አባትና ልጅ ሻለቃና ጄነራል - በነገራችን ላይ! ከደረጀ ኃይሌ ጋር - ክፍል 3 BENEGERACHIN LAY

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 8. 05. 2021
  • አባትና ልጅ ሻለቃና ጄነራል - በነገራችን ላይ! ከደረጀ ኃይሌ ጋር - ክፍል 3
    Subscribe: / @artstvworld
    Facebook : / artstvworld
    Website : artstv.tv
    Instagram : / artstvworld
    Twitter : / artstvworld
    Telegram : t.me/joinchat/AAAAAFbB3kEu63_...
    Get The Latest Brand New Ethiopian Entertainment Videos by Subscribing Here: / @artstvworld
    #ArtsTvWorld #EthiopianEntertainment #Ethiopia
    unauthorized use, distribution and re upload of this content is strictly prohibited
    Copyright ©2021 Arts Tv World

Komentáře • 364

  • @samsonwoldemichael5742
    @samsonwoldemichael5742 Před 3 lety +38

    ጋሽ ጳውሎስ ስለራሱ በጐ ስራዎች መናገር አልፈለገም እንጂ ቢናገር ዘርዝሮ አይጨርሰውም፡፡ ምናልባትም ረስቷቸው ይሆናል፡፡ እኔ ግን በብላቴ የጦር ማሰልጠኛ ካምፕ እና ከዚያም በኋላ በኬንያ ስደት ወቅት ከቅርቡ ሆኜ ያየሁት ብዙ በጣም ብዙ መልካም ስራዎችን ሲሰራ በአይኔ ያየሁና መቼም የማልረሳው ነኝ። አንድ የማይረሳኝን ታሪክ ላካፍል፡፡
    ከአየር ወለድ ወታደሮች ጋር የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችም ተቀላቅለን ወደኬንያ ተሰደን ነበር፡፡ በስደተኛ ካምፑ ውስጥ በተለያየ ግዜ ልዩ ልዩ አደጋ እየደረሰ ሰዎች ይሞቱ ነበር፡፡ አንድ ተማሪ እንዲሁ ሞቶ ሬሳው የሆነ ክፍል ውስጥ ተዘግቶበት የሚቀብረው አጥቶ ከርሞ ነበር፡፡ ጋሽ ጳውሎስ አፉንና አፍንጫውን በጨርቅ ሸፍኖ የልጁን ሬሳ ብቻውን ገንዞ እንዲቀበር አድርጓል፡፡ ከዚያም ከሽታው የተነሳ ታሞ እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ ይህ ታሪክ ለምሳሌ ያህል እንዲሆ ጠቀስኩት እንጂ በአይኔ ያየኋቸው ብዙ ታሪኮች አስታውሳለሁ፡፡
    ጋሽ ጳውሎስ፡ በዋዝ ጂፕ መኪናህ 13 ሰዎች ጠቅጥቀኸን የጉጂ ሲሳይ እንዳንሆን አድርገህ በሰላም ኬንያ እንድንገባ ያደረከውና በተለይ ደግሞ መንገድ ላይ ሁለት ተማሪዎችን ሊገድሏቸው ሲሉ የጂፑ ኮፈን ላይ አስቀምጠህ ይዘሃቸው በመሄድ ያተረፍካቸው ትዝ ይልሃል? እግዚአብሄር ቀሪ ዘመንህን እንዲባርክ ጸሎቴ ነው፡፡ ደግሞም መልካም ስራህ ስለተከተለህና ስለባርከልህ ይህንንም እድል አግኝተህ ታሪክን ሁላችንም እንድንማር ስላበቃን እግዚአብሄር ይመስገን፡፡
    ደሬም ይህን ታላቅ ስራ ለመስራት እግዚአብሄር ስለተጠቀመብህ እግዚአብሄር ይባርክህ፡፡

    • @Dt_Td
      @Dt_Td Před 3 lety +1

      Migerm tarik new ....sent yaletsemu tarikoch begelesb west alu

    • @samuelkebede7007
      @samuelkebede7007 Před 3 lety

      Wow what a great Ethiopian!!! Thank you sir.

    • @nehemiahmekonnen3276
      @nehemiahmekonnen3276 Před 3 lety

      በደንብ ዘርዘር አድርገው ፃፈው ፊልም ይመስላል።

    • @yonasworkie6720
      @yonasworkie6720 Před 3 lety +2

      እንዴ ሳሚ አንተ እራስህ ባለ ታሪክ አይደለህ እንዴ በጣም ነው የገረመኝ አላውቅም ነበር ወደ ኬንያ መሄድህ ለማንኛውም እጅግ በጣም መሳጭ ቃለ መጠይቅ ነበር እኔ ድሮም የደረጄ አድናቂ ነኝ

    • @samsonwoldemichael5742
      @samsonwoldemichael5742 Před 3 lety

      @@yonasworkie6720 yes Yoni, tinish tarik ayichalew..haha..

  • @sibhatasfaha5792
    @sibhatasfaha5792 Před 3 lety +20

    ኤርትራዊ ነኝ
    ልሶስት ሰዓት ኣንዲት ቃል ሳያልፈኝ በጥሞና ነው የተከታተልኩት፡ ማራኪ ታሪክ።
    ጌታ እድሜ ና ጤና ያብዛላችሁ

    • @gualbahtahagos7001
      @gualbahtahagos7001 Před 3 lety +1

      Kkkkkk eritreawi da nay eritrea tarik whiduka 3ሰዓት mm a amharu tarik

    • @sibhatasfaha5792
      @sibhatasfaha5792 Před 3 lety +2

      ኩሉ ታሪኽ ምፍላጥ ጽቡቕ እዩ፡
      ናትና ደኣ ናበይ ከይከደኒ፡ ኣይሓልፈንንዩ
      ክአኣ።ኤርትራዊ እየ።

    • @sibhatasfaha5792
      @sibhatasfaha5792 Před 3 lety

      ክክክክክክ ሰገን ነታ ናተይምጥማትኪ ግና ገሪማትኪ ኣይግድን ክክክ

    • @gualbahtahagos7001
      @gualbahtahagos7001 Před 3 lety

      @@sibhatasfaha5792 entay felite elkani gerimuni endiu ezom ab gizye naxnet ziabena ko confused koina hmak nay amharu enda mharuna eri tv nbaela amharay seb kemzeykone +amharic music kisemie ziterekebe kiesere endareana abina hji dma tedemirna hade hzbi ena ybluna slezis aythazelna

