ርዕስ ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 1. 12. 2022
  • #ሁላችንም_ልንማርበት_የሚገባ_ወቅታዊ_ልዩ_ትምህርት_Subscribe_Share_like_በማድረግ_አገልግሎቱን_ይደግፉ።
    እርሱ እግዚአብሔር ነው፡፡ እኔ ደግሞ ሳውቀው በፍቅሩ በኩል ነው፡፡ ስለእርሱ ከፍቅሩ ውጪ ሌላ እውቀት እንዲኖረኝ አልሻም፡፡ እንዳፈቀርሁት በተሰማኝ ቁጥር ገና ምኑንም እንዳልጀምርኩት ገብቶኝ እገኛለሁ፡፡ ላላፈቅረው ስሞክርም፤ ድክመቶቼን ሁሉ ያውቃቸዋልና መልሶ በክንዱ ውስጥ ያኖረኛል፤ ሳይጫነኝ ይከብደኛል፤ ሳይናገር ያወራኛል፤ ራቅሁት ብዬ አቅጣጫ ስቀይር ከፊት ቀድሞ ወደራሱ ይመራኛል፡፡ አንዳንድ አባቶች "ኃይለኛው!" እያሉ ሲጠሩት እሰማለሁ፡፡ እውነትም እርሱ ኃያል ነው፡፡
    ባሕሪይው ንጹሕና ቅዱስ ነው፡፡ በእርሱነቱ ቤት ውስጥ እውነት ብቻ አለ፡፡ ከሁሉ የሚገርመኝ ግን ገርነቱ ነው፡፡ እያየ ዝም፣ እየሰማ ዝም፣ እያወቀ ዝም፡፡ ይህን በጥሞና ባሰብሁ ጊዜያት ላይ ነፍሴን እስኪቀዘቅዘኝ ድረስ መልካምነቱ ያንሰፈስፈኛል፡፡ ያደረኩበትን ሁሉ አስታውስና የምቆምበትን የመሬት ቦታ ሳይቀር እጠላለሁ፡፡ "እንደምን ያለው ዓመፀኛ ልጅ አለህ?" እለዋለሁ፡፡ እርሱ ግን እቅፉን ከዙሪያዬ በቀንም በሌትም አያነሣም፤ ይወደኛል!
    ምን ባደርግለት በቃ እል ይሁን? ምን ብሆንለት ደስ ይለው ይሁን? ምን ብሠራለት እረካ ይሁን? .. በብዙዎች ዘንድ ስለ ሃይማኖት ሲነሣ የመድረሻውን ነጥብ ከገነት አሊያ ከሲዖል አንጻር ያስቡታል፡፡ ትክክል የሆኑበት የራሳቸው እይታ አለ፡፡ ለእኔ ግን ይህ አያሰጨንቀኝም፡፡ ይሄን ዓለም ተሻግሬ ስለምደርስበት ቦታ ማሰብ አያሳስበኝም፡፡ ይልቅ እስከፈቀደልኝ የምድር ቀኔ ስሙን ማውሳት እፈልጋለሁ፤ በዮርዳኖስ አንቀጽ "የምወደው ልጄ" የሚል ድምፁን ማድመጥ እመርጣለሁ፤ እመቤቲቱን ካየሁበት ከመስቀሉ ግርጌ መቆምን እፈቅዳለሁ፤ እንደ ጴጥሮስ "ትወደኛለህን?" እያለ ሦስቴ እንዲጠይቀኝ አልማለሁ፡፡
    ሙሴ ከፍርድ ሸሸ ግን እግዚአብሔር ተጠቀመበት ዮናስ ከእግዚእብሔር ፊት ሸሸ እግዚአብሔር ግን ተጠቀመበት ። ሳምሶን የማትገባ ሴት ዘንድ ገባ
    ያዕቆብ በክቡ ውስጥ ሮጠ ፤ ሳራ ተስፋ ቆረጠች ፤ ሎጥ ከተሳሳተ ህዝብ ጋር አብሮ ተጓዘ አምላክ ግን ሁሉንም ተጠቅሞባቸዋል

