የጌታ ኢየሱስ ባሪያዎች (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 33)

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 24. 05. 2024
  • ጌታ ኢየሱስ በደሙ ዋጅቶናልና በዋጋም ገዝቶናልና ባሪያዎቹ ነን። እንዲያውም ድነትን ያገኘነው ጌታ ኢየሱስን በመታዘዝ ነው፤ መጽሐፍ፣ “እርሱን ለሚታዘዙ ሁሉ የዘላለም ድነት ምክንያት ሆነላቸው” ብሏልና (ዕብ. 5፥9፤ አመት)። እዚህ ላይ ሐዋርያትንና ነቢያትን ጨምሮ አማኞች ሁሉ የእግዚአብሔር ባሪያዎች መሆናቸውን ማስታወስ የተገባ ነው። የጌታ መልአክ ሐዋርያው ዮሐንስን፣ “ከአንተ ጋር … ከወንድሞችህም ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ” በማለት ሁላቸውም የእግዚአብሔር ባርያ ስለ መሆናቸው ተናግሯል (ራእ. 19፥10)። መጽሐፍ ቅዱስ በብዙ ቦታዎች ይህን ደጋግሞ ያወሳል። የእግዚአብሔር ልጅ መሆን የእግዚአብሔር ባሪያ ከመሆን ጋር ተቃርኖ የለውምና “ልጅ እንጂ ባሪያ አይደለሁም” ማለት አይቻልም። የእግዚአብሔር ልጅ የተባለችው እስራኤልም (ዘፀ. 4፥22-23፤ ኤር. 31፥9)፣ የእግዚአብሔር ባሪያ ተብላለች (ዘሌ. 25፥42፡55)።
    የእግዚአብሔር ባሪያ መሆን ደግሞ የጌታ ኢየሱስ ባሪያ መሆንም ነው። ስለዚህ ቅዱስ ያዕቆብ “የእግዚአብሔርና የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ” በማለት ራሱን ሲያስተዋውቅ (1፥1)፣ “የእግዚአብሔር ባሪያ” በማለት ራሱን የሚጠራው ሐዋርያው ጳውሎስም (ቲቶ 1፥1) የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ስለ መሆኑ ጨምሮ ይናገራል (ሮሜ 1፥1፤ ገላ. 1፥10፤ ፊልጵ. 1፥1)። እነርሱ ብቻ ሳይሆኑ ኢየሱስ ጌታ መሆኑን የሚያምኑ ሁሉ ከሰይጣን ባርነት ያመለጡ የክርስቶስ ባሪያዎች ናቸው።
    እንግዲያውስ ኢየሱስን አዳኛችንና ጌታችን አድርገን የተቀበልን ሁሉ “ኢየሱስ ጌታ ነው” ስንል፣ ባሪያዎቹ መሆናችንን እንደምናውጅ ከቶውኑ አንዘንጋ። ኪዳናችን የተመሠረተው በሁለት እኩዮች መካከል አይደለም፤ በጌታና በባሪያዎቹ መካከል ነው። በኪዳኑ ውስጥ ባለው ግንኙነት ውስጥ ተወዳድረን የምንይዘው ወይም በዕድገት የምንደርስበት ክፍት የጌትነት ስፍራም የለም። ጌታነት በእኛና በኢየሱስ መካከል በውድድር የሚያዝ ቦታ አይደለም። “ኢየሱስ ጌታ ነው” ስንል፣ የእርሱ ባሪያነታችንን መቀበላችን ነው። ክርስቲያንነት የክርስቶስ ባሪያ መሆን ነውና አማኞች በሙሉ ከሰይጣን ባርነት ነጻ የወጡ የክርስቶስ ኢየሱስ ባሪያዎች ናቸው። የእውነተኛ ነጻነት ትርጕሙም ይኸው ነው። ጌታ ቀይረናል እንጂ ባሪያነታችን አልቀረም። ታላቁ ወንድማችን ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታችንም ነው። ይህ ጌታ ደግሞ እጅግ የሚወደንና የሚራራልን ደግና ቸር አምላካችን ነው። ለዚህ ደግና መልካም ጌታ ባሪያ መሆንም እጅግ ታላቅ በረከት፣ ክብርና ሹመት ነው!

Komentáře • 2