ኢየሱስ ኀጢአትን ይቅር ይላል (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 19)

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 28. 08. 2023
  • “ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ኀጢአት ሊያስተሰርይ ማን ይችላል?” ለሚለው የተቃውሞ ጥያቄአቸው ጌታ ኢየሱስ የሰጠው ምላሽ ወሳኝ ነበር። “ተሳስታችኋል፤ ሰዎችም እንደ እግዚአብሔር ኀጢአትን ማስተስረይ ይችላሉ” አላላቸውም። “እኔ ይቅር እያልኩሁት አይደለም፤ እግዚአብሔር ይቅር እንዳለው እያበሰርሁኩት እንጂ” የሚልም አልነበረም። በዚህ ስፍራ “ኀጢአትህ ተሰረየችልህ” የሚለውን መልእክት የያዘው የግሪክ ቃል አፌንታይ (ἀφίενταί ወይም ἀφέωνταί) ሲሆን፣ የሚያመለክተውም የአሁን ጊዜን (present tense) ነው፤ ስለዚህም “ልክ በዚህ ቅጽበት የኀጢአት ይቅርታ ተደርጎልሃል” የሚል ትርጕም አለው። የሰውዬውን ኀጢአት በዚያው አፍታ የሰረዘለት ኢየሱስ በእግዚአብሔር ቦታ ቆሟል። የእነርሱ ጥያቄ ግን፣ “ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ኀጢአት ሊያስተሰርይ ማን ይችላል?” የሚል ነበር። ኢየሱስ በዚህ ጕዳይ እግዚአብሔርን እንደ ተዳፈረ ነበር ያሰቡት። ሰዎቹ በግማሽ ትክክል ናቸው፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ብቻ ኀጢአትን ይቅር ማለት ይችላል። ጌታ ኢየሱስ ግን እግዚአብሔርን እየተዳፈረ አልነበረም፤ አምላክነቱን እየጠቈማቸው ነው። “በምድር ላይ ኀጢአትን ሊያስተሰርይ ሥልጣን እንዳለው” (ቍ. 10) ሲነግራቸው ጕዳዩን ይበልጥ ግልጽ አድርጎታል። (ለመሆኑ፣ ኢየሱስ “ምድራዊ” ብቻ ቢሆን ኖሮ፣ “በምድር ላይ” በማለት ለምን ይናገራል? ) ይህን ያደረገው በራሱ ሥልጣን ነው። ኢየሱስ ኀጢአትን ይቅር የማለት ልዩ መብት ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔራዊ ሥልጣን አለው።

Komentáře • 13

  • @tigistketema6695
    @tigistketema6695 Před 4 měsíci +1

    ❤❤❤

  • @yalfaltarekegn
    @yalfaltarekegn Před 11 měsíci

    Tebarekkkkk
    Miin yahlil kifil yikeral

    • @PaulosFekadu
      @PaulosFekadu  Před 11 měsíci +1

      ምናልባት የእስካሁኑን የሚያህል

  • @meralenaaida2316
    @meralenaaida2316 Před 11 měsíci

    ተባረክ ወንድማችን የቃሉ ብርሃን አብዝቶ ይብራልህ ::እኔ ተጠቅሜብሃለሁ

  • @Kidist_
    @Kidist_ Před 11 měsíci

    Thank you, Paulos!

  • @fikru-xe8iv
    @fikru-xe8iv Před 10 měsíci +1

    Ere dimistu ayisemam

    • @PaulosFekadu
      @PaulosFekadu  Před 10 měsíci +1

      በደንብ ይሰማል። የምትሰማበትን ዲቫይስ ቀይረህ ሞክረው

    • @fikru-xe8iv
      @fikru-xe8iv Před 10 měsíci +1

      @@PaulosFekadu minalbat kesilke new endalil yante leloch videoch yisemalu gin ye Egziabher lij yemilew 20ውም part ayisemam telegram lay yalewin mokirialew device ayimesilegnim

    • @PaulosFekadu
      @PaulosFekadu  Před 10 měsíci +1

      @fikru-xe8iv ሌሌቹ ሁሉ እየተሰማቸው አንተ ብቻ ነው ያልተሰማህ። የሆነ ችግር አለ ማለት ነው። ግዴለህም ስልክህን ቀይረህ ሞክረው።

    • @fikru-xe8iv
      @fikru-xe8iv Před 10 měsíci +1

      @@PaulosFekadu Eshi amesegnalew geta ye agelgilot zemenihin yibarek amen🙏🙏🙏🙏🙏❤️❤️❤️❤️❤️🙏❤️🙏🙏🙏