የማቴዎስ ወንጌል ትምህርት 1- የንጉሡ የዘር ሐረግ- በማሙሻ ፈንታ Matthew Teaching 1- The King’s Genealogy - By Mamusha

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 21. 08. 2024
  • ይህ ] ትምህርት በኢትዮጵያ የሕይወት ብርሃን ቤተ ክርስቲያን፣ በአዲስ ክርስቲያን ላይፍ አሴምብሊይ አጥቢያ ዘወትር አርብ በማሙሻ ፈንታ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ነው።
    ትምህርቱን በቀጥታ ስርጭት መከታተል ለምትፈልጉ
    ዓርብ ምሽት 11:30 - 1:30
    Yoututube - Equip Media / @equipmedia2577
    Facebook - Equip Media Mamusha Fenta
    / 312726798871156
    አድራሻችን፡ ካዛንቺስ ከመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን ባሻገር 200 ሜትር ገባ ብሎ
    ጉግል ማፕስ - google maps address
    maps.app.goo.g...

Komentáře • 127

  • @equipmedia2577
    @equipmedia2577  Před rokem +72

    #እነሆ_ንጉሥሽ
    #የማቴዎስ_ወንጌል_ትምህርት
    #የንጉሡ_የዘር_ሐረግ
    📖 ማቴ 1 : 1 - 17
    - ኢየሱስ ክርስቶስ ከስጋ ስላልተወለደ የስጋ አባት የለውም፤ ህጋዊ አባቱ ግን ዮሴፍ ነው።
    - ማቴዎስ 1 ዝም ብሎ የዘር ሀረግ መቁጠር አይደለም፤ ወንጌል ነው የሚነግረን።
    - ማቴዎስ በዚህ ምዕራፍ ሊነግረን የፈለገው መልዕክት ይህ ነው "መዳን ታላቅነትና ስራችን ታይቶ የሚሰጥ ደመወዝ ሳይሆን በእግዚአብሔር ጸጋ ለተመረጡ ኃጢአተኞች የተዘረጋ ቸርነት ነው"።
    - ወደ እግዚአብሔር መንግስት ውስጥ መግባት በታላቅነት ላይ የተመሠረተ አይደለም፣ በስራ ላይ የተመሠረተም አይደለም፤ በእግዚአብሔር ጸጋ ላይ ብቻ ተመሥርቶ ለተመረጡ ሀጢአተኞች፣ ምሥኪኖች የተዘረጋ የእግዚአብሔር ቸርነት ነው።
    - የማቴዎስ ወንጌል ሲጀምር የኢየሱስን ማንነት አውጆ ነው። ኢየሱስ ማነው?
    * ክርስቶስ ነው (የተቀባ ፣ መሢሕ ፣ ንጉሥ)
    ✔️ የዳዊት ልጅ
    * ንጉሣዊ ማንነቱ ነው (የንጉሥ ዳዊት ልጅ ነው)
    - የተስፋ ፍጻሜነቱን አመላካች ነው። ያንን ተስፋ ፈጻሚ ነው ይሔ ንጉሥ።
    - ይሔ ንጉሥ እግዚአብሔር ለዳዊት የሰጠውን ዙፋን አልጋ ወራሽ ነው።
    - እግዚአብሔር ከተናገረ፤ ያለው ሳይሆን አይቀርም።
    📖 2ሳሙ 7:12 ...ዙፋንህ ለዘለዓለም ይጸናል
    📖 2ዜና 7:-18 .....ከዘርህ አይታጣም
    📖 ኢሳ 9:6 ..በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ይመጣል
    📖 ኢሳ 11:1 ....አበቃለት የተባለለት ግንድ
    - ማቴዎስ "ይሔ ንጉሥ" ብሎ ሲጀምር ለዳዊት የተገባው ተስፋ ፍጻሜ ንጉሡ ኢየሱስ መሆኑን ሊነግረን ነው።
    📖 ራዕ 22:16 ...የዳዊት ስርና ዘር ነኝ