    • @sibhatasfaha5792
      @sibhatasfaha5792 Před 3 lety +1

      ሓቅኺ ርዱእ እዩ ሰገን ሓፍተይ ጸገም የለን፡ኣነ ድማ ኣብ ናይ ደርጊ ግዜ ስለ ዝዓበኹ፡እቲ ኹነታት ስለ ዝፈልጦ ገሊኡ ከኣ ምስጢር ዝነብረ ስለ ዝበርሃለይ እየ፡ተመሲጠ ሰሚዔዮ፡
      ካልእ ብዙሕ ውን ኡሰምዕ እየ፡ታሪኽ ስለ ዝኾነ ምስማዑ ዘገም የብሉን።
      ናይ ሃገርና ታሪኽ ድማ የንብብን ይሰምዕን ዘይፈልጦ ብዙሕ ድማ ይማሃር።
      ኣጆኺ እርዳኣልኪ እየ፡
      ኣዚኺ ብርኽቲ ኢኺ።
      ማሓዛይ ኮንኪ ኣሎኺ።

  • @kibebewbenti2857
    @kibebewbenti2857 Před 3 lety +43

    ውድ የኢትዮጵያ ልጅ ማር ማር የሚል አንደበት የጫወታ ብልት አዋቂ አንደበተ ርቱ እውነተኛ ታማኝ ሙሉ የሰው ልክ ትልቅ አባት የኢትዮጵያ አምላክ እድሜን ከጤና ጋር ያብዛልን ደሬ የሁል ጊዜ ምርጤ አንተም ኑርልን ተመጣጣኝ ጥያቄዎችን በቦታው እና በሰዓቱ አሳምረህ እና እሸሞንሙነህ ስለምታቀብል በጣም አስደሳች ጊዜ ስለሰጠኝ ምስጋናዬ ላቅ ያለ ነው የድሮ ወዳጅህ ክቤ ነኝ ከካናዳ

  • @samuelkebede7007
    @samuelkebede7007 Před 3 lety +49

    What a great Ethiopian!!! He still remembers 561,564.75Birr. I salute you sir, a proud, honest and great Ethiopian with integrity!!!

  • @danieltiruneh2024
    @danieltiruneh2024 Před 3 lety +33

    ሀብት ያለኝ ሰው ብሆን ለእኚህ የሰው ጥግ ለሆኑ ሰውዬ በቀሪ ዘመናቸው ሁሉ እደግፋቸው ነበር። እግዚአብሔር ሀሳብዎን ይሙላልዎ ከተጨማሪ የጤና እክል ይሰውርዎ ጌታዬ🙏🏽

    • @selammamo4166
      @selammamo4166 Před 3 lety

      Egiziabihar Edima yisitilini Shaleka

    • @selammamo4166
      @selammamo4166 Před 3 lety

      Miniga Metadeli new erisiwo beta mesahafiti nowoti

    • @senda9782
      @senda9782 Před 2 lety +1

      ሻለቃ ጳውሎስ እንኳንስ ከባዳ ከልጆቻቸው እንኳን ምንም የማይፈልጉ ለሌሎችም የሚተርፍ ሃብት ያላቸው ሰው ናቸው ። እርዳታ ቢፈልጉ ልጆቻቸው የተማሩ አሜሪካን የሚኖሩ ወንዱም ልጃቸው ኢትዮጵያ ዉስጥ በጣም የታወቀ ሙዚቀኛ የቴዲ አፍሮን ዘፈኖች የሚያዘጋጅ ስለሆነ እርዳታ ከማንም አይፈልጉም ።
      አትድከም

    • @danieltiruneh2024
      @danieltiruneh2024 Před 2 lety

      @@senda9782 minun keminu adebalekew. Ene yalkut lehager bekefelut waga lik endezega yemitagezu nachew lemalet new hasabe. Hulun hasab yekifat kaba deriben enchilewalen??? Libona yistih wodaje

  • @yeteshagebrehiwot1149
    @yeteshagebrehiwot1149 Před 3 lety +17

    ደሬ ብዙ ቃለ መጠይቅ እንዳደረግህ አውቃለሁ እንደ እኝህ ሰው ግን ኢትዮጵያን ሙሉ አድርጎ ያስቀመጠ ተወዳዳሪ አላገኘሁም በግሌ እና እግዚአብሔር እንደናንተ አይነት ሰው ሀገራችንን አያሳጣት

    • @zerifekadu
      @zerifekadu Před 3 lety

      እውነት ነው ግለሰቡም በጣም ሚዛናዊ ናቸው

  • @zelalembelay1621
    @zelalembelay1621 Před 3 lety +17

    Wow እኒህ ሰው እጅግ እጅግ ቤተመዘክር ናቸው ደሬ አመሰግንሃለሁ ለካ ሀገሬ እንዲህ አይነት ሰው አላት ሀገር ብትጠቀምባቸዉ ምን አለ??? አይ ሀገሬ አስተምራ ታደነቁራለች!!! ወይኔ ሀገሬ።።።።

  • @solomontesfaye3717
    @solomontesfaye3717 Před 3 lety +22

    ደሬ ምንአይነት ታሪክ እየበረበርክ ነው የምታመጣልን።እናመሰግንሃለን ። ሻለቃ ጳውሎስ ምንአይነት ሚዛናዊና አዋቂ ሰው ናቸው። እግዚያብሔር ቀጣይ እድሜዎ አስደሳችና ጤናማ ይሁንልዎት።ደሬ ሰላምህ ይብዛ። ወገን !እባካችሁ ከእነዚህ አባቶች እንማር ❤❤❤

  • @abrahamt2356
    @abrahamt2356 Před 3 lety +33

    This is a real Ethiopian hero.we thank you that you dedicated your whole life for your beloved Country.May God bless your life !

