እንዴት እንጸልይ?

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 27. 11. 2023
  • መጽሐፍ ቅዱስ ይልቁንም አዲስ ኪዳን ጸሎትን በተመለከተ ግልጽና የማያሻማ ንድፍ አስቀምጦልናል። ጸሎት በመንፈስ ቅዱስ ኃይል፣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ወደ አብ እንጸልያለን። ይህ እውነት ግራጫ በሌለው መንገድ ጥቁርና ነጭ ሆኖ ተቀምጧል። በመንፈስ ቅዱስ ሃይል መጸለያችን የመንፈስ ቅዱስን መለኮትነት አጉልቶ ያሳያል እንጂ እያሳንሰውም። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም መጸለያችን የኢየሱስን አምላክነት ያጎላል እንጂ አያሳንሰውም። ወደ አብ በመጸለያችን አብን ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ በተለየ መንገድ መለኮት አያደርገውም። በቅድስት ሥላሴ አብም፣ ኢየሱስ ክርስቶስም መንፈስ ቅዱስም አንዱን መለኮት የሚካፈሉ ሦስት አካላት ናቸው። የአብ የሆነ ሁሉ የወልድ እና የመንፈስ ቅዱስ ነው። የወልድ የሆነ ሁሉ የአብና የመንፈስ ቅዱስ ነው። የመንፈስ ቅዱስ የሆነ ሁሉ የአብና የወልድ ነው።
    እዚህ ጋ መጠየቅና መመለስ ያለበት አንድ ጉዳይ አለ። ምንም እንኳ በአዲስ ኪዳን በግልጽ የተቀመጠ ሥርዓት ሆኖ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ወደ አብ ብንጸልይም። ወደ ወልድ (ኢየሱስ ክርስቶስ) ወይም ወደ መንፈስ ቅዱስ አንጸልይም ማለት አይደለም። ሁለቱም አካላት ሁሉን የሚያውቁ፣ ሁሉን የሚችሉና በሁሉ ሥፍራ የሚገኙ ናቸውና። ስለዚህ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር እንነጋገራለን። ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እንነጋገራለን። ምንም እንኳ ወደ መንፈስ ቅዱስ እንደምንጸልይ በቀጥታ የሚነግሩን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ባይኖሩም ለዘለዓለም ከእኛ ጋር ሊኖር የመጣ፣ በእኛም ዘንድ የሚኖሮ ጴራቅሊጦስ (ጠበቃ፣ አጽናኝ) ነውና ማንኛውም በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ አማኝ ሳያነጋግረው ሊውል ሊያድር የሚችልበት ሁኔታ አይኖርም።

Komentáře • 45

  • @kumeinkosagalata8195
    @kumeinkosagalata8195 Před 7 měsíci +2

    Ameen tebrk wendm Yared tsga ybzalh❤❤❤🙏🏻🙏🏻🙏🏻🙏🏻

  • @Jesus_is_love7777
    @Jesus_is_love7777 Před 7 měsíci +6

    ያሬዳ እንኳን ደህና መጣህልን ስላየሁህ ደስ ብሎኛል አልጠግብህምኮ ምክንያቱም ጌታዬን ባንተ ስለማየሁ እባክህ አትጥፋብን እሺ የዮሐንስን ወንጌል አስተምረን በጣም እየጠበቅሁ ነው ጌታ ኢየሱስ በነገር ሁሉ ከአንተ ጋር ይሁን🥰🥰🥰🥰🥰🥰❤

  • @Sam-xx3tu
    @Sam-xx3tu Před 7 měsíci +1

    እንኳን ደህና መጣህ ከብዙ ጊዜ ጀምሮ ትምህርትህን በተለያየ መልክ ተጠቅሚለሁ የባረክህ ጌታ ይባረክ

  • @tigestermayse8641
    @tigestermayse8641 Před 7 měsíci +3

    Amen Amen Amen Egzaibher Selamike Yebizaha shalom shalom shalom ✅ 🙌 👏🏻

  • @ELSHADDAI4443
    @ELSHADDAI4443 Před 7 měsíci

    ወንጌላዊ ያሬድ ፡ ወሳኝ ትምህርት ነው፥ እግዚአብሔር ይባርክህ።

  • @user-ki1sf9hn9z
    @user-ki1sf9hn9z Před 7 měsíci +3

    እስጢፋኖስ ሲወገር ጌታ ሆይ የምያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው ብሎ ሲፅልይ ስማይ ተከፍቶ ጌታን በአብ ቀኝ ተቀምጦ አየው