Komentáře • 30

  • @user-zh8vs1py5p
    @user-zh8vs1py5p Před rokem +4

    ቅዱስ አባታችን ረጅም እድሜ ከሙሉ ጤና ጋር ይስጦት የድንግል ማርያም ልጅ የሚሳነው የሌለው እስከ አለም መጨረሻ ድረስ ያቆዮትና ጨርቆትን እየነካ ትውልዱ ሁሉ ይዳን አባዬ እንወዶታለን በረከቶት ይደርብኝ

  • @tesfayeayalewg3290
    @tesfayeayalewg3290 Před rokem +2

    አባታችን የተባረከ ጉዞ ሆኖ በሠላም ተመልሰው የጠጋዎ በረከትን ለማግኘት ያብቃን አሜን!!!!!!!

  • @mariyamzxcv7982
    @mariyamzxcv7982 Před rokem +2

    እግዚአብሄር ይክበር ይመስገን አባታችን ቃለሄወትያሰማልን ጸጋዉን ተጤናጋር ተድሜጋር ይስጥልን የሠማነዉን በልቦናችን ያሣድርብን አሜን አሜንአሜን

  • @user-lb4nc8mc4z
    @user-lb4nc8mc4z Před rokem +6

    ውድ አባታችን ውድድድድ…. ነው የማረግዎ ረጅም እድሜ ይስጥዎ እግዝሐብሔር አሜን አሜን አሜን

  • @Ewnetmedia2303
    @Ewnetmedia2303 Před rokem +2

    አባታችን እድሜና ጤና ይስጡት ኑሩልን🙏🙏🙏

  • @FasikaAragaw
    @FasikaAragaw Před rokem +6

    ውድ አባታችን ቃለሒወት ያሰማልን አንዳንደ ሰወች ሲቃወሙ ሲከሱ ሲሳደቡ የ 85 አመት አባት አለኝ ገጠር ከሱጋ ወስጀ ልጡራቸው እንደ ብየ አሰብኩ መልሸ ደሞ አየ እኔ ሞኝነቴ እኛን የሚጦሩ አባት እንደት እንድህ አሰብኩ ብየ በራሴ ሞኝነት በራሴ ሳኩ
    እግዚአብሔር እድሜ ይስጥዎ ገና ሳይዎ እምባ ይቀድመኛል የሒወት መምህሬ አባቴ

  • @user-fg5nx4tj8d
    @user-fg5nx4tj8d Před rokem +4

    የኛ ዉድ አባት እረጅም እድሜ ከጤና ጋር ያድልልን

  • @user-hp7px1rs8d
    @user-hp7px1rs8d Před rokem +2

    አሜን አሜን ቃለህወት ያሰማልን

  • @yohannesyenealem3447
    @yohannesyenealem3447 Před rokem +3

    እግዚአብሔር እድሜና ጤና ይስጥልን አባታችን 😇😇😇

  • @reethareetha2319
    @reethareetha2319 Před rokem +2

    እድሜ. ከጤናጋ. ይስጦት. ፀጋውን. ያብዛሎት. የአባት.

