ክርስቲያን እና ፖለቲካ (ቤተ ክርስቲያን እና ፖለቲካ) A Christian and Politics (Church and Politics)
Vložit
- čas přidán 21. 07. 2018
- ወደ ጀመርኩት ፈውስ እና የፈውስ ቀውስ እመለሳለሁ። የሰሞኑ የፖለቲካ ትኩሳት ይህንን እንድል አስገደደኝ።
ከቪድዮው ጥቂት ቃላት . . .
. . . በዚህ ቪድዮ ደጋግሜ ያልኩት መፈክሬ፥ 'ክርስቲያኖች ጤናማ ፖለቲካውያን ይሁኑ፤ ቤተ ክርስቲያን፥ ወይም አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ግን ከፖለቲካ ትጽዳ። ክርስቲያኖች ፖለቲከኛ ሲሆኑና ከሆኑ ጥሩ ፖለቲከኛ፥ ክርስቲያን ፖለቲከኛ ይሁኑ።' የሚል ነው።
. . . አቢይሜኒያ እኔ የቀመርኩት ቃል አይደለም። አለመሆኑን ያወቅኩትም ለዚያ ጽሑፍ ከተሰጡት ምላሾች ውስጥ ነው። ስጽፈው ከዚያ በፊት አልሰማሁትምና ስለዚያ ነው የተረጎምኩት። ቃሉን ዶ/ር ብርሃኑ ሌንጂሶ የተባለ የሳን ሆዜ ካሊፎርኒያ ሰው ነው የጻፈው። እኔ የጻፍኩት ጁን 28 ነው፤ እርሱ የጻፈው ደግሞ ኤፕሪል 26 ነው፤ ከሁለት ወራት ቀድሞ ማለት ነው።
. . . ክርስትናን እንደ ክትባት የተወጉ ወይም የተለበለቡ ክርስቲያኖች አደገኞች ክርስቲያኖች እንደሆኑት ሁሉ የተለበለቡ ወረተኛ ፖለቲከኞችም አደገኞች ፖለቲከኞች ናቸው። በሰሞነኛ ፖለቲካዊ ወላፈን ተገርፈን ወረተኛ ፖለቲከኞች እንዳንሆን እፈራለሁ።
. . . አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ፖለቲከኛ መሆን የለባትም ስል በዚያች አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስን የሚያመልኩ ሆነው ፖለቲካዊ አቋምን በተመለከተ በተለያየ ጎራ የተሰለፉ ሰዎች ሊኖሩ ስለሚችሉ ነው።
. . . አንዳንድ ሰዎች ቤተ ክርስቲያን የመንግሥት ሕሊና ናት፥ የኅሊና ሚና መጫወት አለባት ይላሉ። ይህንን አሳብ ከየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እንዳገኙት አላውቅም። . . . ቤተ ክርስቲያን የመንግሥት ሕሊና አይደለችም። ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ እጮኛና ሙሽራና የእርሱ አካል ናት። መንግሥት የራሱ ሕሊና አለው። ሕሊናውን አደድቦ፥ ሕሊናውን አደንዝዞ፥ አልሰማም ብሎ ካልተቀመጠ በስተቀር የራሱ ሕሊና አለው። ጋዜጠኞች፥ ጦማሪዎች፥ ደራሲዎች ሕሊና ናቸው፤ ከያንያንና አርቲስቶች ሕሊና ናቸው፤ የሕዝብ ውክልና ያላቸው እንደራሴዎች ሕሊና ናቸው፤ ሌሎችም በመንግሥታዊ መዋቅር ውስጥ የሚገኙ የሕሊና ሚና የሚጫወቱ ክፍሎች . . .
