የልብ ወግ (YeLeb Weg) ዲ/ን ሄኖክ ሃይሌ እና ትዕግስት ታፈረ

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 21. 08. 2024
  • #Maya_Media
    #ዲያቆን_ሄኖክ_ሃይሌ ደራሲ እና ጋዜጠኛ
    #ትዕግስት_ታፈረ_ደራሲ
    ዘዉዱ ጌታቸው ዘማሪ
    በአጭር ጊዜ ውስጥ ተወዳጅነትን ያተረፈው "የልብ ወግ" የተሰኘው ፕሮግራማችን ከእናንተ ተመልካቾቻችን ጋር በስፋት ለመድረስ በፋና ቴሌቪዢን ይዘንላችሁ መተናል፡፡
    በዚህ ዝግጅት ላይ ድርጅትዎ በአጋርነት እንዲተዋወቅ እና እንዲታይ ማድረግ የሚችሉበትን እድል አመቻችተናል፡፡
    ከታች በተቀመጠው ስልክ ይደውሉ
    ምርትና አገልግሎቶንም ያስተዋውቁ፡፡
    ሰልክ ቁጥር ፦ 09-11-64-42-80
    :-011-6-63-13-58/59
    በተጨማሪም
    @maya_digitalmedia በማህበራዊ ሚዲያ የትስስር ገፆቻችን
    መልዕክት ሊያስቀምጡልን ይችላሉ ፈጣን መልስ እንሰጣለን!
    "የልብ ወግ "
    ዘውትር እሁድ ምሽት 3:00 ሰዓት ላይ በፋና ቴሌቪዥን እንዲሁም
    በማያ ሚዲያ የዩቱዩብ ቻናል እሁድ ምሽት 4:00 ሰዓት ላይ ይከታተሉን፡፡
    አዝናኝና አስተማሪ የሆኑ ቪዲዮዎችን ዘወትር እሁድ ምሽት 4:00 ሰዓት ላይ ይከታተሉን፡፡ / @mayamediaethio
    የልብ ወግ በማያ ሚዲያ
    Enjoy! Subscribe!
    instagram
    / mayaflicks
    / maya_digitalmedia
    tiktok
    hl=envm.tiktok.com/...
    facebook
    / ethio.maya

Komentáře • 594

  • @ruthgesesse3595
    @ruthgesesse3595 Před 2 lety +420

    የኔ አንደኛ ትሁት የዋህ ጥበበኛ መምህር በእግዚአብሔር ቃል ያጌጥክ ….ኑርልኝ ❤️❤️

  • @user-td9bp2hj7g
    @user-td9bp2hj7g Před 2 lety +334

    አቤት ውበት እቤት ግርማ ሞገስ አቤት አንደበት እግዚአብሔር ይጠብቅልን ብቻ መምህር እድሜና ጤና ይስጣችሁ የተዋህዶ እንቁዎች💚💛❤

  • @hiwotloha9070
    @hiwotloha9070 Před 2 lety +264

    በዚ ዘመን አንተን የመሰለ መምህር ተዋህዶ ስላላት ፈጣሪ ይመስገን በቤቱ ያፅናቹ እረጅም እድሜና ፀጋ ያድልልን❤👏🙌

    • @user-qo3xp8hz6f
      @user-qo3xp8hz6f Před 2 lety +2

      Amen

    • @amarechwolde658
      @amarechwolde658 Před 2 lety

      ይቅርታ እህቴ/ወንድሜ ‹‹ፈጣሪ›› ከማለት ክቡር ስሙን መጥራት ይኖረብናል፡፡ ሆነ ብለው በአላማ ከሌሎቹ አንዱ በማለት የሚያለማምዱት ስለሆነ ከታጋጀ ወጥመድ ለማምለጥ የእግዚአብሄርን ክቡር ስሙን ብንጠቀም፡፡

    • @debirebisrat6892
      @debirebisrat6892 Před 2 lety

      memherinet kemenifesawi hiwet gar yalew sew lenie Doctor Yaregal Abegaz bicha new.

  • @zeestifanostube
    @zeestifanostube Před 2 lety +252

    ዲ/ን ሔኖክ የቤተ ክርስቲያን እንቁ ልጇ በፀጋ ላይ ፀጋ ይጨምርልህ እህታችን ቲጂዬ አንቺም በብዙ ተባረኪልን።
    ዘማሪ ዘውዱ የአገልግሎት ዘመንህ ይብዛልን🙏❤❤ኦርቶዶክሳውያን በተጋበዙበት መድረክ የእኛነት መለያቸውን ነጠላቸውን መስቀልኛ አገልድመው ሳይ ልቤ በሐሴት ይሞላል❤።

    • @user-bc3hx7kg3g
      @user-bc3hx7kg3g Před 2 lety +6

      እንዲህ ነው ኦርቶዶክሳዊነት🥰

    • @Danshalomneba
      @Danshalomneba Před 2 lety +2

      ትዕግስት ማለት የባሲሊቆስ እንባ የተሰኘ መጽሐፍ ደራሲ ነች ወይ?

