እውነተኛ እስራኤል (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 27)

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 20. 02. 2024
  • ኢየሱስ ክርስቶስ በእውነተኛ እስራኤልነቱ የእስራኤልን የእግዚአብሔር ልጅነት ወክሏል። ከዚህም የተነሣ ለእስራኤል የተነገሩ ብዙ ትንቢቶች የተፈጸሙት በእርሱ ሕይወት ነው። የሐዋርያው ማቴዎስም ጥረት፣ የጌታ ኢየሱስ ሕይወት ከቅዱሳት መጻሕፍት ጋር የሚጋጭ ሳይሆን፣ ለእስራኤል የተገቡት ተስፋዎች ሁሉ ፍጻሜ መሆኑን እስራኤላውያኑ ተደራስያን እንዲገነዘቡ ነው። ለእስራኤል የተሰጠው ተስፋና ኪዳን በኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተፈጸሙ እንጂ እንዳልተሻሩ የምናምነው ለዚህ ነው። እነዚህ ክፍሎች እንደሚያስተምሩን፣ “ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው” ማለት “ኢየሱስ እውነተኛ እስራኤል ነው” ማለት ነው። ጌታ ኢየሱስ በእስራኤል ቦታ ገብቶ እርሷ ማድረግ ያቃታትን ሁሉ ሊያደርግ የቻለ፣ እርሷ መሆን የተሳናትን ሊሆን የቻለ እውነተኛ እስራኤል (The True Israel)፣ በዚህም የእግዚአብሔር ልጅ ነው።

Komentáře • 14

  • @selamahmedahmed1896
    @selamahmedahmed1896 Před 5 měsíci +1

    ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ወይ ይህንን ትምህርት ሁሉም እንድሰማ የትውልድ ልብ ይከፈት ❤❤😢😢😊

  • @endashawchernet7958
    @endashawchernet7958 Před 5 měsíci +1

    እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክህ መንፈሳዊ አባታችን ጳውሎስ!!

  • @Kidist_
    @Kidist_ Před 5 měsíci +1

    Thank you, Paulos! Blessings.

  • @birukmaidi6723
    @birukmaidi6723 Před 4 měsíci

    እናመሰግናለን 🙏🙏

  • @selammenberu6359
    @selammenberu6359 Před 5 měsíci +1

    ወንድሜ ፖዬ , ስላንተ እግዚአብሔር ይመስገን የፀጋ ሁሉ ባለቤት እርሱ ነውና አሁንም ፀጋ ይብዛልህ ❤❤።

    • @PaulosFekadu
      @PaulosFekadu  Před 5 měsíci

      እግዚአብሔር ይስጥልኝ

  • @Wen-gel
    @Wen-gel Před 5 měsíci

    ስለ ሴቶች አገልግሎት የተወሰነ ነገር ብትለን

  • @solomongeberekidan2904
    @solomongeberekidan2904 Před 4 měsíci +1

    ጶል ጌታ ይባርክህ ቁጥር ስታነብ ትንሽ ቀስበል