  • @adamfisshaye1170
    @adamfisshaye1170 Před 3 lety +19

    ቃላት አጣሁልህ እንዴት ላመስግንህ ደሬ እግዚአብሔር ያክብርህ፣ ለሻለቃ ረጅም እድሜ ከጤናጋ ፈጣሪ ይስጥልን፣ በዚህ አጋጣሚ የዚህ ትውልድ ዘመን ልጅ ብሆንም ታሪኮትን በምችለው አቅም የኔ ትውልድም ከኛ ብኃላ ለሚመጣው ትውልድ እንዲሰሙትና እንዲማሩበት የእቅሜን አደርጋልው።
    በድጋሚ እግዚአብሔር ክብረት ይስጥልኝ።

  • @natnaelmebratu2819
    @natnaelmebratu2819 Před 3 lety +8

    በጣም የሚደንቁ አባት ናቸው ታማኝነታቸው የማስታወስ ችሎታቸው የታሪክ እውቀታቸው የሚገርም ነው በሶስት ክፍል ብቻ መቅረቡ አላጠገበኝም ደሬ በሌላ ርእስም ቢሆን ቢቀርቡና ተጨማሪ እውቀት ብናገኝ ደስ ይለኛል

  • @yonasgudu2956
    @yonasgudu2956 Před 3 lety +24

    “………ሻለቃ እንዴት እንደማመሰግንዎት አላውቅም ………....ቁጭ ብዬ የልቤ አይሞላም………..ብድግ ብል ……. ልበል ልነሳ ……….….ልክ እንደውም እንደቀድሞ ወግና ሥርዓት……..…… እንዲህ ብዬ ነው ማመሰግንዎት …እግዜር ያክብርልኝ ……….…እግዚአብሄር ፈጣሪ ጤናዎን ይጨምርልዎ………..……. ….ከእድሜውም በርከት ያድርግልዎ……..“ አሜን !!!
    እኛ ደግሞ አንባቢውን ታታሪውን ትሁቱን ሽቁጥቁጡን ሰው አካባሪውን ምርጡን የፕሮግራሙን አዘጋጅ ደረጀ ሀይሌን በማመስገን ቀጣይ እንግዶቹን በጉጉት በናፍቆት እንጠብቃለን ………

  • @netsitesfaye5704
    @netsitesfaye5704 Před 3 lety +10

    በዘመኔ ተመስጬ ያደመጥኩህ ረጅም እድሜ ለሁለታችሁም

  • @haymizee
    @haymizee Před 3 lety +34

    Thank you General Paulos. The reason why I said "General" is because you deserve it from the Ethiopian people although you were denied of it for a long time. I hope, your book or books will come out soon, and we will have a chance to document history and teach our children. Again, thank for your excellent services for Ethiopia. Dereje, as usual, you keep impress us with your award winning and professional presentations. Thank you for this wonderful interview. Respect!

  • @michaele9632
    @michaele9632 Před 3 lety +14

    … ባላለቀ… ባላለቀ… ባላለቀ… ምርጥ።

  • @user-gy4lq1id1z
    @user-gy4lq1id1z Před 3 lety +38

    Dereje thank you again for this extremely awesome interview. Your IQ of rembering names and events are amazing. I wish the current prime minister can use person like Paul as an advisor. It's not easy to find in Ethiopia a person like Paul with full of knowledge, sharp memory, articulate and rich in life experiences.
    Long live Ethiopia!

    • @merafwolde4601
      @merafwolde4601 Před 3 lety +3

      The current prime minister fell in love with himself and himself only.... There are a difference between what you do and what you talk.... Abiy is the person who talks and doing nothing....he doesn't have a real knowledge and a passion dear. He is in his illusion world. But Shaleka was a real hero who did their work beyond anything with knowledge..... passion and dedication. So he couldn't understand the value of a real worker lemalet new. ☺️

    • @tsegayetekle5336
      @tsegayetekle5336 Před 3 lety +1

      @@merafwolde4601 ምኑን ከምኑ አገናኘሀው ወዳጄ ? ለነዚ ሁለት ታላቅ ክብር ለሚገባቸው ኢትዮጵያኖች ምስጋና እድሜ ጤና ማቅረብ ትተህ ማወዳደር ገባህ ? ብቃቱስ አለህ ይህን ለማረግ ? ከሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ኢንተርቪው ሲያረግ አስተያየትህን ያኔ ብታሰፍር መልካም ነው ።ይሄን ጥሩ ታሪክ ጨዋታ ባታጠልሻው ሌላ ሃሳብ እየነከርክበት።

    • @merafwolde4601
      @merafwolde4601 Před 3 lety

      @@tsegayetekle5336 erasih banesahew hasab lay new asteyayet yesetehut abatu.... Advisor bihonut silalk new.... The current prime minister hears his own voice. Metadel yiteyikal endeshaleka Paulo's aynet sewochin advisor argo "mesrat" silethiopia mawrat bicha lemichil sew aymetinachewim lemalet new gebah?

    • @tsegayetekle5336
      @tsegayetekle5336 Před 3 lety

      @@merafwolde4601 ሲጀመር የኔ አይደለም አስተያየቱ በደንብ ተመልከተው ሲቀጥል ሃሳቡ በጣም መልካም ነው ደግፈዋለሁም። ይህን የመሰሉ ሰው አባታቸውም ተገድሎባቸው ለስርም ተዳርገው ለሃገራቸው ሲሉ የቆሙ ናቸው ሌላውን ወደ ጎን ብለው። ደሞ ሌላ ላሁን ላለን ሰዎች ጠቃሚ መልክት ያስተላለፉት 1.01.05 ላይ መልሰህ አዳምጠው የመለስ ስራ ስህተት መሆኑን አውቀው( ይሄን ማንም ሚረዳው ነው ) በጨዋ መልኩ" እኔ እሳቸውን የማረም ችሎታውም የለኝም ..." ነው ያሉት ። አብረሀው ሳትውል ውስጥ ሚስጥሩን ሳታውቅ ከትንተናው ብትቆጠብ ለማለት ነው። ደሞ ብርቱ የተጣመመን ዛፍ በለው ሃሳብ ሚያቃኑ ለኢትዮጵያ ሚያቀነቅኑ የሳቸው መሰል ገጎኑ ቢሆኑ ማን ያውቃል ነገን መልካም እድል ይኖረናል ለኛ ባይሆን ለልጆቻችን።

    • @michaelcorleone1861
      @michaelcorleone1861 Před 3 lety

      @@merafwolde4601 i disagree with you.

  • @bemewodushetube6327
    @bemewodushetube6327 Před 3 lety +5

    እጅግ በጣም እውነት ስሜታዊ ያልሆኑ
    እናት ሀገሬን አገልጋይ ወታደር ነኝ
    እናት ሀገር ታከብሮታለች
    እናመሰግናለን ለአገልግሎቶት!!

  • @thomas5820
    @thomas5820 Před 3 lety +2

    ምንም ቃል የለኝም እርሶን የማመስግንበት ሻለቃ ለሀገራችን የከፈሉትን ውለታ እግዚአብሔር ይክፈሎት !! ትክክለኛዋን ኢትዮጵያን እርሶ ስራ ውስጥ እና እርሶ ልብ ውስጥ አያዋት በእውነት ይሄ በእግዚአብሔር መባረክና መመረጥ ነው!!!