    • @yordanosaram7605
      @yordanosaram7605 Před 2 lety

      Eritear and Ethiopien❤ 💒❤🍀🍀🍀🍀🍀🍀

    • @amleworkketema5211
      @amleworkketema5211 Před 2 lety

      Amennn betam tameralachu ehit wendemocha

  • @maskihiwot6165
    @maskihiwot6165 Před 2 lety +41

    እኔ መምህር አንተ ስታስተምር በጣም የተሰማኝ እና ያሳዘነኝ "ሠርግ" ስታስተምር እንዲህ ብለሀል "በ ሰርጋችን አባታችን እንዲኖር እንፈልጋን አይደል አልክ?ምን አይነት ጥያቄ ነው ነበር ያልኩት ያው አባቴን በሞት ስላጣሁ ማግኘት ስለማልችል፡፡ ግን የባስ መልስህ አስለቀሰኝ" ጋብቻ ከቤተክርስቲያን ዉጪ ማድረግ እግዚአብሔርን በደስታዬ ቀን አልፈልገውም እንደማለት ነው" የዛኔ ነበር ያለቀስኩት እኔ በደስታዬ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ነገር እንዲኖር ስለምፈልግ የዛኔ ነበር የወሰንኩት እግዚአብሔር ይስጥልኝ♥♥♥

    • @user-sj3tl2ep9q
      @user-sj3tl2ep9q Před 2 lety +3

      ፀጋዉ የበዛለት ሳስተምር እዲህ ልብ ድርስ ይገባል። እኔም ነኝ ካሳን ወዲህ ነው የወሰንኩት

    • @maskihiwot6165
      @maskihiwot6165 Před 2 lety +2

      @@user-sj3tl2ep9q አሜን አሜን

    • @user-iv5sg7ks4f
      @user-iv5sg7ks4f Před 3 měsíci

      የሚገርም ነው ወደሁላችንም ልብ ይግባ አሜን

  • @user-el5fh1fe5k
    @user-el5fh1fe5k Před 2 lety +99

    እኔ ምንም የምናገረዉ ሚጠፋብኝ አተን ሰምቼ አስተያየት ለመስጠት ስሞክር 😢 ሲያስተምር መጮህ አይወድ እረጋ ብሎ በየሰከዱ እልል በሉ አጨብጭቡ አይል በቃ ዝም ብሎ ቃለ እግዚአብሔርን አብራርቶ የሚቀርብ ትልቅ መአድ ነክ ህመማት ሚለዉን መፀሐፍክን ሁልግዜ በእንባ የማነበዉ 😢😢😢😢 እድሜክን ያርዝምልን የኛ እንቁ ነክ 🙏🙏🙏💒💓💓💓💒

  • @seblekahsay6417
    @seblekahsay6417 Před 2 lety +109

    የተዋህዶ ልጆች የድንግል ወዳጅ ዲያቆን ሄኖክ ሀይሌ እረጅም እድሜ ከጤና ጋር ይስጥህ:: ፀጋውን ያብዛልህ::

