ኢየሱስ ከኀጢአት ስለ ማዳኑ (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 16)
Vložit
- čas přidán 31. 07. 2024
- ኢየሱስ በምድር ሳለ አምላክነቱን ጥሎ ሰው ብቻ ከነበረ፣ የዓለምን ሁሉ ኀጢአት ሊሸከም አይችልም፤ እናም እስከ አሁን ከነኀጢአታችን በቀረን ነበር። ለድነት አምላክ አምላክነቱን ሳይተው ሰው መሆኑ ግድ ነው። ምክንያቱም አምላክ ሰው ባይሆን ኖሮ መሰቀል አይችልም፤ አምላክ ረቂቅ ነውና! ሰው ብቻ ቢሰቀል ደግሞ ዓለምን ሊያድን ባልቻለ ነበር። ኢየሱስ ሰው ብቻ ቢሆን ኖሮ የኀጢአት ዕዳችንንም የሚከፍለው እንደ ሰው ብቻ በሆነ ነበር። የኀጢአት ዕዳ ዘላለማዊ ነው፤ በውሱኑ ሰው ተከፍሎ አይጨረስም። በመሆኑም ማንም ዕዳውን ማወራረድ አይችልም፤ ለዘላለም ሲከፍል ይኖራታል እንጂ። ኢየሱስ ኀጢአት የሌለበት ሰው ሆኖ እንኳ ይህን ማድረግ አይችልም። ስርየት ተግባራዊ የሚሆነውና ተፈጻሚነት የሚኖረው ጌታ ኢየሱስ ከሰዎች ወገን ምሉእ ሰው፣ ከአምላክ ወገንም ሙሉ አምላክ የሆነ እውነተኛ መካከለኛ ከሆነ ብቻ ነው። የኢየሱስ ሰው-ነት ከተጓደለ፣ ስርየት የተጓደለ ይሆናል፤ የኢየሱስ መለኮትነት ከተጓደለም ስርየት የተጓደለ ይሆናል። ስርየት ከተጓደለ ደግሞ ከነኀጢአታችን እንቀራለን። ኢየሱስ በሰው-ነቱም ሆነ በመለኮትነቱ ምሉእ ከሆነ ግን፣ የእርሱ ሞት አምላክ በራሱ ሰው-ነት የፈጸመው ሥራ እንጂ የሰው ብቻ ድርጊት አይሆንም።
Thank you, Paulos! Many blessings 🙏
Same to you!
እግዚአብሔር የባህሪያቱ ድምር አይደለም 🙏❤🙏
የኢዮብ ቅሬታ በክርስቶስ ተመልሶል
እግዚአብሔር ሰው ሆኖ መካከለኛ ሆኖልናል
ሃሌሉያ
ግን ይሔ የአዲስ ኪዳንን ሰዎች ብቻ የሚመለከት አይደለም የእግዚአብሔር ሰው መሆን ወደ ኃላም የሚመለከት ነው ምክንያቱም በብሉይም የኃጥያት ስርየት አልነበርም እንደውም መስዊያወቹ ኃጢያትን ያስታውሱ ነበር
#ቀድሞ የተፈፀመውን ኃጢያት ሳይቀጣ በማለፍ
ኃጢያት የሚቀጣበት ቀን አለ በማለት በይደር አቆይቶት ።
#መስቀሉ የእግዚአብሔር ፍቅርም ቅድስናም መገለጫ ነው 🙏❤🙏
የብሉይ ሰዎች መስቀሉን ወደፌት በማየት ሲደኑ
የአዲስ ሰዎች መስቀሉን ወደኃላ በማየት ይድናሉ
#አንድ መዳኛ አንድ አዳኝ 🙏❤🙏
እግዚአብሔር ይስጥል
ተባረኪልኝ።
@@PaulosFekadu አሜን በአንተ የተማረኩበት ቀን ይባረክ ጨካኝ አርጓኛል ብዙ ፍቅር ብዙ ክብር 🙏❤❤🙏
በጾም በጸሎት ሆኜ በዚህ ድንቅ ትምህርት ተጠቀጠቅኩ!
መዳኛው አንድ ብቻ ከሆነ በብሉይ ዘመን የነበሩ አህዛብ በምን ሊድኑ ነው?ህግን ሳያውቁ ነብያት ሳይላኩላቸው ስለሚመጣው መሢህ ሳይሰሙ እንዴት ሊፈረድባቸው ነው, ወንጌል ያልሰሙ ስለኢየሱስ ሰምተው ቢሆን ኖሮ የማመን እድል ሊኖራቸው ነበር እኮ
እባክዎ ከክፍል አንድ ጀምረው ይማሩ 🙏
የእግዚአብሔር ልጅ የሆነው መቼ ነው? ከማርያም ሲወለድ ወይስ ከመጀመርያውኑ?
ኢየሱስ ከአብ የወጣ ከሆነ, መንፈስ ቅዱስስ ከአብ ስለሚወጣ ለምን የእግዚአብሔር ልጅ አልተባለም?
ከክፍል 1 ጀምረው ይማሩ 🙏
ከክፍል 1 ጀምሮ ትምህርቱን መከታተል ለዚህ ጥያቄ መልስ ያስገኛል። እባክዎን ይሞክሩት