  • @tigestermayse8641
    @tigestermayse8641 Před 7 měsíci +2

    Amen Amen Amen ✅ 🙌 👏🏻 Tabareke

  • @mekedesmezmur4057
    @mekedesmezmur4057 Před 7 měsíci

    እንኳን ደህና መጣህ ወንጌላዊው ያሬድ እኛን እንደባርክህ ጌታም አንተንና ቤተስብህን ይባርክ በጽሎትና በምስጋና በልጅ በእየሱስ ስም በመንፈስ ቅዱስ ምሪት ለሁላችንም ወደ አብ መቅርብ ሆኖልናል አሜን አሜን አሜን

  • @lidiyarashad3097
    @lidiyarashad3097 Před 7 měsíci +1

    Amen amen 🙏🙏 God bless you 🎉❤❤❤

  • @Ashenafi.Regasa
    @Ashenafi.Regasa Před 7 měsíci +3

    Thanks for the very precise and clear message.

  • @user-te5gb5vm8o
    @user-te5gb5vm8o Před 7 měsíci

    አመሰግናለሁ ያሬዶ በተገለጠልህ በረከት እኔንና ቤተሰቤን እያካፈልከን በብዙም እየጠቀምከን ስለሆነ አሁንም አመሠግንሀለሁ

  • @tilahuntadeese4091
    @tilahuntadeese4091 Před 7 měsíci +1

    love &respect man of god❤

  • @tigi886
    @tigi886 Před 7 měsíci

    በሚገባን መልኩ ነዉ ገልጠህ ያሳየኸን ተባረክ🙏

  • @HalemaS-ww3kk
    @HalemaS-ww3kk Před 7 měsíci +1

    ያሬዶ እንኩዋን ደህና መጣህልን ❤

  • @selomephoto2757
    @selomephoto2757 Před 7 měsíci

    Amen ❤!

  • @Eagle1503
    @Eagle1503 Před 7 měsíci

    Amen 🙏

  • @maranatha1308
    @maranatha1308 Před 7 měsíci

    ❤❤❤❤
    ❤❤❤
    ❤❤

  • @user-jf9em3nw1q
    @user-jf9em3nw1q Před 7 měsíci +1

    ይህ ማብራሪያ በኢንተርቪው ላይ ተሰጥቶ ቢሆን በብዙዎች ዘንድ ጥያቄ አይፈጠረም ነበር
    በእርሶ ትምህርቶች በጣም ተጠቅሜአለሁ ፀጋ ይብዛሎት🙏

    • @EvangelistYaredTilahun
      @EvangelistYaredTilahun  Před 7 měsíci

      ቃለ መጠይቅ በርዕስ ትምህርት የሚሰጥበት መድረክ አይደለም። በአንድ ጥያቄ የመጽሐፍ ቅዱስን ምክር ሁሉ መመለስ አይቻልም። የተናገርኩት ስለ ጸሎት ፓተር ነው። አሁንም ቢሆን መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረን የጸሎት ሥርዓት በመንፈስ ቅዱስ ሃይል፣ በኢየሱስ ስም፣ ወደ አብ እንድንጸልይ ነው። ጌታ ኢየሱስ አንድም ቦታ ወደ እኔ ጸልዩ ብሎ አላስተማረም። ይህንን ያላደረገው ፍጹም አምላክ ስላልሆነ ሳይሆን ሥርዓት እያስተማረን ነው። ያ ማለት ግን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስም ሆነ ወደ መንፈስ ቅዱስ አንጸልይም ማለት አይደለም።

    • @user-jf9em3nw1q
      @user-jf9em3nw1q Před 7 měsíci

      ረጅም እድሜና ጤና ይስጥልኝ ወንጌላዊ ያሬድ
      ያነሱት ሀሳብ አሳማኝ ነው።
      ትምህርቶትን ደጋግሜ ነው የምሰማው ተባረኩልኝ !

