እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 35)

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 21. 06. 2024
  • ክርስቶስ በገዛ ደሙ ወደ መቅደስ በመግባቱ ክርስቶስና ደሙ የተነጣጠሉ አድርገን ማሰብ ግን የለብንም። ክርስቶስ ሊቀ ካህንም መሥዋዕትም ነውና። ይህም ከብሉይ ኪዳኑ ጥላ በእጅጉ ይልቃል። ምክንያቱም የብሉይ ኪዳን ጥላዎች ሊቀ ካህናቱ ስለ ሕዝቡ መሥዋዕት ማቅረቡን እንጂ ሊቀ ካህናቱ ራሱን በመሥዋዕትነት ማቅረቡን አይናገሩም። በብሉይ ኪዳን የኀጢአት መሥዋዕት ሲቀርብ፣ ኀጢአተኛውን የሚወክለውና በኀጢአተኛው ምትክ የሚቀርበው የታረደው በግ ወይም ፍየል እንጂ መሥዋዕት አቅራቢው ካህን አይደለም። መሥዋዕቱ ያለ ካህኑ ኀጢአተኛውን ሊወክል በቂ ነው።
    ታዲያ የካህኑ ሥራ ምንድን ነው? በብሉይ ኪዳን በስርየት ቀን መሥዋዕት የሚያቀርበው ሊቀ ካህናቱ ነው። መሥዋዕቱ ኀጢአተኛውን ሊወክል በቂ ቢሆንም፣ ካህኑ በሌለበት በጉ ወይም ፍየሉ በመሥዋዕትነት ወደ እግዚአብሔር አይቀርብም። መሥዋዕቱ ራሱን በመሥዋዕትነት ለመሥዋዕት ተቀባዩ ለማቅረብ አይቻለውምና። ሊቀ ካህናቱ መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜም የመሥዋዕቱን ደም በመሠዊያው ላይ በመርጨት ሕዝቡንና ቤተ መቅደሱን (የመገናኛ ድንኳኑን) ከርኩሰት ያነጻል (ዘሌ. 16፥15-19)። በዚህም እግዚአብሔር በኪዳኑ መሠረት ከሕዝቡ ጋር እንዲኖር ለማመቻቸት መሠዊያውን ያበጃጃል። ስለዚህ መሥዋዕቱ ራሱን በራሱ ለእግዚአብሔር ሊያቀርብ አይቻለውም። ያለ ካህን መሥዋዕት የለም።
    ይህን በልቡናችን ስንጨብጥ ነው በትእምርቶችና በተምሳሌቶች የታጨቀውን የዕብራውያን መልእክት ጭብጥ የምናስተውለው። በኀጢአተኞች ምትክ መሥዋዕት ሆኖ የቀረበው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እግዚአብሔር አስቀድሞ በመሠዊያው ላይ እንዲደረግ የፈለገው ሁሉ በመስቀሉ ላይ ሆኗል። የኢየሱስ መሥዋዕትነት ለሁሉ ይበቃል። ነገር ግን ይህ መሥዋዕት ለእግዚአብሔር መቅረብ አለበት። እናም በሰማያዊ ስፍራ ይህን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ያቀረበው፣ ደሙን ይዞ ወደ ሰማያዊቱ መቅደስ የገባውም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው (ዕብ. 9፥12)። እንከን የለሹ ካህን፣ እንከን የለሹን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቀረበ። ቅዱሱ ካህን የገዛ ደሙን ይዞ ወደ ቅድስት ገባ። ከሁሉ የሚሻለው ካህን፣ ከሁሉ የተሻለውን መሥዋዕት፣ በምትሻለው መቅደስ ውስጥ አቀረበ። ሊቀ ካህናቱ ኢየሱስ፣ መሥዋዕቱም ኢየሱስ። ምንኛ ድንቅ ነው!

Komentáře • 6

  • @AsinuUgebo
    @AsinuUgebo Před 27 dny +1

    wow ba geta mini ayinati megelat newu yibizaliki tsaga abate tabaraki kahine iyesus simiki yibaraki

  • @henokhenok
    @henokhenok Před měsícem

    ተባረክልንንን ተባረክልንንንን

  • @God_Is_Love1111
    @God_Is_Love1111 Před měsícem

    ❤❤❤

  • @shimelisabate8953
    @shimelisabate8953 Před měsícem +2

    ሰላም ወንድሜ ጳውሎስ ድምጽ አይሰማም እንደገና ኢዲት ይደረግ

    • @PaulosFekadu
      @PaulosFekadu  Před měsícem +2

      ድምፁ በደንብ ይሰማል። ምናልባት ችግሩ ያለው ከምትሰማበት ዲቫይስ ሊሆን ይችላል

    • @henokghebremeskel1243
      @henokghebremeskel1243 Před 28 dny +2

      ይሰማል