. . . እስካሁን ባለው አካሄድ በዶ/ር አቢይ ላይ ከምስጋናና ከአድናቆት ቃል በቀር ሌላ ምንም ሊጻፍ አይቻልም። . . . ዶ/ር አቢይ እያደረገ ያለው አካሄድ ያልተለመደ ብቻ ሳይሆን ብዙዎችን የሚያስፈነጥዝ አካሄድ ነው። ፍቅር፥ ምሕረት፥ ይቅርታ፥ ዕርቅ፥ ሰላም፥ እነዚህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ፥ ክርስቲያናዊ እሴቶች ናቸው። ስለዚህ ይህ የማያስደስተው ክርስቲያን ሊኖር አይችልም፤ የለምም። . . . እንደ መጥፎ ዕድል ሆኖብን እኛ አፍሪቃውያን፥ እኛም ኢትዮጵያውያን የሕዝብ ልብ ያለው፥ ሕዝብ ሕዝብ የሚሸትት መሪ አይወጣልንም። ወይም ቢያንስ፥ እስካሁን አልወጣልንም። አሁን ሕዝባዊ ሰው ማየት (መኪና እያስቆመ ከሕዝብ ጋር መተቃቀፍ የሚፈልግ መሪ ማየት) እንግዳ ነገር ሆኖብናል።
. . . ክርስቲያኖች እንደ ቤተ ክርስቲያን ሳይሆን እንደ ክርስቲያን በፖለቲካው መስክ መሰማራታቸው በጣም አስፈላጊ መሆኑን መጀመሪያ የተማርኩት ለሴሚነሪ ትምህርት ወደ ካናዳ ካመጡኝና ከቤተ ሰባቸው ጋር እየኖርኩ እንድማር ካደረጉኝ ከዶ/ር ራበርት ቶምሰን ነው። ከመጽሐፎቻቸው አንዱ From The Marketplace የተባለው እንዲያውም በዚህ ዋና ጉዳይ ላይ የሚያጠነጥን ነው። ያኔ የደርግ ዘመን መጨረሻ ነበረና ፖለቲካና ክርስትና ዓይንና ቁልቋል ከሚመስሉበት ጊዜና አገር ነው የመጣሁት። ዶ/ር ቶምሰን ደግሞ በካናዳ የተቀመሙ ፖለቲከኛና ቀደም ባሉት ዓመታት የፓርቲ መሪም ነበሩ። ኢትዮጵያን ደግሞ ከውስጥ እስከ ውጪ የሚያውቁ፥ ጣሊያን ሲወጣ የእንግሊዝ ጦር የአየር ኃይል አብራሪ ሆነው የገቡ፥ . . .
. . . ጳውሎስ ከፊልጵስዩስ ሲወጣ እንጂ ወደ ፊልጵስዩስ ሲገባ እንደ ሮም ዜጋ ሆኖ አልገባም። የገባው፥ ያገለገለው፥ መከራ የተቀበለው እንደ ሮማዊ ዜጋ ሳይሆን እንደ ሰማያዊ ዜጋ ሆኖ ነበር። ወንጌልን ነው የሰበከው፤ ስለ ወንጌል ነው ያንን መከራም የተቀበለው። . . . በሁለቱ ዜግነቶቹ መሐል መስመር አሰመረ።
. . . አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ማተኮር ያለባት ዋና ተልእኮ፥ ታላቁ ተልእኮ፥ የወንጌል ጉዳይ ነው። ወንጌልን መስበክ፥ ማጥመቅ፥ ማስተማር፥ ደቀ መዛሙርት ማድረግ። . . . ቤተ ክርስቲያን ልዩ ተልእኮ ያላት አካል ናት። እርሱም ወንጌል ነው። የእርሷ ዓይነት ልዩ ተልእኮ ያለው ሌላ አካል በምድር ላይ የለም። በፍጹም የለም። መንግሥት ውጪያዊ ቁጥጥር ሊያደርግ የተሾመ ሲሆን ቤተ ክርስቲያን ግን ውስጣዊ ለውጥን ለመፍጠር ልዩ አደራና ተልዕኮ የተሰጣት አካል እና ተቋም ናት።
መልካም መመልከት ይሁንላችሁ።
ዘላለም ነኝ።
በርታ ወንድም ዘላለም ። ጠለቅ ያለ የቃሉም መረዳት ስላለህ ያስተዋለ ይጠቀማል።
ስሜትና አህምሮ አይፋቱ። ቅንነት ያለበት አስተምሮ። ተባረክ! ጸጋ ይብዛ!
