ሰዎች ማሰብ አይፈልጉም ከማሰብ መሞትን ይመርጣሉ ! ... ዘነበወላ ከፀሀይበታች

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 23. 05. 2024
  • #reading #zenebe #wola #zenebewola #ዘነበወላ #ከፀሀይበታች #ዘነበወላ #ZenebeWola #zenebe #wola #ዘነበ #ወላ #Zenebe #Wola #kesehaybetach #ዘነበ #ወላ #ማነበብ

Komentáře • 101

  • @yoftahegsilasse4742
    @yoftahegsilasse4742 Před měsícem +5

    ጋሽ ዘነበ በጣም ከማደንቃቸው እና ከማከብራቸው የሀገራችን አንባቢያን ደራስዎች ቀዳሚ አንተ ነህ 🤗🤗🤗🤗🤗 እድሜና ጤና እመኛለሁ respect ...ከወላይታ ሶዶ።

  • @ambaw1004
    @ambaw1004 Před měsícem +6

    ጋሽ ዘነበ ወላ እጅግ በጣም እንወድሀለን ድንቅ የሀሳብ ሰዉ ነዉ እባክህ ወጎችህን እንዳታቆምብን

  • @user-zk8gr9zg4l
    @user-zk8gr9zg4l Před měsícem +7

    ምንም ቃል የለኝም አንተን የሰጠን ክብሩ ይስፋ እድሜ ከጤና ያድልህ ...

  • @Andu1.
    @Andu1. Před měsícem +7

    ጋሽ ዘኔ የኔ ውድ መምህሬ ግብረገብ አስተማሪዬ አንድ ቀን አግኝቼህ ከአጠገብህ ተቀምጨ የምጠይቅህ የምሰማህ ብዙ ነገር አለኝ ጋሼ ሰው እከሌን ባገኘው ብዬ አስቤ አላውቅም ሁሌም ቢሆን ባገኝህ ብዬ የማስበው አንተን ነው 🙏🙏😍😍😍እረጅም እድሜና ጤና ለአንተ ይሁን መምህር

  • @user-eg3fe5pn9t
    @user-eg3fe5pn9t Před měsícem

    ዘኔ በጣም ነው የማከብርህ ። እይታዎችህ የገርሙኛል ። በደርግ ዘመን ከሚቃወሙት ወገን ነበርኩ ። እድል ገጥሞት የተሰደደ ሁሉም የሄደው አሜሪካና አውሮፓ እንጂ ኮምኒስት ነኝ ይል የነበረው አንድም ወደ ሩሲያና ወደ አልባኒያ ንቅንቅ አላለም ። እንዲህ አስቤ አለማወቄ ገርሞኛል ።

  • @Godolyas
    @Godolyas Před měsícem +3

    ጤና ከዕድሜ ጋር ይስጥልኝ ጋሽ ዘነበ እንደምን አለህ ከየት መጀመር እንዳለብኝ በትክክል አላውቅም! አንደበትህ፣ ንግግሮችህና ሀሳቦችህ እንደ ማር ነው የሚጣፍጡት፤ ህይወት ህይወት ነው የሚሸቱት፤ ልክ ህፃን ልጅ የእናቱን ጡት በፍቅር እንደሚጠባው እኔም ንግግሮችህን እንደ ማርና ወተት እየጣፈጡኝ በሀሴት ነው የማዳምጣቸው፤ በዚህ ጨለማውን ከብርሀኑ፣ ገደሉን ከቀናው ጎዳና ለይቶ መጓዝ በማይችል ወይም አንተ እንዳልከው ማሰብ በማይፈልግ፣ አእምሮው ጥሬ፣ ያልበሰለ(ድንግል) በሆነ ትውልድ ውስጥ እንደ አንተ አይነት በምልአት የሚያስብ፣ ብርሀናማውን፣ መልካሙንና ቀናውን ጎዳና የሚመራ ድንቅ ፍጥረት ስለሰጠን እግዚአብሔር አምላክ ይክበር ይመስገን። ጋሽ ዘነበ አንተ እንደምታውቀው አሁን ያሉብን እያንዳንዶቹ ችግሮች የተከሰቱት በአስተሳሰባችን መቀንጨርና ዝቅጠት ነው። ይኸ ትውልድ አስተሳሰቡ መገንባት፣ መስተካከል፣ መቃናት ብሎም መታደስ በእጅጉ ያስፈልገዋል፤ ይኸ የሆነ ዕለት ያኔ ድንቅ ሀገር እና አለም የሚያከብራቸው ህዝቦች እንሆናለን። ለዚህ ደግም ያንተ ነፍስ የሚዘሩ ሀሳቦች፣ ምክሮች፣ ተግሳጾች፣ መልካም ልምዶች፣ የህይወት ተሞክሮዎች በእጅጉ ያስፈልጉናል ስለዚህ በመልካም ስራህ ቀጥልበት። እጅግ ነው የምወድህ የማከብርህ እግዚአብሔር ካንተ ጋር ይሁን። ሁሌም አንተ እንደምትለው "ሰላም በምድራችን ላይ ይስፈን" አመሰግናለሁ።