    - ኢየሱስ የተስፋዎች ሁሉ ፍጻሜ ነው። እግዚአብሔር የተናገረው ጊዜው ረዝሟል? ጨለማ ውስጥ ገብቷል? ተግዳሮት ገጥሞታል? የተናገረው ግን በክርስቶስ ሆኗል።
    ✔️ የአብርሃም ልጅ
    * የአህዛብ ሁሉ መባረኪያው መንገድ እሱ መሆኑ ነው።
    - እግዚአብሔር በምንም ነገር Challenged አይሆንም፤ ክፋት የሚጎዳው እኛን ነው እንጂ እግዚአብሔርን አያገኘውም።
    - የሰው ከፍታ የእግዚአብሔር ዝቅታ ነው።
    📖 ዘፍ 22:18 ..በዘርህ ይባረካል
    - "ዘርህ" የሚለው ክርስቶስን ነው።
    - አለም ሁሉ እንዲባረክ ኢየሱስ የአብርሃም ልጅ ሆኖ መጣ።
    - ለዳዊት የተገባውን የንጉሣዊ ተስፋ (ዙፋን)፣ ለአብርሃም የተገባውን የድነታዊ ተስፋ (ድነት) ሁለቱንም ያጠናቀቀበት የተስፋዎች ሁሉ ፍጻሜ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
    📖 ማቴ 1 : 2-17
    = የንጉሡ የዘር ሐረግ ምን ይመስላል?
    - የእስራኤልን ታሪክ በ3 ትውልድ 14/14 አድርጎ ይዘረዝራል።
    * ከአብርሃም - ዳዊት
    * ከዳዊት - ባቢሎን ምርኮ
    * ከባቢሎን ምርኮ - ክርስቶስ
    - የአይሁድ ስሞች ፊደላት ብቻ ሳይሆኑ ቁጥርም አላቸው። ለምሳሌ ፥ ዳዊት የስሙ ፊደላት ድምር 14 ነው።
    📖 1ነገ 1-3
    - ንጉሡ የሚመጣው ከይሁዳ ነገድ ነው።
    ✔️ የንጉሡ የዘር ሐረግ ውስጥ ለመግባት እንዴት ነው የተመረጡት? በምን መለኪያና መስፈርት ነው?
    - ኢየሱስ ጋር መጠቃለል /መዳን ስራችንና ማንነታችን፣ ጥርት ማለታችን ታይቶ እንደ ደመወዝ የሚሰጥ ሳይሆን ለማይመጥኑ ሀጢአተኞች እንዲሁ በችሮታ የሚሰጥ ጸጋ ነው።
    - በንጉሡ የዘር ሐረግ ውስጥ የተቀላቀሉትን ስንመለከት ያልተለመደውን ሴቶችን አካቷል።
    - ሴቶች ከገቡ ደግሞ ደህና ደህናዎቹን ማስገባት ነበረበት። ነገር ግን የገቡትን ሲነግረን፦
    * እስራኤላውያን ያልሆኑ
    * ሴቶች
    * ከሴቶችም የማይመረጡ
    1➲ትዕማር (ቁ.3)
    📖 ዘፍ 38
    - ከነአናዊት ነበረች (ከአህዛብ ወገን ናት)
    - ጋለሞታ ነበረች
    - ከአማቿ ጋር የተኛች ነበረች (አረገዘች)
    - ወንጌልን ያማረ እንዲሆን ያደረገው የሀጢአታችን ጥልቀት ነው።
    - ያላማረ ታሪክ፣ ዘግናኝ ታሪክ ይነግረንና ወደ ዘር ሐረግ ውስጥ አስገባቸው ይለናል። አስደናቂ ታሪክ ያላቸው፣ ምርጥ ምርጦቹ አልገቡም።
    - ከዚህ የቆሸሸ ታሪክ ውስጥ የተገኙ ሰዎች ናቸው የንጉሡ የዘር ሐረግ ውስጥ የገቡት።
    2➲ ራኬብ (ቁ.5)
    - ራብ ነበረች
    - ጋለሞታ ነበረች
    3➲ቤርሳቤህ (ቁ.6)
    - ባሏ ከአህዛብ ወገን ነው
    - የኦሪዮን ሚስት የሰለሞን ዘር
    - እግዚአብሔር አስደናቂዎቹን እየመረጠ በችሎታቸው በህይወታቸውና ጥራት ያስገባ አምላክ አይደለም።
    - ወንጌል እግዚአብሔር አንስቶ በንጉሡ የዘር ሐረግ ውስጥ ያካተታቸው እንጂ የተመረጡ ስለሆኑ አይደለም።
    4➲ ሩት
    - ሞዓባዊት ናት
    📖 ዘዳ 23:3
