ማደሪያውን መውደድ መዝሙር 84

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 22. 06. 2021
  • በዘመናችን አይተነው ከማናውቀው ዓለማችንን ከወረረ ብዙዎችን በደዌ ካደቀቀና ሚሊዮኖችን በሞት ከነጠቀ ወረርሽኝ ውስጥ እየወጣን ነው። በዚህ ጊዜ በአካል ተሰብስቦ ማምለክ ስላልተቻለ አቅሙ ያላቸው በቴክኖሎጂ ታግዘው በርቀት ያልቻሉም በቤታቸው ተቀምጠው ከርመዋል። አሁን ግን እንደ ቀድሞው በአካል ተሰባስበን የምናመልክበት በር እየተከፈተ ነው። መሸሸግ ባለብን ጊዜ መሸሸጋችን መልካም ሲሆን በአካል መሰብሰብ ባለብን ጊዜ መሰብሰቡ ለነገ የማይባል ጉዳይ ነው። በእርግጥ ባደጉት አገራት ለምንኖር በዙም እና በስልክ የምናደርገው ሕብረት ከፍተኛ ምቾት ስላለው ወደ በፊቱ ለመመለስ ጊዜ ሳይወስድብን አይቀርም። ሆኖም የቅዱሳንን በአካል ተገናኝቶ ጸጋ መካፈልን ሊተካ የሚችል ምንም ነገር የለም። ከዚህ በመነሳት ቀደም ሲል በእግዚአብሔር ቃል "ሕዝቤ ሆይ ና! ወደ ቤትህ ግባ! ቁጣ እስኪያልፍ ድረስ ለጥቂት ጊዜ ተሸሸግ" ሲለን የነበረው ወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁን አሁን ደግሞ "ማደሪያዎችህ እንደምን የተወደዱ ናቸው!" በማለት ወደ አካላዊ ሕብረት እንድንመለስ ይመክረናል። ይህ መዝሙር (መዝ. 84) ከመዝሙሮች ሁሉ እጅጉን የተወደደና በአንድ የእግዚአብሔርን ቤት አደባባዮች በናፈቀ፣ ከቆሬ ልጆች መሐል የሆነ ሌዋዊ በፍቅር፣ በናፍቆት፣ በቅዱስ ቅናት እና በእርካታ የዘመረው ነው። ዛሬ የእግዚአብሔር ማደሪያ በኢየሩሳሌም የሚገኝ መቅደስ ሳይሆን በአቅራቢያችን ያለ የቅዱሳን ሕብረት ነው። ይህም በኢየሩሳሌም ነጭ ድንጋዮች ሳይሆን ከክርስቶስ በተገኘን ሕያዋን ድንጋዬች ተገጣጥሞ የተሠራ ነው። ስለዚህ ብርድ ልብሳችንን ገፈን፣ ከአልጋችን ተስፈንጥረን ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ፤ ማደሪያዎቹን (ቅዱሳንን) እንውደድ፣ አብረናቸውም እናምልክ። መልካም የመልዕክት ጊዜ።

Komentáře • 93

  • @sphonetastic1965
    @sphonetastic1965 Před rokem

    አሜን ማደረያዎችህ እንደምን የተወደዱ ናቸዉ ተባረክ ጸጋና እደሜ ይጨምረልን

  • @christiantsegaytewelde450

    Yaredo anten yeseten Egziabiher ybarek.