ውድ ወንድሜ ዘላለም እግዚአብሔር ዘመንህን ይባርክልኝ ።ብዙዎቹ ጽሁፎችህ ለእኔና እኔን ለመሰሉ ግራ ለተጋቡት እጅግ በጣም ጠቃሚዎች ናቸው ።እውነትን ላለመካድ ብዬ ለምሰጠው አስተያየት ብዙዎችን አስቆጥቻለሁ ።ያንን በማድረጌም እራሴን ኮንኛለሁ።ዛሬ ግን በጥቂቱም ቢሆን ብር ሃን በርቶልኛል እግዚአብሔር ይመስገን ለእውነት እቆማለሁ ።እግዚአብሔር ይባርክህ የኔ ውድ ወንድሜ ያንተ የሆኑት ይባረኩ።በአንተ ብዙ ተጠቅሜአለሁ ብዙዎችንም ጠቅሜአለሁ አብሶ በሃሰተኞች ነብያት ዙርያ ።አሁንም በርታና አበርታን ።
💙💙 Hakika ika emo Tabarki
ጌታ ይባርክህ ወንድሜ
ጌታ እኛን ሀጥያተኞች ሌሎችንም በፍቅር ነው የማረከው በሀይልና በግዴታ አልነበረም ስለዚህ ቤተክርስቲያን ማለት እኛ በፍቅር በጨውነት በብርሀንነት በመፍትሄነት ስንገለጥ ሁሉም ወደጌታ ይመጣል ለጌታም ይገዛል
ሃገር የጋራ ነው ሃይማኖት የግል ነው። ሁሉም ሃይማኖት በያለበት ለገዥው መንግስት ይፀልይ። ፖለቲካና ሃይማኖትን እንለይ። የዘርና የሃይማኖት ልዩነትን አጥብቀን እንቃወም። ጥሩ መልክት ነው ወንድሚ።ተባረክ።
ኣሜን ጌታ ይባርክህ በጣም ኣስተማሪ ነው ተምሬበታለው።ኣሁንም ለቅዱሳን ሁሉ ማስተዋልን ይስጠን።
ውንድሜ ዘመንክ ይባርክ ፀጋው ይብዛልክ 😚😚😚😚😚😚❤❤❤❤❤❤👈
ወድሜ ጌታይባርክ በጣም ትክክል ነው ጌታ ማስታውል ይስጠን ።
በጣም። ትክክል ።ጌታ። ይባርክህ።
go ahead
እግዚአብሄር ይባርክካ ኩሉ ግዜ ምሀሪ ለባም ካብ ስምዒት ውጽእ ኢልካ ን እግዚአብሄር ትርኤሉ ኢካ ትምህር እሞ ከማካ ይብዝሑ አምላክ ይባርክካ።
,stayed blessed; Brother!!!
WE Have To PRAY For our country and leaders God blessed Ethopiya 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
Geta Abzto ybarkh yemtastelalfewen SMS hulem Esmawalew Berta ketle
May God bless you this is spiritual understanding to have Authority of God by through the word of God.
Brother, i highly agree with you. we Christians , they say, IF WE ARE NOT ON THE TABLE WE WILL BE ON THE MENU. so we should influence with biblical principles. however it is to early to say ." P.M Abiy is a special person that he is for the people" and to give him all adoration and praise. we should continue pray without medrmer to politician's ideology.
O my GOD this is word of GOD please all Christian let's check our self back to the Bible.bless you Sir.
Ya u r right bless u
ኦኦኦኦ ተባረክ
God bless you brother.
GBU more and more! ! !
You are a blessing to all of us. Your insights and advices on current issues help to redirect Christians attention to Christ and eternity. Stay blessed!
Are your teachings broadcasting on Ethiopian Christian television programs?
zola ahunim tsega yibazalih, wodalew, ketilibet tasfeligenaleh!
ሰላም ላንተ ይሁን 😍😍😍😍
Atebya Church malet menden newe?
eyisuse,get.new.taberke
bayee garii dha... Addaa bafachuu fi waqayoof akkaa jiranuu nuu damaqsaa!!!!!! jaladhen sii dhagahee!!!!!!!!!!!!!!
ወንድሜ ዘለአለም በጌታ ስም ሥልክህ ማገኘት ብችል እንዴት ደስ ባለኝ።
ዘሌ በመፅሐፍ መልክ ብታጠናክርልን??????
anten.bilokrystiyan..leba.eshi
Egeziabeher meheret yaregelachehu sewen gera tagabalachehu ande wenegel anede wedemochen be mekeses badebabay mawared be ewenet agelegayoch nachehu???????????????
