አማን ሻሎም ይቅርታ ጠየቀ :: ከምኩራብ ሾው ጋር የተደረገ ልዩ ቃለምልልስ | Aman Shalom

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 7. 07. 2023
  • #Aman_Shalom #christian_tube #mukrab_Show
    #Aklile_Shimels
  • Zábava

Komentáře • 342

  • @rev.terefediriba3023
    @rev.terefediriba3023 Před 11 měsíci +30

    ይሄ ልጅ ትልቅ ተስፋ የሚጣልበት ነው። እግዚአብሔር እንዲህ አይነቱን ሞጋች ያበዛልን ዘንድ የዘወትር ልመናዬ ነው!

    • @Godisgood-yd7xv
      @Godisgood-yd7xv Před 11 měsíci

      Amen 🙏🙏🙏🙌

    • @naodlulu1023
      @naodlulu1023 Před 10 měsíci +3

      ትልቅ ተስፋ የሚጣልበት Because he always has presuppositions in mind which he take into the bible ?

    • @SamuelChrist-im9kt
      @SamuelChrist-im9kt Před 7 dny

      በመንፈስ እና በቅባት አንድ ሰው ከሚልዮን ሞጋቾች ይበልጣል እኔ የተቀቡ እንድነሱ እፀልያለው

  • @abelwondu5085
    @abelwondu5085 Před rokem +42

    አማን በእግዚአብሄር ቃል የተሞላህ አንባቢ ወጣት እንደሆንክ ንግግርህ ያሳያል።በርታ ለቤተክርስቲያን እንዲ አይነት ወጣቶች ብዙ ያስፈልጉናል።

  • @lovemab2256
    @lovemab2256 Před rokem +25

    አማን ሻሎም የእግዚአብሄር ቃል እውቀት አሁንም ያብዛልህ በዚህ ትውልድ መገኘትህ እግዚአብህር ይመስገን!!

  • @ebenezeryenesewalamirew3190

    ስላልተረዳንህ በጣም ይቅርታ፣ የእግዚአብሔር ቃል ብቻውን እውነተኛ መመዘኛችን ነው።

  • @user-je2od2mh3e
    @user-je2od2mh3e Před rokem +31

    አማንን በጣም የምወደው ወንድም ነው የእግዚአብሔር ቃል እውቀት አለው ንግግሩ ሁሉ በእውቀት ነው በርታ አማንዬ በዚህ ዘመን ታስፈልገናለህ❤❤❤

  • @emebaemuti951
    @emebaemuti951 Před rokem +11

    የእግዚአብሔርን ኃይል አግኝቶ የትኛው አካል ነው የማይወድቀው ? ሳውልን ወይም ጳውሎስን በደማስቆ የጣለውንስ ምን ሊል ነው? ሲቀጥል እስከ መጨረሻው የሚፀና እርሱ ይድናል፡፡ ለዚህም የፅድቅ ትጋት ግ-ድ ይለናል ካልሆነማ ባለመታዘዝ እንደ አዳምና ሔዋን ከገነት መውጣትን ያመጣልና እ-ጅ-ግ እናስተውል !! ፀጋው ይብዛልን !!!

  • @henoksisay1224
    @henoksisay1224 Před rokem +12

    tnxs ምኩራብ ሾዎ አማንን ስለጋበዝክልን። አማን ድፍረቱን እወድለታለሁ፣ ጎበዝ ነው፣ ያነባል፣ ይሞግታል።እኔ የማልወድለት፣ የሚናገርበትን መንገድ ብቻ ነው። እሱን ቢያርም ቢያሻሽል እላለሁ በተረፈ ፀጋ ይብዛለት።

    • @tigistedosa5990
      @tigistedosa5990 Před rokem +4

      እባኮትን እድሜውንም ግንዛቤ ውስጥ አስገቡልን ልጁ ገና ወጣት ነው ወደፊት የስተካክላል

  • @cristianocr74102
    @cristianocr74102 Před 11 měsíci +4

    2 በልሳን የሚናገርስ ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው አይናገርም፤ የሚያስተውለው የለምና፥ በመንፈስ ግን ምሥጢርን ይናገራል፤

  • @agajedessie3541
    @agajedessie3541 Před 11 měsíci +3

    ጌታ ማስተዋልን ይሰጠው።ነብያት፣ሐዋሪያት ወዘተ አሁን አይሰራም እያለ በመንፈስ ቅዱስ ያምናል ማለት ተገቢ አይደለም።ያለባት ቸርች መሠረት ማስያዝ አለባት።የጌታን ስጦታ እየተቃወመ ሙሉ ወንጌል ነኝ ማለቱም አሳፋሪ ነው።

  • @yetnotIbutChristinme
    @yetnotIbutChristinme Před rokem +8

    ጳውሎስ ካልተተረጎመ በጉባኤ አታውሩ አለ እንጂ በልሳን ከትጸልይ አላለም::

  • @isaaco6542
    @isaaco6542 Před rokem +21

    ኣማን ምርጥ ሰው ከ እግዝኣቢሄር ስጦታችን ነህ

  • @bereketasfaw7168
    @bereketasfaw7168 Před 9 měsíci +4

    አማን ያቃልም ይፈላሰፈል ዝም ተብሎ መደመጥ የለበትም ሁሉ የሚለው ልክ ብቻ አይደለም በልዩ ቋንቋ መናገር የአማኝ ምልክት መሆኑን ቃሉ ይናገራል መንፈስ የተሞሉ ሰወች መንፈስ ቅዱስ የሰጣቸውን ቋንቋ ይናገራሉ አንዳንዶች በሰወች ቋንቋ አንዳንዶች በመልእክት ልሳን ይናገራሉ የመተርጎም ሰጦታ ያለው ሰው ካለ ይተረጉማል ተርጓሚ ከሊለ አለመተርጎሙ ልምምዱ የለም ማለት አይደለም ይሄ ልጅ ማለት አማን ይፈላሰፋል ጠንቀቅ ነው ጉበዜ

  • @sinidumelese7376
    @sinidumelese7376 Před 13 dny +3

    ይሔ እኮ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ማንም በራሱ አያገኘውም ለምን አማን እራስህ በዚህ አገልግሎት አታገለግልም በመንፈስ ቅዱስ ሥራ ላይ ጣልቃ ባትገባ ጥሩ ነው ፍልስፍናህን ብታቆም ጥሩ ነው።

  • @shewaneshtesema
    @shewaneshtesema Před rokem +5

    አማን በእግዚአብሔር እውቀት ላይ ያለእን ባደንቅም ነገር ግን ስለ መንፈስ ቅዱስ ያለህ አመለካከት አስተምሮህ ላይ ያለህ ግራ የተጋባ ትንታኔህ መምታታት ወደ ክደት እንዳትገባ እፈራልአለው ስለዚ የአንተን የተምታታን አስተምሮ መስማቲን አቁሚያለው ስትናገር ለሊላው ክርስቶስን መጠንቀቅ እንዳለብህ ይሰማኛል ።

  • @user-ml2jj7cd2q
    @user-ml2jj7cd2q Před rokem +3

    የሙሉ ወንጌል አባል ነኝ በሙሉ ወንጌል በነበርኩበት ዘመን የሚገርም የመንፈስ ቅዱስ አሰራርን አይቻለሁ በነዚህም ልምምዶች ተጠቅሚያለሁ ነገር ግን ይህ ሰው እንደተባለው የባእድ ልምምድ እንዳይሆን ልንጠነቅቅ ይገባል ፡፡

  • @amanuelabako3640
    @amanuelabako3640 Před rokem +6

    ከአማን በከፊል እስማማለሁ በአንድ አንድ ነገሮች ነገር ግን በአንድአንድ ንግግሮቹ መጸሐፍቅዱሳዊ ያልሆነ ፍልስፍና ነው በደንብ ከንግግሩ ከሰመነው!!!
    ዕውቀት ጥሩ ነው ነገር ግን ያለመነፈስ ቅዱስ ባዶ ጩወት ነው!! ....የመለኮትን አሰራር በአሰራርና በስርዓት ለመመዘንና ለመለካት መመኮር ሞኝነት ነው!!!!