  • @shunumii7214
    @shunumii7214 Před 3 lety +6

    ደሬ እንደነዚህ እውነተኛ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት መኮንኖች ስታቀርብ የዚያን ጊዜ ኢትዮጵያ ትናፍቀኝና እንደ ማንባት ያደርገኛል። ሁልጊዜ የዛን ጊዜ ጀግና ኣቦቶች ኣቅጣጫው ለጠፋው ያሁኑ ትውልድ ትምህርት ሰጪ ስለ ሆኑ ዘወትር እንድራቀርብልን። ጤናና ዕድመ እመኝልሃለሁ።

  • @aulamath3849
    @aulamath3849 Před 3 lety +7

    ሚገርም ነው ኢትዬፕያ ግን ስንት አይነት ጀግና አፍርታለች ባካቹህ ሻለቃ ፓውሎስ እጅግ ጀግና ታሪክ አዋቂ ሀቀኛ ሻለቃ ኖት እውነተኛ ንፁህ ኢትዬኘያዊ ኖት አከብሮታለው ስላወኮት እጅግ በጣም ደስተኛ ነኝ, ,,,,,,, ደሬ እንደዚ አይነት ኩሩ ሀቀኛ እና ጀግና ኢተወዬኘያዊ ስላስተዋወከን እጅግ በጣም አመሰግንሀለው

  • @yonasghebre2411
    @yonasghebre2411 Před 3 lety +5

    wowww im Eritrean but i Love this Man Strong,faithful and honesty may GOD bless u abundantly also Thank u Dere

    • @yonasghebre2411
      @yonasghebre2411 Před 3 lety

      እንደዚህ ያለ ታማኝነት በዚህ ግዜ እንኳንስ ከወታደር ከቤተ ክህነት ኣይገኝም so amazing GOD bless u

  • @bekaluyirgalem9429
    @bekaluyirgalem9429 Před 3 lety +8

    ምን ይባላል እውነተኛ ኢትዮጵያዊ እግዚአብሔር ረጅም እድሜ ከጤና ጋር ይስጠወ።

  • @TommTube
    @TommTube Před 3 lety +11

    ደሬ ዙምባቤ ሄዶ መንግስቱን ካለመጠየቅ እንዲያደርጋቸው የምትመኙ እስቲ!✋

  • @adoalemayehu9498
    @adoalemayehu9498 Před 3 lety +8

    tears in my eyes wow dere ፣ እግዚአብሄር ይስጥልን ጌታዬ!

  • @SOLStudioCHANNELSolstudio
    @SOLStudioCHANNELSolstudio Před 3 lety +10

    Wow wow ትልቅ ታሪክ ትልቅ ሰው እኝህ አባት ለዚህ ትውልድ ትልቅ ምሳሌ ናቸው ደሞ ዕውቀታቸው ኢትዮጵያን ምንድነው ወደኃላ የመላሳት እግዚአብሔር ያስበን

  • @tilahunewnet4042
    @tilahunewnet4042 Před 3 lety +1

    የሚገርም ፅናት
    የሚገርም ስብእና
    የሚገርም የሀገር ፍቅር
    ደረጀ ከእየሱስ ክርስቶስ በቀር በሰው ልጅ እንዲህ አይነት ሰው አላየሁም
    አልሰማውም
    ሻ/ቃ ጳውሎስ ጌታቸው
    የጀግናው ብ/ጀ ጌታቸው
    ናደው ልጅ እናመሰግናለን ።
    ኢትዮጵያ የአንተና የመሰሎችህ እዳ አለብን =110ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን !!
    እናመሰግናለን ❤
    በመጨረሻም
    ሻለቃ ጳውሎስ ሙሉ ታሪክ በኢቲቪ ቢቀርብ
    በሀገር ደረጃ ቢሸለም
    ለትውልድ መልካም ነው።

  • @dawitabebe223
    @dawitabebe223 Před 3 lety +4

    ድንቅ የተጨመቀ መልዕክት ነው
    ብዙ አወቅን ተማርን እ/ር ዕድሜ እና ጤና ይስጦት ወደፊትም ብዙ እንጠብቃለን መልካም ዘመን ይሁንላችሁ !

  • @haletahandmade
    @haletahandmade Před 3 lety +10

    እኝህ ሰው አምላክ እስከፈቀደላቸው እድሜ ድረስ እንደቅርስ ቢጠበቁ ኢትዮጵያውያን ልንረባረብላቸው ይገባል

  • @SeneduAbebe
    @SeneduAbebe Před 3 lety +4

    በጣም ድንቅ ውይይት ።
    ጀግና አባት ደስስስስ ሲሉ ።❤😇

  • @meseretasfeha6329
    @meseretasfeha6329 Před 3 lety +8

    ታሪክ በባለ ታሪክ ሲተረክ አብየት መጣፈጡ ። እናመስግናለን ጋሽ ጳውሎስና ደረጀ ።

  • @kidisttessema4500
    @kidisttessema4500 Před 3 lety +3

    ሻለቃ ረጅም እድሜ ከጤና ጋር እመኝሎታለሁ ደረጀ እኝህን ምርጥ ኢትዮጵያዊ ስላቀረብክልን በጣም እናመሰግናለን ተባረክ

  • @user-hf5xo5gs5c
    @user-hf5xo5gs5c Před 2 lety

    ጀግና አባት እድሚ ይስጥልኝ ላገሩ ታማኝ ጅግነ የጀግና ልጅ ታሪክ በነተ ሲነገር እንዲት ያሰደስታል ክብር ይገባውታል👮👮👮👮👮👮🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹👑👑👑👑👑

  • @azoe6561
    @azoe6561 Před 3 lety +2

    በጣም የሚገርም ደስ የሚል እንዳያልቅ የፈለግኩት ቃለ መጠይቅ ነበር።
    በመጀመሪይር አቶ ደረጄን በጣም አመስግንሀለሁ!!!
    የምታቀርባቸው ሁሉ ጣዕም ያላቸው ስለሆኑ ፕሮግራምህን እወደዋለሁ።
    ሻለቃ ጳውሎስ በጣም ደስ የሚሉ ክቡር አዋቂ ንግግራቸው ለዛ ያለው ሥርዓት ያላቸው ሀቀኛ ስው፣ ለእውነት የቆሙ መሆናቸውን ያሳያል።
    ከዚህ ቃለ መጠይቅ በጣም ብዙ ነገርን እንዳቅ እና እንድማር አርጎኛል። ለሀገራችንም ምልካም ያረጉትንም ከነስማቸው እያስታወሱ መናገራቸውን ወድጃለሁ። እውነት ሁሌ ትወጣለች!!!
    ብዙ ያልተነገረላቸው በታሪክ ስማቸውንም ስማሁ እን በጣም ደስ አለኝ።
    ከነዚህ መልካም ከስሩ ስዎች አንዱ አጎቴ አቶ መኮንን ዘውዴ ለከርቸሌ ያበረከቱለት መልካምነት ስስማ በጣም አኮሩኝ።
    ባጠቃላይ አቶ ጳውሎስን አመስግናቸዋለሁ!!!🙏🏽
    እድሜና ጤና ይስጥልኝ!!!