Azenalehu
ante ko kali atkime wushetami neki tensh atafirmi kali setanabi
ወንድም ዘላለም ስለ ወቅታዊና በሳል ጽሁፍህ ጌታ ይባርክህ። ዶ/ር ዐቢይ ወደ ስልጣን የመጡበት ወቅት የተወሰኑ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት የቅርብ ደጋፊዎችና አባላት ካልሆኑ በስተቀር ኢትዮጵያውያን እጅግ የተጨነቅንበት፣ ከቅኝ ግዛት በማይተናነስ ስነልቡናና ሰብእና የሚመሩትን/የሚገዙትን ሕዝብ የሚጠሉ ገዥዎች የሰለጠኑበት፣ እርስ በርሳችን ልንጠፋፋ አፋፍ ላይ የደረስንበት፣ ወጣቶች በአገራቸው ኖረው የስራ እድልና ተስፋ አጥተው ስደትና በባእድ ምድር ሞትን የመረጡበት፣ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ተዘርፎ በጥቂት ስግብግቦች እጅ የገባበትና ስንት ትውልድ ከፍሎ የማይጨርሰው እዳ የተዘፈቀበት፣ የሀገር ድንበርና ለአላዊነት ማስከበር የተገባው ሰራዊት ደመወዙን የሚከፍለውን ሕዝብ የሚጨፈጭፍበት፣ መሪና በተለያዪ የመንግስት መዋቅሮች የተቀመጡ ባለስልጣኖች ሕዝቡን በውሸትና ኢሞራላዊ አንደበት እጅ እጅ ያሉበት በአጠቃላይ ሀብታም ድሃ የተማረ ያልተማረ ገጠር ከተማ ሳይለይ አገሩን ጥሎ ለመሄድ መውጫ እየፈለገ ባለበት ጊዜ መሆኑ ለእርሳቸው የተሰጠውን ድጋፍና አክብሮት ዐቢይማኒያ ሊያሰኘው ቢችል አይገርመኝም። እርግጥ ዶ/ር ዐቢይን የምንደግፈው እርሳቸውን በእግዚአብሔር ፋንታ ሁሉን ቻይ ሆነው ሁሉንም ችግሮቻችን እርሳቸው ብቻ ይፈቱልናል ብለን አስበን ሳይሆን ከሌብነትና ዘረኝነት በጸዳ ማንነትና ምሳሌያዊ አመራር የተበላሸውን የመንግስት መዋቅሮች አድሰው ሕዝብን በአገር ውስጥና ውጭ ዜጎችን አነቃንቀው ሁሉም ወገን የሚጫወትበትን ሜዳ ይፈጥሩልናል ብለን ነው። እርሳቸውን ስንደግፍ የምንጠብቀው ለውጥ በወራትና ውሱን አመታት ብቻ ይመጣሉ ብለንም አይደለም። በአመታት መካከል የተፈጠረውን ምስቅልቅል ከለውጡ ተጻራሪዎች ጋር እየተናነቁ ማስተካከል ቀላል ጥረት እንደማይጠይቅም እንገነዘባለን። ሕዝብ የሚሳተፍበት እድል ሲፈጠር ተችና ተተች አይኖርም ባይባልም የተችው ቁጥር ስለሚቀንስ ለውጡ አበረታች ይሆናል። እርሳቸው ሰው በመሆናቸው ስህተት ሲሰሩ "ስቀለው" አንልም እንዲታረሙ በተገቢው መንገድ ቅሬታን ማስተላለፍ ይገባናል እንጂ። ይህንን ሰዋዊ ውሱንነታቸውን በመዘንጋት "worship" አደርግሃለሁ ወይም ስህተት ተሰርቶ ሲገኝ ትችት የሚያቀርቡትን አካላት መቃወም ዶ/ር ዐቢይንም ሆነ እኛ ኢትዮጵያውያንን ስለማይጠቅመን ልንታረም ይገባል። ምን ያህል ሰው እንደሚሰማው ባላውቅም መልእክትህ ግን ጥሩ ግንዛቤ የሚፈጥር መልእክትና ማስጠንቀቂያ ነው። ጌታ አብዝቶ ይባርክህ!!!
No give you attention for your word .... Stop Pointing your hands against God's Anointed once..... leave it for God, because God gives everyone according to His ways;therefore,mind your business ...
I will come from UK and talk you....
God said touch not my anointed and do not harm my prophets.....
You will pay for that.....!!!!!
Abet ante seweye! Hulu gize tekawemo becha??
Jerusalem Fessehaye
ምኑ ነው ተቃውሞ? ልታሳዪ ትችያለሽ?
እሺ ጥሩ ነው ግን በ5ኦፊሶች ውስጥ ያሉ አገልጋዮች የመንግስት ሹመኛ ሆነው መስራት ይችላሉ?
ሞዛዛ፤ያንተና ሳሚ ተብየ ነገረ ሥራ ሁሉ ለዛ ቢስ ነው።