  • @kingdom-channel478
    @kingdom-channel478 Před rokem +20

    😮😮አማን ሲቃወምም ሲደግፍም በእውቀት ነው በጭፍንና በጥላቻ አደለም ልቡም ቅንነት እንዳለው ይታያል❤❤

  • @thionlema7724
    @thionlema7724 Před 11 dny +3

    ንግግሩ ፍልስፍና ይመስላል እንደነዚ አይነቶች ያወቁ እየመሰላቸው በቅዱስ ቃሉ የሚፈላሰፉ የሚያስቱ ናቸው ሲያወራ እኔ ብቻ አውቃለሁ የሚል መንፈስ አለበት መንፈስ ቅዱስን የሚቃወም መንፈስ በናዝሬቱ እየሱስ ክርስቶስ ስም የፈረሰ ይሁን በእየሱስ ስም ይሄ ታድያ በመንፈስ ቅዱስ ሳያምን ሳይቀበል በስጋ መስበክ ሆነ ማስተማር እንዴት ይሆናል የቅዱስ ቃሉ ተቃዋሚ ነው

  • @samsungsamsung8431
    @samsungsamsung8431 Před 11 měsíci +3

    ጋዜጠኛው ግን ለመሞገት ነው ያመጣከው ወይንስ አማን የራሱን ሃሳብ እንዲናገር ነው ያመጣከው ? አማን የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን ነው እየተቃወምክ ያለከው:: ከእግዚአብሔር ቃል ይልቅ በሰዎች እውቀት ላይ ነው የተመሰረትከው:: ከንግግርህ መረዳት እንደሚቻለው ያነበብካቸውን የሰዎች ትምህርት ነው ማሳያ እያደረክ እምታቀርበው ያው ጥቅሶችን በመቀባባት:: እንጂ ጳውሎስ የቆሮንቶስ ሰዎችን በልሳን እንዳይናገሩ አላገታቸውም በስርአት እንዴት መናገር እንዳለባቸው በልሳን የሚናገር እንዲተረጉም ይፀልይ እንጂ የትርጉሙ ፀጋ እስኪሰጠው ልሳን አይናገር አላለም:: የሰዎችን መፅሐፍ ማንበብ ክፋቱ ይሄው ነው::

  • @joshalomshalom8461
    @joshalomshalom8461 Před rokem +5

    አማን የቃል እውቀት ሊኖርህ ይችላል፡ አውቀህ አንዳልጨረስክ አወቅ፡ ፡ ስለ ቛንቛ አልገባኝም አላውቅም ማለት እኮ ሀጥያት የለውም፡ ፡ አልገባኝም ለማለት አፍረህ ነው?

  • @ey504
    @ey504 Před rokem +7

    I like Aman's ground stand, his knowledge and confidence is amazing 👏 May God give him more grace 🙏

    • @yeselamhasabmenged8643
      @yeselamhasabmenged8643 Před 11 měsíci

      Indeed he has confidence ..but sadly his knowledge on word of God looks not healthy. In his conversation he has tried to defend his own understanding rather than Holyspirit affiliated understanding. Proudly he complained others by saying "ወተት የሚጋቱ " ግን እሱ "አጥንት የመቆርጠም የህይወት ከፍታ ያለው አድርጎ ያስባል። አሳዘነኝ የምር።

  • @senbetgebre
    @senbetgebre Před 9 dny

    አማን ሻሎምን ገና ዛሬ የእምነት አቌሙን ተረዳሁት ጥሩ መረዳት አለህ ጌታ ያብዛልህ በርታ በተለይ ብዙ ግርግር በበዛበት ግርግሩንም ተጠቃሚ ለቦች በሞሉበት በዚህን ጊዜ እንዲንተ ዓይነቶች ይብዙልን ማለት ዝም ብሎ በጭፍን የምቃወም ሳይሆን እንደዚህ በዕውቀት የተደገፈና አሳማኝ የእግዚአብሔር ቃል ዕውቀት ያለበት ሲሆን ደስ ይላል ተባረክ ፀጋ ይብዛልህ ❤

  • @habtamuwogakela1257
    @habtamuwogakela1257 Před 11 měsíci +2

    መጽሐፍን በደንብ ካጠናን ስለልሳ መናገር
    የመላዕክት ልሳን የተባለ በየትኛው የቋንቋ ላብራቶሪ ተንጉሙን የማናገኝለት ሰማያዊ (መለኮታዊ ልሳን አለ በፀሎት ከእግዚአብሔር ጋር የምናወራበት “በልሳን የሚናገርስ ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው አይናገርም፤ የሚያስተውለው የለምና፥ በመንፈስ ግን ምሥጢርን ይናገራል፤”
    - 1ኛ ቆሮንቶስ 14፥2
    እንዲሁም ሰማያዊ ቋንቋ ሆኖ በልዩ ልሳን መናገር የተባለና የፀጋ ስጦታ የሆነ ተናጋሪው የመተርጎም ስጦታ ካለው ተርጉሞ ወይም የመተርጎም ስጦታ ያለው ሰው በጉባዔ ካለ ስተረጉም ጉባዔ የየምታነጽበት አለ።
    እንዲሁም የሰው ልሳን የተባለ የሰው ቋንቋ ተናጋሪ የማያቀው ግን ቋንቋውን የሚችሉ ሰዎች በጉባዔ ስኖሩ መንፈስ ቅዱስ የሚያናግራቸው አለ“በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሽዋሽዋ ጸናጽል ሆኜአለሁ።”
    - 1ኛ ቆሮንቶስ 13፥1
    በበዓለ ሃምሳ 120ዎቹ የተናገሩት በዚህ የሰውዐልሳን ወይም ቋንቋ ነበር። የሐዋ 2 ያንብቡ።ሁሉንም ን

  • @meketagebremeskel3469
    @meketagebremeskel3469 Před rokem +3

    በጉባኤ ውስጥ ነው የሚለው በልሳን የተነገረን እንዴት በድምፅ መቅረፃቸው ተቀርፆ ትርጉም ይተረጎማል በልሳን የተነገረው የመተርጎም ስጣታ ነው እኔ አማርኛ እናገራለሁ ያ ተርጎሚው የማያውቀውን የማይነገረውን ልሳን መንፈስ ቅዱስ አቃበለው ተናገረ ሪከርድ የተደረገን መንፈስ ቅዱስ አላቃበለው እንዴት መንፈስ ቅዱስ ትርጉሙን ከነገረው ጋር ለማማሳከር ሁሉ ግራ የሚያጋባ ነው እንደገና እኔ ቴዌሌጂ ኮልጅ መ ምሬ ልሳን ሲተረጎም አውቃለሁ አሁን አሁን እየቀረ መጣ እንጂ ብዙ ግዜ በልሳን የተነገረን ስተረጎም ሰምቻለሁ ደግሞ በእምነት ነው እነዚህ ስጦታዎች የሚሰሩት እንዴ የሚታየውን ሳይሆን የማይታየውን አምነን ድነናል