    - በህጉ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ እንዳይገቡ የተከለከሉ ነበሩ።
    📖 ማቴ 1:21...ከሀጢታቸው ያድናቸዋል
    - እርሱ ጠራ ጠራ ያሉትን እየመረጠ የሚያስገባ ሳይሆን ሀጢአተኞችን የሚያድን ነው።
    - ማቴዎስ በንጉሡ የዘር ሐረግ ውስጥ የሚነግረን ዋና መልዕክት፥ ኢየሱስ የአብርሃም ልጅ፣ ኢየሱስ የዳዊት ልጅ፣ ኢየሱስ ንጉሥ፣ ኢየሱስ የአብርሃምን ተስፋ ፈጻሚ፣ ክርስቶስ፣ ንጉሥ፣ መሢሕ መሆኑን ነው።
    - ዘሩ ሲቆጠር መልካም መልካሞቹ ተቆጥረው በስራቸው የገቡ ሳይሆን የማይመስል ታሪክ ያላቸውን፣ ደካሞችን፣ ከእስራኤል ውጭ ያሉትን፣ ክፉ ነገስታትን፣ ደግ የሚመስሉትንም ጨምሮ በእነርሱ የሚመካ፣ እነርሱን "ዘሬ" ብሎ የሚቆጥር አዳኝ ነው ኢየሱስ።
    - በመዳናችን ልንገረም ይገባናል፤ በእግዚአብሔር የተሰጠን የዘለዓለም ህይወትና፣ በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ መግባታችን፣ የንጉሡ የዘር ሐርግ ውስጥ መግባታችን በራሱ ካላስገረመን፣ ካላረካን፣ ሌላ ተጨማሪ ነገር ይጨመርልን ካልን መዳን አልገባንም።
    📖 1ቆሮ 1:26 ..መጠራታችሁን ተመልከቱ
    - እንደሰው መለኪያ ምርጥ ምርጥ አልተጠራም። እንደሰው ጥበብ፤ በሀብት ይመረጥ ቢባል፣ የሚመረጡ ብዙ ነበሩ ነገር ግን እግዚአብሔር የአለምን ጥበበኞች እንዲያሳፍር የአለምን ሞኝ ነገር፣ ደካማ ነገር፣ ምናምንቴ መረጠ።
    ➲ ጸጋ፦ ከነቆሻሻ ታሪክ መርጦ የንጉሡ የዘር ሐረግ ውስጥ አስገባቸው።
    - ወንጌል የምርጦች አይደለም፤ የዳንነው ጥርት ያልን ስለሆንን አይደለም፤ ጥርት ያለው ውስጥ ስላስገባን እንጂ።
    - የተናቁትን መረጠ፤ ለምን? ስጋ ለባሽ በእግዚአብሔር ፊት እንዳይመካ፣ ምን ይጎድለኛል እንዳይል።
    - በክርስቶስ ውስጥ እንድንጠቃለል ያደረገን፣ ጻድቃን የተባልነው፣ ቤዛነት ያገኘነው በእርሱ፣ ከእርሱ፣ ለእርሱ ነው። የእኛን ማንነት አይቶ ሳይሆን የልጁን ስራ አይቶ እግዚአብሔር አከበረን፣ አጸደቀን።
    - የማቴዎስ ወንጌል ይሔ ነው፤ በትህትና ተመላለሱ፣ በትምክህት አትኑሩ ነው መልዕክቱ።
    - ወንጌል ያልገባው ሰው ትምክህተኛ ነው። በራሳችን ስራ መመካት ክርስቶስን መስደብ፣ መስቀልን ማርከስ ነው። ከክርስቶስ መስቀል ውጭ ሌላ ትምክህት የለም።
    - ያጸደቀን ልጁን ክርስቶስን አይቶ ነው። እንዳስቆጠረ ሰው አንመላለስ። በወንጌል እኛ ያስቆጠርነው ጎል የለም፤ ያስቆጠረልን ኢየሱስ ነው።
    - ወንጌል ሲገባ ያስገርማል፣ ያስደንቃል፣ ትሁት ያደርጋል።
    - የቀለለ ነገር እንደርካሽ እንቆጥራለን፣ እውነት አይመስልም። አቀለልን ማለት ርካሽ ነው ማለት አይደለም።
    - እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ጸዳ ስትሉ ኑ አላለም፥ ከነድካማችሁ ኑ ነው ያለው።
    - ነጻ ቀልድ አይደለም፤ ርካሽ አይደለም፤ መዳን ነጻ ቢሆንም ታላቅ ነው።
    - ማቴ 1፥ የዘላለምን ህይወት በምርጥነታቸው፣ በማንነታቸው፣ በዘር ሐረጋቸው ለሚመጥኑ ምርጦች እንደ ደመወዝ የተሰጠ ሳይሆን ለማይመጥኑ ሀጢአተኞች በጸጋ የተሰጠ ችሮታ ነው።