  • @abenezertesfaye1430
    @abenezertesfaye1430 Před 7 měsíci

    Amen! Much grace

  • @danielah4508
    @danielah4508 Před 7 měsíci

    ሰላም ወንጌላዊ ያሬድ ሰፋ ብታደርገው መልካም ነው ብዬ አስባለው ምክንያቱም ብዙው ሰው አሁንም ያልከውን ጭብጥ የያዘ አልመሰለኝም ተመልካች እየጨመረም ሲሄድ ተመሳሳይ እየታ እንደሚኖር እገምታለ::ተመልካቾችም በመጨረሻ ላይ ማሰሪያ ያበጀለትን አስተውላችሁ ስሙት እላለው;;ተባረኩ!

  • @user-cf8xn3td6o
    @user-cf8xn3td6o Před 7 měsíci

    ተባረክ

  • @zewditugesesse385
    @zewditugesesse385 Před 7 měsíci

    እግዚአብሔር ፡ ሰምላክ ፡ ይባርክህ።

  • @alemnesheth2165
    @alemnesheth2165 Před 7 měsíci

    Wow tebareki❤❤❤

  • @Anumma572
    @Anumma572 Před 7 měsíci

    Egziabeher Ymesgn Tbarek

  • @alemtshaygetachew3493
    @alemtshaygetachew3493 Před 7 měsíci

    ሰላምህ ይብዛ እግዚአብሔር ይባርክህ

  • @yihuneteshome9262
    @yihuneteshome9262 Před 7 měsíci

    God bless you brother!

  • @truthseeker4873
    @truthseeker4873 Před 7 měsíci

    Thank you evangelist! I hope you'll continue teaching us about the answers of prayer!

  • @jesusislord4747
    @jesusislord4747 Před 7 měsíci

    Morning bread❤

  • @selomephoto2757
    @selomephoto2757 Před 7 měsíci

    God bless you my brother Yared!

  • @Sunem7
    @Sunem7 Před 7 měsíci

    Welcome back brother Yared we miss you so much. You are so blessed 🙏🥰

  • @abenezerkebede9429
    @abenezerkebede9429 Před 7 měsíci

    Thank you dear brother Yaredo! God has thought and benefited us abundantly through you since long time ago! Stay blessed!

  • @tedegachufebo4042
    @tedegachufebo4042 Před 7 měsíci +1

    የዮሐንስ ወንጌል ትምህርት ለምን ተቋረጠ ?ወይም በሌላ ፔጅ ከሆኔ ልንኩን ለኩልን

  • @user-eu2yb3qk8y
    @user-eu2yb3qk8y Před 7 měsíci

    ወንድም ያሬድ ጌታ ይባርክህ! ስንፀልይ በኢየሱስ ስም ባንል ፀሎታችን ይሰማል ወይ? ምክንያቱም በቸርቻችን ብንልም ባንልም ምንም አይደለም እየተባልን ስለሆነ ጥያቄ ፈጥሮብናልና::

    • @bamyayire9673
      @bamyayire9673 Před 7 měsíci

      በኢየሱስ ስም የሚለው ንግግር ጸሎት እንዲሰማ የሚያደርግ መጨረሻ ላይ የሚመጣ ማህተም አይደለም። ብንለው የተሻለ ነው በማስተዋል እንበለው እንጂ። መጨረሻ ላይ እሱን ፊርማ ማስቀመጣችን ሳይሆን ዋናው ነገር እግዚአብሔር አብን የቀረብነው ብለን የምናስበው በማን ሥራ ነው? ቅዱሱ አምላክ ፊት የምንቀርበው እና የማንጠፋው ለምንድነው? ኢየሱስ ጽድቃችን ስለሆነ ነው። እግዚአብሔርን አባት ብለን የምንጠራው ልጆቹ የተደረግነው በማን አማካኝነት ነው? በልጁ በክርስቶስ አይደለምን? እንግዲህ በኢየሱስ ስም መጸለይ ማለት አብ ፊት የመቅረብ ድፍረታችን ጽድቃችን ክርስቶስ መሆኑን አውቀን መልሱም ለክርስቶስ ክብር የሚሆን ከሆነ ብቻ እንዲፈጸም አምነን የምንቀርብበት የልብ አቋም ነው እንጂ ጸሎታችንን ማሳረጊያ ፊርማ አይደለም። መተማመኛችን እርሱ መሆኑ ነው የተፈለገው። ተባረክ።

  • @Hanan6073
    @Hanan6073 Před 7 měsíci

    Why u change ur minde? Wede geta antselyn bleh nebef eko? Wey begilts sehtet neber atlim.