  • @ethiopiayeneyene8265
    @ethiopiayeneyene8265 Před 3 lety +3

    ጋዜጠኛ ደረጄ ከልልልብ አከብርካለሁ አመሰግንሀለሁ ለአባታችንም እድሜና ጤናውን ይስጥልልልልን

  • @abywasg6813
    @abywasg6813 Před 3 lety +2

    ሻለቃ ቀሪ ዘመኖዎትን እግዚያብሄር ጤና ና ሠላም ይስጥዋት።የሚጣፍጥ የማይጠገብ ትምህርታዊ ጨዋታ፨አቤት አገር ወዳድነት ደረጄ እኔ ለአንተ ቃላት የለኝም እንደዚህ የተረሱና ለሀገር ብዙ ዉለታ የሰሩ ታላላቅ ሰዋችን ከምርጥ ብቃትና አቀራረብ ጋር ስለምታደርሰን እግዚያብሄር ሁሌም ከጎንህ ይሁን እናመሰግናለን፨

  • @dawitg25
    @dawitg25 Před rokem

    ደስ የሚሉ የዋህና ቅን ኢትዮጵያዊ ሰው ናቸው። ቂም፣ ጥላቻ ወይም በቀል የሚባል ነገር የላቸውም።
    ሰውየው በትክክል እርሳቸውም እንዳሉት ምንም አይነት የፖለቲካ እውቀቱም ሆነ ፍላገቱም የላቸውም። ውትድርና እና የሀገራቸው ፍቅር በሚገርም አይነት በደምና ባጥንታቸው ውስጥ ነው ያለው።
    የአይምሮአቸው የማስታወስ ችሎታና የአነጋገራቸው ለዛቸው የሚገርም ነው።
    እድለኛ ነን በህይወት ኖረው ይህን ለመስማት መብቃታችን።
    ደሬ አንደኛ ነህ ወደር የለህም

  • @alemwerku1940
    @alemwerku1940 Před 3 lety +3

    ኣይ ኤትዮጵያ ! ጀግና የማይከበርባት ኣገር ! ኣዝማሬ እና ፌዘኛ የሚወደስባት ኣገር ፣ ወዲ ጌታዬ ሻለቃ እድሜ ከጢና ተመኘሁሎት ።

  • @user-xy6iw4ke8t
    @user-xy6iw4ke8t Před 3 lety +8

    ለጆሮ መሳጭ ነው እድሜ ከጤና ጋር ይስጦ (ደሬ የልጅነት ትውስታዬ ነክ ጥያቄ እና መልሰ ላይ የድምጸህን ነገር እማ ተወው !እርጅም እድሜ ተመኘው!!🥰

  • @menduwonde2967
    @menduwonde2967 Před 2 lety +1

    እግዚአብሔር ድንቅ ነው! ሻለቃን በሒወት አቆይቶ ከደረጄ ጋር አገናኝቶ በጣም ጣፋጭና እውቀት የሚሆን ታሪክ ደስ በሚል እና በሚጣፍጥ አነጋገር እንዲሁም የንግግር ለዛው የሚያምር ..... አላውቅም እኔም ደረጄንም ሻለቃንም እንዴት እንደማመሰግን ለሁለቱም እረጅም እድሜን ከጤና ጋር ተመኘሁ ኢትዮጵያ ሰላምሽ ይብዛ!!

  • @getachewasmamaw8233
    @getachewasmamaw8233 Před rokem

    ከልብ ከልብ አመሰግናለሁ በዚህ ጀግና ሰው መነፀር እራሴን ሳይ ባዶ ነኝ እንጀራ ቆርሼ መብላቴ ይገርመኛል ብርታቱን ይስጥህ በሉኝ አመሰግናለሁ ፈጣሪ እድሜና ጤና ይስጥልኝ ጌታየ ብየ ልጥራው እንደ አባቴ እንደ አባተው
    በዚህ አሻሮ ትውልድ መወለዴ በጣም ያበሳጨኛል

  • @baryawbaryaw1390
    @baryawbaryaw1390 Před 3 lety +10

    የሚገርም ነው የድሮ ኢትዮጲያን በጣም ነው ምናፍቀው

  • @kalkidanatnaf5954
    @kalkidanatnaf5954 Před 3 lety +5

    በሚገርም ሁኔታ ኢትዮጵያን በሳችዉ ላይ እንደ ፀሀይ በርታ ትታያለች ከዉሰጣችዉ ነው ያላችዉ ፍቅር ቢሰሞ ቢሰሞ በፍፁም አይጠገብም ደረጀ በዉንት በጠአም ነው የማምሰግነው እድሚነ ጤና ይሰጣቸዋ ማን ይነገረ የነበረ

  • @abelkebede4623
    @abelkebede4623 Před 3 lety +6

    Unbelievable moment of my life, Ethiopian man hero

  • @alphaville7115
    @alphaville7115 Před 3 lety +2

    Such a beautiful interview, what a closing!Dereje is just the right match for such kind of figures. The Major - what can I say…Eloquent, energetic, a story teller with photographic memory. Could hardly believe in his 70s.I wouldn’t mind waiting another week if it was to have a 4th installment.His book is certain to be a good read. Major, I wish you long life full of health and happiness.

  • @jesuschristislord6940
    @jesuschristislord6940 Před 3 lety +7

    What a wonderful story it is? Thank you Major Paulos and amazing journalist Dereje!