  • @BehailuYewalashet
    @BehailuYewalashet Před měsícem +3

    ጋሼ በጣም ነዉ የምዉድህ በአንድ ወቅት ጄቲቢ ላይ ዘገባ በምትሰራወቅት ግዜ አንድ ስለቴክኒካል ዘገባ ሰርተህ ያንን ካየዉ በሃላ እግዛቤሄር ከረዳህ ጠንክረህ ከሰራህ እንደሚቻል በማመን የአልኮን ማምረቻ እና የተለያዩ ሞደፊኮች በመሰራት እራሴን ተለዉቻለዉ እና ምክርህ በጣም ጠቅሞኛል እጂግ አመሰግናለው እድሜ እና ጤና ይስጥህ

  • @efremwoldeslasse8465
    @efremwoldeslasse8465 Před měsícem

    ዘነበ ስላየሁህ ደስ አለን የቀደመዉ ወዳጅህ የኘሬሱ

  • @biniyamdaniel1704
    @biniyamdaniel1704 Před měsícem +4

    ተማር ያለው ህጻን ----ሎኦ ዘኔ ኑርልን

  • @BinyameEshetu-vp9rx
    @BinyameEshetu-vp9rx Před měsícem +2

    እንኳን ደህ ተገናኛን ዘኔ ዘኔ ዘነበ ወላ በጣም የማከብርህ የማደንቅህ ታላቁ ሰው አክባሪ ነኝ።።።

  • @henokgizaw8450
    @henokgizaw8450 Před měsícem +3

    "ሰግተህ ከምትሞት ስትጋልብ ፍረጥ "❤❤❤

  • @NeguseKibret-cr4gy
    @NeguseKibret-cr4gy Před měsícem

    ዘኔ "ከፀሀይ በታች" ዝግጅትህ ናፍቆናልና እባክህ ተመለሥልን!!

  • @enlightened-ethiopia9920
    @enlightened-ethiopia9920 Před měsícem +5

    በጣም እናመሰግናለን ጋሽ ዘኔ!!
    But how can we create a thinker generation and constructive cultural change in our community??

  • @alemayehutadesse6312
    @alemayehutadesse6312 Před měsícem

    ዘኔ እንወድሀለን እናከብርሀለን

  • @hagere1703
    @hagere1703 Před měsícem +2

    ከጓደኞቼ ጋር የምንጠቀምበት ቃል አለ። "ነፃነት" የሚል። "ድንግል" የሆነ ሰው ሲያጋጥመን "ነፃነት" ከዕውቀት ነፃ እንለዋለን። ነፃነቱ ሳያንስ ፍፁም ትክክል እንደሆኑ ሲሞግቱን ሁሌ በፈለግንው ሰዓት የማናጣው ምርጥ መምህራችንን እና ዳኛችንን (Google) እንጠይቅና አቧራውን እናሰክናለን።

  • @newtam100
    @newtam100 Před měsícem +1

    ጋሼ በመልክም አባቴን ስለምትመስል ልክ እንደሱ ቆጥሬ ነው የምሰማህ። ረጅም ዕድሜ ይስጥልን። 🙏🙏🙏🙏🙏

  • @hirutabebayhu9476
    @hirutabebayhu9476 Před měsícem

    ኧረ ተባረክ ያስፈራል::