    • @habatamhabatam8769
      @habatamhabatam8769 Před rokem +3

      ጸጋው ይብዛላችሁ እጅግ ጣፋጭ የተባረኩበት ትምህርት ነው
      ዶክተር ማሙሻ
      ዶክተር አብርሃም
      ሮቤል ሁላችሁንም እንወዳችጝለሁ💚

    • @user-xs4cx2ve3j
      @user-xs4cx2ve3j Před rokem +1

      Wow betam enamesegnalen wagachu be abate zend yekebere new

    • @abenezertefera7927
      @abenezertefera7927 Před rokem

      God bless you Dr. Mamusha! God bless you the Equip media crew! Is it possible to have the message in audio, may be in the telegram channel? Thanks.

    • @equipmedia2577
      @equipmedia2577  Před rokem +3

      @@abenezertefera7927 Sure we will do that

    • @tamirutakele9331
      @tamirutakele9331 Před rokem

      Amen!
      Thank you for this service.

  • @hanafeleke7048
    @hanafeleke7048 Před rokem +8

    ምን አይነት መወደድ, መፈቀር, መፈለግ ነው የሆነልኝ!!!
    ጌታ ኢየሱስ ሆይ ወንጌል አይቅለልብኝ.ለእኔ በነፃ የተሰጠኝ ቢሆንም አንተ ግን ከፍለህበታልና እባክህ እርዳኝ.

  • @mahederbiltibo2749
    @mahederbiltibo2749 Před rokem +4

    ዕፁብ የሆነ መስታወት ፊት ቆሜ እራሴን እያየው የአምላኬን የመድሃኒቴን ፍፁም ፀጋ በብዙ እንባ ደግሜ ደግሜ ምምግበት ልዮ ማዕድ ኡፍፍፍ በፍፁም ልቤ ልገዛልህ ኢየሱስዬ መድሃኒቴ...ትሁቱ አምላኬ

  • @URIMAGAPE
    @URIMAGAPE Před 14 dny

    ፀጋ ይብዛልህ ዶ/ር እኛም ነፍስም አልቀረልን😍

  • @lemlemghebremedhinweldeghi5205

    እንደ ጣዕመ ዜማ ደጋግሜ ብሰማውም ያልጠገብኩት መልዕክት ነው። እግዚአብሄር እኛን ለማዳን የተጓዘውን ሩቅ መንገድ እያስደነቀኝ ፡ የመዳን እውነት እንዴት አብርሆቱ አገኘኝ እያልሁ በመደነቅና በምስጋና ተሞልቻለሁ። ወንድም ማሙሻ ተባረክ ከዚህም በላይ ትጋት ይብዛልህ።

  • @hiwigelaye6509
    @hiwigelaye6509 Před rokem +4

    አሜንንንንንንንንንንንንንንንንንንንንንንንንንን👏👏👏
    ኢየሱስ ላንተ ክብር ሰግደት ይገባሃል 🙇‍♀️🙇‍♀️🙇‍♀️

  • @hanayeknashewa8639
    @hanayeknashewa8639 Před rokem +2

    በዚህ ትምህርት ህይወቴን ያለኝን የክርስትና አካሄድ በጣም አየሁበት ዶ/ር ማሙሻ እግዚአብሄር አብዝቶ ይባርክህ ባንተ የሚፈሰው የትምህርት ፀጋ የእውነት መንፈሳዊ ህይወትን የሚያሳግድ ከቃሉ የሆነ የህይወት ምግብ ነው.
    Be Blessed, Be expand, Equip media

  • @user-db1wm3jj7l
    @user-db1wm3jj7l Před rokem +1

    Amen eeeeeeeeeee

  • @haregmulat1gmail
    @haregmulat1gmail Před rokem +2

    የመረጠን እንዲሁ የወደደን ለዘለአለም ስሙ ይባረክ ህያው ቃሉ ሁልግዜም አዲስ ነው ዶር ማሙሻ ተባረክ

  • @hanaweba1541
    @hanaweba1541 Před rokem +1

    ሁሌም የሚደንቀኝ መመረጤ እየሱስ እኔን ያዩ አይኖችህ የተባረኩ ይሁኑ። ስሜ በህይወት መዝገብ ላይ መፃፉ የዚህ እድል ተካፋይ ስላደረከኝ ስምህ ይባረክ። ዘመኔን ሁሉ እገዛልሀለሁ።ዶር ማሙሻ አንተ ለምድራችን በረከት ነህ ፀጋዉ ይብዛልህ እንወድሀለን።