  • @michaelmelaku3749
    @michaelmelaku3749 Před 3 lety +10

    ይገርማል መምህር የንተን ትምርት የዮሐንስ ወንጌል ብቻ ቀርቶኝ እሱን እየተከታተልኩ ይሄ ትምርት ሲለቀቅ ደስ አለኝ እያለቀብኝ እየደጋገምኩነው የምሰማው ትምርቶችህን በተለይ ዮሴፋ የፋሬዛፋ 10ግዜ ይሆናል የደጋገምኩት እጅግ እድሜ ከጤና ይስጥህ እኔ ኦርቶዶክስ ነኝ የጌታን ቃል ግን እንደ ቆየ ወይን ጠጅ እየጣፈጠኝ እንድታነፅበት አርገሀኸኛል

    • @saramesfin6511
      @saramesfin6511 Před 3 lety +2

      ወንድም ሚካኤል, በጣም ጥሩ ነው የእግዚአብሔርን ቃል መስማትህ አንድ ነገር ታውቃለህ ብዬ አምናለሁ መዳን በክርስቶስ ብቻ እንደሆነና ልንድንበት የተሰጠን ስም ከሰማይ በታች ኢየሱስ ብቻ እንደሆነ እንድታውቅ እፀልይልሃለሁ:: ጌታ ይባርክህ!!

    • @eyesusgetanew3346
      @eyesusgetanew3346 Před 3 lety

      እጅግ የከበረ፣የእውነት መርሕን የተከተለ፣ ወቅታዊ መልዕክት፣ሁልጊዜ ልናስበው፣ልንጠብቀውና የሕየወወታችን መመሪያ አድርገን ዘወትር በሐሳባችን ፊት ለፊት ላይ ከፍ አድርገን ልናቆመው የተገባ ትምሕርት ነው፣፣
      ያሬዴ፣
      በረጅም እድሜ ከነሙሉ ጤንነትሕ ተባረክ።

  • @gigiriri4865
    @gigiriri4865 Před 2 lety

    እውነት ነው ተባረክ ወደ እግዚአቢሄር እንሄድ ሲሉኝ ደስ አለኝ ነው ዩሚሎው አሜን ይዝራብን

  • @deguyegetalij5199
    @deguyegetalij5199 Před 2 lety

    የእግዚአብሔር ሰው ያሬድ የምታስተላልፈው ትምህርት እጅግ በጣም ድንቅ ነዉ ዘመንህ ይባረክ እንደዉ በጌታ ፍቅር አንድ ጥያቄ እጠይቃለሁ በትምህርት ይልቀቅ አንድ አንድ ሰዎች ክርስቶስ ከአዳም ዘር ተካፍለዋል ይላሉ ለሎቹ ከማርያም ደምና ስጋን ተካፍለዋል ይላሉ ዕብራውያን 2/14/15 በጥቅስ በጌታ የሆኑት ናቸው ስለዝህ ጉዳይ በጥልቀት ቢታስተምር ደስ ይለኛል

  • @awelmohammed6821
    @awelmohammed6821 Před 2 lety +1

    God bless You dear brother Evangelist Yared Tilahun!!!

  • @danielhailemelekotambaye4030

    ሃሌሉያ የመቅደስ ሽግግር አደረጉ ያኛውን መቅደስ ትተተው ምን መጣ ብለው ወደዚኛው መጡ ሕዝቡን
    በፉጨት ጠራ በሺህ የሚቆጠሩ ይህ ድምጽ ምንድ
    ነው ብለው መጡ ስትል እንባዬን መቆጣጠር አልቻልኩም ዕብራዊያን 1-3 በልጁ በዚህ ዘመን
    መጨረቫ ለኛ ተናገረን እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና
    የባህርው ምሳሌ ሆኖ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ
    ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኃላ በሰማያት በግርማው ተቀመጠ
    ክብር ሁሉ ለኢየሱስ ይሁን
    የማከብርህ ወንድሜ ወንጌላዊ ያሬድ ላንተና ለቤቴሰቦችህ ሁሉ አሁንም የላይኛው ምንጭ
    የታችኛው ምንጭ ይፍለቅላችሁ ተባረክ

