የእግዚአብሔር ልጅ ምን ማለት ነው? (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 26)

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 30. 01. 2024
  • መላእክት የእግዚአብሔር ልጆች ተብለው ተጠርተዋል (ኢዮብ 1፥6፤ 2፥1፤ 38፥7)። የዕብራውያን ጸሓፊ ግን ከመላእክት መካከል እግዚአብሔር ማንንም ልጄ በማለት እንዳልጠራና አባትም ሊሆናቸው ቃል እንዳልገባ ይናገራል (1፥5-6)። ስለዚህ መላእክት የእግዚአብሔር ልጆች የሆኑበትና ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ የተባለበት ልጅነት አንድ ዐይነት አይደሉም ማለት ነው። በአንድ በኩል፣ “እስራኤል የበኵር ልጄ ነው” በማለት ስለ ተጻፈ የእስራኤልን የበኵር ልጅነት እናውቃለን (ዘፀ. 4፥22፤ ኤር. 31፥9)። ነገር ግን መላእክት የተፈጠሩት ከእስራኤል መመረጥ በፊት ነው። ታዲያ መላእክት ቀድመው ተፈጥረው፣ እንዴት እስራኤል የበኵር ልጅ ልትሆን ትችላለች? በሌላ በኩል ደግሞ፣ ኢየሱስ የእግዚአብሔር በኵር መሆኑን መጽሐፍ ይመሰክራል፤ “ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ …” የተባለው ስለ እርሱ ነውና (ሮሜ 8፥29፤ ዕብ. 1፥6)። ታዲያ እስራኤል በኵር ሆና፣ ኢየሱስም እንዴት በኵር ይሆናል? ይህም የተለያየ ዐይነት የእግዚአብሔር ልጅነት ስለ መኖሩ ተጨማሪ ማስረጃ ነው።
    አይሁድ ከጌታ ኢየሱስ ጋር በሚከራከሩበት ወቅት፣ “አንድ አባት አለን፤ እርሱም እግዚአብሔር ነው” በማለት ተናግረዋል (ዮሐ. 8፥41)። ኢየሱስ “እግዚአብሔር አባቴ ነው” ሲል ግን ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር እኩል እንዳደረገ ገብቷቸው ሊገድሉት ወስነዋል (ዮሐ. 5፥18፤ 19፥7)። ለምን? ምክንያቱም የእግዚአብሔር ልጅነት ሁሉ አንድ ዐይነት አይደለም።
    በዚህም ላይ መጽሐፍ ቅዱስ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር አንድያ (ብቸኛ) ልጅ መሆኑን እየነገረን፣ በእርሱ የሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ልጅነትን እንደሚያገኙ ጨምሮ ያስተምረናል። ስለዚህ የተለያየ ዐይነት የእግዚአብሔር ልጅነት መኖሩን መቀበል ይኖርብናል።

Komentáře • 16

  • @Kidist_
    @Kidist_ Před 6 měsíci +1

    What a precious message! Many more blessings for your dedication and love of the truth. 🙏

  • @surafeleyob5914
    @surafeleyob5914 Před 6 měsíci

    wooooooooooooooooow TEBAREK zemenh yilemilm .................ewinetm paulos

  • @tutukebede2236
    @tutukebede2236 Před 6 měsíci

    ጌታ አብዝቶ አብዝቶ ይባርክህ ፀጋው ይብዛልህ ወንድም ጳውሎስ

  • @selammenberu6359
    @selammenberu6359 Před 6 měsíci

    የጌታ ፀጋና ሰላም ይብዛልህ ወንድሜ ፖል ❤።
    ይህንን ታላቅ የምስራች ለብዙዎች እንደታደርስ ባንተ ውስጥ የሰራ መንፈስ ቅዱስ ይባክ ።ወንድሜ በዚህ ትምህርት ብዙ ተጠቀምሁ መፅሐፉንም ገዝቼ እያነበብኩ ነው ህይወት የሚገኝበት ትምህርት ነው ❤
    ባለጠጋ የሆነው ጌታ በብዙ ይባርክህ ❤❤።

    • @PaulosFekadu
      @PaulosFekadu  Před 6 měsíci

      እግዚአብሔር ይመስገን። ለእርሱ ክብር ስለዋለ ደስ ይለኛል።

  • @user-zt5xg9qs5r
    @user-zt5xg9qs5r Před 6 měsíci

    ፀጋ ይብዛልህ

  • @tigistketema6695
    @tigistketema6695 Před 4 měsíci

    ፖልዬ እንዴት እንደምወድህ በጣም ስዕላዊ ከጭንቅላት በማይጠፋ መልኩ ነዉ ምታስረዳዉ ጌታ ኢየሱስ ይባርክህ❤

    • @PaulosFekadu
      @PaulosFekadu  Před 4 měsíci +1

      የጸጋው ባለቤት ክብር ይሁንለት።

  • @elsaweldemariam1682
    @elsaweldemariam1682 Před 6 měsíci

    welcom back beloved brother Geta abzito yabrkih❤

  • @Yared-hq1ys
    @Yared-hq1ys Před 5 měsíci +1

    ሰው እንዴት እንደዚ አይነት እውቀት ይኖረዋል። ኦኦ ጳውሎስ ዘመንህ ይባረክ። አንድ ነገር ግን አስተያየት ልስጥ:- ሶሻል ሚዲያ ብዙሀኑን የሚደርስ ነው እና አሁን ደሞ ብዙሀኑንን ለመድረስ እንደ ቲክታክ ያለ አይመስለኝም። የኛ ልጆች በብዙ ነገር ተወስደው ጭምልቅልቅ ቢልም እናንተ ስላላችሁን ነው ምንፅናናው።እና ጳውሎስ ወደ ቲክቶክ ብቅ ብለህ ብታሳርፈን። ቲክቶክ ብትጀምር ብዙ የደበዘዘው ነገር ይጠራል ብዬ አምናለው።እኛም ብዙ እንማራለን ቲክቶክ ላይ ያሉ እቅብተ እምነት ላይ ለመስራት እየተፍጨረጨሩ ያሉትም ከአንተ ስር ሆነው ይማራሉ ብዬ አስባለው።ብታስብበት ደስ ይለኛል።ወንጌል አማኝን የሚታደግ በአንተ ደረጃ ያለ ሰው ሶሻል ሚዲያው እየቃተተ ነው።

    • @PaulosFekadu
      @PaulosFekadu  Před 5 měsíci

      አመሰግናለሁ። አሁን ያልጨረስሁት ሥራ አለብኝ፤ ያን ስጨርስ በስፋት ልመጣ እችላለሁ።