    • @tsegakt2012
      @tsegakt2012 Před 2 lety +1

      አሜን 🙏🙏🙏ብዝት ይበልለት የልጅ ትልቅ ትእግስተኛና አስተዋይ እንዳይቀይሩቡን የጠላቱን አንደበት ይዘጋለት

  • @user-bs2gp5lv7k
    @user-bs2gp5lv7k Před 2 lety +135

    መምህሬ ትለያለህ እረጅም እድሜ ከጤና ጋር ይስጥልን 💚💛❤🙏🙏🙏

    • @frehiwot27
      @frehiwot27 Před 2 lety +1

      ለመምራችን ፀጋውን አብዝቶ ይስጥልን

    • @genettube1107
      @genettube1107 Před 2 lety +1

      ሰብስክራይብ አድርጊኝ ሀኒ

    • @tadelasemu6857
      @tadelasemu6857 Před 2 lety

      አሜን🙏🙏🙏

  • @sarahana7929
    @sarahana7929 Před 2 lety +63

    ቅዱስ ሚካኤል ሁሌም ካንተ አይለይህ ደስ ትላላችው አይለያችው ጅማሬያችንን ሳይሆን ፍጻሜያችንን ያሳምርልን

  • @kiyornach4458
    @kiyornach4458 Před 2 lety +64

    "ይታደሉታል እንጂ አይታገሉትም" ሚለውን ብሒል አካል ነስቶ ምናየው በእንዲህ ያሉ ወንድሞች ነው 💛💛

  • @belayfikre555
    @belayfikre555 Před 2 lety +62

    ውድ የቤተክርስቲያን ጌጣችን መምህራችን እረጅም እድሜ ቅዱስ አማኑኤል ያድልን

  • @Birtukan21
    @Birtukan21 Před 2 lety +75

    መምህር የወገል ዘመን ያርዝመልህ ከከንቱ ወዳሴ ይጠብቅህ
    ዘማሪ ዘውዱ ዝማሬ መልዕክት ያሰማልን

  • @user-st2vr1tw6h
    @user-st2vr1tw6h Před 2 lety +42

    መምህር በጣም ነው የምወድህ እድም ጤና ይሰጥህ ❤❤❤🙏🙏

  • @user-ch5rp1mu9u
    @user-ch5rp1mu9u Před 2 lety +35

    የኔ እንቁ መምህሬ እድሜ ጤና ይስጥህ በጣም ነው የምወድህ🥰❤🙏

  • @yordanosasimelash5147
    @yordanosasimelash5147 Před 2 lety +54

    እግዛብሄር ፀጋዉን ያበዛልህ ሰዉ ነህ መምህሬ በጣም ነዉ እምወድህ እረጅም እድሜ ከጤና ጋር ይስጥህ ፈጣሪ
    ❤❤❤🙏🙏

  • @eskedareetp4314
    @eskedareetp4314 Před 2 lety +42

    እዉነት ነዉ መምህራችን እኔም ሥለእምነቴ ያወኩት አረብ ሀገር ከመጣሁ ነዉ እናም እዉነት ነዉ ብዙ እማቃቸዉ ጠንካራ ልጆች አሉ በሀይማኖታቸዉ 😘😘😘

    • @dmulugeta
      @dmulugeta Před 2 lety +3

      አንሰማ ስንለው ጌታ በስደት ወስዶ አስተማረን። ክብር ምስጋና ለሥሉስ ቅዱስ ይሁን! ምን ይሳነዋል እግዚአብሄር?

    • @tirongotirongo9390
      @tirongotirongo9390 Před 2 lety +1

      @@dmulugeta ማርያምን ትክክል ነሽ እኔም በስደት ነው የተማርኩት

    • @user-ss6bm3py6f
      @user-ss6bm3py6f Před 2 lety +1

      @@dmulugetaእውነት ነው አሁንም ማስተዋሉን ይጨምርልን እኔ ሰንበት ተማሪ ነበርኩ የምማረውም አለ የተባለ ቤተክርስቲያን ነበር ማለቴ ብዙ መምህራንንና ሰባኪያን ያሉበት ግን መስሚያየ ጥጥ ነበር ዋለኔ የምሔውም ከበሮ ለመምታት ነበር ትርጉሙንም አላውቅም አሁን ግን ይቆጨኛል በጣም

    • @Ass-tl6pe
      @Ass-tl6pe Před 2 lety +1

      ልከ ነዉ የሀገር ፍቅር የቤተሰብ ፍቅር የሀይማኖት ፍቅር የሚገባን

    • @Ass-tl6pe
      @Ass-tl6pe Před 2 lety +1

      ሰደት ላይ ሰንሆን ነዉ

  • @hailemichael41
    @hailemichael41 Před 2 lety +16

    በወንድማችን ዲ/ን ሔኖክ ሃይሌ እና በእህታችን ትዕግስት ታፈረ የተፃፈ መፅሃፍ አለ ''ደንገጡሯ እመቤት'' ገዝታችሁ አንብቡት

  • @chaseyourdreamsin2024
    @chaseyourdreamsin2024 Před 2 lety +20

    ሶስት ምርጥ በአንድ ማዕድ 👌👌👌እድሜና ጤና ይስጥልን

  • @tgyedengellej6865
    @tgyedengellej6865 Před 2 lety +43

    ደስ ብሎኝ በተመስጦ ያዳመጥኩት የዲን ሄኖክ ሀይሌ 'በልብ' ወግ'' የነበረዉን ፕሮግራም እንድትከታተሉ በአክብሮት እጠይቃችኃለን👏
    የኔ ዘመን ምርጥ መምህር በእዉነት አንተን አለማመስገን ንፉግነት ነዉ ብዙዎች የአረብ ሀገር ሴት እያሉ ያለስሟ ስም በሚሰጡት አለም ዉስጥ አመስጋኝ እዉነትን ተናጋሪ መምህር በዘመኔ በማየቴ እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ በእዉነት ቃለ ህይወት ያሰማልን መምህር👏

    • @asugualkeshi2082
      @asugualkeshi2082 Před 2 lety

      መ/ር ተስፋዬ አበራ በጣም ያመሰግናል ለአረብ አገር ያለች ሴት

    • @amleworkketema5211
      @amleworkketema5211 Před 2 lety

      Amennn kalehiwoten yasemalen

  • @maryy852
    @maryy852 Před 2 lety +2

    ዘመንህ በቤቱ ይለቅ መምህሬ እግዝያብሔር ይጠብቅህ

  • @solianaberihun
    @solianaberihun Před 2 lety +50

    ዝማሬ መላእክት ያሰማልን ዘማሪ ዘውዱ
    ድንቅ ውይይት ነው እህታችን ትግእሥት ተፈሪ ና መምህር ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ በእድሜ በጤና ይጠብቅልን እግዚአብሔር ይስጥልን
    መምህሬ ብቻ ሁሌም ተናገር ንግግርህ ሁሉ ትምህርት ነው !

  • @user-et2ny6cy8g
    @user-et2ny6cy8g Před 2 lety +31

    መምህር ትለያለህ እዉነት መተኛት አልቻለኩም ፈጣሪ ረጅም እድሜ ይስጣቹ ❤️❤️❤️🙏🙏🙏

  • @lijnatty2082
    @lijnatty2082 Před 2 lety +16

    ፍፃሜህን ያሳምረው ድንቁ መምህራችን

  • @hulumlebgonew2902
    @hulumlebgonew2902 Před 2 lety +9

    ውበት ሲለካ
    እምነታችን ነው ለካ❤!!!