  • @salamsalam2325
    @salamsalam2325 Před 2 lety

    እግዚአብሔር ይባርክህ ፀጋው ይብዛልህ ወንጌላዊ ያሬድ

  • @amengetachew4485
    @amengetachew4485 Před 2 lety

    አንተ ስታስተምር ነገሮች ግልጥልጥ ነው የሚልልኝ። ጌታ ይባርክህ ፓስተር ያሬድ።

  • @senaitbekurestion1037
    @senaitbekurestion1037 Před 2 lety +1

    The unseen God . . . I can see you in your doweling place Amen 🙏🏼

  • @jesussaves1198
    @jesussaves1198 Před 2 lety

    ወንድም ያሬድ እግዚአብሔር ይባርክህ:: በትምህርቶችህ በጣም ተጠቅሜአለሁ እግዚአብሔር ይህንን ፀጋ ስለሰጠህ ስሙ ይባረክ::

  • @getahunyohanes1729
    @getahunyohanes1729 Před 3 lety +1

    አወነተኛ የወንጌ አስተማሪ..... ተባረክ

  • @tsegeabebe2793
    @tsegeabebe2793 Před 3 lety

    ጌታ አብዝቶ አብዝቶ ይባርክህ

  • @nardoesmezmur8582
    @nardoesmezmur8582 Před 3 lety +7

    ወንድሜችን ያሬድ ጌታ ይባርክህ ዘመን ሁሉ ከነ ቤተሰብህ በጌታ ቤት ይለቅ

  • @betslot2366
    @betslot2366 Před 3 lety

    ጌታ ይባርክ እናመሰግናለን

  • @aazewde9394
    @aazewde9394 Před 3 lety +1

    ባዲስ ኪዳን ማደሪያቹ እኛበ ክርስቶስ እንደገና የተወለድን ክርስቲያኖች ነን የሥላሴ ማድሪያዎች ነን

  • @amanuelyohannes4100
    @amanuelyohannes4100 Před 3 lety

    እግዚአብሔር ተናገረ እኔም ሰማሁ! ወንድሜ ያሬዶ ጌታ ይባርክህ!

  • @salameskyes7240
    @salameskyes7240 Před 4 měsíci

    እግዚአብሔር ይባረክ❤

  • @habatamhabatam8769
    @habatamhabatam8769 Před 3 lety +3

    ያሬዱ የስማሁት ገና ስትለቀው ነው ስሞኑን ውስጤ ሳስበው ነበር ይህን ትምህርት አሁንም ውስጤ ላይ አለ እግዚአብሔር ይባርክህ

  • @betelhemgirma9736
    @betelhemgirma9736 Před 3 lety +1

    እጅግ የተወደድክ የእግዚአብሔር ሰው ያሬዶዬ ጌታ ሕይወት ዘመን ዘላለምህን ይባረክ 🙏🙏👏👏👏ድንቅ ትምህርት ነው 👏👏👏👏👏👏❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