  • @rodasgetachew9347
    @rodasgetachew9347 Před rokem +4

    አሜን !! አሰደናቂ ህይወት ሰጠን የማንመረጠውን መረጠን ጌታ !!!በዚህ መመረጥና መዳን ካልተደነቅን ካልረካን በምንም ልንረካ ልናርፍ አንችልም!!!!ጌታ ኢየሱስ ይባርክህ የተወደድህ ወንድማችን ዶ/ር ማሙሻ ጸጋም ይብዛልህ🙏❤ሁላችሁን ጌታ ኢየሱስ ይባርካችሁ !!

  • @furnodagne
    @furnodagne Před rokem +1

    ደጋግሜ ብሰማውም የማይጠገብ ነው እግዚአብሔር ይባርክህ ዶክተር አንተ በረከታችን ነሀ።

  • @user-db1wm3jj7l
    @user-db1wm3jj7l Před rokem +1

    WOWWW GOd

  • @felenuna8034
    @felenuna8034 Před rokem +3

    በዘዴና በጥበብ የእግዚአብሔርን ቃል አስተማርከን እግዚአብሔር ይባርክህ

  • @user-lq5ow8vo2x
    @user-lq5ow8vo2x Před rokem +1

    ድንቅ ነው ጌታ እየሱስ ፀጋ ያብዛልህ

  • @user-sb8rp1yp1m
    @user-sb8rp1yp1m Před 9 měsíci

    Amen

  • @tesfaaman5291
    @tesfaaman5291 Před rokem +2

    የመረጠን ይባረክ ሳይገባን በፀጋ ያዳነን ክብር ይሁንለት ለንጉሡ

  • @DulumeRobi
    @DulumeRobi Před 8 měsíci

    በእርሱ፡ፀጋ፡ብቻ።

  • @glorytogod6635
    @glorytogod6635 Před rokem +5

    Amen. All honor be to the lamb that was slain. Blessed be the name of the Lord our God. God bless you all.

  • @Kirubelzebene-xo4sm
    @Kirubelzebene-xo4sm Před 4 měsíci

    ተባረኩ❤❤❤

  • @ashenafigedion6025
    @ashenafigedion6025 Před rokem

    ወንድም ማሙሻ(ዶ/ር) እግዚአብሔር ስለሰጠህ ጸጋ ክብሩን ይውሰድ። አምላካችንና አባታችን ትጋትንና ጸጋን ያብዛልህ!

  • @jesuschrist15111
    @jesuschrist15111 Před rokem +1

    ✞ክብር ለእግዚአብሔር አብ ክብር ለእግዚአብሔር ወልድ ክብር ለእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ይሁን አሜን።✟❤
    “ሁሉም ከእርሱ፣ በእርሱ፣ ለእርሱ ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።”
    - ሮሜ 11፥36 (አዲሱ መ.ት)

  • @frehiwotkelelaw5401
    @frehiwotkelelaw5401 Před rokem +3

    እግዚአብሔር ይባርካቹሁ

    • @johnhappy6854
      @johnhappy6854 Před rokem

      እግዚአብሔር ለዘላለም ይባርካቹሁ

  • @selamawitalemu881
    @selamawitalemu881 Před rokem +6

    What an Amazing Grace!!!!! Glory to JESUS 🙏🙏🙏
    This is my story. God bless you Dr. Mamusha and Equip family!

  • @easypc8806
    @easypc8806 Před 8 měsíci

    ❤❤❤ክብር ለእግዚአብሔር አብ
    ክብር ለእግዚአብሔር ወልድ
    ክብር ለእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንተ አምላክህ ይሁን
    የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ፀጋ ሰላም ያብዛልህ ወንድማችን እናመሰግናለን እንወዳለን ❤❤❤

  • @tamratwada8211
    @tamratwada8211 Před rokem

    በእውነት እግዚአብሔር ሰለማይነገረዉ ምህረቱ በክርስቶስ ኢየሱስ የተባረከ ይሁን ወንድማችን ዶ/ር ማሙሻ እግዚአብሔር ፀጋዉን ያብዛልህ።