  • @tube7667
    @tube7667 Před 2 lety +37

    ዘማሪ ዘውዱ በጣም እኮ ትለያለህ በእግዚአብሔር በጣም ነው የምወድህ እግዚአብሔር እድሜ ጤና ይስጥህ ድምፅ ልቤ ከፍሎት ሲገባ ይሰማኛል ምን አይነት ፀጋ ነው በአዛኝቷ

  • @fikrassfa135
    @fikrassfa135 Před 2 lety +19

    አቤት! ፡❤ድምቀት,እውቀት,ትህትና,ሙሉነት,ፀጋ,መታደል ነው ሁላችሁንም እግዚአብሔር ያክብርልን

  • @user-oj3co7yz2w
    @user-oj3co7yz2w Před 2 lety +30

    ቃለህይወትን ያሰማልን መምህራችን በዕድሜ በጤና ፈጣሪ ያኑርልን

  • @user-zw1qd7cj8e
    @user-zw1qd7cj8e Před 2 lety +14

    የኛ ዕንቁ መምህር ፀጋውን ያብዛልህ የፆም ጥቅም ምሳሌ እኔ በጣም ማይግሪን አለብኝ ሲፆም አያመኝም በጣም ደስተኛነኝ ኦርቶዶክስ ሰለሆንኩ 🙏

  • @munaqatar683
    @munaqatar683 Před 2 lety +22

    የኛ እንቁ መምህር ዲ/ን ሂኖክ ሀይሌ እድሜን እና ጤናን ፈጣሪ አብዝቶ ይስጥህ 😍😍

  • @user-mv3tv1mu8c
    @user-mv3tv1mu8c Před 2 lety +11

    ማረያምን ስወድህ ዲ/ን ሄኖክ ተባረኩ ሁሌም አንጣችሁ

  • @fikrusinshaw2721
    @fikrusinshaw2721 Před 2 lety +12

    ሁላችሁንም እግዚአብሔር ይጠብቅልን። የቲጅ ጥያቄ የመምህር ማብራሪያ ግሩም ነበር። ሁለተኛ ክፍል ቢኖረው እና ቲጅም ብትጠየቅ ደስ ባለኝ።

  • @adi-my1cq
    @adi-my1cq Před 2 lety +4

    በስመአብ ምን አይነት መባረክ ነው አንደበትህ እንደ ማር ይጣፍጣል 🙏

  • @user-bg5sf8sz2c
    @user-bg5sf8sz2c Před 2 lety +33

    አቤት እንዴት ደስስስ እንደምትሉ እንቁ የተዋህዶ ልጆች ከነ ነጠላችው ፈጣሪ እረጅም እድሜ ከጤናጋር ይስጣችው

  • @sulamtesesulamtese7253
    @sulamtesesulamtese7253 Před 2 lety +8

    የተዋሕዶ መኩሪያ አንተን የወለደች ማሕጸን ምንኛ የተባረከች ናት ድንቅ መምሕር አምላክ እጹብ ድንቅ አድርጎ የፈጠረክ መምሕር ቃለሕይወትን ያሠማልን

    • @user-is1je9sx2r
      @user-is1je9sx2r Před 2 lety

      የወለደችው ብቻ ሳትሆን እሱን የምታገባ ሴት የታደለች የተመረጠች ናት ሱስ እኮ ነው ማርያምን እኔ ሳልደፋ አልቀርም እሱን በመውደድ።

  • @tinsaegirma9926
    @tinsaegirma9926 Před 2 lety +5

    መምህራችን ዲያቆን ሄኖክ ሃይሌ እግዚአብሔር እንደ አይን ብሌኑ ይጠብቅህ

  • @emuew6480
    @emuew6480 Před 2 lety +15

    ውድ የኦርቶዶክስ ልጆች የአብይ ፆማችን እያለቀብን ነው የ።ፆሙን የበረከት ያድርግልን የተዋህዶ እንቁ መምህራችን አንክዋን ደህና መጣክልን ንግግሮችክ አይጠገቡምኮ የተዋህዶእንቁመምህራችንአንክዋንደህናመጣክልንንግግሮችክአይጠገቡምኮ ዛሬ ደግሞ ዳጊሾው ላይ እጠብቃለው እድሜ ከፀጋውጋር ይስጥክ

    • @tsehayemelaku6103
      @tsehayemelaku6103 Před 2 lety +1

      የተዋህዶ ልጅ ዘመንህ እግዚአብሔር ይባርከው 🙏🙏

  • @zinuyefekadu7350
    @zinuyefekadu7350 Před 2 lety +34

    እድሜ ፀጋ በረከትን ያድልህ መምህሬ ተባረክልኝ !!!!!ዝማሬ መላእክትን ያሰማልን

  • @amorthodox661
    @amorthodox661 Před 2 lety +67

    Heni am glad to see you.i always got new knowledge when i watch ur videos. your way of teaching really amazed me. We are so lucky generation to have you