  • @AmanuAbdu
    @AmanuAbdu Před 7 měsíci +1

    ለምን ዝቅ ማለት ያቅተናል ፣እንደዐለም ሰዎች ለምን ብልጣብልጥ እንሆናለን፣ የመጣኸው ስለፀሎት ለማስተማር ሳይሆን እየተወራብህ ያለውን ነገር ለማጥራት ነው ታዲያ የሚሻለው ወንድሞቼ እህቶቼ ባለፈው ቃለመጠይቅ ላይ እንዲህ እንዲያ ብዬ ነበር ልል የፈለኩት እንዲህ ነው ተብሎ ለምን በጨዋነት አይቀርብም ለእኔ የሚያሳየኝ ዝቅ ማለት አለመፈለግን ነው

    • @yilikalmetenu3316
      @yilikalmetenu3316 Před 7 měsíci

      የተሳሳተውን ነገር ለማጥራት መምጣቱ በራሱ ከጠንቃቃ የቃሉ መምህር የሚጠበቅ ትልቅ quality አይደል እንዴ! ብዙዎች ይሄንን ለማረግ ያልታደሉ የሉም? ግብዝ ቢሆንማ ለሌላው ግድ ባይለው በተነሳው ጉዳይ ዝምታን በመረጠ ነበር። ወንድሜ ደሞ ልብን እና ኩላሊትን ለሚመረምር አምላክ ሌላውን ብንተው አይሻልምን? ለምን ለፍርድ በመቸኮል በራሳችን ላይ ሃጢአት እንስባለን!

    • @ruthyohannes4007
      @ruthyohannes4007 Před 7 měsíci

      ደግ አደረገ

    • @AmanuAbdu
      @AmanuAbdu Před 7 měsíci

      @@yilikalmetenu3316 ፍርድን እዚህ ምን አመጣው ፣ ሃሳብን መሰንዘር መፍረድ ማለት አይመስለኝም ደግሞ ፍርድም ለሰው አልተሰጠም፣ እኔ ልል የፈለኩት በዝቅታ ብዙ በረከት እና ከፍታ ስላለው እንደ አስተማሪ ለምን ቢሄቭ አላደረገም ነው ያልኩት ይህ ደግሞ የእኔ የግሌ አመለካከት ነው፣ ነፃነቴን ፍርድ ሃጢያት ምናምን በማለት አታድፈራራ ለነገሩ የሚፈራ የለም ፍርሃትም አልተሰጠኝ

  • @brukkebede6812
    @brukkebede6812 Před 7 měsíci +1

    Dear Evangelist Yared Tilahun, please you need to repent about your statement on the topic whom should Christians pray 🤲…. On your recent interview at Tigist E CZcams channel. So your statement is not biblical and I was shocked when you said that please repent…

    • @BernabasMesfin-zd9iy
      @BernabasMesfin-zd9iy Před 7 měsíci

      ጸሎት ወደ እግዚአብሔር አብ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል መደረግ እንዳለበት!

    • @EvangelistYaredTilahun
      @EvangelistYaredTilahun  Před 7 měsíci +1

      ቃለ መጠይቅ በርዕስ ትምህርት የሚሰጥበት መድረክ አይደለም። በአንድ ጥያቄ የመጽሐፍ ቅዱስን ምክር ሁሉ መመለስ አይቻልም። የተናገርኩት ስለ ጸሎት ፓተር ነው። አሁንም ቢሆን መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረን የጸሎት ሥርዓት በመንፈስ ቅዱስ ሃይል፣ በኢየሱስ ስም፣ ወደ አብ እንድንጸልይ ነው። ጌታ ኢየሱስ አንድም ቦታ ወደ እኔ ጸልዩ ብሎ አላስተማረም። ይህንን ያላደረገው ፍጹም አምላክ ስላልሆነ ሳይሆን ሥርዓት እያስተማረን ነው። ያ ማለት ግን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስም ሆነ ወደ መንፈስ ቅዱስ አንጸልይም ማለት አይደለም።