እግዚአብሔር ይመጣል (መዝ. 50)

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 22. 08. 2024
  • መዝሙር 50 በዳዊት ድንኳን ውስጥ መዘምራንና የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋቾችን እንዲመራ ከተሾመው ከአሳፍ ዝማሬዎች አንዱና የመጀመሪያው ነው። አሳፍ እግዚአብሔር ሊፈርድ ወደ ቤቱ እንደሚመጣ፣ ፍርድንም ከቤቱ እንደሚጀምር ይጽፋል። በሲና ተራራ ለእስራኤል ሕግን የሰጠው እግዚአብሔር ሕጉ መፈጸም አለመፈጸሙን ሊቆጣጠር ወደ ጽዮን፣ ወደ መቅደሱ እንደሚመጣ ይነግረናል። ሲመጣም የሚፈርደው በሁለት ነገሮች ነው። አንዱ ሕዝቡ ለእሱ ባለውና እርስበርሱ ባለው ፍቅር ነው። ይህም በአዲስ ኪዳን ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርት ጋር ይስማማል። የጌታ ትምህርት የሚጠቃለለው እግዚአብሔርን … ውደድ፤ ባልንጀራህን … ውደድ በሚል ነው። ዛሬም ጌታ ፍርድን ከቤቱ እንደሚጀምር ጴጥሮስ ይነግረናል። ፍርዱም የሚመዘነው ለጌታ ባለንና እርስበርስ ባለን ፍቅር ነው። ይህ መልዕክት ጁላይ 22፣ 2021 በፎር ኮርነርስ ቤተክርስቲያን ሲልቨር ስፕሪንግ፣ ሜሪላንድ የተላለፈ ሲሆን ከልብ ለሚሰሙት መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለው የጊዜው ቃል ነው።
    www.goldenoil.org

Komentáře • 78

  • @loveworks8432
    @loveworks8432 Před 3 lety +14

    የመንፈሳዊ ሂወቴን እንደዋዛ እንዳላየዉ አስተምሮትህ ብዙ ብዙ አግዞኛል ጌታ ይባርክህ ጌታ ፀጋዉን ያብዛልህ

  • @tedrosteklu9771
    @tedrosteklu9771 Před 3 lety +15

    እጅግ ድንቅ ትምህርት ስለ አንተና አንተን ስለሚመስሉ እውነተኛ ምስክሮችና ቅሬታዎች ሁልጊዜ አምላኬን አመሰግናለው በአንተ በኩል እግዚአብሔር ብዙ ነገር እያስተማረኝ ነው በነገር ሁሉ ተባረክ ወንጌላዊ ያሬድ።

  • @emebetyohannes3744
    @emebetyohannes3744 Před 2 lety

    Those 13 people who did thumbs down 👎 to this amazing man of God/ who preach nothing but the true gospel/ they need help. I pray to them that God will enlighten their heart and mind.

  • @tedro713
    @tedro713 Před 3 lety +14

    እጅግ በጣም ነው የሚገርመኝ በስብከቱ ውይም በትምህርቱ ውስጥ ሁሌም እግዚአብሔር አብን: እግዚአብሔር ወልድን: እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን: እግዚአብሔር አንድ አምላክን ነው የማይበት::
    እጅግ በጣም ነው የሚገርመው በዚህ መጨረሻው ዘመን እንዲህ ስላሴን የሚያመለክቱ ሰባኪዎችን ያብዛልን::

  • @liyaliya1302
    @liyaliya1302 Před rokem

    እግዚአብሔር ይባርክህ ውይ እንዴት ደስ እንደሚለኝ

  • @mekedesmezmur4057
    @mekedesmezmur4057 Před 3 lety +3

    አዎ እግዚአብሔር ይመጣል ምንም እንኳን የዘገየ ቢመስል እደሚመጣና ስንዴውን ከእንክርዳደ እደሚለይ እውን ነው ይህን እናምነለን ምክንያቱም ጌታ ስለ ቃሉ አይዋሽምና እግዚአብሔር ሆይ የቃልህን ብርሃን አብራልን መንገዳችንም በፊትህ የተቃና ይሁን የስማነውን በልባችን አሳድርልን በተግባርም እንሄድበት ዘንድ እርዳን አሜን መንጌላዊ ያሬድ ጌታ ያክብርህ

  • @derartutola7404
    @derartutola7404 Před 2 lety

    ጌታ አብዝቶ ይጨምርብህ ያጥለቅልቅህ በጣም አሰተማሪ ና የነፍስ ምግብ የመንፈስ ተሐድሶ ነው።የተባረህ ነህ!