  • @emmyt311
    @emmyt311 Před 3 lety +1

    እጅግ በጣም ደስ እሚል ጫወታ!! የእውነት ኢትዮጵያ ብዙ ታሪክ እና ብዙ ጀግና ልጆች አሏት!! ሻለቃ ደሞ ላይብረሪ ማለት ናቸው!!! እግዚአብሔር እድሜና ጤና ይስጦት!!! ደሬ ያንተ ፕሮግራም ሱሴ ነው!! ሰላም ለሀገራችን!!
    💚💛❤🙏

  • @mesleteshale3968
    @mesleteshale3968 Před 2 lety

    ደረጄ ግን እውነት ትልቅ ሰው ነህ እግዚያብሔር አብዝቶ ይውደድህ ክብር ለሚገባው ሰው የክብር ሰላምታ ሰተሃል

  • @zerihunbalta5636
    @zerihunbalta5636 Před 3 lety +1

    ድንቅ እንተርቪውና የሻለቃም ምላሽ ታሪካዊና ትምህርታዋዊ ነበር እናመሰግናለን ደሬ::

  • @ethiopiayeneyene8265
    @ethiopiayeneyene8265 Před 3 lety +5

    ጀግና ሰው!!!እግዚአብሔርን ጸጋውን ያብዛሎት

  • @danielabebe3443
    @danielabebe3443 Před 3 lety

    ትንታጉና ጀግናውና ትሁቱ ምርጡ ጋዜጠኛው ደረጀ ሀይሌ ሁሌም እናመሰግናለን እድሜ ከጤና ጋር ቱመኘሁ

  • @feyselahmed4581
    @feyselahmed4581 Před 10 měsíci

    Thank you for your service major. We are lucky to have fathers like you who can be really exemplary

  • @user-vl3xn6us6t
    @user-vl3xn6us6t Před 3 lety +3

    እንኳን ኖራችሁልን እናት ኢትዮጵያ የሞቱትን ነብሳቸውን በገነት ያኑርልን

  • @endalksisay6918
    @endalksisay6918 Před rokem

    እሚንቀሳቀሱ "ቤተ መፅሐፍት"!
    እረጅም እድሜ ከጤና ጋር ይስጠልን!

  • @dawitdave6328
    @dawitdave6328 Před 2 lety

    እድሜ ይስጦት ሻለቃ እናመሰግናለን🙏 ደሬ በመጨረሻ ላይ ቆመህ ለሰጠሀቸው ክብር እኔም ቆሜ እክብሬሀለው🙏

  • @user-hv1sk2zx6u
    @user-hv1sk2zx6u Před rokem

    ኢትዮጵያ ይሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ ብላ. አባቴ ክብር ይገባዎታል. እውነት መፅሀፋቸው እንዲታተም ትብብር እናድርግላቸው. ❤

  • @sitotawabebe4285
    @sitotawabebe4285 Před 3 lety +1

    ዋው ደ ሬ እሚገርም ኢትዮጵያ ዊነት ከ ቀይ ኮከብ ጥሪ ከኦሮማይ በሁዋላ አስቀምጡኝ የማይል ትልቅ መፀሀፍ አጣ ጣምኩ እውቀት የህይወት ልምድ ፅናት ጥንካሬ ብዙ ብዙ ለሻለቃ እድሜና ጤና ይስጥልን እናመሰግናለን ደሬ ኡፍ

  • @ys7474
    @ys7474 Před 2 lety

    ደሬ ምን ብዬ !!! ማመስገኛ ቃል አጣሁ። ለሻለቃ እድሜና ጤና ይስጥልን።

  • @alemayehuzenebe4119
    @alemayehuzenebe4119 Před 3 lety +1

    Major Paolos shows us country is above self interest, family, or clans allegiance. Honesty and truthfulness don’t change with times or circumstance. Also to respect everyone, gives the credit to whom it belongs and the necessary criticism and the solutions.
    Journalist Dereje shows us respect, preparedness, intelligence questions with the professional and Ethiopian manner.
    God bless you and your family both of you.

  • @W.W.J.D
    @W.W.J.D Před 3 lety +2

    Ethiopia should honer such brave and intellectual solder!
    Deri you are so amazing, no word to say your quality of work, you are the level of journalist s.
    God bless you all.

  • @jonilion9368
    @jonilion9368 Před 2 lety

    እኔ ሻለቃ ጳውሎስን ከልጅነቴ ጀምሮ ነው የማውቃቸው ምክንያቱም የአክስታቸውም ፣ የአጎታቸው ፣ልጆች ፣ ጎደኛ ነበርኩ ፣ ነበርኩ እና ትልቅ ብዙ ቤተሰቦች ናቸው ፣ስለዚህ ፣ የቤተሰብ ማህበር አላቸው ፣ አክስቱ ፣ቤት ሁለት ፣ ግዜ ለመሀበሩ ብለው ሲመጡ ፣ አይቻቸዋለሁ ፣ የዛ ግዜ ገና ወጣት ነበሩ ፣ በጣም ተጫዋች ናቸው ፣ ይህን ብዙ ቤተሰቦቻቸው ፣ ሲያወሩ እሰማለሁ ፣ ለሻለቃ ጳውሎስ እድሜና ጤና

  • @mickimaraki7886
    @mickimaraki7886 Před 3 lety +2

    ሻለቃ እግዚአብሔር እድሜ ጤና ይስጥዎ:: ደሬም እንደሁሌው እናመሰግናለን:: አንድ ቀን በድጋሚ እንደዚህ ሀገሩን የሚወድ ትውልድ እንደሚፈጠር ተስፋ አለን❗️

  • @abrahamt2356
    @abrahamt2356 Před 3 lety +3

    After watching this excellent interview, I can not sleep.Many many things come to my mind .Look, a single hero like Mr.Paulos Can bring a huge change in the society . Where we are now..? Why we go back than forward..? Why our country unable to get a lot heros like Mr.Paulos ...? Ahhhhffff Very painful

  • @zewdugobena5013
    @zewdugobena5013 Před 3 lety +8

    What a beautiful mind በጣም ንግግር አወቂ ምርጥ ሰው

  • @teshometesema7213
    @teshometesema7213 Před 3 lety +3

    Dere you're realy a great man. Thank you for what you're doing. God bless you.

  • @firehiwotbelay2180
    @firehiwotbelay2180 Před 3 lety +2

    Weeeehhhh, I have never seen an interview like this, omg Dereje, thank you very much! Shaleqa ema minim Qatar yelegnim, edmewot yerzem, genius , my God, so eloquent, knowledge nitir Yale, wow, thank you

  • @mulatabebe4469
    @mulatabebe4469 Před 3 lety +2

    ሙያው የሚፈልገው ሰው በሙያው ላይ ሲገኝ እንደዚህ እውቀትን ያሰተምራል ሁለታችሁንም እናመሰግናለን!!!!