  • @yeselamhasabmenged8643
    @yeselamhasabmenged8643 Před rokem +5

    ልሳን ለእግዚአብሔር ሚስጢር የምንናገርበት ስለሆነ ሀሉ ልሳን የግድ መተርጎም ላይኖርበት ይችላል። እንዲተረጉም ይጸልይ ተባለ እንጅ የማይተረጎም ልሳን አትናገሩ አልተባለም።
    👇👇👇👇👇👇
    “በልሳን የሚናገርስ ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው አይናገርም፤ የሚያስተውለው የለምና፥ በመንፈስ ግን ምሥጢርን ይናገራል፤”
    1ኛ ቆሮንቶስ 14፥2
    👇👇👇👇👇👇
    “በልሳን የሚናገር ራሱን ያንጻል፤ ትንቢትን የሚናገር ግን ማኅበሩን ያንጻል።”
    - 1ኛ ቆሮንቶስ 14፥4
    👇👇👇👇👇👇👇
    “ስለዚህ በልሳን የሚናገር እንዲተረጉም ይጸልይ።”
    - 1ኛ ቆሮንቶስ 14፥13

    • @zenebezenebu1567
      @zenebezenebu1567 Před 9 dny

      በልሳን መፀለዩ አላንጽ ያለው ሰው ልሳኑ ትክክል ስለማይሆን በጊዜ እንደ ማነው ልበል ማቆም አለበት። በልሳን መፀለይህ አንተን አለማነፁና ትርጉም አልባ መሆኑ ልሳንን የሚያጣጥል የሆነብህ እንደሆነ ከሰማኸኝ እነግርሃለሁ ፍራ። በልሳን እየፀለዩ የሕይወት ለውጥ የሌላቸው ሰዎች ግን እነርሱም ልሳናቸው ትክክል ነው የሚል እምነት የለኝም ምክንያቱም በልሳን ፀልዮ መታነጽ የሕይወት ግንባታን ያመለክታልና። መንፈሳዊ ስም በያዙ ነገሮች ዙርያ ያለው ግሳንግስ አይነቱና ብዛቱ አያድርስ ነው። አለን የምንለው ቃል እውነተኛ ልሳንንም በእርግጥም ሊወገዙ ከሚገባቸው ከሌሎች ልምምዶች ጋር ካስወገዘን ቃላችን የራሳችን ቃል ይሆናል እንጂ ከቅዱሳት መፃሕፍትና እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ተተርጉሞ እንደሚሰበከው የእግዚአብሔር ወንጌል ሊሆን አይችልም። እደግመዋለሁ ሊሆን አይችልም። መሳት አንድ ነገር ነው፤ስቶ ማሳት ግን የሚያመጣው ኪሳራና ፍርዱ ብዙ ነው። በመጽሐፍ ያለውና በሕይወታችን ሊገለጥ የሚገባው እውነት አልፈጸም ሲለን እግዚአብሔርን እንጠይቅ እንጂ እራሳችንን ጠይቀን የተሟላ መልስ እንደማናገኝ እንወቅ። በነገራችን ላይ ልሳንን በተመለከተ የሚተረጎም ከሆነና የመተርጎም ስጦታ ያለው አማኝ ከሌለ ሌሎች በማይሰሙት ቋንቋ ድምጻችንን ከፍ አድርገን መፀለያችን ሌሎችን ይረብሻል ነው አንዱ ፍሬ ሀሳብ እናም አንረብሽ(አናውክ) ነው። ሌላው ደግሞ ልክ እንደ ትንቢት መልእክት የሌለው አማኞች የሚናገሩት ልሳን መኖሩ ግልጽ ነውና እንዲህ አይነቱን ልሳን ትርጉም ካልኖረው ብለን ለትርጉም የምንፀልይ ካለን ለትርጉም ፀልዩ የሚል ትምህርት የለም። ነገር ግን እንዲህ ባለው ልሳን የሚናገር(የሚፀልይ) አማኝ ልሳኑ ከመረረቱ የሚተረጎም ስላይደለ በጉባኤ መካከል ድምጽን ከፍ አድርጎ በዚህ ልሳን መፀለይ ትክክል አይደለምና አማኙ ለራሱ ይፀልይ ሌላውን አማኝ ድምጡን ከፍ አድርጎ በመፀለይ አይረብሽ ነው። በልሳን ብቻ አይደለም አፋችንን በፈታንበትም በምንችለው ቋንቋ በጉባኤ ስንፀልይ መሪ ፀላይ ሆነን ሌሎች አድምጠው አሜን የሚሉት ፀሎት ካልሆነ በቀር በቋንቋችንም ድምጣችንን ከፍ አድርገን በመጠለይ ከጎናችን ያለውንና ጉባኤውን ልንረብሽ አይገባም። የግል ፀሎት ማለትም ወደ እግዚአብሔር የምንፀልየውን ፀሎት መሪ ፀላይ ካልሆንን በቀር ለምን ሌሎች እስኪሰሙት ድረስ እንፀልያለን?

  • @jesussaves1474
    @jesussaves1474 Před 11 měsíci +8

    # የአማን ስህተቶች ።
    1) ልሳንን በተመለከተ ያነሳው ሃሳብ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም።
    በመጸሐፍ ቅዱስ :- የሚታየው ፣ ሁለት አይነት ልሳን ነው
    1)ለእግዚአብሔር ብቻ የሚነገር ልሳን ( ሊተረጎም የሚችል )
    ይህ በምድር ላይ ያለ የሰው ቋንቋ አይደለም። እግዚአብሔር ብቻ የሚሰማው ነው
    “በልሳን የሚናገርስ ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው አይናገርም፤ የሚያስተውለው የለምና፥ በመንፈስ ግን ምሥጢርን ይናገራል፤”
    - 1ኛ ቆሮንቶስ 14፥2
    2) በምድር ያለ ልሳን ቋንቋ
    እንግሊዝኛ ፣ ስፖንሽኛ ፣ አማርኛ....
    መተርጎም አያስፈልገውም ፣
    በቀጥታ እንደ ሐዋርያቱ ዘመን ሊሰሙት የሚችሉ ሰዎች ስላሉ።
    ለምሳሌ :- እኔ አማርኛ ብቻ ብችል ፣ ስፖንሾች ባሉበት ስፖንሸኛ ብናገር ፣ ማለት ነው።
    ሐዋርያት 2
    ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
    ⁴ በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥ መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደ ሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር።

    ¹¹ የቀርጤስና የዓረብ ሰዎች፥ የእግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ በልሳኖቻችን ሲናገሩ እንሰማቸዋለን።
    በዚህ መልኩ ነው መታየት ያለበት።

  • @mimilam5753
    @mimilam5753 Před rokem +13

    ይሄ ልጅ በቂ እዉቀት ያለዉ ጠያቄ ያስፈልገዋል ጠያቂዉ ከአሉባልታ ወሬዎች የዘለለ መሞገትና መጠየቅ አልቻለም ። አማን ግን ጎበዝ ነዉ ። በርታ ሁሉ ነገር በእዉቀት ሲደገፍ ደስ ይላል።

  • @user-pm5so5uu8t
    @user-pm5so5uu8t Před 10 dny

    WOW! ግሩም የሆነ የእግዚአብሔርን ቃል መረዳትና እውቀት ያለህ ወጣት ነህ በርታ እውቀትህ የአዕምሮ ዕውቀት ብቻ እንዳሆን ነገር ግን እውቀትህ በእግዚአብሔር ፀጋ የተቃኘ ይሆን ዘንድ የፀሎት ህይወትህ የበረታ መሆን አለበት ብየ ወንድማዊ ምክሬን እሰነዝራለሁና በርታ የእግዚአብሔር ፀጋ ይብዛልህ

  • @birhan3282
    @birhan3282 Před rokem +3

    ልሳን በእናንተ ሰፈር ካልተተረጎመ ብለን አለማመንን ባናስቀድም ጣሊያንኛ በሌላም የኢትዮጵያ ቋንቋ ተነግሮ ተተርጉሞ ደግምም የተነገረው ተፈጽሞ አይተናል ስለዚህ በእኔ ካልሆነ አላምንም የሚለውን እይታ ቢስተካከል

  • @gentimesfin9154
    @gentimesfin9154 Před rokem +11

    በጣም ነው ማደንቀው ምክንያቱም ሙግቱ ከዕውቀት ጋር ነው❤❤

  • @fraolgirma3755
    @fraolgirma3755 Před rokem +9

    Thank you, Amani. It is an insightful conversation. The so-called prophet and Apostles are the source of confusion and disarray.