  • @mail2hasset
    @mail2hasset Před rokem

    ከአህዛብ ወገን ነበርኩኝ
    ከእሴይ ግንድ ተጣበኩኝ
    እጀግ ከተወደደው
    ከክስራኤል ወገን ሆንኩኝ
    ሳስበው ይገርመኛል በምን ድልድይ እንዳለፍኩኝ
    ምህረቱ አሳለፈኝ ቸርነቱ መንገድ ሆነኝ
    በጎነቱ እኔን እረዳኝ አሃ
    እንደሆነልኝ መጠን ለኔ እንደተደረገልኝ
    ምስጋናዬን አበዛለሁ እየሱስ ይክበርልኝ አሃ
    አይደለምና በብቃቴ የሆነው እስራኤል ቤቴ
    ቸርነትህ አግዞኝ ነው ሆኖኝ በጎነትህ ብቃቴ አሃ
    የማውቀው ይሄንን ነው መዳኔ በምህረትህ ነው (2)

  • @tsehayegetachew4599
    @tsehayegetachew4599 Před rokem +1

    እግዚአብሔር ይባርክህ የቃሉን መገለጥ የሰጠ እግዚአብሔር ይባረክዘር ይባረክ።

  • @senaitgebeyhu5021
    @senaitgebeyhu5021 Před rokem

    እግዚአብሔር አብዠቶ ይባርክህ ረጀም እድሜ ኑርልን

  • @user-zs8yk3qp6c
    @user-zs8yk3qp6c Před rokem +1

    I don't know how can I tell you how much I love hearing words off God from you doc stay blessed and I wish you more grace ❤

  • @mossesg
    @mossesg Před rokem

    አቤት ጌታ ሆይ እውነት ባንተ ፊት አይደለም በሰውም ፊት መቆም የማይገባኝ ሰው ሆኜ ሳለሁ ሳትጸየፍ ያነሳሃኝ የመረጥከኝ ስምህ ይባረክ ጌታ እየሱሴ፡ ዶክተር ማሙሻ ዘመንህ ይባረክ አንተ በረከታችን ነህ ተባረክልን።

  • @tagesechtesema6195
    @tagesechtesema6195 Před rokem +1

    ሃሌሉያ እንሆን ንጉሤ
    ሃሌሉያያያ መዳኔ ያስደንቀኛል
    መመረጠ ያስገርመኛል
    ሃሌሉያ ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን ለመረጠን ሳይገባን ጠርቶ ላዳነን ክብር ይሁንለት
    ፀጋ ይብዛልክ ዶክተር ማሙሻ

  • @mesertkebede4115
    @mesertkebede4115 Před rokem +1

    Amen Amen Amen Geta Eysus hoye temsgm 🙏

  • @sosenanaser8565
    @sosenanaser8565 Před rokem

    ስላንተ እግዚአብሔር ይመስገን እውነትም እግዚአብሔር ቅሪት አለው

  • @wendesenhaile2321
    @wendesenhaile2321 Před rokem +4

    Glory to our God for his amazing grace and forgiveness. The teaching is Excellent, pure & clear. Thank you Dr. Mamusha & all co-workers.

  • @tensumamush9918
    @tensumamush9918 Před rokem

    Amennn.Amenn.Amennn.😭😭😭😭😭 aba ameseginhalehu enen.koshashawan meretikegn lijih aderekegn aba ameseginhalehu meretikegn.kefff bel Dr mamusha tebarek

  • @merhawitgebremeskel
    @merhawitgebremeskel Před rokem

    Geta eyesus yebarikh wendime Mamusha.

  • @fevenygetaliji
    @fevenygetaliji Před rokem

    Ameeeeeen Ameeeeen Ameeeeeen Ameeeeeen yigebahale 🙌🙌🙌🙌🙌🙌Eyesus kiber lezelam Yhununleti🙌🙌🙌🙌🙌🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏😍😍😍😍😍😍

  • @abenezersimon4318
    @abenezersimon4318 Před rokem +1

    አሜን ሃሌሉያ🙏🙏🙏 ተባረክ ዶክ ከጅማሬም በጣም እየተጠቀምኩ ነው።😭😭😭😭👏👏🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌

  • @marthamule9997
    @marthamule9997 Před rokem

    እግዛብሔረ ይመስገን ስለተሰጠኝ ስለበዛልኝ ፀጋ እግዛብሔረ ዘመንን ይባረክ

  • @user-kv7jd3dj5f
    @user-kv7jd3dj5f Před 6 měsíci

    kibr lewededegn geta yihun

  • @tinsucreativeidea901
    @tinsucreativeidea901 Před rokem +1

    😭😭😭😭 እንዴት ውስጤ ሀሴት አደረገ❤❤❤❤❤ ጌታ ይመስገን። ማሙሻ ፀጋው ይብዛልህ❤

  • @desta5885
    @desta5885 Před rokem

    አቤት መታደል!! እግዚአብሔር ይባረክ።ተናረክ ዶር። ይብዛልህ ይጨመርልህ።

  • @zinashmamo9676
    @zinashmamo9676 Před rokem

    አሜንንንንንንን እንሆኝ ንጉስሽ አሜንንንን. ክብር ለእግዚአብሔር ይሁንንንንንንንንን አሜንንንንንንን እልልልልልልልልልል

  • @fasikamarkos7465
    @fasikamarkos7465 Před 9 měsíci

    This is my story...😭😭🙌

  • @HanaHailu016
    @HanaHailu016 Před rokem

    ጌታ ሆይ አመሰግንሀለሁ.....ጸጋ ይብዛልህ

  • @bereketfeleke8973
    @bereketfeleke8973 Před rokem +1

    አሜን "በጸጋ" ከንጉስ ዘር ሆኛለሁ።

  • @bereketgebregziabher444
    @bereketgebregziabher444 Před rokem +2

    አቦ ብርክ በሉ የ EQUIP program አቅራቢዎች እና አገልጋዮች ሁሉ 100ግዜ ብሰማው አዲስ ነው በርቱልን በፀሎት አለን ከጎናቹ ነን

  • @hanytamitretamire3771
    @hanytamitretamire3771 Před měsícem

    ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤

  • @selamugenetu9253
    @selamugenetu9253 Před rokem

    ፀጋ ፀጋ ፀጋ ፀጋ

  • @mesfingose759
    @mesfingose759 Před rokem

    ተባረክ ወንድሜ። ባንተ ትምህርቶች ብዙ ተጠቅሜያለሁ ።

  • @fevenygetaliji
    @fevenygetaliji Před rokem

    Mamushaye tbarekilgntsaga ybizalhi❤❤❤❤

  • @tsedeywubneh7715
    @tsedeywubneh7715 Před rokem

    Wow! Medane sigermegn liju aderegegn

  • @nazrawi1710
    @nazrawi1710 Před rokem

    🙌🙌

  • @eyobtessema7748
    @eyobtessema7748 Před rokem

    One of the best preach ክብሩን እግዚአብሔር ይዉሰድ!

  • @tedlacherkosteddy8662

    ❤❤❤

  • @Ruth137-T
    @Ruth137-T Před rokem

    Kbr lezelalem le Medanitachn Gieta Yesus Krstos❤️❤️❤️

  • @GelfetoGebre
    @GelfetoGebre Před rokem

    ewnetem yehe yene tarik nw. egziabher yebarek

  • @adanemekonnen737
    @adanemekonnen737 Před rokem +1

    Kale Hiwot Yasemalen as always Dr. Mamusha 🙏🙌🇪🇹

  • @marthakifle5060
    @marthakifle5060 Před rokem

    ዶክተር ማሙሻ እግዚአብሔር አሁንም አብዝቶ ይባርክህ።

  • @abebachekol3611
    @abebachekol3611 Před rokem +1

    አሜን ጌታዬ ተባረክ ፓስተርዬ

  • @sissis8459
    @sissis8459 Před rokem

    ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤

  • @Rehobote
    @Rehobote Před rokem

    ወልካም ዶ/ር ማሜዬ❤❤❤❤❤❤

  • @Scupiyt_
    @Scupiyt_ Před rokem

    ጌታ አብዝቶ ይባርክህ ማሙሻ

  • @ilubko8609
    @ilubko8609 Před rokem +1

    Wow to be honest with you I always skip that part when I read Mathew because it was boring but know I realized why it is very important ! Thank you Dr. Mamusha

  • @samrawitlemma5915
    @samrawitlemma5915 Před rokem

    ፀጋ አይጉደልባችሁ🙏🙏🙏

  • @awotashtefera9728
    @awotashtefera9728 Před rokem

    Wow... yigermal. Min yibalal ke amen beker. Amen ...🙏 🙏 🙏 ...