  • @sulamtesesulamtese7253
    @sulamtesesulamtese7253 Před 2 lety +9

    እንቁ የተዋሕዶ መምሕር የተዋሕዶ ኩራት ኑርልን እንወድሐለን እመብርሐን በዘርፍፍ ቀሚሦ ከክፍ ነገር ትከልልሕ ዘመንሕ ይባረክ አንተ የተዋሕዶ ኩራት

  • @AM-dc5hd
    @AM-dc5hd Před 2 lety +2

    Yetewahido lijochi wub nachihu 🥰🥰🥰

  • @AlexTheKing
    @AlexTheKing Před 2 lety +2

    ሁሌም ብሰማህ ባደምጥህ ባይክ የማልጠግብህ ተባረክ::

  • @tegestmulugeta8946
    @tegestmulugeta8946 Před 2 lety +16

    መምህር ሄኖክ የኛ አደበተ እርቱ ሰውድህ ወደር የለኝም ፀጋውን ያብዛልህ ፍፃሜህ ያማረ ይሁን ለዝማሬው ዝማሬ መላአክትን ያሰማልን አሜን

  • @amharicbooks7381
    @amharicbooks7381 Před 2 lety +17

    ስለሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን ።
    ለሁላችሁም ቃለህይወት ያሰማልን!
    ማያዎች እንግዳ አድርጋችሁ ስለጋበዛችሁልን ከልብ እናመሰግናለን ።

  • @user-uf9wp9tn2t
    @user-uf9wp9tn2t Před 2 lety +20

    እግዚአብሔር እድሜአችሁን ያርዝምልን የቤቱ ምሶሶ ያርግልን ትውልድን ከእሳት የምታድኑ አውራ ያርጋችሁ
    ዝማሬ መላህክት ያሰማልን ❤️

  • @aximaros1725
    @aximaros1725 Před 2 lety +9

    እግዚአብሔር እረጅም እድሜ ከጤና ጋር ያድልልን 🙏

  • @habeshawitcamper1337
    @habeshawitcamper1337 Před 2 lety +2

    ጋዜጠኛ ትዕግሥት ሥነሥርዓትሽ እና ንግግርሽ ለኛ ለሴት እህቶች ትልቅ አርአያ ነው። እግዚአብሔር በቤቱ ያፅናሸሸ። መምህር ኄኖክ እናመሠግናለን ።

  • @tewo7technology181
    @tewo7technology181 Před 2 lety +8

    💞አንጀት አርስ የልብ ወግ 💞 ቃለ ሂወት ያሠማልን💞

  • @saramitku7868
    @saramitku7868 Před 2 lety +6

    መምህሬ እግዚአብር የጠብቅክ 😍😍

  • @kifleabebew9568
    @kifleabebew9568 Před rokem +1

    ልዪ እንቁወች የኦርቶዶክስ ልጆች እንዴት እንደምታምሩ ልዪ ግርማ ሞገስ ተሰቶችሆል
    እመቤቴ ትጠብቃችሁ

  • @user-bc3hx7kg3g
    @user-bc3hx7kg3g Před 2 lety +23

    ተምሬበትአለሁ ስለሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን።
    ስለመዝሙሩ ዝማሬ መላእክት ያሰማልን
    ለሁላችሁም ቃለህይወት ያሰማልን።
    ለመጀመርያ ጊዜ እስከመጨረሻው አድምጨ ኮመንት ስሰጥ።
    ድንቅ ፕሮግራም!
    እንግዳ ኣድርጋችሁ ስለጋበዛችሁልን እናመሰግንአለን!

    • @hanaabera3778
      @hanaabera3778 Před 2 lety

      Namni mana tokko ijaruu qorqoro wali hin saamu.....ye andi bet yemisera sew korkoro ayshamam

  • @aboneshworku8027
    @aboneshworku8027 Před 2 lety +2

    ያለችኝ ጊዜ ሁሉ የአንተን ትምህርቶችንና ፅፍችህን ባአነብና ብሰማህ የማልጠግብህ የማትሰለች ማን ይሆን እንደኔ ስብከትህ ሲሰማ ውስጡ ሰላም ሚሞላው አንተን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጅ አድርጎ የሰጠን የቅድስት ድንግል ማርያም ልጅ ይክበር ይመስገን መምህሬ

    • @user-zw9mm2kb1i
      @user-zw9mm2kb1i Před 2 lety

      ማርያም እኔም ደጋግሜ ነዉ የምሰማዉ አንደበቱ አይጠገብም እግዚአብሔር ይጠብቅልን እኛንም በቤቱ ያጽናን

  • @kuwaitkwt1205
    @kuwaitkwt1205 Před 2 lety +8

    እግዚአብሔር ይመስገን ተዋህዶ ሀይማኖት ለዘላለም ትኑር

  • @lemlemseyfu8765
    @lemlemseyfu8765 Před 2 lety +2

    መምህር ሄኖክ ስለ አንተ ጓደኛሄ ነበረ የነገረችኝ ከዛ ጊዜ በኅላ የተመቸኝ ጊዜ ትምህርቶችህን አዳምጣለው ከውስጥ የማይወጣ ጭንቅላቴ ውስጥ ያሉትን ጥያቄዎች ሁሉ የምትመልስልኝ እያዳመጥኩ ውስጤ ጥያቄ ይፈጠር እና ወድያው በእርጋታ መልሱን ከትምህርቱ ውስጥ ይመለስልኛል ከሁሉም እርጋታህ ትህትናህ ይማርከኛል ወንድሜ የአገልግሎት ዘመንህን ያብዛልን እድሜ ጤና ይስጥልን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ብዙ በእውቀት የመጠቁ እውቅናን እና ዝናን የማይሹ ትሁት እና እራሳቸውን ዝቅ የሚያረጉ መምህሮች ስላሏት እኮራለውኝ