  • @berekettufo3240
    @berekettufo3240 Před rokem +4

    ለራሱ ልሳን መናገርኮ ይቻላልኮ በአንዱ አቅጣጫ ብቻ ለምን እናያለን ጎበዝ

  • @koketlemesa9966
    @koketlemesa9966 Před rokem +7

    Thank you Aman shallom,we need you more

  • @nanitsige7310
    @nanitsige7310 Před 10 dny

    አማኒ ገና ወጣት ነው ከእድሜው በላይ በስሏል ጌታ ይርዳህ እስከመጨረሻው

  • @yeselamhasabmenged8643
    @yeselamhasabmenged8643 Před rokem +4

    አማን ከባድ ስህተት ተናገርክ "ጳውሎስ ልሳንን ዜሮ አድርጎታል" አልክ ግን ጳውሎስ ያለው ይህንን ነው 👇
    “ከሁላችሁ ይልቅ በልሳኖች እናገራለሁና እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤”
    - 1ኛ ቆሮንቶስ 14፥18
    1ኛ ቆሮንቶስ 14
    ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
    ³⁹ ስለዚህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ትንቢት ለመናገር በብርቱ ፈልጉ፥ በልሳኖች ከመናገርም አትከልክሉ፤
    ⁴⁰ ነገር ግን ሁሉ በአገባብና በሥርዓት ይሁን።😊

  • @JamboSintayehu-ub5pk
    @JamboSintayehu-ub5pk Před rokem +7

    አማን ሚዛን ሥራለት ለትምህርትህ አእምሮዬ ያለፍሬ ይሁን ብዬ ሳይሆን እራሴን ለማነጽ ነው በልሳን የሚጸልይ እራሱን ያንጻል ስለሚል ይሄ ይቀርብሃል ወንድሜ ለትምህርትህ ሚዛን ሥራለት የምልህ ለዚህ ነው

  • @habtid
    @habtid Před 11 měsíci +2

    ልሳን የመተርጎም ጸጋ ያላቸው ሰዎች ሁሉንም የሚሰሙትን ልሳን ትርጉም ይሰማሉ/ያውቃሉ ወይም መስማት/ማወቅ አለባቸው የሚል አመለካከት ያለው ይመስለኛ አማን ሻሎም፤ ሲናገር "አንድ ልሳን ሪከርድ አድርጌ ሁለት የሚተረጉም ሰዎች ጋር ሄጄ እንዲተረጉሙ ጠየቋቸው" የሚለው ሀሳብ ራሱ ትክክል ነው ወይ? ቃለ መጠይቅ አድራጊው ለምን አልጠየቀውም ወይስ "እሱን ልስማ" ብለህ ብቻ ነው ያቀረብከው? ይተረጉማሉ የሚባሉ ሰዎች በዚያ ጸሎት ቦታ ላይ መገኘት አለባቸው የሚል አመለካከት አለኝ፤ በዚያን ጊዜ ጌታ መንፈስ ቅዱስ ሊናገርና ጉባኤ ውስጥ ያሉት ሰዎች ሊሰሙት የሚገባቸው ነገር ሲኖር ይመስለኛ መንፈስ ቅዱስ ትርጉሙን የመተርጎም ጸጋ ላላቸው ሰዎች የሚገልጽላቸው ብዬ አምናለሁ። ምክንያቱም ጉባኤን ሊያንጽ ሲፈልግ ይመስለኛል ትጉሙን የሚሰጣቸው። አለበለዚያማ ቃሉ እንደሚል "ከእግዚአብሔር ጋር ሚስጢር ያወራል" ወይም ራሱን ያንጻል። እኔ ለምሳሌ አንዲት እህት አለች እኛ ቤ/ክ ውስጥ ልሳን የመተርጎም ጸጋ ያላት ግን በጉባኤ ውስጥ የሚነገሩ ልሳኖችን ሁሉ አትተረጉምም። አንዳንድ ቀን መድረክ ላይ ትወጣና "እክሊት/እከሌ የተናገረው ልሳን እንዲህ ነው" እያለች ብዙ ጊዜ ለጉባኤ የሚሆን የትርጉም መልዕክት ትናገራላች። እኔ ጠይቄያት አውቃለሁ "ሁሉንም የሚነገሩ ልሳን ትርጉም ትሰሚያለሽ እንዴ" ብዬ። መልሷ "አይ አልሰማም አንዳንድ ልሳኖችን ነው መንፈስ ቅዱስ ትርጉሙን የሚሰጠኝ" ብላኛለች። በልሳን መናገርን ላለመቀበል ያቀረበው argument ትክክል ወይም በቂ ነው ብዬ አላስብም። ሌላው ደግሞ ሐዋሪያት ነብያት አሁን ላይ የሉም ብሎ እንደሚያምን ተናግሯል ታዲያ ኤፌ 4 ላይ የተገለጹትን እንዴት ነው የሚያየው? በአንድ ጥቅስ ላይ "በሐዋሪያትና ነብያት መሰረት ላይ ታንጻችኋል" የሚለውን ይዞ ከሆነ ቃሉ refer ሊያደርግ የፈለገው በራእይ ላይ "የበጉ ሐዋሪያት" የተባሉትን ቢሆንስ? ያ ጥቅስ ብቻ በቂ ነው እንደዚያ ዓይነት ድምዳሜ ላይ ለመድረስ?! እኔ ቃለ መጠይቅ አድራጊው ወንድም በቂ ዝግጅት ያደረገ አይመስለኝም እንደዚህ ዓይነት ጥያቄዎችን ለመጠየቅ ካሰበ አቋሙን አስቀድሞ እንደሚያውቅ ተረድቻለው በመግቢያው ላይ ሲናገር ምናልባት እሱን እንዲጋብዘው ያደረገው አስቀድሞ የተከሰቱ ነገሮች ይመስሉኛል ታዲያ ያ ከሆነ challenge ለማድረግ እንደጠያቂ ሊዘጋጅ ይገባል ባይ ነኝ። ሰዎችን በሚገባ ካልጠየቅናቸው የሚናገሩት ሁሉ ትክክል ስለሚመስል እሱ የስነመለኮት ተማሪ ሊሆን ይችላለ ግን እሱ የሚያምንበት view ብቻ አጽዕኖት አድርጎ ሊናገር ስለሚችል።

  • @birhanfeleke1629
    @birhanfeleke1629 Před 9 hodinami

    ዮሐንስ 16:13፤ ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል።

  • @user-ml2jj7cd2q
    @user-ml2jj7cd2q Před rokem +3

    ይተረጎማል የሚተረጉሙ ብዙ ሰዎችን አይቻለሁ

  • @aazewde9394
    @aazewde9394 Před rokem +10

    ከትልቅ ይቅርታ ጋራ ለሚድያው ባለቤት የምለው ነገር እባክህ በመንፈስ ቅዱስ አሰራር ላይ በጣም ብዙ ልምምድና ብዙ እውቀት ያለውን ስው አምጥተህ እንዲጠይቀው ብታደርግ መልካም ነበር ምክኒያቱም አማን ለሚናገርውራ ነገር ብዙ challenge የሚያደርገውን ጥያቄ መጠይቅ ይቻል ነበር

