የእግዚአብሔር ልጆች (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 31)

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 19. 04. 2024
  • እግዚአብሔር የሰዎች ሁሉ ፈጣሪ፣ ደጋፊና አኗሪ መሆኑ እውነት ነው። ነገር ግን በክርስቶስ ውስጥ ያልሆነ ሰው እግዚአብሔርን አባቱ አድርጎ መጥራት አይችልም። “የእግዚአብሔር ልጅነት በተፈጥሮአዊ ልደት ወደዚህ ምድር ለገባ ሁሉ የሚበረከት ሁሉን አቀፍ ሹመት አይደለም፤ ሰው ኢየሱስ ክርስቶስን በመከተል የሚቀበለው ልዕለ ተፈጥሮአዊ ስጦታ እንጂ። … የእግዚአብሔርን ልጅነት ያገኘነው ሰው ሆኖ በመወለድ ሳይሆን፣ ዳግመኛ በመወለድ ነው።” በልጁ በጌታ በኢየሱስ ሞት ከእርሱ ጋር ታርቀው አዲስ ልደትን ላገኙና የመንፈሱ ማደሪያ ለሆኑ ብቻ እንጂ እግዚአብሔር ለሰዎች ሁሉ አባት አይደለም። ሰዎች የእግዚአብሔር ልጅነትን ሥልጣን የሚያገኙት በልጁ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር ሲቀበላቸው ብቻ ነው። ግና የአማኞች የእግዚአብሔር ልጅነት ትርጓሜው ምንድን ነው? የኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅነትና የአማኞች የእግዚአብሔር ልጅነት በሁሉ ነገር አንድ ዐይነት ነው ማለት ነው? ወይስ ልዩነትም አለው?

Komentáře • 10