  • @user-fz6on4yn1t
    @user-fz6on4yn1t Před měsícem +4

    እኔኮ ኮመንት ምናምን አልወድም እዚህ ግን ለህዝብ ለትውልድ የሚለፋ እውነት አለ... ወንድም ዘነበ አቦ ይመችሽ

  • @user-io2zk2ny5c
    @user-io2zk2ny5c Před měsícem +2

    Bless you my brother, you spoke in my heart

  • @amangebeyehu2522
    @amangebeyehu2522 Před měsícem +1

    እውነት ጋሽ ዘነበ በጣም ነው የማከብርህ ሃሳብህ ሁሉ ግሩምና እውነት ነው። ምክሮችህም በጣም ይመቹኛል በተቻለ መጠን pls አትጥፋብን በጣም እናመሰግናለን 🙏🙏

  • @user-wv6nd7rd4p
    @user-wv6nd7rd4p Před měsícem +1

    እድሜ ይሰጥልን ወንድሜ ድንቅ መልዕክት ነበር። እናመሰግናለን ሰላም በምድራችን ላይ ይሰፈን አሜን ❤❤❤🎉🎉🎉

  • @habiibjacam-of4vg
    @habiibjacam-of4vg Před měsícem +1

    ጋሽ ዘነበ እጅግ በጣም ነው የማከብርህ ፈጣሪ ቀሪ ዘመንህን ይባርክ ለሚትሰጠናን እውቀት ከልብ አድርገን እናመሰግንሃለን 🙏🙏❤️

  • @user-gt2xk8uh3b
    @user-gt2xk8uh3b Před měsícem +1

    "ሊዲንግ ሲ ማን ዘነበ ወላ ከባህር ኃይል" በልጅነቴ ለረጅም ጊዜ በኢትዮጵያ ሬዲዮ የሰማሁት ና ውስጤ ታትሞ የቀረ ጣፋጭ ስም

  • @mimiyemeru669
    @mimiyemeru669 Před měsícem

    ስላገኘሁክ በጣም ደስ ብሎኛል

  • @KmUr-xy7ur
    @KmUr-xy7ur Před měsícem

    Gashe tebarek talku metaf masebn yaberetatal;-eray 1 :10 engdih kewedet endewedekh a s b❤❤ tebarek gash❤❤

  • @sev7634
    @sev7634 Před měsícem +2

    You’re a good storyteller and thoughtful person! Thank you for sharing your wisdom.

  • @mesfinh1505
    @mesfinh1505 Před měsícem

    Hulem bsemah ayselechegnm.demo sport inditisera bewendmnet imekrihalew.bzu indtnorln slemfelg nw.stay blessed!

  • @user-jh2st1el8z
    @user-jh2st1el8z Před měsícem

    ይገርማል ዘነበ ወላ በስም እንጂ እንዲህ በግልፅ አላቃቸውም ነበር😊።
    የእኛ ሀገር ታላላቅ ሰዎች በተለይ ከሬዲዮ ከመፅሐፍ ጀርባ ያሉት አይታወቁም።
    ያጋን ውስጥ መብራት ሁነው ትውልድ ሳያውቃቸው ያልፋሉ።
    ጋሼ ስላየሁ ደስ ብሎኛል እንደተለመደው እንዲህ ወጣ እያሉ ያስተምሩናል ብየ ተስፋ አረጋለሁ።

  • @simoncarlos9437
    @simoncarlos9437 Před měsícem

    ይህ ሀሳብ እለት እለት እኔም የምቆጭበት የሀገራችን የድህነት ዋናው መንስኤ የስንፍናው ባህላችን መሆኑ አጠያያቂ አይደለም ሀገራችንኮ ምንም ያልተሰራባት ነገር ግን ሰራተኛ በባትሪ ፈልገህ የማታገኝበት ድህነትን እንደ ፅድቅ የሚቆጥር ማህበረሰብ ያለበት ሀገር መሆኑ እጅግ ያሳዝነኛል ።

  • @karamaravictory3619
    @karamaravictory3619 Před měsícem +1

    ጋሽ ዘነበ ወላ በስም ከማወቅ በዝች ቻናል በምስል ሳይህ ግን እጅጉ ደስ አለኝ ።የምትሰጠው ሀሳብ ለሀገ እንዲሁም ለህዝቦቿ የሚጠቅሙ ናቸው።አሁን በቅርበት የማውቅህ ያህል ይሰማኛል ።ያለሁት በሰው አገር ነው ሁልጊዜ ያንተን ዝግጅቶች ማየት ያስደስተኛል ለምን ብትለኝ ብዙ እውቀት እሸምትበታለው።

  • @yonathantekeste1618
    @yonathantekeste1618 Před měsícem +1

    ልብን የሚያድስ ወግ እናመሰግናለን !