  • @abebaseyiume8949
    @abebaseyiume8949 Před 3 lety +1

    የምወድህ የአባቴ ልጅ ተባረክልኝ

  • @sebeleg7835
    @sebeleg7835 Před 3 lety +1

    God bless Brother Yaredo

  • @Rashy_Amp_12
    @Rashy_Amp_12 Před 3 lety

    God bless you wengelawi yared

  • @rosemare8314
    @rosemare8314 Před 3 lety +1

    Yemedeqe temhret new bezu temerebetalehu. Tebark yechemerleh

  • @zewditugesesse385
    @zewditugesesse385 Před 3 lety +1

    እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን ። ተባረክ 🙏🏽

  • @woinshetkumazeleke1600
    @woinshetkumazeleke1600 Před 3 lety +1

    ወንድም ያሬድ የጌታ ፀጋ እየበዛ ይብዛልህ 🙏🙏🙏

  • @beamlakayire4897
    @beamlakayire4897 Před 2 lety

    እግዚአብሔር ይባርክህ። የሙሽራይቱን ፍቅር ይመልስልን። እነ ኤርምያስ ስለ ራሳቸው ሳይሆን ስለ ጽዮን ነበር ጩኸታቸው።

  • @tihonhaan1258
    @tihonhaan1258 Před 3 lety +1

    Geta ybarek sleant ageliglot

  • @Aki-rl2wz
    @Aki-rl2wz Před 3 lety

    God bless you W/l yared 🙏🙏🙏

  • @PT-yn7bx
    @PT-yn7bx Před 3 lety

    Thanks God

  • @biniambermeji4323
    @biniambermeji4323 Před 3 lety

    ታላቅ ወንድማችን የእግዚኣብሄር ሰው ወንጌላዊ ያሬድ አሁን ካለህበት መንፈሳዊነት ብዕጥፍ ድርብ ጨምርልን ባስተማርከው ትምህርቲ ኣምላካችንን እንድንናፍቅ እንዲሁም የቅዱሳኑን ህብረት ዋጋ እንድንሰጠው ስላደረከን ይሄ የሰበከን አምላክ ይባርክህ ካንተ ብዙ ተምርያለው ባስተማርክ ቁጥርም እንደምማር አምናለው እንደገና ሳንዲያጎ ብትመጣም ጥሩ ነበር። ስላንተ እግዚኣብሔር የተባረከ ይሁን ።

  • @girmaanbasieordolo5238

    እግዚአብሔር ይባርክህ ወንድሜ አስደነቅ መልዕክት ከትክክለኛ ምንጭ የሚፈልቅ በረከት

  • @user-nc4my6sh3e
    @user-nc4my6sh3e Před 3 lety +1

    እንኳን በሰላም በጤና መጣክል ወንጌላዊ ያሬድ

  • @neza8166
    @neza8166 Před 3 lety +1

    Yaredo zemeneh agalgiloteh yibarek be ante lay silalewu yekeberewu liyu ye tsega setota getan amesegenslehu andebetocheh yibareku ahunem kezih bebeleta tsega yigenagneh ewnet newu yihe melkekt le ene new 1amet ke hibret teleyiche neber.

  • @eyosiasbereda3461
    @eyosiasbereda3461 Před rokem

    Amen

  • @elenitesfaye7816
    @elenitesfaye7816 Před 2 lety

    Makon mareke...stotanim le beta chrstian seta....anten marko le egna ye seta Gata ybarek!!!!!!!!!!

  • @abebalolamo3233
    @abebalolamo3233 Před 3 lety +1

    አሜን! !አሜን!!አሜን!!አሜን!! ጌታ ሆይ እርዳን ! የተወደድክ ወድማችን ያሬዳችን ስለ አንቴ እግዚአብሔር አሚላክ ይባረክ !!🙏🙏💕💜እንወድሃለን 💙💕

  • @legesebelachew2640
    @legesebelachew2640 Před 3 lety

    አሜን ህያዋን ማደሪያ ያደራጋን ጌታ ይመስጌን አንቴንም ጌታ ይባርክ በብዙ

  • @mekedesmezmur4057
    @mekedesmezmur4057 Před 3 lety +1

    Amen 🙏amen 🙏 God bless you and nice to see you again

  • @elizabethkassa7047
    @elizabethkassa7047 Před 3 lety +2

    ወንድሜ ያሬድ ጌታ ኢየሱስ አብዝቶ ይባርክህ !!! በጣም ድንቅ እና እውነተኛ መልእክት ነው። በዚህ ዘመን ከእኛ ህይወት እየደበዘዘ የመጣ ግልፅ የሆነ ት/ት ነው። ጌታ መንፈስ ቅዱስ በአንተ በኩል ግልጹን ስለነገረኝ አመሰግነዋለሁ አንተም ተባረክልኝ !!!