  • @achildofgod9954
    @achildofgod9954 Před 3 lety +2

    I could listen to this honorable man forever.

  • @user-gw3ly1vd3z
    @user-gw3ly1vd3z Před 3 lety +2

    ድሬ በጉጉት ስጠብቅ ነበር ሶስተኜው ክፍል ልብ ውይ ምስጋና
    ሻለቃ ህይወት ውጣ ውርድ ጥንክሬ ጄግንነት ለሀገር ፍቅር ያላቼው ወኔ ጥንካሬ ይገርማል
    አይ ኢትዬጵያ
    እኒህን ያህል ትልቅ ወታደር ለሀገር ይህን ሀሉ ሰርተው ያለ ጡሮታ
    ያሳዝናል እጂግ በጣም ያሳዝናል

  • @antealehegnhailu2589
    @antealehegnhailu2589 Před 3 lety +1

    የሚገርም ነው የደር ታሪክ ለኔ ብቻነው አንደወይን ጠጅ የሚጣፍጠኝ😍😍😍

  • @temesgenmolla6470
    @temesgenmolla6470 Před 3 lety +3

    ደሬ ለስራዎችህ ሁሉ ታላቅ አክብሮትና ሙገሳ አለኝ፡፡ በስራዎችሁ ሁሉ ልትመሰገን ይገባሃል፡፡"ትክክልኛው ሰው በትክክለኛው የቴሌቪዥን ጣቢያ" ላይ ሰምና ወርቅ ሆነው ተገኝተዋል፡፡ ክብረት ይስጥልን!!
    ዛሬ ባቀረብክልን የሻለቃ ጳውሎስ ጌታቸው ታሪክ በእጅጉ ተደስቻለሁም፡፡ የቀደሙት አባቶቻችንን ሰብዕና እና ለዚች ሃገር የከፈሉትን ዋጋና መስዋትነት በእጅጉ ያስቃኘንና ያስተማረን ነው፡፡ በዚህም እንደ አንድ ኢትዮጲያዊ አባቶቻችን በከፈሉልን ዋጋ ኮርቻለሁ፡፡ በቀጣይም የዚህ ዓይነቱን ታሪክ ሰርተው ግን አስታዋሽ ያጡትን በባትሪ ፈልገህ በቀጣይም ታስመለከተንና ታሰማን ዘንድ ረጅም እድሜ ከጤና ጋር ተመኘሁልህ፡፡ ዛሬ ትውልዱ በሃሰት ትርክትና ባልተፈፀም ታሪክ ነጋሪዎች እየተሸወደ ያለበት ጊዜ ስለሆነ የዚህ ዓይነት ታረክ በተጨባጭ ሰርተው ያለፉት አባቶቻችን ታሪክ ከገባንበት አዘቅት ጎትቶ ስለሚያወጣን ፈጣሪ ብርታቱን እንዲሰጥህ በድጋሜ እመኛለሁ፡፡ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ፡፡

  • @Real_2015
    @Real_2015 Před 3 lety

    በጣም በጣም ደሱ የሚሉ አዋቂ ብለህ ኢትዮጵያዊ ናቸው እግዚአብሔር ዕድሜ እና ጤና ይሰጦዎት!

  • @tadessegosaye6057
    @tadessegosaye6057 Před 3 lety +2

    Both of you are rational keep it up wish you long life with health! Thank you!

  • @kingaklilu9665
    @kingaklilu9665 Před 3 lety +3

    ሻለቃ ጳውሎስ ጌታቸው ፍፁም ኢትዮጵያዊ የሆኑ አባታችን እንኳን እግዚአብሔር ዕድሜና ጤና ሰተዎት ይህንን የኢትዮጵያ ጀግና ወታደሮች ታሪክ ተዳፍኖ ሳይቀር በታሪክ እንዲመዘገብ በህይወት አቆየዎት

  • @eliasabebe7429
    @eliasabebe7429 Před 3 lety +1

    ድንቅ የሆኑ ሰው ናቸው የኢትዬፕያን ታሪክ ጠንቅቀው ያውቃሉ ውትድርናን ሲተነትኑት ልዩ አድርገው ነው የምህድስና ችሎታቸው የሚገርም ነው እኝህን ድንቅ ሰው እንድናውቃቸው በማድረግህ ደሬ አንተም ድንቅ ነህ...እድሜ ከጤና ይስጥልን

  • @haletahandmade
    @haletahandmade Před 3 lety +2

    ውይ ደሬ ታድለህ ስራህ ድንቅ ነው እግዚአብሄር ይባርክህ

  • @teferitegegne4312
    @teferitegegne4312 Před 3 lety

    ጀግና የጀግና ልጅ ናቸው ።ዛሬም ከነ ግርማ ሞገሳቸው ነው ያሉት ።የዛሬ 40 ዓመት ታሪክ ልክ እንደ ዛሬና ትላንት እንደሆነ ነው የሚናገሩት።ደረጀ የትላንቱን የሀገራችንን ታሪክ እያንዳንዷን እንድናውቅ እያገዝከን ስለሆነ ምስጋናም ይገባሃል።ያንተም ታሪክ አዋቂነት እጅግ እጅግ እጅግ የሚገርም ነው።

  • @samsonloha7537
    @samsonloha7537 Před 3 lety +3

    What a story! I am speechless! So beautiful!

  • @dawitteklemariam5827
    @dawitteklemariam5827 Před 3 lety

    በጣም እናመሰግናለን በጣም ምርጥ ሠው እድሜ ከጤና ይስጥልን አባታችን ጥሩ ሠው ለመጀመሪያ ግዜ እንደነዚህ አይነት ሠው ማይት በጣም ደስ ይላል አይጠገቡም ደጋግሜ ነው የማዳምጠው አሁንም አባታችን ብዙ ታሪክን ያውቃሉ በደንብ ሊያዙ የገባል ደሪ እባክህ እርዳቸው መጽሐፈንም ማውጣት አለባቸው ደሪ አንተንም እናመሰግናለን በጣም ምርጥ!!!!