  • @kumnegerbelete5451
    @kumnegerbelete5451 Před 2 lety +1

    ያሬድዬ ስወድክ እኮ አንተ የጌታ ባርያ በትምህርትህ እንዴት ጌታ እደሜባርከኝ ይብዛልህ !!!! ❤❤❤❤ አገርቤትም ብቅ በል ደግሞ !

  • @fruityegeta2248
    @fruityegeta2248 Před 3 lety +1

    እግዚአብሔር በየዘመኑ ጀግኖች የጨከኑ አሉት
    እግዚአብሔር ዘመንህን ሁሉ ይባርከዉ በምድር ላይ እንዳንተ አይነቱን የወንጌል ሰባኪዎች ያብዛልን ተባረክ ።

  • @tamirumathewos5
    @tamirumathewos5 Před 3 lety +3

    የእግዚአብሔር ሰው ወንጌላዊ ያሬድ ጌታ አብስቶ ዘመንህን ይባርክ ትምህርቶችህ ሁሉ 2016 ዓመት ጀምሬው እሰማለሁ ህይወትን የሚጥቅም ህያው ቃል ታምራለሁ ጌታ ዘመንህን ይባርክ!!!!!!

  • @tigist3038
    @tigist3038 Před 3 lety +1

    ጌታ ዘመንህን ይባርክ ይህንን ቃልበዚ መንገድ ሰምቼ አላውቅም ታላቅ መገለጥ ነው ዋው!!

  • @habatamhabatam8769
    @habatamhabatam8769 Před 2 lety

    ዛሬም ደግሜ ስማሁ እግዚአብሔር አሁንም ተናገረኝ እግዚአብሔር ይባርክህ ያሬዶ

  • @nardoesmezmur8582
    @nardoesmezmur8582 Před 3 lety +2

    ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን !! ምስጋና ሁሉ ለአንተ ይሁን ! አሜን 🙏🙏🙏

  • @ሳርዬ
    @ሳርዬ Před 3 lety +1

    Esiye ጌታ ይክበር ይመስገን ውንጌላዌ ያሬድ ዘመንህ ይለምልም በጣም ተባርካለሀ ፀጋ ይብዛልህ።

  • @romanzeleke8654
    @romanzeleke8654 Před 3 lety +3

    ሌላ ምንም አልልህም እግዚአብሔር አብዝቶ አብዝቶ ይባርክህ የጨምርልህ አመረን

  • @sebleaklilu284
    @sebleaklilu284 Před 3 lety +1

    እለት እለት ይበልጥ እግዚአብሔርን እንድፈራ ስለድርጊቴም ስለምናገረውም እያንዳንዱ ነገር እንድጠነቅ ይህ ትምህርት አስተምሮኛል። መንፈሴ እግዚአብሔርን በመፈለግ ተሞልቷል። ተባረክ ያሬዶ! ሄሜራ ይሁን 🙏

  • @semharasevaw4817
    @semharasevaw4817 Před 3 lety +1

    ክብርና ምስጋና ለ እግዚአብሔር

  • @blenberhanmamoye5801
    @blenberhanmamoye5801 Před 2 lety

    Amen tebarekelegn

  • @edenhailemariam2240
    @edenhailemariam2240 Před 3 lety +3

    መዝሙር ዳዊት 50
    23፤ መስዋእቲ ምስጋና ዚስውአለይ የኽብረኒ፣
    ነቲ ብመገዱ ዚጥንቀቕ ከኣ ምድሓን ኣምላኽ ከርእዮ እየ። 🙌🏽
    Stay blessed Evangelist Yared

  • @user-wl6zn3hk9q
    @user-wl6zn3hk9q Před 2 lety

    እግዚአብሔር የልቦናችንን አይን ይክፈት አሜን የምንጠብቀው ጌታ ድንገት ይመጣል ተባረክ በብዙ

  • @lizabellalulu7297
    @lizabellalulu7297 Před 3 lety +1

    Amen ትክክለኛው አገልጋይ

  • @marticool8700
    @marticool8700 Před 3 lety +1

    እግዚአብሔር ዘመንህን ይባርክ ያሪ፥ፀጋው ይብዛልህ!!!!