  • @fanikumamarkos8176
    @fanikumamarkos8176 Před rokem

    እግዚአብሔር ይባርክህ ወንድም ማሙሻ በጣም ነው የተጠቀምኩት

  • @user-sb8rp1yp1m
    @user-sb8rp1yp1m Před 9 měsíci

  • @sentayehudebele2332
    @sentayehudebele2332 Před rokem

    👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👌👌👌👌👌👌👌👌👌👌👌👏👏👌👌❤️አሜን አሜን አሜን 🙏🙏🙏

  • @hattahatta1921
    @hattahatta1921 Před rokem

    አሜን አሜን ዋውውውውውውውውው እግዚአብሔር ይባርካችሁ

  • @zakariasasefa4702
    @zakariasasefa4702 Před rokem +1

    ድንቅ ነው ተባረክ❤❤❤🙏🙏

  • @saradalma9089
    @saradalma9089 Před rokem

    God bless you man of God

  • @elinaselam6915
    @elinaselam6915 Před rokem

    እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክህ ❤❤❤

  • @hamelmalargu6894
    @hamelmalargu6894 Před rokem +1

    ዘመናችሁን ጌታ ይባርክ

  • @Aki-rl2wz
    @Aki-rl2wz Před rokem +1

    Amen Amen praise God. Bless you more 🙏🙏🙏💙❤️

  • @adisemosisa2262
    @adisemosisa2262 Před rokem

    God bless you Dr Mamusha for this amazing word and your devotional teaching always 💕 💕

  • @peterich1982
    @peterich1982 Před rokem

    እግዚአብሔር ይባርክህ

  • @negashgebre6433
    @negashgebre6433 Před rokem

    Glory and amazement be to Almighty God. God bless you Dr. Mamusha

  • @bettybogale6720
    @bettybogale6720 Před rokem +1

    May God bless you so Munch .

  • @bogaleagga9026
    @bogaleagga9026 Před rokem

    አሜን🙏🏾እልልልልልል ... እኔንም አስገባኝ 😭😭😭
    this’s my history

  • @frehiwottsige6774
    @frehiwottsige6774 Před rokem

    Tebarek

  • @tsigeredaendale6434
    @tsigeredaendale6434 Před rokem

    I thank God about you dear Dr. Mamusha!
    Be blessed more and more!

  • @azmeraderbew2312
    @azmeraderbew2312 Před rokem

    Tebareku

  • @shalomdr7shalomdr757
    @shalomdr7shalomdr757 Před rokem

    Amen
    Hallelujah!

  • @ejigayehuretebo6811
    @ejigayehuretebo6811 Před rokem

    This is my story this is my song

  • @abenezerkebede9429
    @abenezerkebede9429 Před rokem

    Stay blessed dear brother Mamusha!

  • @mekonnenseyifu3947
    @mekonnenseyifu3947 Před rokem

    This my story. Amazing Grace!!

  • @danielgemechu
    @danielgemechu Před rokem

    ክቡር የሆነው ፀጋው ይመስገን!

  • @BirtukanKebededemise
    @BirtukanKebededemise Před rokem

    🥰😍🤩😘😭

  • @yonitadady9717
    @yonitadady9717 Před rokem

    geta yikber

  • @masiiyesuus747
    @masiiyesuus747 Před rokem

    Amezing

  • @fifififi1119
    @fifififi1119 Před rokem

    What a wonderful grace! To be very honest i used to take this chapter as boring part but now wowowowowoowowwoo. My dear brother Mamusha thank you and God bless you many more.

  • @eliaszeleke4634
    @eliaszeleke4634 Před rokem

    wey gud endene yalewema kegeba, lij kehone, werash kehone i dont think any body will remain unchanged by the gospel of our Christ

  • @tesfamariamgebrehiwot8160

    ቡሩክ ሁን ወንድሜ

  • @metadesermiaslemedo7848

    🥰🥰🙌

  • @habatamhabatam8769
    @habatamhabatam8769 Před rokem +1

    ባለፈው ስምቸ ዳግም እስኪለቀቅ በጉጉት የጠበቅኩት ትምህርት ጸጋው ይብዛላችሁ።

  • @habtid
    @habtid Před rokem

    ምን ዓይነት መልዕክት ነው?! ይሄ መረዳት/መልዕክት ከላይ ነው። ጌታ ኢየሱስ ይባርክህ ጸጋው የሞላብህ ዶ/ር ማሙሻ።

  • @tsionzewdu7509
    @tsionzewdu7509 Před rokem

    🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰

  • @desta5885
    @desta5885 Před rokem

    እልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልል