ኢየሱስ እግዚአብሔርን መግለጡ (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 15)

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 27. 06. 2023
  • ስለ እግዚአብሔር ያለን የተሳሳተ ዕውቀት በእውነተኛው የእግዚአብሔር ዕውቀት የሚቀየረው በኢየሱስ ነው። ሰው ስለ እግዚአብሔር በያዘው ግምታዊ ግንዛቤና በእግዚአብሔር እውነተኛ ማንነት መካከል የተዘረጋውን ታላቅ ገደል መሻገሪያው ድልድይ ኢየሱስ ብቻ ነው። ከኢየሱስ ውጭ እውነተኛ የእግዚአብሔር ዕውቀት የለም። ወልድ አብን በመግለጥ ጕዳይ ፍጹም ሉዐላዊ ነው። እግዚአብሔር የሚታወቀው በእግዚአብሔር ብቻ ነው። እናም ወልድ ሰው ሲሆን መለኮትነቱን ጠብቆ ካልሆነ፣ ቃል ሰው ሲሆን ቃልነቱን ትቶ ከሆነ፣ እርሱ እግዚአብሔርን ሊገልጥ አይችልም። ወሰን የለሹን አምላክ ውሱን ሰው ችሎ አይገልጠውምና።

Komentáře • 23

  • @alula961
    @alula961 Před rokem

    በጣም ድንቅና ጉሩም መልእክት ነው ተባረክ ዘመንህ ይባረክ

  • @Kidist_
    @Kidist_ Před rokem

    A wonderful explanation Paulos! Learning so much Praise the lord🙏!

  • @selamsemanhe-iw3jy
    @selamsemanhe-iw3jy Před rokem +1

    ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ስለሆነ እግዚአብሔርም በእግዚአብሔር ብቻ ስለሚገለጥ ሰው የሆነው አምላክ እግዚአብሔር ወልድ አባት የሆነ አብ አባት ፍቅሩን በልቤ ያፈሰሰ መንፈስ ቅድስ ።
    እንኳን እግዚአብሔርን የእራሴን የመኖር ትርጉም በጠፍኝ ሰአት ከራሴ ያስታረቀኝ እሱ
    እንደገና በእውነተኛው የእግዚአብሔር ፍቅር እውቀት መሰጠት እና ትጋትህ በፍቅሩ እየነደድኩ የበለጠ ልቆ ከአይምሮም በላይ ሆኖብኝ እግዚአብሔር እግር ስህ እንደገና ምንም አላውቅህም እኮ ብየ እንድንበረከክ ደግሞ ላውቀው ልኖረው ልገኝለት የእኔን እያስጣለ የእሱን እንዲጭንብኝ እንዳለው አይነት ምህረት እንደተቀበልኩት ፍቅር ቸርነት ይቅርታ ብዛት ይቅር እንድል በእሱ ከእሱ ለእሱ ልኖር እንድናፍቅ ያረገኝ
    አንተን አስተምሮ ለእኔ እና ለወገኖች ያሳጠቀልን የረዳህ ጌታ ይባረክ
    አመሰግናለሁ እግዚአብሔር ይስጥልኝ 🙏❤🙏
    ማነው እኔን ያነሳኝ 😭😭😭😭😭😭😭
    አባባ እውድሃለሁ ❤
    ሃሌ ሉያ አንተ እኔን መስለህ አምላክነትህን ሳትቀይር ባትመጣልኝ እንዴት እንዴት እንዴት እሆነበር አንተ አንተ ነህ

    • @PaulosFekadu
      @PaulosFekadu  Před rokem

      አስተያየቶችሽ የሚያበረታቱ ናቸው። እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

    • @selamsemanhe-iw3jy
      @selamsemanhe-iw3jy Před rokem

      @@PaulosFekadu “በጎውን ማን ያሳየናል? እኔን ጨምሮ ብዙዎች ናቸው በአንተ በባለቤትህ በወንድምህ በጓውን መንገድ ካሚያዮት ዋነኛዋ ነኝ ብዙ የተደረገለት እንደሚባል እየቀናሁባችሁ ያገኛችሁ እንዲያገኘኝ እየተገኘሁለት ነውና በድጋሚ ስለትህትናህም አመሰግናለሁ እውነተኛ መሰረት ያለው እውቀትን ያወቀ እንዳንተ እንደሚሆንም ተምሬያለሁ 🙏❤🙏

    • @PaulosFekadu
      @PaulosFekadu  Před rokem

      ክብር ሁሉ ለጌታ ይሁን። በጸሎትሽ አስቢኝ።

    • @selamsemanhe-iw3jy
      @selamsemanhe-iw3jy Před rokem

      @@PaulosFekadu አሜን 🙏❤🙏
      ድፍረት እሱ ሆኖኝ እንዳውቀው ባስተማርከኝ ቁጥር ሁሌም እንዲረዳህ እፀልይልሀለሁ አሁንም ይረዳኛል
      ለቤትህ ሰዎች ሁሉ እፀልያለሁ።

  • @yisehakkebede5400
    @yisehakkebede5400 Před 10 měsíci

    ወንድም ጳውሎስ በጣም በጣም ደስተኛ ነኝ። በእውነት የሚገርም የማስተማር ፀጋ አለህ ። የዚህን ትምህርት ክፍል 1 እንደተማርኩ "የእግዚአብሔር ልጅ" የሚለው መፅሃፍህን በችኮላ ነው የገዛሁት። በእውነት ካንተ ብዙ መማር ችያለሁ ።ጌታ ኢየሱስ ፀጋውን ያብዛልህ!

  • @AshenafiAdisu-dg8sl
    @AshenafiAdisu-dg8sl Před měsícem

    Thank you,But why not episode 14

  • @KeepsakeSelamu
    @KeepsakeSelamu Před měsícem

    tsega yibzalih paul
    gin ene bicha negn part 14n maggnet yalchalkut ?

    • @PaulosFekadu
      @PaulosFekadu  Před měsícem

      czcams.com/video/-LuPMlMNp-U/video.html

  • @abeldebero9167
    @abeldebero9167 Před rokem +2

    ወንድም ጳውሎስ ፈቃዱ Comment ማደርግልህ ነገር👉 ትምህርቱ እጅግ ድንቅና መሰረታዊ ቢሆንም ግን ኦዲዖ ብቻ መሆኑ ትንሽ ቦሪንግ እንዲሆን ሳያረገው አይቀረም፤ እኔ አሁን እስከ ክፍል ስድስት ተከታትዬው ነበር፤ ነገር ግን "ነገር በዓይን ይገባል" እንዲሉ ቪዲዖ ቢሆን የተሻለ ነውና ኦዲዖ ምታረግበትን ጊዜ ላይ ትንሽ መስዋዕትነት ወስደህ ቪዲዖ ብታረግልን በይበልጥ እያየንህ እየሰማንህ እንማራለን ማለት ነው። በተረፈው ለእስካሁኑ ትጋትህ ፀጋ ከመጠን ይልቅ ይትረፍረፍልህ።

    • @PaulosFekadu
      @PaulosFekadu  Před rokem +3

      እግዚአብሔር ይስጥልኝ ወንድሜ። ስለ አስተያየትህ አመሰግናለሁ፤ ትክክልም ነህ። ይህን ግን በዚህ መልኩ ማዘጋጀት የጀመርሁት ከሁኔታዎች አስገዳጅነት ብቻ ሳይሆን፣ መኪና እያሽከረክሩ ወይም በእግር እየተጓዙ መስማት ለሚፈልጉ ሰዎች ነው። በቅርቡ በሌሎች ርእሶች ላይ በምስል የታገዙ ዝግጅቶችን እናቀርባለን።

    • @abeldebero9167
      @abeldebero9167 Před rokem +1

      በጣም አመሰግናለሁ ስለ መልሱ። እኔም ጥያቄዬን ያነሳሁት በምስባከ ጳውሎስ ላይ ምታስተምራቸውን ትምህርቶች ኖት በመያዝ ስለምማረው ነው። ኦዲዖ ግን ብዙም ኖት ለመያዝ አመቺ ስላሎነልኝ ነበር። ጥያቄዬ ተመልሷል አመሰግናለሁ🙏 በሌላ ቪዲዖ እጠብቃለሁ ስለሁሉም ግን ተባረክልኝ።።።።

    • @PaulosFekadu
      @PaulosFekadu  Před rokem +1

      @@abeldebero9167 ክብረት ይስጥልኝ

  • @fikru-xe8iv
    @fikru-xe8iv Před rokem +1

    ይህን መጽሐፍ በነፃ በpdf ማግኘት ይቻላል?

    • @PaulosFekadu
      @PaulosFekadu  Před rokem

      በነጻም በዲኤፍም አይገኝም

    • @fikru-xe8iv
      @fikru-xe8iv Před rokem +1

      @@PaulosFekadu ok tnx God bless you betimihirtu ejig eyetebarekin new be blessed forever

    • @PaulosFekadu
      @PaulosFekadu  Před rokem

      @@fikru-xe8iv አሜን

    • @nemo-setsup.7636
      @nemo-setsup.7636 Před rokem

      መጋቢ እንደ ሁልጊዜው እጅግ ማራኪ አቀራረብ ነው። We are lucky to have such the great brother..
      We thank you God through Jesus christ. Where shall we get ur book in Addis dear brother?