  • @salameskyes7240
    @salameskyes7240 Před 6 měsíci

    ኢየሱስ ይባረክ ያሬድዬ❤❤❤❤❤❤

  • @saronyegeta6382
    @saronyegeta6382 Před 3 lety +1

    አሜን ሀሌሉያ ክብር ሁሉ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ይሁን ድንቅ ትምህርት ነው ወንጌላዊ ያሬድ እግዚአብሔር ይባርክህ ፀጋውን ያብዛልህ

  • @abebaseyiume8949
    @abebaseyiume8949 Před 3 lety +1

    በጌታ የተወደድክ ወንድማችን ያሬድ የባረከህ ይባረክ

  • @segidbrhane2738
    @segidbrhane2738 Před 3 lety +1

    የእግዚኣብሄር ፍርድ ሲባል እግዚኣብሄር ይመጣል ማለት ነው። ፍርድ የእግዚኣብሄር መምጣት ነው!

  • @Mezmur_360global
    @Mezmur_360global Před 2 lety

    ሁሌ ከሰማሁህ በውኋላ ሌላ አዲስ የቃሉ ፍቅር ይይዘኛል.ይገርመኛል!...ጌታን ላየው ቃሉን በሌላ አዲስ መንፈስ ላነብና ላጠና እሄዳለሁ.እገረማለሁ ከምር!...ምስሉ ውስጥ አንተ ለምን እንደማትታየኝ...!ደሞ እንደ ሀፒታይዘርም ነህና በል...ፀጋ ይብዛልህ ያሬዶ

  • @beshaafina4433
    @beshaafina4433 Před 3 lety +2

    Tebarkehal yaredo bante hono geta bzuwochn lerasu eyazegaje nw

  • @bitsitasefa7971
    @bitsitasefa7971 Před 2 lety

    E/r yibarkh wendim yared

  • @fatimaathopia7378
    @fatimaathopia7378 Před 3 lety +1

    Ameen Ameen Yimtali Yee Tasifau Kali Yifatamali

  • @tagesechtesema6195
    @tagesechtesema6195 Před 3 lety +1

    አሜን

  • @EseyVS
    @EseyVS Před 3 lety +1

    Amen hallelujah... elelelelelelllllll
    Yesemay Amlak Egziabher yetemesegene yehun.
    Thankyou so much for your amazing teaching 👌👌

  • @selomephoto2757
    @selomephoto2757 Před 3 lety +4

    Amen!!

  • @healingtube9082
    @healingtube9082 Před 2 lety

    When I was small girl the way he used to narrate scripture used to inspire me. In fact God trained me after that and took me to the best theological university!

  • @romangetachewgebremariam5472

    ወንጌላዊ ያሬድ ። ጌታ ዘመንህን ይባርክ። ትምህርትህ መቼም አይጠገብም ። በዚህ ጊዜ እግዚአበሔር አንተን ስለ ሰጠን ስሙን በእውነት እባርካለሁ። አንዱ እግዚአብሔርን ከልቤ የማመሰግንበት ምክንያቴ ነህ። እራሳችንን እንድንፈትሽበት ስለመጣው ቃል ጌታ ይክበር። በግልፅና በቀላል ሁኔታም ስለ ተናገርከው ተባረክ። ለኛም ፀጋው ይብዛልን ። አሜን

  • @mesitesema9089
    @mesitesema9089 Před 3 lety +1

    Tebarek 🙏🏻🙏🏻🙏🏻

  • @eleniwoldetsadik5890
    @eleniwoldetsadik5890 Před 3 lety +3

    God bless you 🙏 I always learn a lot from Your teaching 🙏 🙌 ❤

  • @habatamhabatam8769
    @habatamhabatam8769 Před 3 lety +2

    ያሬዶ ፀጋው ይባዛልህ

  • @saved1580
    @saved1580 Před 3 lety +1

    አሜን ። ማራናታ።

  • @masaratphonetastic4360
    @masaratphonetastic4360 Před 3 lety +2

    Ameeenn haleluyaa

  • @hodanamen7083
    @hodanamen7083 Před 3 lety +5

    Glory to the almighty who used u to talk to me today🙏🏽 u have no idea how much I really needed that push ups for my spiritual life,which have been pretty dry lately. I love your ministry and the way God is using u!! It is through ur ministry that I am growing and understand who God really is and what his will is too.which has been narrated through his son Jesus Christ!! I needed God himself I needed to know him more.And through ur ministry the Holy Spirit thought me a lot. So for that reason,I want to say ,Thank you!from the bottom of my heart. My God bless you and your family.May ur Heart overwhelmed with God’s LOVE for ever and ever AMEN!

  • @aklilu.g7023
    @aklilu.g7023 Před 3 lety +3

    Dear Beloved Brother Yaredo, i always see christ in your service and I praise God for that! Keep Up the good work, may the grace of God be added more and more to your Service!

  • @mercyghebre7963
    @mercyghebre7963 Před 2 lety +1

    You are blessed 🙌🙏

  • @sl6109
    @sl6109 Před 3 lety +1

    yetesasete meredaten, zibrikrik yalen astesasaben Yeferaresewn hiwoten geta bante bizu gize aremegn… silante Getan Ameseginalhu.
    gin gena bizu endemikeregn ayalahu .. tseleyelegn..

  • @jerusalemtermeer5982
    @jerusalemtermeer5982 Před 3 lety +2

    Amen amen 🙏🏼 ❤️

  • @litahaile6749
    @litahaile6749 Před 3 lety

    ያለ እግዝኣብሄር ምንም አይደለንም ። ይምጣልን ይገኝልን ። ውድ ያሬዶ ጌታ ጸጋ ያብዛልህ ።

  • @caleba.5075
    @caleba.5075 Před 2 lety

    What a Convicting word, God bless you yaredo for listening to the spirit… I believe real revival is coming, but before that kidisina yasfeligal. Thank you.

  • @genetbushra6979
    @genetbushra6979 Před 3 lety +2

    Amen Ameen

  • @henokabraha6918
    @henokabraha6918 Před 3 lety +2

    God bless you

  • @yonasgebreyohannes6444
    @yonasgebreyohannes6444 Před 3 lety +1

    Almighty God bless you brother yaread .

  • @chamogezahegn4909
    @chamogezahegn4909 Před 3 lety +1

    I am Always Glad To Thank God That Equipped Us Throgh You. Stay Blessed.

  • @jonaswubetu8853
    @jonaswubetu8853 Před 3 lety +1

    Bless you

  • @abaytesfaye3391
    @abaytesfaye3391 Před 3 lety +1

    🙏amen

  • @mrkthry427
    @mrkthry427 Před 3 lety +3

    Waw!!! This is amazing exposition of the word of God! May God continue to bless you richly, brother Yared! We have to share it as many people as possible.

  • @abejebelay8930
    @abejebelay8930 Před 2 lety

    May God reveal more of him in your life and let his blessings bestowed up on you and your family. Lots of love and respect!

  • @misganaguchie9293
    @misganaguchie9293 Před 2 lety

    Yaredo, I really like the, "Rapture", it seems you saw my house the day I left hurrying up.

  • @Aki-rl2wz
    @Aki-rl2wz Před 2 lety

    Woww powerful teaching. God bless you 🙌🙌💙💙💙💙

  • @gammachuuturaa5319
    @gammachuuturaa5319 Před 3 lety +1

    I'm bessed with your preach, but what is the importance of telling us once again and again about the house you bought. Just praise God for what he did for you and the people of God.

  • @bereketsiyum74
    @bereketsiyum74 Před 3 lety +2

    Nice teaching, God bless!

  • @liyahailemariam7038
    @liyahailemariam7038 Před 3 lety +4

    የንጥቀት ልብስ አቀማመጡ በጣም አስቂኝ ግን ትክክለኛ አገላለጥ ነው፣ የደረሰበት ያቀዋል😃😃😃😃

    • @lalahi4412
      @lalahi4412 Před 3 lety +2

      😂😂😂😂 so true 😂😂 ቀላል ራፕቸር የተካሄደ

  • @user-rp3gw7ge7w
    @user-rp3gw7ge7w Před 3 lety +1

    ያሬዶ እንዴት ሰነበትህ

  • @segidbrhane2738
    @segidbrhane2738 Před 3 lety +1

    ፍርድ ሆነ ማለት ብርሃን ሆነ ማለት ነው!

  • @engineerhenok1136
    @engineerhenok1136 Před 2 lety

    አንተ ለትውድ በረከት ነህ

  • @ag7541
    @ag7541 Před 3 lety

    Ye Yaredon contact kalachu pls lakulgn?

  • @user-ko6sv8wn6x
    @user-ko6sv8wn6x Před 2 lety

    Foolish man with his foolish follower.
    According your philosophy God created us. But who created God is not knowen?????

  • @netsahonkubeeyesus1667
    @netsahonkubeeyesus1667 Před 3 lety +1

    Yarado yarado w/c sewede eko sayeke des yelegnal bro lemelem