በማዕበሉ ላይ ጌታ - ኢየሱስ (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 21)

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 25. 09. 2023
  • በመዝሙር 107፥23-30 እንደ ተገለጸው ማዕበሉን ጸጥ ባሰኘው አምላከ እስራኤልና ጌታ ኢየሱስ ማዕበሉን ጸጥ በማሰኘቱ መካከል (ማር. 4፥35-41) የሚታየው ተመሳሳይነት እጅግ ትኵረት ይስባል። ያህዌ በባሕሩ ረብሻ ላይ ሥርዐት በማስፈን ሕዝቡን ከውሃ ማዕበል እንደሚታደግ ሁሉ፣ ኢየሱስም በደቀ መዛሙርቱ ሕይወት ተመሳሳይ ኀይሉን ገልጧል። እግዚአብሔር በመርከበኞቹ ላይ የገለጠውን፣ ኢየሱስም በገሊላ ባሕር በደቀ መዛሙርቱ ላይ አድርጓል። ብሉይ ኪዳን ለእግዚአብሔር ብቻ የሰጠው ይህ ኀይል የናዝሬቱ ኢየሱስም እንዴት ሊኖረው ይችላል? አሳማኙ ምላሽ፣ ኢየሱስ በሥጋ የተገለጠ የእስራኤል አምላክ መሆኑ ነው።

Komentáře • 14

  • @solomongeberekidan2904
    @solomongeberekidan2904 Před 10 měsíci

    መልካም ትምህርት ነዉ ።ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይባርክህ ተባረክ

  • @selammenberu6359
    @selammenberu6359 Před 9 měsíci

    የምወድህ ወንድሜ ፖዬ ጌታ ረዥም እድሜ ና ጤና ይስጥህ ባንተ አገልግሎት ብዙ ተባርኬአለሁ ❤❤ ፀጋ ይብዛልህ ።❤❤❤

  • @Kidist_
    @Kidist_ Před 10 měsíci

    Egziabher yistiline, Paulos! Learning a lot as usual.

  • @solomongeberekidan2904
    @solomongeberekidan2904 Před 10 měsíci

    1:49 መልካም ት/ም ነው ።ትልቅ የቃልመገለጥ ነው ።ከዚህም በላይ እ/ር አምላክ የቃል እውቀት ይሰጥህ

  • @weldiyestibebu2485
    @weldiyestibebu2485 Před 9 měsíci +1

    ጌታ ይባርክ እውነተኛ የክርስቶስ ወንጌል ነው በጌታ ኃይል በርታ እኔ ወ/ዊ ወልድየስ ጥብቡ ነኝ ከገጠር አሁን የድግር መጽሐፍ ቅዱስ ለመማር አድስ አበባ መካነ የሱስ ዶም ነኝ ለበለጠ የሕይወት ቃል ለመረዳት ነው ወንድም የሚከተለውን

  • @yisehakkebede5400
    @yisehakkebede5400 Před 10 měsíci

    ወንድሜ ጳውሎስ "የእግዚአብሔር ልጅ " የሚለው መፅሀፍህን ሳነብ አጠገቤ ሆነህ የምታስተምረኝ እስኪመስለኝ የምታነሳቸው ነጥቦችን እረዳቸዋለሁ ። ጌታን ስላንተም እኔንም ፀጋውን ስላበዛልኝ አመሰግነዋለሁ ።I strongly recommend you all to read his book.God bless you.

  • @biblestudyinamharic
    @biblestudyinamharic Před 3 dny

    እንዴት ነህ ወንድሜ ሰላምህ ይብዛ።
    ኦዲዮቹን እስከዚህ ድረስ ያሉትን ያዳመጥኮቸው ከመጽፉ ጋር አብሬ እየተመለከትኩ ነው።
    በጣም በሚገርም መልኩ አሳማኝ በሆነ መልኩ ኢየሱስ በምድር ላይ ፍጹም ስው ሆኖ ሳለ በአምላክነቱ ደግሞ ፍጹም አምላክ ሆኖ ከአምላክነቱ ለአንዲትም ሰከንድ ሳይጎል እንደተመላለሰ በጣም ገብቶኛል።
    ጥያቄ 1ኛ ዮሐንስ 2፥6 ላይ የተመሰረተ ነው።
    “በእርሱ እኖራለሁ የሚል እርሱ እንደ ተመላለሰ ራሱ ደግሞ ሊመላለስ ይገባዋል።”
    - 1ኛ ዮሐንስ 2፥6
    በዘህ ጥቅስ እርሱ እንደ ተመላለሰ
    እኛ እንድንመላለስ ያዘናል።
    እርሱ በምድር ሲመላለስ ደግሞ መለኮትም ጭምር እንጂ ሰው ብቻ አልነበረም።
    እኛ ግን ሰው ብቻ ነን እንጂ አምላክ አይደለንም ስለዚህ 1ኛ ዮሐንስ 2፥6 ትንሽ ገለጥ አድርገህ እንዴት በህይወታችን እንደሚተገበር አስረዳኝ።
    ስላንተ ግን እግዚአብሔርን በጣም አመሰግናለሁ ብዙ ጥያቄ የሚሆኑብኝ ነገሮች አሳማኝ በሆነ መልኩ በዚህ መጽሀፍ ተመልሶልኛል።
    ጌታ አንተንና ቤተሰብሀ አብዝቶ ይባረክ።