    • @maranatha391
      @maranatha391 Před rokem +3

      ከቃሉ ውጪ የሰው ልምምድ ቻሌንጅ አያደርግም አማን በብዙ ዕውቀት የተሞላ ነው የሚያስፈልገን ወደ ቃሉ እውነት መመለስ እንጂ የሰውን ልምምድ ወደ መከተል አይደለም ቃሉ በቂ ነው

    • @mimik1569
      @mimik1569 Před rokem +2

      በጣም ትክእል አኔም እንደሲነው ያሰብኩት

    • @aazewde9394
      @aazewde9394 Před rokem +1

      @@maranatha391 እስቲ ልጠቅ(ህ)ሽ የሚገርመኝ መንፈስ ቅዱስ ህልውናው ከ እኛ ጋር አለ ካላችሁ ስለዚህ አረሰራሩን አስቀምጦ ነው ማለት ነው ከእኛ ጋር ያለው? እሱ እኮ ካለ ራሱ ህልውናው ሁሉንም ያጠቃልላል
      ሃይሉንም ጥበቡንም etc.
      ወይም ከእኛ ጋር የለም ብላችሁ ትናገሩ

  • @DanZfire
    @DanZfire Před 10 měsíci +1

    መሉውን ቃለምልልስ ሰምቸዋለሁ ብዙ መልካም ነገሮች አሉት ስለእርሱም አክሊለንም አማንንም ማመስገን እፈልጋለሁ!
    የኔ ስጋት ግን አማን ስለልሳንና ስለደህንነት እንዲሁም ስለ predestination ያለው ምልከታ ብዙ ያልጠራ ነገር አለው እና ክፍል ሁለት ላይ እነዚህን የክርስትና አንኳር ጉዳዮች በደንብ አጥርቶና አመዛዝኖ እንዲናገር ደግመህ ብታጠይቀው ጥሩ ነው አክዬ ለምን ኮሜት ላይ ረጅም ነገር መጻፍ ጥሩ ስላይደለ በአንተ ያምራል ብዬ ነው!

  • @mayasura9916
    @mayasura9916 Před 9 dny

    Waw ,,,, Aman Just waw
    Aman is the grace of Man Like his father GOD. his voice is such golden.... I saw this kind of voice one in a million.

  • @yeselamhasabmenged8643
    @yeselamhasabmenged8643 Před rokem +2

    አማን አንድ የተሳሳትከው ነገር አለ።
    አንድ ቃል በተለያዩ ቋንቋዎች የተለያዩ ትርጉም ሊሰጥ ይችላል።
    ለምሳሌ "ቁላው" የሚለው ቃል በሲዳምኛና በአማርኛ ፍጹም የተለያየ ትርጉም አለው።
    ስለዚህ በልሳን የተነገረ ቃል በሁለት የተለያዩ ቋንቋዎች አስተርጉሞ የተለያየ ትርጉም ስላገኘህ የጌታ ስጦታ የሆነውን ልሳን disproved ማድረግ ትልቅ ስህተት ነው።

  • @user-sp4sy1xc8x
    @user-sp4sy1xc8x Před rokem +5

    Yes we love you Aman! Gobez geta yagezeh bekalu yetemolah denk you geta barya neh ! Beraseh metemameneh des yelal !❤❤❤❤❤❤

  • @dannytilaye5226
    @dannytilaye5226 Před 11 měsíci +3

    I have been listening to the most knowledgeable pastor and preachers here in West for many years and learn so much from them. When I hear Aman explaining his beliefs and hermeneutics, it's extraordinary. I hope we will see more young apologists emerge in the future. Keep up the good work, brother.

    • @yohan7782
      @yohan7782 Před 11 měsíci

      You should listen to Richard Dawkins

  • @yamsrachgerimagebisa9152
    @yamsrachgerimagebisa9152 Před rokem +10

    አማኒ ጌታ ይባርክክ ግልጥ አርገክ ነው ያስረዳከን

  • @hagos9183
    @hagos9183 Před rokem +3

    I live in America I heard Amaan repeatedly saying that Pentecostal are minorities but in fact it’s the Only Christian denomination growing and producing fruits in all of the world. For instance in the UA where I live the majority of American denomination is Pentecostalism and the main reason is the presence of the Holy Spirit and it’s work

  • @abebaabrham1655
    @abebaabrham1655 Před 11 měsíci +4

    አማን ልጄ ጌታ እየሱስ አሁንም ፀጋውን ያብዛልህ በጌ ቤት ዘመንህ ይሉቅ ጌታ ይጠብቅህ እዱግ ተባረክ!!❤️❤️❤️

  • @RK-rd9nb
    @RK-rd9nb Před rokem +4

    Don’t interrupt the guest when they’re answering your questions

  • @rahelbelete4991
    @rahelbelete4991 Před rokem +1

    ሁለተኛውን ክፍል እየጠበቅን ነው፤ አማኑ ጌታ እየሱስ በነገር ሁሉ እንዲያሳድግህ ፀሎታችን ነው። ታድያ መሪህን ጠበቅ አርገህ ያዝ እሺ እንወድሀለን ወንድማችን እደግልን።

  • @betsegawjohn9558
    @betsegawjohn9558 Před rokem +1

    ልሳን ራስን ያንጻል የሚለውን በልሳን መጸለይን ትቃወማለ ስለዚህ አገልግሎት መስመር ያስዋል ብለክ ነገርልንን ደግም ቤተክርስቲያን የሚያስቅይር መንፈስ ዋጋ እያስከፈልው ነው።።

  • @chakurchakur9704
    @chakurchakur9704 Před 7 dny

    ኖኖኖ እዲጸልዩ ነው እጂ ማይ ጸልዩ ለማለት ኣንተነው ያልከው ደሞ ለባቶች ልትዘልፍቻው ጀመርክ እድሜክ እዲበዛ ለኣባቶች ክብር ይኑርክ ማይነኩ መንካት በደለኛ እንዳስብልክ

  • @sewmehon5245
    @sewmehon5245 Před rokem +1

    Thats so true! When someone is filled with the Holy Spirit, they become bold to preach the gospel of JESUS CHRIST

  • @yeselamhasabmenged8643
    @yeselamhasabmenged8643 Před rokem +1

    #ምኩራብ_ሾው እባካችሁን ስስለርእሰ ጉዳዩ በቂ ልምምድና አውቀት የሌላውን ሠው ለዚህ ቃለመጠይቁ መምረጣችሁ ልክ አይደለም። ወንድሜ አማን በዚህ በቃለመጠይቅ ብዙ የእውቀት ክፍተቱን አጋልጧል። ሌላ የተሻለ ሰው ቢጠይቀው በበዙ ሊሞግተውና ምናልባትም ሊያቃናው ይችላል።
    ጌታ መንፈስቅዱስ ለቤተክርስቲያን የሠጠውን አማኞች ለማመናቸው ምልክት ተደርጎ የተሠጡትን መለኮታዊ ስጦታዎች በዚህ ልክ ማቃለል አይገባም።
    “ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋል፤ በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፤ በአዲስ ቋንቋ ይናገራሉ፤ እባቦችን ይይዛሉ፥”
    - ማርቆስ 16፥17