  • @konjitgeremew8837
    @konjitgeremew8837 Před 2 lety

    ደራይ መነው ጠፍህ በስላምነው ስላምና ጤና እመኝልሀለሁ እባክ አትጥፉ እባክህ ክብር ይስጥህ🌷🌷🌷🌷

  • @dulahulukegna3746
    @dulahulukegna3746 Před 2 lety

    ደሬ ምርጡ በሳል እና እውቀት ያለህ ሁሉንም ያሟላህ ጀግና ጋዜጠኛ

  • @habibseifu9293
    @habibseifu9293 Před 3 lety

    ድሬ እድሜ ይስጥልኝ ያላወኩትን ለሃገራቸው ዋጋ የከፈለቱን እንዳውቅ ስለረዳኸኝ የኢትዮጵያዊነትን ፀጋ ደጋግሞ ያጎናፅፈን... ስለ አገራቸው የተጨነቁ የደከሙና የታመሙ እና ህይወታቸውን ላጡ ክብር ለዘላለምም ይስጥልን

  • @zemenmedia3824
    @zemenmedia3824 Před 3 lety

    What a man he is ! How honest and patriotic he is !!! May God bless you Shaleka ! And Derie awesome Journalist! Please he should be Honored by any means !!!!! Bless you !!!

  • @kiyasolomon8764
    @kiyasolomon8764 Před 3 lety +1

    በደርግ ጊዜ የነበሩ ወታደሮች የንግግርና የማስታወስ ብቃት እንዲሁም ሃገር ወዳድነታቸው ሁሌም ይደንቀኛል ደሬ እነዚህ ዓይነት ሰዎች አፈላልገህ ለታሪክ አስቀራቸው።ክብረት ይስጥልኝ

  • @birhanuteshome2368
    @birhanuteshome2368 Před 3 lety +1

    ደሬ መቸም ያንተን ዉለታ እኛ ኢትዮጵያዊያን አንረሳውም አንድ ቀን ያስገረሙህን የታዘብካቸዉ ያስደነቆህን ያሳዘኑህን ተጠርዘዉ እንደምናየው ተስፋ አደርጋለሁ እግዚአብሔር ካንተ ጋር ይሁን

  • @queencrown1674
    @queencrown1674 Před 3 lety +2

    Just listening to him 🤣🤣🤣😍😍😍😍😍 and cry with happiness what a gentleman
    I will meet him when I go to ETHIOPIa just to shake his hand 💚💛❤️

  • @amenelectronicsandliquiddeterg

    ደሬ በጣም አመሠግናለው ሻለቃን አጠገቤ ሆነው ያላገኘውትን እውቀትና ኢ/ያን አሣወከኝ ይገርማል ጎረቤት ሆኜ በድጋሚም አመሠግናለሁ ወ/ወሰን ገ/ማሪያም ከሀዋሳ

  • @KunaVenue
    @KunaVenue Před 3 lety

    አገር አፍራሽ ወያኔ እኝህን የመሳሰሉ የአገር ኩራቶችን ደብቃ የዚህ ትውልዶች ተጫወተችብን , ሻለቃ ክብር ይግባዎታል , ረጅም እድሜ ከጤና ጋር ያድልኦ, ደሬም እናመሰግናለን 🙏🏽

  • @wengaleamaha3751
    @wengaleamaha3751 Před 3 lety

    በእውነት ቃላት ያጥረኛል እድሜ ይስጦት ሀገር ወዳድ 💚💛❤️👏👏👏👏

  • @arefatsalah226
    @arefatsalah226 Před 3 lety

    በጣም ቆንጆ ቃለምልልስ ነዉ። ትልቅ ታሪክ አዋቂ ሰው ናቸው። አምላክ እድሜ ይስጣቸው።
    ደረጀ እጅግ በጣም ድንቅ ቃለምልልስ ነዉ። በርታ። እንደዚህ ያሉ ታላላቅ ሰዎችን እንግዳ በማድረግህ ምስጋና ይገባሀል።

  • @mekuriyazeleke6820
    @mekuriyazeleke6820 Před 6 měsíci

    አባኮትን የመፅሐፎን ነገር ነገ ዛሬ ሳይሉ በፍጥነት ያድርሱልን እድሜና ጤና ይስጦት

  • @neaminab8786
    @neaminab8786 Před 3 lety +1

    ደሬ በምን ቃል ይገለፃል የአንተ ጨዋነት፣ ብስለትና የታሪክ እውቀት!? እግዚዓብሔር ዕድሜና ጤና ይስጥህ! አክባሪህ ነኝ

  • @akliladmasu1244
    @akliladmasu1244 Před 3 lety +1

    እንዴት ያለ ብሩ አዕምሮ ነው ያላቸው ደስ ሲሉ

  • @henokamelga1650
    @henokamelga1650 Před 2 lety

    ጌታዬ ትልቅ ሰው ነዎት እግዚአብሔር እድሜ ጤና ይስጥዎት❤

  • @davidteklehaimanot4377
    @davidteklehaimanot4377 Před 5 měsíci

    Thank you kibur shaleka Pawlos; indesiwo Yale real Ethiopiawi sai, Ethiopiawineten yaxenekirewal! Igziabiher indesiwo Yale wendim yabzalin, iswom yalew indale huno, bedesta lebizu ametat legna bilo yanurwot; belijochwo iske mechereshaw igziabiher yasdesitwot. Inem sisemawot beagere wusx (Tenben) yalehu meselochih yisemegnal iswom lick agotochen yagegnehu meselochih indisemagn adrigewal. Wede agerachin Ethiopia simeta (ruk iyhonim) xeike selam lilot imexalehu. Thank you Shaleka.

  • @alemsani5007
    @alemsani5007 Před 2 lety

    ደሬ ምርጥ ጋዜጠኛ ደጋግሜ ሰማሁት። የማይሰለች። እኒህ ሰው ሞት ሳይቀድመን ብንጠቀምባቸው ምንኛ ጽሩ ነው። ብዙ እውቀት ብዙ ጉልበት። ይገርማል።

  • @hayalsewhayal9104
    @hayalsewhayal9104 Před 3 lety +4

    Dere Min Libelih ? I love your program & baying books from most of your Guests. Keep Marching

  • @ashebirdemissie4916
    @ashebirdemissie4916 Před 3 lety +1

    I might be the only person for attending this interview more than 3 times, since it is more interesting, historical , professional and deserves to be downloaded in the computer for future references, finally i want to say thank you very much for both of the interviewer and the interviewee!!!!!

  • @binyamcheynet6615
    @binyamcheynet6615 Před 3 lety

    wooo...unknown Ethiopian hero
    what a great person..God blessed you .🙏i salute you sir..

  • @bisratalebachew6719
    @bisratalebachew6719 Před 3 lety +2

    Wow it is indeed amazing interview. Dere you are the best

  • @ephremhailu4744
    @ephremhailu4744 Před rokem

    Amazing story great speech thank you for share 🙏