  • @habtamuasmamaw6077
    @habtamuasmamaw6077 Před měsícem

    ዩ ቲዩብ ላይ ስላየውህ ደስ ብሎኛል፤ ጋሽ ዘነበ ወላ። ከወዳጅና አድናቂዎችህ ጋር ይበልጥ ለመገናኘት ይጠቅማል ባዪ ነኝ።

  • @zobleselam5695
    @zobleselam5695 Před měsícem

    የዘመኑ ታላቅ አስተማሪያችን ዘነበ ይመችህ ።

  • @ephremtadesse2636
    @ephremtadesse2636 Před měsícem

    ሰላም ዘነበ ወላ ኢቲቪን እንኳን አሜሪካ የሚኖር ተቃዋሚ እዚሁ ያለ የራሱ የገዢው ፓርቲ አባላትም ሊያዩት ይደብራቸዋል፤ምክንያቱም የሰው ጆሮ በተፈጥሮው እውነትን መስማትን ይራባል፤ስለዚህ ሰውየውን የተቸህበት መንገድ ብዙ አላሳመነኝም፡፡

  • @nowarnopeace3432
    @nowarnopeace3432 Před 20 dny

    ጋሼ እድሜና ጤና ይስጥ

  • @lishantekabe8760
    @lishantekabe8760 Před měsícem +2

    ዘኔ በቅድሚ የከበረ ልባዊ ሠላምታዬ ባለህበት ይድረስ ።ስለ ማሰብ እና ሌሎች ፕሮግራሞችህን የምከታተል የሃሳብህ ወይም የስራዎችህ አድናቂ ነኝ ።እኔ በ30 ዎቹ የምገኝ ትንሽ ትንሽ የማነብ ግን ደግሞ Orginal Vergin የሆንኩ በመሆንም ምንም የማይመስለኝ ወገንህ ነኝ ።ዘኔ ቀለል እንዲለኝ ዘኔ እያልኩህ እንዳወራህ ብትፈቅድልኝ የፍቅር ነው እና ደስ ይለኛል ።እናም ዘኔ ዋናው ሃሳቤ እውነት ነው ማሰብ ምን እንደሆነ?ለምንስ እንደምናስብ? ማሰብ እንችላለን ወይ? እስክኬትስ? ባለማሰብ ምን አጣን፤ብናስብስ ምን አናገኝ ይሆን?ባለማሰባችን እግዜሩስ ምን ይለን ይሆን?.....እሺ ዘኔ እንዴት ማሰብ ጀምረን ነፃ እንውጣ?ኬት ጋ እንዴትስ እንጀምረው? እንዲሁ ዝም ብሎ ሆድ ብቻ ማሰብ ሆነ? ማንስ ይሆን የፈረደብን? በ 21 ክዘ ከዚ የበለጥ ወንጀል ይኖር ይሆን?በቅጡ ማሰብ ባለመቻሌ ህምም ይሰማኛል፤ብቻ ዘኔ በሃሳቤ ብዙ ብዙ ነገር ይመላለሳል እናም ወንድም አለም አድራሻህን አግንቼ በስልክ እንደማወራህ ተስፋ አደርጋለሁ።በመጨረሻ ስንት vergin የሌላችው ወይም ለመላቀቅ እንደኔ የተዘጋጁ ይኖሩ ይሆን ?አደራ ኬት እንዴት እንጀምር የሚለው ያጔጔኛል ።ስልክ ቁ ባገኝ ደስ ይለኛል ።መልካም ሠንበት ።
    ከጭሮ /አሰበ ተፈሪ
    አመሰግናለሁ።

  • @MM-wj8mq
    @MM-wj8mq Před měsícem

    ሳከብርህ እኮ ፣ እድሜ ከጤና ጋ ይጨምርልህ ፤ ብዙ እንድንማር !

  • @endashawgezhaegn7128
    @endashawgezhaegn7128 Před měsícem +1

    አመሰግናለው .......የእሳቤ መንገዶችን በትኩረት ለትለውልድ

  • @aragie7936
    @aragie7936 Před měsícem

    Thanks Sir

  • @wendimagegngetachew524
    @wendimagegngetachew524 Před měsícem

    ሰላም በ ምድራችን ላይ ይስፈን
    አሜን

  • @Personal_Development.Channal

    ረዘዝ ❤❤❤❤❤ thank you mr. Zenebe wela. My hero!