  • @yetnotIbutChristinme
    @yetnotIbutChristinme Před rokem +1

    ሁሉን ነገር አውቃለው የምትል እየመሰለኝ ነው፤ጌታ መንፈስ ቅዱስ የሚሰራበትን በዚች የሰው ቁንጽላ አእምሮ ይዘህ ተረድቼህ ካልጨረስኩ የምትለው ነገር እኔ ካልገባኝ የለም የሚባል አስተሳሰብህን አርም:/

  • @addgizaw7059
    @addgizaw7059 Před 11 měsíci +3

    ወንድሜ የሚተረጎም ልሳን አለ ሁለት ወይም ሶስት ሆነው ይናገሩ ሌላ ይተርጉም ። ትንቢትም ሁለት ወይም ሶስት ሆነው ይናገሩ ሌሎች ይተርጉሙ ። እነዚህ ስጦታዎች የተሰጡት ቤተክርስቲያን ለማነጽ ከሆነ ። እንደ ሳሙኤል ዘመን የነቢያት ጉባኤ ወይም እንደ ኳየር አንድ ላይ የሚፀልዩ የሚያገለግሎ ቢሆኑ ይህ ችግር አይፈፀምም ነበር ። ሐዋሪያት 17 ነቢያት ወደ አንጾኪያ ወረዱ ይላል ። በጋራ ያገለግሉ ነበር ማለት ነው። እና 1ኛ በቆሮንቶስ 14:28 መሠረት በአንድ ሰው የሚመጣውን ትንቢት ሐዋሪያው ጳውሎስ ለመቀበል ይቸገር ነበር ። እንግዲህ ወገኖች ማወቅ ያለብን ያልገባንን ከማውራት በደረስንበት ብንመላለስ መልካም ነው። በመንፈስም መዘመር አለና ። ወደንም ጠላንም በልሳን መናገር እጅግ አስፈላጊ ነውና። መንፈስ ድካማችንን ያግዛል እንዴት እደምንፀልይ አናውቅምና በማይነገር መቃተት ይማልድልናል ። ተብሎ ተጽፏል ።

  • @yeselamhasabmenged8643
    @yeselamhasabmenged8643 Před rokem +2

    በልሳን መናገር ከመንፈስቅዱስ ሙላት ጋር ስለመገናኘቱ መጽሐፍቅዱሳዊ ማስረጃዎች
    👇👇👇👇👇👇👇👇
    ሐዋርያት 10
    ⁴⁵ ከጴጥሮስም ጋር የመጡት ሁሉ ከተገረዙት ወገን የሆኑ ምዕመናን በአሕዛብ ላይ ደግሞ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ስለ ፈሰሰ ተገረሙ፤
    ⁴⁶ በልሳኖች ሲናገሩ እግዚአብሔርንም ሲያከብሩ ሰምተዋቸዋልና።
    👇👇👇👇👇👇👇👇
    “ጳውሎስም እጁን በጫነባቸው ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ወረደባቸው በልሳኖችም ተናገሩ፥ ትንቢትም ተናገሩ።”
    ሐዋርያት 19፥6

  • @user-nt3hf1my1n
    @user-nt3hf1my1n Před rokem +3

    Amen you are amazing, b ezbher kale laye yalke wekte amazing nw You are blessed

  • @tesfayefichala9036
    @tesfayefichala9036 Před 11 měsíci +1

    በበዓለ ሃምሳ ዕለት ፡-
    1. አንድ ልሣን ሳይሆን ልሳኖች ናቸው የወረዱት፡፡
    2. ልሳኖቹ ምድራዊ ናቸው፤
    ማለትም ያን ጊዜ ይሰሟቸው የነበሩ ሰዎች፡-
    2.1. እየተናገሩ ያሉት እኮ በቋንቋዎቻችን ነው ብለዋል፡፡
    3. በአሁኑ ጊዜ በሁሉም ቦታ ልሳን ተብሎ ሲነገር እየተሰማ የቆየውና ያለው ደግሞ፡-
    3.1. በአብዛኛው ፕሮናውንሴሽኑ/ቅላጼውና ቃላቱ ባብዛኛው የአንድ ልሳን ብቻ እንደሆኑ ያሳያሉ፤ ለዚያውም የየትኛውም ሕዝብ ያልሆነ አንድ ልሳን ነው፡፡
    3.2. ሁሉም ተናጋሪ ይህንን አንድ ዓይነት ልሳን መናገሩ፡-
    3.2.1. ለሆነ ሰው ተሰጥቶ የተሸመደደ ይመስላል፡፡
    3.2.2. ከአምላካችን ከመንፈስ ቅዱስ ስለመሆኑም ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡
    4. በአሁኑ ጊዜ ለምንድነው በየቤቴክርስቲያኑ በበዓለ ሃምሳ ላይ እንደነበረው ብዙ ልሳኖች ያልተሰጡትና የማይቀርቡት?
    5. ያለውንስ ልሳን የኔ ነው የሚል ሕዝብ ጠፋሳ?

  • @asnakeshewaseyasib2284
    @asnakeshewaseyasib2284 Před rokem +4

    God blessing you Aman bro.

  • @user-om7fx3od7z
    @user-om7fx3od7z Před 10 měsíci +1

    ተናጋሪው የማያውቀው 1ቆሮ 14:16-17 ተርጓሚ የማያስፈልግ ሐዋ2:6-12 ሌላ የማይተረጎም 1ቆሮ 14:2

  • @fatemaabarra8114
    @fatemaabarra8114 Před rokem +3

    Amen tabarki geta tsagawunhi abizaliki❤

  • @user-ov1ir3sv1w
    @user-ov1ir3sv1w Před 10 dny

    በውን ይህስው መፈሳዌ ሳይሆን ጥቄት እውቀት ብጤ አለኝ የሜል ስው ይመስለኛል ግን ቃለመጠይቅ ባታደርጉለት ለብዙ ወጣቶች ውድቀት እዳይሆን እፈራለሁ ይህስው። አደገኛ የመጽሀፍ ቅዱስ ተቃዋሜና አደገኛ አካሔድ ያለው ሰው ነው

  • @mamojoffe6778
    @mamojoffe6778 Před rokem +2

    Thank you Amanu!

  • @kebrontariku9405
    @kebrontariku9405 Před rokem +3

    Stay blessed Aman

  • @hagos9183
    @hagos9183 Před rokem +2

    I don’t understand why are those Christians giving big deal about people who’re like Aman ?? They’re saying God stopped working no !! God is the same as the Bible says Jesus is the same yesterday, today and forever that means Our God has the same plane. Aman because you don’t have it doesn’t mean there’s no any more.
    Look at the churches who believe no more of the work and gift of the Holy Spirit they’re dying and accepting the gay and human philosophy

  • @diborayejesus7720
    @diborayejesus7720 Před rokem +2

    አማንሻ የተወደድክ ፀጋው ያግዝህ።አንተኮ መፅሐፍ ነህ ተባረክ ጌታ ስላንተ አመሰግነዋለሁ ክብር ለጌታ

  • @user-ml2jj7cd2q
    @user-ml2jj7cd2q Před rokem +1

    የደንቆሮ አስተሳሰብ ካልሆነ እንጅ እኔ በህወቴ የማታዉቅ አንድት ሴት ሀሁን የማታውቅ አሮጊት በእግሊዘኝ ስትፀልይ ሰምቻለሁ ግን ቋንቋውን አታውቀውም እኔ የተረጎምኩት በተማርኩት እንጅ የመተርጎም ስጣታ ስላለኝ አይደለም፡፡

    • @danielbizuneh1221
      @danielbizuneh1221 Před 11 měsíci

      ENEM AWKALHU BROTHER BRASHA LOUNAGE YMTSLEY YAWUM K ERTFRA BRHA YMETACH SETYO RASHA LTMHERT HEDO TILO YMETA (SUDAN ) LIFE HISTRY TENAGERECH SETYWA ENKWAN RASHA LTAWK KERTO RASAWE SW AYTAM ATAWKE LOCAL SCHOOL GBTAM ATwkem shabbat hona breha gebta stwaga ynberch set nberch .enem yhen awkalhub.