  • @netsahonkubeeyesus1667
    @netsahonkubeeyesus1667 Před 3 lety +2

    ያሬዳ bro ጌታ እየሱስ ይባርክክ በየሳምንቱ የምታሰተምረው ትምርት እንዴት እንደምባረክ አባክክ አትጥፉ

  • @buroukteklemichael5186

    ይህን ትምህርት ሌላ ቃል ባገኝለት እኔም ዋው ዋው ዋል እንዲሁ ልበል

  • @betelihemhabte2261
    @betelihemhabte2261 Před 3 lety

    God Bless you

  • @semharasevaw4817
    @semharasevaw4817 Před 3 lety +1

    እልልልልልልልልል 🙏

  • @eyesusgetanew3346
    @eyesusgetanew3346 Před 3 lety

    እጅግ የከበረ፣የእውነት መርሕን የተከተለ፣ ወቅታዊ መልዕክት፣ሁልጊዜ ልናስበው፣ልንጠብቀውና የሕየወወታችን መመሪያ አድርገን ዘወትር በሐሳባችን ፊት ለፊት ላይ ከፍ አድርገን ልናቆመው የተገባ ትምሕርት ነው፣፣
    ያሬዴ፣
    በረጅም እድሜ ከነሙሉ ጤንነትሕ ተባረክ።

  • @yishakabrhame5824
    @yishakabrhame5824 Před 3 lety +4

    ግሩም! ድንቅ፣ ክብር ያለው መልዕክት ነው! የጌታ ፀጋ ተትረፍርፎ ይብዛልህ ያሬድዬ! እወድሃለሁ!

  • @berhaneghide5842
    @berhaneghide5842 Před 3 lety +1

    ኣዎን እንኳን ደህና መጣ።
    ይባረክ።
    ተባረክልን ውድ ያሬዳ።

  • @user-sh5ek5cg8b
    @user-sh5ek5cg8b Před 3 lety +1

    Yemwedih silagegnewuh betam dess blognal

  • @christiantsegaytewelde450

    "Yemekdes shigigir " Egziabiher ymesgen.

  • @whitney5003
    @whitney5003 Před 3 lety +2

    I was searching everday ...wellcome back dear teacher yared

    • @tsinulegeta6919
      @tsinulegeta6919 Před 3 lety +1

      Me too every day searching if anything new. I'm glad too welcome brother yared

  • @belaynesheabey8834
    @belaynesheabey8834 Před 3 lety

    Blessed😍

  • @honeyb4984
    @honeyb4984 Před 3 lety

    ጌታ አብዝቶ አንተንም ቤተሰብህን ይባርክ🙏🏽💕

  • @user-yc4gs1yr2o
    @user-yc4gs1yr2o Před 3 lety +1

    GOD bless you yaredo❤

  • @eleniwoldetsadik5890
    @eleniwoldetsadik5890 Před 3 lety +1

    Welcome back yarddo God bless you 🙏

  • @jerusalemtermeer5982
    @jerusalemtermeer5982 Před 3 lety +1

    Amen hallelujah 🙏🏼

  • @loveelroi4453
    @loveelroi4453 Před 3 lety +6

    I can literally listen 👂 to you every day .. Powerful teaching .. can you teach about Fasting pls if you can or if you already have can u leave a link here pls ? Much appreciated and I thank God fir saying YES to your calling .. Thank you God bless you ..

  • @lebentsegaye9402
    @lebentsegaye9402 Před 2 lety

    Bless you Yared!I am really blessed from your teachings!

  • @astergudu4723
    @astergudu4723 Před 3 lety +1

    Welcome back we miss u.hope u had good time to pray

  • @tigistdagne9716
    @tigistdagne9716 Před 3 lety

    Waaw great messege thanks evangelist Yaredoo.

  • @mederine
    @mederine Před 3 lety

    Yeredo tefache dese belogale
    Tebareke wedeme geta ne benete selemaye dese yelegale 🙌🙌

  • @dinkudagu4959
    @dinkudagu4959 Před 3 lety

    Amen 🙏🙌, wondme Yared geta Eyesus babizu yebarki yasfeh

  • @bezawit256
    @bezawit256 Před 3 lety

    Amennnnnn Haleluya Ellllll thanks god

  • @tizitanegash6648
    @tizitanegash6648 Před 3 lety

    Yarediye it is a great teaching God bless you more!!! Miss you all!!!

