ለባዕድ - ቅይጡ ወንጌል የዘላለም ጌታቸው (ፖዝ) የድንጋጤ የአጸፋ ምላሽ።

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 2. 07. 2020
  • ተልእኮ ለትውልድ ወይስ ከልት ለትውልድ?
    ዘላለም ፖዝ ለባዕድ - ቅይጡ ወንጌል ዘጋቢ ፊልም በድንጋጤ ምላሽ የሰጠበትን ሥራውን፥ 'የክርስቶስ ተቃዋሚው መንፈስ' በእንግሊዝኛ ANTI-CHRIST - documentary ብሎ ነው ስም የሰጠው። ለዚያኛው የሰጠው ስያሜ መሆኑ ነው፤ ግን አውቆ ይሁን ወይም ሳያውቅ ለራሱ ቪድዮ ነው ይህን ስያሜ የሰጠው።
    ዘጋቢ ፊልሙን የሠሩትንና የተሳተፉትን እንዲሁም ቆንስላውን የሚቃወሙትን ደግሞ፥ ጥቅማቸው የቀረባቸው፥ ቀድሞ የወንጌል አማኙን ሲመሩ የነበሩ፥ መሪዎች የነበሩ፥ ሕጋዊነት የሌላቸው፥ ተንኮላቸው አልሳካ ያላቸው፥ ስላለፍንበት 30 ዓመት ምንም ነገር የማያውቁ፥ ሶሻል ሚዲያ ላይ የሚጮሁ፥ ከአንዳንዶች ጋር ፀብ ያላቸው፥ የጥፋት ተልእኮ ያላቸው ሰዎች ብሏቸዋል፤ አስብሏቸዋል።
    በቆንስላው ጉያ ተተግኖ ክርስቲያኑን ማኅበረ ሰብ አስተማሪና አስጠንቃቂ የሆነ ዘጋቢ ፊልምን፥ 'የክርስቶስ ተቃዋሚው መንፈስ' ወይም ANTI-CHRIST - documentary ብሎ መሰየምና ተቃራኒ ምላሽ መስጠቱ የራሱን ብቻ ሳይሆን የቆንስላውንም መልክና ቅርጽ ብቻ ሳይሆን አቋምና መደበቂያነትም ማሳየቱ መሆኑን እንዲሁም በቆንስላው ውስጥ እንደ ዘላለም ፖዝ ያሉ የመናፍቃን መሪዎች የተሰገሰጉ መሆናቸውን መግለጡ መሆኑን ያሰበበት አይመስልም።
    ዘላለም ነኝ።

Komentáře •