  • @abelnigussie566
    @abelnigussie566 Před rokem +1

    አክሊልዬ አማን አሁን ባነሳቸው ጉዳዮች ላይ የምንወያይበት ዕድል ቢኖረኝ ደስ ይለኝ ነበር።

    • @mikurabmedia2572
      @mikurabmedia2572  Před rokem

      እሺ መጋቢ አቤል :: ስልክህን በሚሴንጀር ላክልኝ

  • @andishman
    @andishman Před rokem +5

    Aman, በጣም ምሁር ነህ። God bless you

  • @zenebezenebu1567
    @zenebezenebu1567 Před 9 dny

    በልሳን መፀለዩ አላንጽ ያለው ሰው ልሳኑ ትክክል ስለማይሆን በጊዜ እንደ ማነው ልበል ማቆም አለበት። በልሳን መፀለይህ አንተን አለማነፁና ትርጉም አልባ መሆኑ ልሳንን የሚያጣጥል የሆነብህ እንደሆነ ከሰማኸኝ እነግርሃለሁ ፍራ። በልሳን እየፀለዩ የሕይወት ለውጥ የሌላቸው ሰዎች ግን እነርሱም ልሳናቸው ትክክል ነው የሚል እምነት የለኝም ምክንያቱም በልሳን ፀልዮ መታነጽ የሕይወት ግንባታን ያመለክታልና። መንፈሳዊ ስም በያዙ ነገሮች ዙርያ ያለው ግሳንግስ አይነቱና ብዛቱ አያድርስ ነው። አለን የምንለው ቃል እውነተኛ ልሳንንም በእርግጥም ሊወገዙ ከሚገባቸው ከሌሎች ልምምዶች ጋር ካስወገዘን ቃላችን የራሳችን ቃል ይሆናል እንጂ ከቅዱሳት መፃሕፍትና እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ተተርጉሞ እንደሚሰበከው የእግዚአብሔር ወንጌል ሊሆን አይችልም። እደግመዋለሁ ሊሆን አይችልም። መሳት አንድ ነገር ነው፤ስቶ ማሳት ግን የሚያመጣው ኪሳራና ፍርዱ ብዙ ነው። በመጽሐፍ ያለውና በሕይወታችን ሊገለጥ የሚገባው እውነት አልፈጸም ሲለን እግዚአብሔርን እንጠይቅ እንጂ እራሳችንን ጠይቀን የተሟላ መልስ እንደማናገኝ እንወቅ። በነገራችን ላይ ልሳንን በተመለከተ የሚተረጎም ከሆነና የመተርጎም ስጦታ ያለው አማኝ ከሌለ ሌሎች በማይሰሙት ቋንቋ ድምጻችንን ከፍ አድርገን መፀለያችን ሌሎችን ይረብሻል ነው አንዱ ፍሬ ሀሳብ እናም አንረብሽ(አናውክ) ነው። ሌላው ደግሞ ልክ እንደ ትንቢት መልእክት የሌለው አማኞች የሚናገሩት ልሳን መኖሩ ግልጽ ነውና እንዲህ አይነቱን ልሳን ትርጉም ካልኖረው ብለን ለትርጉም የምንፀልይ ካለን ለትርጉም ፀልዩ የሚል ትምህርት የለም። ነገር ግን እንዲህ ባለው ልሳን የሚናገር(የሚፀልይ) አማኝ ልሳኑ ከመረረቱ የሚተረጎም ስላይደለ በጉባኤ መካከል ድምጽን ከፍ አድርጎ በዚህ ልሳን መፀለይ ትክክል አይደለምና አማኙ ለራሱ ይፀልይ ሌላውን አማኝ ድምጡን ከፍ አድርጎ በመፀለይ አይረብሽ ነው። በልሳን ብቻ አይደለም አፋችንን በፈታንበትም በምንችለው ቋንቋ በጉባኤ ስንፀልይ መሪ ፀላይ ሆነን ሌሎች አድምጠው አሜን የሚሉት ፀሎት ካልሆነ በቀር በቋንቋችንም ድምጣችንን ከፍ አድርገን በመጠለይ ከጎናችን ያለውንና ጉባኤውን ልንረብሽ አይገባም። የግል ፀሎት ማለትም ወደ እግዚአብሔር የምንፀልየውን ፀሎት መሪ ፀላይ ካልሆንን በቀር ለምን ሌሎች እስኪሰሙት ድረስ እንፀልያለን?

  • @MmD-jo2sc
    @MmD-jo2sc Před rokem +1

    Thank you for stating the oblivious. For any tongue you speak there shall be a translation and a translator.

  • @kidistimogos409
    @kidistimogos409 Před rokem +2

    Ewente new yemetenagerwe
    Bheyamanote Anegenagnem gen temechegnaleke asetemeroteke betame dese selmilegn new gora yemelwe !!!!
    Thanks 😊

  • @BedahaneGeleto
    @BedahaneGeleto Před měsícem

    የንበቢ ፍልስፍነ ሰማይ አየደርስም እምነት በተጸፈው ቃል በእውነትነ በመንፈስ መመን ነው የድሮ አበቶቻቾን እሄ ሁሉ ትኦሎጅ {ፍልስፍና} ሰይኖር የጌታ እጅ ከነርሱ ጋር ነበረ አሁን ፍልስፍነ ንግድ ሐሰተኛ አስተማር ለድሃ ከመጸለይ ከደሃ ቀምቶ መብለት ለጸሎት መስከፈል ትደር መበተን ድሃን መግፈት ሃብተሙ መስጠገት ብቻ ብዙ ማለት ይቻለል ;;

  • @nile5492
    @nile5492 Před rokem +3

    መማርህ ጥሩ ነው ብዙ ስለወንጌል ከተለያዩ ስህተቶች ትምህርቶች ስትከራከር መልካም ነው ነገር ግን በመንፈስ ቅዱስ ላይ አሁንም የተሳሳተ ደክማ ነጉሮች እየጠቀስ የመንፈስ ቅዱስንን ስራ ማንቃሸሽ ጥንቃቄ ማድረግና ንስሐ መግባት ይገባሃል :: ያለእግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስ ስራ ቤተክርስቲያን ልታድግ አትችልም ደግሞ የእምነት መስራቶች ሃዋርያት ናቸው እንጂ ሪፎርመሮች እይደሉም ከነሱ ምነውስደው መልካምንነው እንጂ ውድቀታቸውን ወንድሜ ውድቀታቸውን እንደትክክል መውሰድህ ትልቅ ስህተት ነው :: በቀና ልብ ወደ መልካሙ ቃል ተመለስ እግዚአብሔር ይርዳህ::

  • @helinatesfaye9947
    @helinatesfaye9947 Před rokem +10

    We love Aman!!❤❤❤

    • @tme251
      @tme251 Před rokem

      Egzabheren klebachewe seleawetu newa bete kerstinachewe yedanse bota argewetal Amrica ,weterne yemtelewe hulu.

