ምን ዐይነት ልጅነት? የልጅነታችን ግብ? (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 32)

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 12. 05. 2024
  • የወልድ የእግዚአብሔር ልጅነት በእርሱና በአብ መካከል ያለውን ልዩ ዐይነት ግንኙነት ያሳያል። በዚህ ዐይነቱ ልጅነት እግዚአብሔር አብ ከኢየሱስ በቀር ሌላ ልጅ የለውም። አንድ አብ ብቻ እንዳለ ሁሉ፣ አንድ ወልድ ብቻ አለ። በዚህ ዐይነቱ አባትነትም እግዚአብሔር ለማንም አባት አይደለም፤ ሌላ ወልድ የለምና። አማኞች የእግዚአብሔር የጸጋ ልጆች ናቸው። . . .
    ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው፤ እኛም የእግዚአብሔር ልጆች ነን። እርሱና እኛ አንድ ወገን፣ አንድ ቤተ ሰብ ነን። “ሰዎችን የሚቀድሰውና የሚቀደሱት ሰዎች ከአንድ ቤተ ሰብ ናቸው፤ ስለዚህ ኢየሱስ ወንድሞች ብሎ ሊጠራቸው ዐያፍርም” (ዕብ. 2፥11፤ አመት)። ይህ ማለት ግን እኛና ኢየሱስ በሁሉ ነገር አንድ ነን ማለት አይደለም። አስቀድመን እንደ ተመለከትነው ኢየሱስ በእግዚአብሔር ልጅነቱ ከእግዚአብሔር ጋር በባሕርዩ ፍጹም ትክክል ነው። እኛ ግን የቅድስናው ተካፋይ ለመሆን መቀጣትና መገራት ይጠብቀናል።

Komentáře •