  • @heucgsyx5609
    @heucgsyx5609 Před 2 lety +1

    እግዚአብሔር የልብህ መሻት ይፈጽምልህ እንቁ ድያቆን ሄኖክ🙏🌺

  • @tsegazeabdejene6685
    @tsegazeabdejene6685 Před 2 lety +6

    የጠያቂዋም የትዕግስት ለዛ የዲ.ን ሔኖክ መልስ እጅግ ደስ የሚል የልብ ወግ። እረጅም እድሜ ከጤና ጋር ያድልልን
    ለዘማሪ ዘውዱም ዝማሬ መላእክት ያሰማልን

  • @negedetobia
    @negedetobia Před 2 lety +6

    ሁላችሁም በቤቱ ያቆያችሁ።እስከመጨረሻ ያጽናችሁ። 🟩🟨🟥

  • @SB-mq2eb
    @SB-mq2eb Před 2 lety +25

    It always Amazes me ,Lot's of wisdom.Kale Hiwot yasemalen mengest semayatn yawrselen!

  • @user-dj6mh3tr8v
    @user-dj6mh3tr8v Před 2 lety +3

    መምህር ምድራዊ ነገር አልመኝልህም ቸር አምላክ መድኃኔዓለም በቀኙ ያቁምህ በቸርነቱ በቤቱ ያፅናህ ዘወትር ምህረቱ አይለይህ አባቴ😍

  • @jakrrbr7271
    @jakrrbr7271 Před 2 lety +1

    ዳቆን መምህር ሄኖክ እኔ ባተ ትምህርት በእግዚአብሔር ቸርነት ከመጥፍ ልማድ ወጥቻለሁ እናም በእውነት እግዚአብሔር አምላክ በጥበብ ያኑርህ ወድሜ !!!!

  • @zahraabdo9944
    @zahraabdo9944 Před 2 lety +1

    ፕሮግራሙ ምርጥ ነው የልብ ወግ ዲ/ን ሄኖክ ምርጥ መምህር ነው ኑርልኝ

  • @user-ug7so1wv6s
    @user-ug7so1wv6s Před rokem +3

    ኦርቶዶክሳውያን አቤት ውበት ረጅም እድሜ ከጤና ጋር ይስጥልን 💚💛❤🙏🙏🙏

  • @anoali8112
    @anoali8112 Před 2 lety +6

    የኔ መምህር ኣንተን የሚገልፅበት ቃላት የለኝም በእዉነት እድሜና ጤና ያድልህ እግዚአብሔር ኣምላክ⛪🙏

  • @beshirabdi4795
    @beshirabdi4795 Před 2 lety +2

    እውነት ስለ አረብ አገር የሰማሁት ደስ ይላል እግዚአብሔር ይባርካችሁ እውነት ነው

  • @msrt2127
    @msrt2127 Před 2 lety +6

    ቃለህይወትን ያሰማልን ❤️

  • @Sara-ok8ri
    @Sara-ok8ri Před 2 lety +15

    የምወድህ መምህሬ እንኳን ደህና መጣህልን የኔ አንደበት ጣፋጭ እመ አምላክ ትጠብቅልኝ ቃል ህይወትን ያሰማልን
    የንሰሀ መዝሙር በሰማው ቁጥር እምባዬ ነው የሚፈሰው 😭😭 ጌታ ሆይ ኃጢአተኛ ሰው ነኝ እና ይቅር በለኝ 🙏

  • @Kinetibebu
    @Kinetibebu Před 2 lety +6

    ወንድሜ ዲያቆን ሔኖክ ኃይሌ አገልግሎትህን እግዚአብሔር ይባርክልህ። የዲያቆን ሔኖክ አገልግሎት የጽድቅ ፍሬ የሚያፈራው የሚያስተምረውን ወንጌል አድምጠን፤በልቦናችን ቀርጸን የተጠቀምንበት ከሆነ ብቻ ነው። አለበለዚያ ግን ሔኖክንና የተናገረውን ቃለ እግዚአብሔር አድንቀንና ተገረመን የምናልፈው ከሆነ የእኛ ነገር "በጭንጫ አለት ላይ እንደ ወደቀው ዘር..." ይሆናል። ማቴ. 13፥5። ስለዚህ ከተማርን በኋላ በቃሉ ለመኖርና ለመገዛት እንጣር።

  • @abicher7289
    @abicher7289 Před 2 lety +8

    መምህር እድሜ እና ጤና ሠጥቶህ በቤቱ ያፅናህ። ስታስተምር ሁሌም በእውቀት ላይ ተመርኩዘህ ነው ስሜታዊነት አላይብህም በዚህም በጣም ነው የማደንቅህ ረጅም አመት ኑርልን

