያን ወቅትም ሆነ ከዚያ በኋላ ሊኖሩ ይችላሉ። የኢየሱስ አሰያየም ግን ከሌሎቹ ለየት የሚልበት ምክንያት እንዳለው ማቴዎስ ግልጽ አድርጎታል፤ “እርሱ ሕዝቡን ከኀጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ” በማለት። አዳኝነት የእግዚአብሔር ነውና፣ “እስራኤል በእግዚአብሔር ይታመን፤ እርሱም እስራኤልን ከኀጢአቱ ሁሉ ያድነዋል” የተባለውን (መዝ. 130፥8) በዚህ ጊዜ ማስታወስ ግድ ነው። ስለዚህ በናዝሬቱ በኢየሱስ የሚያምን፣ “የኀጢአቱን ስርየት እንዲቀበል ነቢያት ሁሉ ይመሰክሩለታል” (የሐዋ. 10፥43)። ስሙንም በእምነት የሚጠራ ሁሉ ይድናል (ሮሜ 10፥12-13)። እግዚአብሔር ሕዝቡን ከኀጢአት ያድናል፤ አሁን ደግሞ ሕዝቡን ከኀጢአት የሚያድነው ኢየሱስ ስለ መሆኑ ተነግሯል። እግዚአብሔር ከኀጢአት ያድናል፤ ጌታ ኢየሱስ ከኀጢአት ያድናል። ይህም የኢየሱስን መለኮትነት ያሳያል።
    በተራራው ስብከት ላይ የቀረበው የኢየሱስ ማንነት ነው። ኢየሱስ በሕግ የተሰጠ ነገርን ሲቀይር፣ ሲያሻሽልና ሲያስተካከል የሕጉ ሉዐላዊ ተርጓሚ እርሱ መሆኑን እየገለጠ ነው። ሕጉ በጠቅላላው “እንደ ተባለ ሰምታችኋል” ሆኖ ሲቀርብ፣ የእርሱ ቃል “እኔ ግን እላችኋለሁ” ሆኖ ቀርቧል። ኢየሱስ በዚህ ስፍራ ሕግጋቱን ሲተረጕምና ሲያስተካክል “እኔ” በማለት በአጽንዖት ነው የሚናገረው። እንዲህ ዐይነቱ ሥልጣንም የእርሱ ብቻ ነው። የቶራው ቃል የእግዚአብሔር ቃል ነው። የመጨረሻ ቃል ነው። ጌታ ኢየሱስ ግን ቶራውን አራት ነጥብ አድርጎ በአስተምህሮው መደምደሚያነት አላቀረበውም። እንደ ነጠላ ሰረዝ አስቀምጦት አዲስ ነገር ማምጣቱን ቀጠለ። በዚህ ሁኔታው ኢየሱስ ከሙሴም በላይ ሆኖ ነው የቀረበው፤ የእግዚአብሔር አቻነቱ ነው የተገለጠው። ሌሎቹ አገልጋዮች ከሕጉ በታች ናቸው፤ እርሱ ግን ከሕጉ የበላይ መሆኑን አሳይቷል። የሕጉ ሰጪ ነውና እርሱ ይህን አድርጓል።

Komentáře • 4

  • @Kidist_
    @Kidist_ Před 11 měsíci

    Learning a lot as usual! Blessings again🙏

  • @generationbuilder1068
    @generationbuilder1068 Před 11 měsíci

    Paul ወንድሜ ተባረክ 🙏
    ሁሌም ትምህርቶችህን stand by ሆነው ከሚጠብቁት ወንድሞች አንዱ ነኝ❗