  • @gedamawitethio6915
    @gedamawitethio6915 Před 3 lety

    HOOOO በየሱስ ስም አይኔን ማመን ነው ያቃተኝ ውድ የኔ ወንድም የሬዲ .......endelig du tilbake……godt å se deg igjen 🙏🏽😇😇

  • @azebahferom182
    @azebahferom182 Před 3 lety

    Amen!!!!!!!!!!!!!!!!

  • @emebetyohannes3744
    @emebetyohannes3744 Před 3 lety

    Y a r e d a c h i n e e e e.......much respect

  • @abejebelay8537
    @abejebelay8537 Před 3 lety

    God bless you brother Yared.

  • @sarahagos9028
    @sarahagos9028 Před 3 lety

    Amazing the word of God. God bless you!

  • @astergudu4723
    @astergudu4723 Před 3 lety

    AMEN.be blessed

  • @mewtat5709
    @mewtat5709 Před 3 lety

    ያሪዬ እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክህ!!!

  • @ritaaraya3439
    @ritaaraya3439 Před 3 lety +1

    WOW, I'M TOUCHED, WITH THE GOSPEL OF GOD, GBU GLORY TO GOD!!!

  • @henokabraha6918
    @henokabraha6918 Před 3 lety

    God bless you

  • @tast684
    @tast684 Před 3 lety +1

    በሰላም ነው የጠፉህው ያሬድ ?

  • @alemneshaleto6032
    @alemneshaleto6032 Před 3 lety

    tebarek mor

  • @meselebegashaw9031
    @meselebegashaw9031 Před 3 lety +1

    GOD bless you more than ever before evangelist yared

  • @amanuel2087
    @amanuel2087 Před 3 lety +2

    እግዚአብሔር ይባርክህ። የሚገርም መረዳት ነው። እኔ ብዙ ጊዜ አንብቤዋለሁ በተለያዮም ሰባኪዎች ሰምቻለሁ እኔ እንደተረዳሁት ነበር ስሰማ የኖርኩት። በተለይ በልቡም የላይኛውን መንገድ የሚያስብ ሰው ምስጉን ነው። የሚለው ቃል አዲስ መረዳትነው እግዚአብሔር መገለጡን ያብዛልህ ተባረክልን🙏❤

  • @semhargulbet3143
    @semhargulbet3143 Před 3 lety

    Geta zemnknen yebark!

  • @habatamhabatam8769
    @habatamhabatam8769 Před 3 lety +3

    ያሬዶ እንኩዋን ደህና መጣህልን

  • @user-rp3gw7ge7w
    @user-rp3gw7ge7w Před 3 lety

    ሻሎም ያሬዶ

  • @rahelsabesbe5053
    @rahelsabesbe5053 Před 3 lety

    ሰላም ያሬዶ

  • @solomonlemma9239
    @solomonlemma9239 Před 3 lety

    እባክህ ወንድም ያሬድ ገላትያ መፅሀፍን አስተምረን

  • @samuelasfaw3802
    @samuelasfaw3802 Před 3 lety +1

    ሰላምህ ይብዛ ጋሽ ያሬድ ጠፋህብን

  • @user-rp3gw7ge7w
    @user-rp3gw7ge7w Před 3 lety

    ሃሌ ሉያ ያሬዶ አንተ ስታስተምር ማስተዋል እችላለሁ ። አንተ ጥቅስ ጠቅሰህ ሳትጨርስ እኔ እጨርሰዋለሁ።

  • @Meme-vk8et
    @Meme-vk8et Před 3 lety

    ጠፍተህብን ናፍቀህን ነበር

  • @mollalignabehodie3195
    @mollalignabehodie3195 Před 2 lety

  • @edenhailemariam2240
    @edenhailemariam2240 Před 3 lety

    2ይ ዜና መዋእል 2
    11፤ ሑራም ንጉስ ጢሮስ ድማ ደብዳበ ጽሒፉ፡ ንሰሎሞን ከምዚ ኢሉ ምላሽ ሰደደሉ፡ እግዚኣብሄር ንህዝቡ ስለ ዝፈተዎ፡ ንኣኻ ኣብ ልዕሊኦም ንጉስ ገበረካ።
    Thank you. To have wonderful teacher lead by Holy Spirit like you Evangelist Yared stay blessed with your family 🙌🏽