  • @frehiwettesfaye5941
    @frehiwettesfaye5941 Před 2 lety +1

    ዲያቆን ሀይሌ በእውነት አንተ ልዩ ነክ እግዚአብሔር እድሜና ጤናን ያድልልን በጣም ነው ምወድህ መምህሬ

  • @user-gm3kz4ii8u
    @user-gm3kz4ii8u Před 2 lety +10

    ለወንድማችን የመላይእክትን ዝማሬ ያሰማልን አሜን❤🙏

  • @Nolawieneye
    @Nolawieneye Před 2 lety +11

    እግዚአብሔር ጸጋውን አሁንም ያብዛልህ:: ከእግዚአብሔር ካልሆነ መቼ አንድ እርምጃ መራመድ ይቻላል!

  • @mesi16-91
    @mesi16-91 Před 2 lety +7

    ዲ/ን ሄኖክ ሀይሌ ፀጋ እግዚአብሔር ይብዛልህ ቆይልን😘🙏ብፁእነታቸው ከቃላት በላይ ናቸው እግዚአብሔር አምላክ እድሜ ከጤና ጋር ያድልልን 😘🙏

  • @adeeadee4633
    @adeeadee4633 Před 2 lety +5

    እንቁ መምህር የስስት ልጅ የተዋህዶ ፀጋውን ያብዛልክ

  • @Kidist19
    @Kidist19 Před 2 lety +4

    ቃለ ሕይወት ዝማሬ መላእክት ያሰማልን በእድሜ በጤና ይጠብቅልን
    ለእኔ ዲያቆን ስባልም ሳነብም ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ እና ስብከቶቹ ነው ከፊቴ ድቅን የሚለኝ
    ስብከቶችህን ሳዳምጥ #እግዚአብሔር በአካል መቶ የሚያስተሚረኝ ያህል ስሜት ነው የሚሰማኝ
    በእውነት ጸጋ በረከቱን ያልብስህ አዛኚቷ እመቤት ቅድስት ድንግል ማርያም በዘርፋፋ ቀሚሷ ከጠላት ሴራ ትሸፍንህ!!!
    ማያ እናመሰግናለን

  • @merrynigusu8316
    @merrynigusu8316 Před 2 lety +6

    እግዚአብሔር ያክብርልን!

  • @asternegeri4123
    @asternegeri4123 Před 2 lety +3

    ዕንቁዎቻችን ኑሩልን ። እንደ እናንተ ያሉትን ያብዛልን

  • @mulugetamesele7189
    @mulugetamesele7189 Před 2 lety +6

    ረጅም የፀጋ ዓመታትን ይስጥልን መምህር ....ፈጣሪ የአንተ አይነቱን ያብዛልን

  • @merimar2500
    @merimar2500 Před 2 lety +2

    ዲ/ን ሄኖክ ሀይሌን አይቼ ነው የመጣሁት ስወደውእኮ አንደበቱ ርቱ ዘመንህ ይባረክ

  • @yeamanuellej2721
    @yeamanuellej2721 Před 2 lety +12

    የኛ እንቁ መምህር የተውህዶ ዓይን በእውነት የህይወትን ቃል ያሰማልን እግዚአብሔር አምላክ በእድሜ በጤና በፀጋ ይጠብቅልን ለመዝሙር ዝማሬ መላእክት ያሰማልን ሁላችሁም እግዚአብሔር ያክብርልን አሜን

  • @zablonprinting7030
    @zablonprinting7030 Před 2 lety +3

    "ክርስቶስን እንደመሰልኩ እኔን ምሰሉ" ይላል ቅ/ጳውሎስ...እስቲ ኦርቶዶክሳውያን ጳውሎስን መሆን ቢያቅተን አይተን፣ አንብበን፣ ሰምተን የወደድነውን መምህር በኑሯን እንምሰለውና ብርሃናችን ለሁሉ ይብራ። የተግባር ሰው እንሁን። መ/ር ቃለ ህይወት ያሰማልን።

  • @biruktayetali8189
    @biruktayetali8189 Před 2 lety +9

    ድንቅ ነው በጣም እኛን በቃሉ ከመጎብኘት በላይ ድርጊት የለም ቃለህይወትን ያሰማችሁ

  • @sarahsh2379
    @sarahsh2379 Před 2 lety +8

    እግዚአብሔር ይመስገን መምህሬ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ እግዚአብሔር ይጠብቅልን እመ ብርሀን እመ አምላክ ሁሌም ካንተ ጋር ትሁንልን የተዋህዶ ልጅ በጣም እምንወድህ ኑርልን ትምህርትህ ንግግርህ ሁሉም መንፈስን የሚያድስ ነው በእውነት።
    ለዘመርህልን አባታችን ዝማሬ መላዕክትን ያሰማልን እንዲሁም እኅታችን እግዚአብሔር ይስጥልን