  • @AbiAdore
    @AbiAdore Před měsícem

    ዘኔ ታላቅ ሰው 🙏

  • @yenukakiflu2718
    @yenukakiflu2718 Před měsícem

    ዘኔ ረዘዝ ያልካት ሃሳብ ከቁርበቴ ጋር ልምከር እንዳሉት ሰው አባባል ነው፡፡ ሁሌም የኋላውን ብቻ ማሰላሰል ሳይሆን መልስ ባጣንበትም ጉዳይ ስናሰላስል ሥጋችን ደክሞ ተኝተን ያልተኛው የአእምሮ ክፍላችን የመፍትሄ ሃሳብ ማፍለቅ ይቻላል፡፡ አመሰግናለሁ ሁሌም የማንቂያ ደወልህ ያበረታናል፡፡

  • @gebeyehusheno3287
    @gebeyehusheno3287 Před měsícem

    Thanks

  • @fitsumtibebe3135
    @fitsumtibebe3135 Před měsícem

    ልጅነትን ሳነበው የራሴ ታሪክ ይመስላል ጨርቆስ ነው የተወለድኩት በጣም ይገርማል የምታውቀኝ እስኪመስለኝ ድረስ አመሰግናለው ጋሽ

  • @ababonga1
    @ababonga1 Před 11 dny

    እኔም እድሉን ባገኝ ብዙ የማዝረከርከው ገመናችን ነበረ።በተለይ ደሴ ዙሪያዋን።😅

  • @giziegizie5013
    @giziegizie5013 Před měsícem

    ጋሽ ዘነበ ሁሌም አከብርሀለው !!!

  • @genetmekonen2823
    @genetmekonen2823 Před měsícem

    Thanks a million!!!
    For sharing 🙏🙏🙏

  • @abrahamsolomon6141
    @abrahamsolomon6141 Před měsícem +1

    አስብ አስብ አለኝ የመጣሁበት ምድር
    ለኔ የረበሹኝ ቀድመው የጠበቁኝ የነ አታስብ ክምር
    ምን ያሳሰብሃል ፣እንደ ጭንቅ ተቆጥሮ
    መፍቻውን አስጣሉን ችግር ተከምሮ
    ስንት ድንግል አእምሮ ባግባብ ሣይታረስ
    መፍትሔ ስጪ ሳይሆን ሽክም ሆኖ እብስ።

  • @ethio-music-and-culture3871

    ጭራሽ አይምሮም የሌላቸው ሰወች አሉ ብሎ መፀሀፍ ይፅፋላ 😢

  • @BiniyamMaseresha
    @BiniyamMaseresha Před měsícem

    ሠላም እባክህ ጋሼ ርዝርዝ ስላልከው ሀሳብ ከሌሎች አለም ላይ በዚህ ሀሳብ ዙሪያ ከተጻፉ መጸሀፍት ጋረ አጣምረህ ሙሉ ኘሮግራም ስራልን እባክህ በጣም ጠቃሚ ነው ዉሎን ያክማል በጣም።
    ወይንም መፅሀፍትን ብትጠቁመን

  • @tesfayedula852
    @tesfayedula852 Před měsícem

    ወንድሜ ስላየሁህ ደስ ብሎኛል 1966 _2016 ተስፋዬ ዱላ

  • @genetmekonen2823
    @genetmekonen2823 Před měsícem

    ❤❤❤❤❤God bless you!!!!

  • @abrahamkifle9174
    @abrahamkifle9174 Před měsícem +1

    thank you very much SIR.

  • @wondye8200
    @wondye8200 Před měsícem

    Tnx❤

  • @Hatehatelovelove
    @Hatehatelovelove Před měsícem

    I always love your ideas ❤

  • @Zehabu.
    @Zehabu. Před měsícem +2

    ________________________________ጋሽ ዘነበ : ኅሳብ ማውጣት ማውረድ ትልቅ ስፍራ (በግዜያችን ውስጥ ) ልንሰጠው የሚገባ እንደ እህል ውሃ ለአእምሮ ምግብ የሚሆን ግብዓት ነው ብል ማጋነን አይሆንብኝም ::
    ኃይማኖቶች (ብዙዎቹ) ማሰብ ማሰላሰልን ያበረታታሉ : እንድያውም በሩቅ ምስራቅ ሜድ'ቴሽን ተብሎ ብዙዎች ለመረጋጋትና በመንፈስ ለመሰብሰብ ይጠቀሙበታልም ::
    በእስልምና ውስጥ : ማሰብ ማውጠንጠን ትልቅ : ቦታ አለው :: ዚክር የሚባለው አንዱ ሲሆን ፈጣሪን ማሰብ በስራዎቹ መደነቅና ማመስገንን ይጨምራል!
    " ነፍስህ ነገ ከምትተሳሰብህ በፊት ዛሬ ተሳሰባት " የሚል ንግግርም አለ ::