  • @ruthyohannes4007
    @ruthyohannes4007 Před 3 lety

    እኔ ግን
    ቤ/ክ መሄድ እፈልጋልሁ ግን one way 2hr መንገድ ነው

  • @birukfekadu
    @birukfekadu Před 2 lety

    የቆሬ ልጆች እንማን ናቸው?
    14 መዝሙሩች የቆሬ ልጆች መዝሙር ነው።
    ቆሬ የሊዊ ልጅ ነው የኮራት ልጅ ነው አራተኛ ትውልድ ነው ። አንድ ጊዜ ትልቅ ነውጥ በእስራኤል ዘንድ ተደርጎ ነበር በነሙሴ ላይ ቆሬ እዛ ላይ የነበረ ሰው ነው። ዘኸልቁ 26፥ 16 ይሄ የአመፅ ታሪክ ተወስቷአል። የቆሬ ልጆች መሞት ቢኖርባቸውም ለይቶ ግን የቆሬ ልጆች አልሞቱም በምህረት የተረፉ ናቸው። ለእግ/ር ምህረት ልዩ መረዳት አላቸው። በዳዊት ዘመነ መንግስት የመዘምራን አለቆች አደረጋቸው።
    እንግዲህ ከቆሬ ልጆች አንዱ በየበአላቱ ይሄ ሰው ረጅም የእግ/ር ቤት ልምምድ አለው፤ ይሄን መዝሙር ሲዘምር ግን መገኘት አልቻለም።
    ከፅሁፍ የእግ/ር ቤት እንዴት እንደሚወደድ ያሳያል። "
    የሰራዊት አምላክ ማደሪያዋችህ እንደምን የተወደዱ ናቸው" የሠራዊት ጌታ የሚያመለክተው የሰማይ አካለትን መላዕክትን ነው። ይሄ እግ/ር በእልፍ መላዕክት የሚታጀብ ነው፤ ነገር ግን ይሄ ጌታ ሕዝቡ ዘንድ ማደር ወደደ። መቅደስህን አይቶ በፍቅር አለመውደቅ አይችልም። "ነፍሴ አደባባዮችህን ትወድዳለች፣ትናፍቃለች” my soul longs, faints እስካደርግ ድረስ ለብዙ ነገሮች ሰዋች faint ያደርጋሉ። ልብ በሉ የድንኳኑ ማማር ላይ አይደለም፣ይልቁንስ አንተ ስላደርክበት ውብ ነው። ምን ማለት ነው ማደሪያዋችህ፦ አንተ ማትታይ አምላክ ነህ፤ በማደሪያህ ግን አንተን አይሃለሁ። አንተ ማትታይ አምላክ ነህ ያየሁህ በዚህ ማደሪያ ነው። አደባባዮች የተባለበት ውጫዊ የሆነው የድንኳን አካል ነው እንደዚህ ያደረገው። 12 ነገዶች በዚህ አደባባይ ይኖራሉ ፣ስንት ውድ ሰው እዚያ ያያል፤ ስጦታቸውን ይዘው ይመጣሉ፤ የሚገርም አይነት felowship
    መናፈቁን በሶስት አካላት በመቅናትያስቀምጣል።
    ① ቁ³ ቀናሁ ትር በሚሉት ወፎች፤ እነርሱ እንኳን ይገባሉ ጫጩታቸውን ይፈለፍላሉ ፤እነዚያ ወፎች ምንኛ የታደሉ ናቸው። ሰው ቢቀና ቢቀና በወፍ ይቀናል? ወፎች መኖራቸውን እንኳን አንገነዘብም
