Video není dostupné.
Omlouváme se.

ስግደት ለኢየሱስ (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 22)

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 25. 10. 2023
  • መጽሐፍ ቅዱስ ለእግዚአብሔር ስለሚቀርብ ስግደት ወይም አምልኮ በተለያዩ መንገዶችና አገላለጾች ያስተምረናል። ታዛዥነትን ለመግለጽ በአምላክ ፊት ወይም በእግሩ ሥር በመደፋት ወይም በመንበርከክ የሚደረግ አምልኮ ከእነዚህ ዋነኛው ነው። ይህን የሚገልጠው የግሪክ ቃል “ፕሮስኩኒዎ” (προσκυνέω) ሲሆን፣ ቃሉ በግሪክኛው ብሉይ ኪዳንም ሆነ በአዲስ ኪዳን በስፋት በጥቅም ላይ ውሏል። መላእክት እንኳ እንዲሰግዱለት የተገለጠው ይህንኑ የግሪክ ቃል በመጠቀም መሆኑ ለጌታ ኢየሱስ የቀረበለት ስግደት ለእግዚአብሔር ብቻ የሚቀርብ አምልኮ ስለ መሆኑ ያጸናል። “ፕሮስኩኒዎ” ስግደትን ብቻ ሳይሆን፣ አምልኮንም እንደሚጨምር የኮይኔ ግሪክ መዝገበ ቃላት ይነግሩናል። እንግሊዝኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጕሞችም ቃሉን “worship” በማለት ተርጕመውታል።
    ጌታ ኢየሱስ ለእግዚአብሔር ብቻ የሚቀርብ ስግደት ሲቀርብለት ካልተቃወመ እግዚአብሔር ነው ማለት ነው! እንዲያውም ጌታችን ራሱም ለእግዚአብሔር የሚቀርበው አምልኮ ለእርሱም የተገባው ስለ መሆኑ በግልጥ ተናግሯል። “ሰዎች ሁሉ አብን እንደሚያከብሩት ወልድን ያከብሩት ዘንድ ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጠው …። ወልድን የማያከብር የላከውን አብን አያከብርም” (ዮሐ. 5፥23)። ወልድ መከበር ያለበት አብ እንደሚከበረው ነው። ልዩነት አልተደረገም። ዮሐንስ ይህን የዘገበው የጌታ ኢየሱስን ፍጹም አምላክነት ሲናገር ነው፤ መልአክን ጨምሮ የቱንም ፍጥረት ማምለክ ለአይሁድ ውጉዝ መሆኑን ለሚያውቅ ሰው ከዚህ ውጭ አይታሰብም።

Komentáře • 5

  • @PerfectGRACEMinistries-2023

    Blessed paul❤❤❤

  • @Kidist_
    @Kidist_ Před 8 měsíci

    Thank you so much Paulos! As usual so interesting and well presented. Blessings.

  • @alula961
    @alula961 Před 9 měsíci

    አቤት የጠፋ ሰው እንዴት ነው ረዥም ጌዜ ሆነ ትምህርትህ እየናፈቀን ጠፋህብን እኮ