  • @hiwet7879
    @hiwet7879 Před rokem +1

    አባታችን ፀጋውን ያብዛሎት ሺ አመት ኑሩልኝ

  • @MrFreshman-ei8hc
    @MrFreshman-ei8hc Před rokem +2

    አባታችን በረከቶ ይደርብን።

  • @danielnegash1796
    @danielnegash1796 Před rokem +2

    አባታችን አሁን ከተሠጥዎት ፀጋ በላይ እድሜ ማቱሣላን ፣ሀብተ ዳዊትን፣ያድልዎት ።

  • @theteacher19
    @theteacher19 Před rokem +2

    እግዚአብሔር እረዠም እድሜ ይስጥልኝ

  • @mariammgtube2112
    @mariammgtube2112 Před rokem +2

    አባቴ መልዓከ መንክራት መምህር ግርማ ረጅጅጅምምም ...እድሜን ከጤና ጋር እመኝሎታለሁ ።

  • @hiwet7879
    @hiwet7879 Před rokem +1

    የኔ ብርቱ አባታ እረጅም እድሜን ከጤና ያድልልኝ ❤❤❤❤❤❤🙏🙏🙏🙏🙏❤❤❤❤❤❤❤አምላክ ይጠብቅልን

  • @sewentmeazameaza3076
    @sewentmeazameaza3076 Před rokem +2

    የእኛ መልካም አባት

  • @taddeselema1646
    @taddeselema1646 Před rokem +3

    ቅዱስ አባታችን መልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ እንኳን በደህና ወደ አዲሱ የህይወት መመገቢያ ቻናል በደህና መጡልን! "ቃለ ህይወት ያሰማልን"የየእለት ስግደትን፣እለታዊ አምልኮን፣የበረከት ስራ መስራት፣ሁልጊዜም ንቁ ሆነን በአምልኮት እንድንኖር ሌላም...ሌላም ያስተማሩን ቅዱስ አባታችን እኔም ቤተሰቤም በእርሶ በቅዱስ አባታችን ዘመን በመፈጠራችን ቅዱስ እግዚአብሔር እናመስግነዋለን።የትህትና መምህር፣የበረከት ስራ መምህር...... እኔም ቤተሰቤም በእርሶ በቅዱስ አባታችን ትምህርት ዲያቢሎስን ረግጠን ከጫማችን ስር አድርገን ቀብረነዋል።"ንቁ"ብለው ባስተማሩን መሰረት ሁሌም ነቅተን የቅዱስ እግዚአብሔርን የጦር
    እቃዎችን ታጥቀን ነቅተን እንጠባበቃለን።ኑሩልን።
    ቅዱስ እግዚአብሔር እረጅም እድሜን ከጤና ጋር
    አብዝቶ ይስጦት!!! ቅዱስ አባታችን በፀሎት አስቡን
    ልጆቾት:- ታደሰ፣ፍቅርተ እና ብርቱኳን ነን።
    ከሲያትል,ዋሽንግተን

  • @worku3723
    @worku3723 Před rokem +3

    አባይዬ እግዚአብሄር ረጅም እድሜ ይሥጦት ለህዝቦት አደራዎትን በሚገባ ነው የተወጡት አባትነቶን በተግባር ነው ያሳዩት

  • @merongetachew1383
    @merongetachew1383 Před rokem +1

    Abatachin kale hiwot yasemalin EGZIABIHER yitbikilin abate

  • @hayfaabdullah4851
    @hayfaabdullah4851 Před rokem +1

    የኛ ብርቱ አባት💚💛❤

  • @hiwotw5404
    @hiwotw5404 Před rokem +1

    Our beloved Memher

  • @reethareetha2319
    @reethareetha2319 Před rokem +2

    ክርስትናዬን. ያሳወቀኝ. የርሶ. ትምርት. ነው. አውንም. ፀጋውን. ያብዛሎት

  • @workueda3560
    @workueda3560 Před rokem +1

    ወይኔ አባ ይፍቱኝ ይባርኩኝ

  • @jerrymegersa1332
    @jerrymegersa1332 Před rokem +2

    Kale hiwote yasemalen abatachen

  • @yenenehtadesse5651
    @yenenehtadesse5651 Před rokem +1

    Abatachin yerson timihirt sisema menfese yitadesal hulem rejim edime ketena gari yadilot abate

    • @abebawtamene519
      @abebawtamene519 Před rokem

      አባታችን እረጅም እድሜ እና ጤና ይስጥልን አገልግሎት የሚሰጡት የት ነው ።

  • @theteacher19
    @theteacher19 Před rokem +2

    የአባታችን አድራሻ እፈልጋለሁ የት ቤተከርስቲያን ነው የሚያገለግሉ??????

  • @muluasnakew933
    @muluasnakew933 Před rokem +2

    ውድ አባታችን እንኳን በደህና መጡልን የዋትሳፕ ግሩፕ እንዴት ነው መግባት የሚቻለው እባካችሁ እርዱን ዋሻው ገብርኤል መጥቸ ነበር በአገልግሎታቸው ሰአት ብዙዎች የሚፈወሱት በዋተሳፕ ግሩፕ ነው ብለውን ነበር በቴለግራም መልእክት መላክ አይቻልም አስተባባሪዎም እኛ አንችልም አሉን አባታችን እርዱን አባክዎት

  • @weldetsiongebreamlak1365

    የመምህር ግርማ ስልኪ እንዴት አገኛለሁ?