  • @user-fu9ix4lc3z
    @user-fu9ix4lc3z Před 2 lety +1

    አቤት መታደል እመብርሀን ቀሪ ዘመንህን ትባርከው እርጋታህ ትህትናህ ድንቅነው

  • @yelmag2511
    @yelmag2511 Před 2 lety +6

    ቃለሂወት ፡ ያሰማን ፡ 💚💛❤️❤️

  • @beztariku2993
    @beztariku2993 Před 2 lety +3

    እንዴት እንደምወድህ ተባረክልን።

  • @tsosenataddesse986
    @tsosenataddesse986 Před 2 lety +6

    በጣም ጥሩ አባባል እና አረዳድ ነው። እግዚአብሔር ይባርክህ ። ሁሉም አገልጋዬች እግዚአብሔር እንደሚጠቀምባቸው እንጂ በራሳቸው እውቀት እና ችሎታ ያለመሆኑን መረዳቱን ይስጥልን።

  • @ninjago9518
    @ninjago9518 Před 2 lety +2

    ውይ የኔ ጌታ አፈር ልብላልህ የኔ መኩሪያ አንተን ሳይ ተዋህዶ ምን ያህል በእግዚአብሔር የተወደደች የተመረጠች እንደሆነች ማሳያ ነህ አባቴ ጌታ እግዚአብሔር ቀሪ ዘመንህ የተባረከ የተባረከ ይሁን ጸጋውን ያብዛልህ እመቤቴ ጥላ ከለላ ትሁንህ ዘመዴ🙏እንቁዬ የጠላታችንን አይን ይድፈነው 🙏

  • @abebaabeba7425
    @abebaabeba7425 Před 2 lety +8

    ሥታምሩ የተዋህዶ እንቁዎች እግዚአብሄር ይጠብቃቹህ

  • @user-gz7cl7uu3t
    @user-gz7cl7uu3t Před 2 lety +1

    አይ ሄኒ በቃ እወድሃለሁ❤❤❤

  • @nanakalu5536
    @nanakalu5536 Před 2 lety +2

    መምህር አንደበትህ እንዲህ እንደጣፈጠ ረጅም እድሜ ኑርልን 🙏🙏🙏 የኛ እንቁ🙏🙏🙏

  • @kibromsabian541
    @kibromsabian541 Před 2 lety +1

    ትዕግስት ደንገጡርዋ እመቤት ላይ ያሉ ድርሰቶችን በጣም ነው የምወድልሽ፡፡ ለእኔ መንፈሳዊ ልብ ወለዶችን ለመፃፍ እንደ ፍኖት መጠቀም የምንችልባቸው ናቸው ብዬ አምናለሁ፡፡ ዲ.ን ሄኖክ የተሠጠህ ፀጋ ግሩም ነው፡፡ ለሁሉም ፀጋውን የሚሰጥ እግዚአብሔር ይመስገን፡፡ በቀጣይነት በኦርቶዶክሳዊ ስነ-ጽሑፍ ዙሪያ መርሐ ግብሮች ብታሰናዱልን ለወጣት ጸሓፊያን ትልቅ ድጋፍ ይሆናል፡፡ አገልግሎታችሁን ፈጣሪ ይባርክ፡፡

  • @user-fe4sj9dc3y
    @user-fe4sj9dc3y Před 2 lety +6

    መምህሬ እግዚአብሄር ይጠብቅልኝ❤❤❤✝️❤✝️❤❤❤♥️♥️😍😍😍😍🙏

  • @amanuelmesfin1732
    @amanuelmesfin1732 Před 2 lety

    ዲያቆን ሔኖክ ስላየነክ ከልብ ደስ ብሎናል

  • @mahletfenta3527
    @mahletfenta3527 Před 2 lety +1

    ሰዓቱ አጠረብኝ እኮ ፀጋውን ያብዛላችሁ

  • @selamkiros4727
    @selamkiros4727 Před 2 lety +4

    ውንድማች ረጅም እድሜ ይስጥልን!!!!!!

  • @meskeremmengste7365
    @meskeremmengste7365 Před 2 lety +3

    ዘማሪ መላዕክት ያሰማልን እግዚአብሔር አምላክ ይጠብቅልን መምህርም እህታችንም

  • @selamteshome9303
    @selamteshome9303 Před 2 lety +1

    ዲያቆን ሄኖክ ሀይሌ ቸሩ መድሀኒዓለም በፀጋ ላይ ፀጋ ይጨምርልህ ቀኑን ሙሉ ስሰማህ ብውል አይሰለቸኝም

  • @suzy1523
    @suzy1523 Před 2 lety +3

    በእውነት እግዚአብሔር ፀጋውን ያብዛላቹ 🙏🙏

  • @mahletzeleke3186
    @mahletzeleke3186 Před 2 lety +6

    We expect part two I hope please 🙏🏻🙏🏻🙏🏻💕💕💕

  • @sisaykebede6540
    @sisaykebede6540 Před 2 lety +3

    የምናከብርህ ውዱ መምህራችን እድሜ ከጤና ጋር ይስጥልን በአስተምህሮትህ እንማር ዘንድ የልኡል እግዚአብሔር መልካም ፍቃድ ይሁንልን አሜን🙏

  • @user-pj7ed1eo8t
    @user-pj7ed1eo8t Před 2 lety +1

    አቤት የተዋህዶ ስርአት ሞገስ ክብር አንተ የወለደች መህፀነ ለምለም