    ②በማደሪያው በሚያገለግሉት ካህናት ‘ በቤትህ የሚኖሩ’ ‘ የተመሰገኑ አመስገኞች’ የተባረኩ ናቸው። ዕድለኞች ናቸው የተመረጡ ናቸው።
    ③ ወደ ማደሪያህ ለመምጣት የሚያቅዱ ፣ ጉዞ የጀመሩ ሰዋች "አንተን ብርታት ያደረጉ የላይኛውን መንገድ የሚያስቡ" ጥም ያለበት መንገድ ከእነርሱ የተነሳ ይለመልለማል፤ ይበረታሉ አይቀሩም።
    ቁ 10 ደጁ መቆም፦ ደጅ የሚቆሙ defect ያላቸው ሰዋች ናቸው፤ እንደነርሱ መሆን ደግሞ ይመርጣል። ተገደው ደጅ ሚቆሙት እርሱ ይሻላል። ይሄ ሰው የእግ/ር ማደሪያ ይወዳል። ይሄ ሰው ከእግ/ር ቤት ጋር ያልተቆራየ ነገር የለውም ነፍሱ ስጋው ልቡ።
    መፅሀፍ እንደሚነግረን የማደሪያ ለውጥ አድርጋል። ማደሪያው ያ ድንኳን ያ መቅደስ ነበር። ኃይለኛው የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ሲመጣ የመቅደስ ሽግግር መጣ። በአለ አምሳን ለማክበር የመጡ አይሁዶች የመጡበትን በልሳን ቋንቋ በመስማታቸው በመደነቅ ወደ አዲሱ ቤተመቅደስ ተጨመሩ።
    እግ/ር በቋሚነት የሕንፃ/የድንኳን ማደሪያነት አልመረጠም። በኀጢያት ምክንያት ከሰው ወደ ድንኳን /ሕንፃ ማደሪያ ለጊዜያዊነት ማደር ጀመረ። እግ/ር አሁን ኦሪጅናል ቤቱን አግኝቶአል፤ በክርስቶስ ደም ማደሪያ በመቀደሱ ፤ የእግ/ር ቤት ተሰራ ፤ በመንፈሱ አደረበት ፤ ይሄ ሕዝብ ወደ ዓለም ተበተነ። ‘የእግ/ር ሕንፃ፣ የእግ/ር ቤተመቅደስ፣ ለእግ/ር መኖሪያ ለመሆን ምትሰሩ ናቸው፣ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሰሩ፣ በእግ/ር ማደሪያ ቤት ’ እግ/ር አይታይም ግን ደግሞ ማደሪያው ሆንን። የእግ/ር ቤተመቅደስ እናንተ ናችሁ። ትልቅ ጥያቄ ላንሳ፦ ምን ያህል ማደሪያውን ትወዳላችሁ? እግ/ር ሕያው ማደሪያውን፣ ቤተክርሰቲያንን ፣ሰዋችን ምን ያህል ትወዳላችሁ? እዚህ ያሏችሁን ጊዜ ምን ያህል ትወዳላችሁ? በኮቪድ ሰዓት ይሄን ማደሪያ ምን ያህል ናፈቃችሁ። ጌታን የምትወዱትን የምትገልጡት ማደሪያውን በመውደድ ነው። ብዙ ሰው ሕብረት አያደርግን በሰብብ "ማደሪያዋችህ እንደምን የተወደዱ ናቸው’ የሚሉ ጥቂቶች ናቸው። እግ/ር ከአንድ ድንጋይ ተፈልፍሎ የተሰራ ቤት የለውም፣ ብዙዋች ተገጣጥመው በሚሰሩ ድንጋዮች የሚሰራ ነው። በንፁህ ልብ ጌታን የሚጠሩ ሰዋች እኛሉ በመንቀፍ ብቻ ከማደሪያወቹ አንለይ ፣እርሱ አድሮበታል።