    • @tme251
      @tme251 Před rokem

      Western

  • @yeselamhasabmenged8643
    @yeselamhasabmenged8643 Před rokem +1

    እግዚአብሔር አምነው የዳኑትን "ቅዱሳን" ብሎ የሚጠራቸው በዳኑበት እውነት አይቶ ነው ነገር ግን ጌታን ከካዱ በራሳቸው ምርጫ ወደ "እርኩሳን" ጎራ ይቀላቀላሉ።
    እግዚአብሔር ሰውን ከፈጠረ በኋላ "መልካም እንደሆነ አየ" ነገር ግን በሃጢአት ሲጨማለቅ ሰውን በመፍጠሩ ተጸጸተ" ይላል ቃሉ።
    ያ ሰው ያለበትን እውነተኛ ነባራዊ ማንነቱን መግለጹ ነው። ስለዚህ ሰው አምኖ ከዳነ ...ክዶ ይጠፋል። ነጻ ፈቃድ ተሰጥቶናል።

  • @bemnetl7442
    @bemnetl7442 Před rokem +1

    amanny, be ewket slemitmogt silante destegna negn egziabher yibarkh.

  • @mihretunikola8
    @mihretunikola8 Před 11 měsíci

    You are amazing Aman! God bless you.

  • @TemesgenNur
    @TemesgenNur Před rokem +7

    አማን ተባረክ ፀጋው ይብዛልህ

  • @aazewde9394
    @aazewde9394 Před rokem +4

    እረ ጠያቂው ልጠይቅህ hyper grace ስትል ሰማሁህ የእግዚአብሔር grace ከ hyper ም ይበልጣል እንደውም ከ hyper የሚበልጥ word ቢኖር እሱን መጠቀም ያስፈልጋል
    Study the WORD of God real good.
    At this point watching this program is a waste of time, goodbye

  • @Mary-gc2py
    @Mary-gc2py Před rokem +7

    I support a lot of your ideas Amani. Keep going ❤

  • @jesussaves1474
    @jesussaves1474 Před 11 měsíci

    "ምኩራብ" ሰላም ይብዛልህ ፣ አገልግሎትህ ፣እና ፕሮግራም ግን እወደዋለሁ፣ በርታ ፣ እርጋታህ እና ጥያቄዎችህ ፣ የበሰሉ ናቸው ።
    ስለ ልሳን በተናገረው ላይ ያቀረብኩትን ሃሳብ ከታች በክፍል ሁለት ብታቀርብልኝ?
    ተባረክ።

  • @Lomi-Wuha
    @Lomi-Wuha Před rokem +2

    እንግዳ የሆነ አስተምህሮት ነው የሰማሁት በተለይ መፅሃፍ ቅዱስ ላይ ያሉት "ሃዋርያትና ነብያት መሰረት ናቸው" እነሱ እየሱስን ስላዩት የተለዩ ናቸው ከእነሱም በኃላ ይሁን አሁን ላይ ነብያት እና ሃዋርያት የሉም ኦፊሱ ግን አለ የሚለው ልቀበለው ከብዶኛል:: አጭበርባሪዎች አሉ ከሆነ ትክክል ያስማማናል

  • @abellewi
    @abellewi Před rokem +4

    Amanu ❤❤❤❤ we love you 😍

  • @saratekle4858
    @saratekle4858 Před rokem

    Please please next part.........

  • @mikiyasendaleASFAWU-pd2uj
    @mikiyasendaleASFAWU-pd2uj Před 11 měsíci

    “በቆሮንቶስ ላለች ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፥ በክርስቶስ ኢየሱስ ለተቀደሱት፥ የእነርሱና የእኛ ጌታ የሆነውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በየስፍራው ከሚጠሩት ሁሉ ጋር ቅዱሳን ለመሆን ለተጠሩት፤”
    - 1ኛ ቆሮንቶስ 1፥2

  • @birhan3282
    @birhan3282 Před rokem +1

    ዕብራውያን 6
    ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
    ⁴ አንድ ጊዜ ብርሃን የበራላቸውን ሰማያዊውንም ስጦታ የቀመሱትን ከመንፈስ ቅዱስም ተካፋዮች ሆነው የነበሩትን
    ⁵ መልካሙንም የእግዚአብሔርን ቃልና ሊመጣ ያለውን የዓለም ኃይል የቀመሱትን
    ⁶ በኋላም የካዱትን እንደገና ለንስሐ እነርሱን ማደስ የማይቻል ነው፤ ለራሳቸው የእግዚአብሔርን ልጅ ይሰቅሉታልና ያዋርዱትማልና።
    ይህን ቃል ከምትከተለው አስተምሮ ጋር አይጋጭምን ። በተጨማሪ ዕብ 2 እና 10 ላይ ያለውስ ቃል።

  • @alemayehugemechu6239
    @alemayehugemechu6239 Před rokem +2

    ጳውሎስ አጋቦስ ስቷል አላለም አጋቦስም አልሳተም ጳውሎስ ግን ከመታሰር ያለፈ ለወንጌል የመሞት ስብዕና እና አቋም ነበረው። ምክንያቱም ጳውሎስ መንፈስ ቅዱስ በሥፍራ ሁሉ ይመሰክርልኛል የሚል ማረጋገጫ ተናግሯል።

  • @habotare-pn6db
    @habotare-pn6db Před rokem +4

    Pentecostal negn gn totally agree with him

  • @danaitdanait9973
    @danaitdanait9973 Před rokem +3

    ፍትህ ለአማርኛ!! የሚሰሟችሁ አማርኛ ተናጋሪዎች እንጂ እንግሊዝኛ አይደለም

  • @user-pm5so5uu8t
    @user-pm5so5uu8t Před 10 dny

    Thank you Aman

  • @faresevitoria5796
    @faresevitoria5796 Před 11 měsíci

    Gazetgawe sew asecherse plz

  • @birhanfeleke1629
    @birhanfeleke1629 Před 9 hodinami

    ፍጥረታዊዉ ሰው መፀሐፍ ቅዱስን ተምሮ በስጋ ሲገለጥ ውጤቱ

  • @kiyatesfaye634
    @kiyatesfaye634 Před 11 měsíci

    ወንድም አኬሊል በጌታ ፋቅር አንድነገር እጠይቅሀለው በመጀመሪያ በዘመናችን እንዲ ህ በእግዚአብሔር ቃል የታነጸሰው ሰላቀረብክልን ጌታ ይባርክህ በመቀጠል አማንን ማግኘት ብትረዳን ብዙ ማር ከእርሱ ሰለምፈልግ ብትረዳኘ ?

  • @isaaco6542
    @isaaco6542 Před rokem

    Can't wait part 2

  • @jesussaves1474
    @jesussaves1474 Před 11 měsíci +2

    ይህ ወንድም የሚናገረው ፣ ግማሽ እውነት ነው።
    ግማሽ እውነት አደገኛ ነው። እንጠንቀቅ።
    ምክኒያቱን ከስር አስቀምጫለሁ :-

  • @bijouxmelaku9370
    @bijouxmelaku9370 Před rokem +1

    ልሳኖች ነው የሚለው ቃሉ የቁዋንቁዋ ብቻ ቢሆን ልሳን ብቻ ይል ነበር በዘመናችንም ያየነው ጌታ ሲሰራ በቤተክርስቲያን ቃሉም እንደሚለው
    1ቖሮ 12 ማርቆስ 16 የሐዋሪያት ስራ 2
    የግል ከእግዚ አብሄር ጋር ሚስጥር የምናወራበት የማይተረጎም ቁዋንቁዋ ያልሆነ
    የጉባኤ የሚተረጎም ቁንቁዋ ያልሆነ ልሳን
    የቁዋንቁዋ የሆነ ልሳን ለዚህ ነው ልሳኖች የሚለው

  • @Godisgood-yd7xv
    @Godisgood-yd7xv Před 11 měsíci

    May God bless and protect you Aman❤❤❤

  • @lydiagrant5958
    @lydiagrant5958 Před rokem +1

    Gobez Aman!