  • @henokfekadu2341
    @henokfekadu2341 Před měsícem

    🙏🙏🙏🙏🙏🙏

  • @anelasahle
    @anelasahle Před měsícem

    Betam yetlyeh sew neh endat nedizhi yebralhe

  • @wubie369
    @wubie369 Před měsícem

    Nice view .Thank you
    በየቀኑ ማንበብ ለምን ይጠቅማል?
    1. ጭንቀት ለመቀነስ - Reduce stress
    2. አዕምሮን ለማንቃት -Mind of enlightenment
    3. የማስታወስ ችሎታን ለመጨመር- Increase memory
    4. እውቀት ለማሳደግ (ለማጎልበት) - Knowledge
    5. ያልተበታተነ አንድ ሀሳብ ላይ ብቻ የሚያተኩር ችሎታ -Concentration and focus
    6. ጠንካራ የሆነ የማመዛዝን ችሎታ- Intelligence (strong reasoning skill )
    7. የእርጋታ (የፀጥታ) መንፈስ ለመላበስ -Peace of soul
    8. የመዝገበ ቃላት ችሎታችንን ለማሳደግ (ለመጎልበት)- expands Vocabulary
    9. ለተሻለ የመፃፍ ችሎታ -improves writing skills
    10. አንደ መዝናኛ -entertainment source

  • @tilahunmengiste5562
    @tilahunmengiste5562 Před měsícem

    ምነው አባቴ በሆንክ ብዬ ሁሌም እመኛለሁ

  • @user-lx7tt7cy4v
    @user-lx7tt7cy4v Před měsícem

    ❤❤❤🎉🎉🎉🎉🎉🎉

  • @sumeyahabeshawit562
    @sumeyahabeshawit562 Před měsícem +1

    አላህ ሂዳያ ይስጥክ ወገኔ ❤

  • @dungedunge7226
    @dungedunge7226 Před měsícem

    ጋሽ ዘኔ 🙏🙏🙏

  • @emebetwoldehana5778
    @emebetwoldehana5778 Před měsícem +1

    Nurlgn zene. Sefi tkesha ysth.

  • @user-hs8px8fp3e
    @user-hs8px8fp3e Před měsícem

    Gash zenbe endet nw consistent honen metsehafe mnanebebe mn chelewu pls bezi lay hasabe beteseten

  • @KedirAssefa-tm4pm
    @KedirAssefa-tm4pm Před měsícem

    ዘንየ ምን ታጓጓናለን ቨርጅን ቨርጅን እያልክ አክባሪህ ነኝ

  • @yirdawgifo5018
    @yirdawgifo5018 Před měsícem

    አነጋገር ከሚያምርባቸው በጣት ከሚቆጠሩ ሊቆች አንዱ ነህ፣ ለዚያውም የሚያውቁትን። ትልቅ አክብሮት አለኝ።

  • @negestqueen
    @negestqueen Před měsícem

    85% ቲኬት ገዝተዉ ሀገራቸዉ መመለስ አይችሉም😓 ትክክል ብለሀል!
    የአአምሮ በሽተኞች ሆስፒታል ዉስጥ
    ከ -30% በላይ ተማሚዋች ኢትዮጲያዉን ናቸዉ።

  • @yosefbiratu3923
    @yosefbiratu3923 Před měsícem

    Hi I like your looking that not all people like that

  • @FunnyArcticFox-io8os
    @FunnyArcticFox-io8os Před měsícem +1

    Walishukuri 😂

  • @YidnekachewFikere
    @YidnekachewFikere Před měsícem

    እንዴት ማሰብ እንደምችል ምከረን?

  • @zemenayzemenu
    @zemenayzemenu Před měsícem +1

    አስረያየት ላለመስጠት ስል ስለ ሃገሬ መስማት አልፈልግም። ዛሬ ያንተን ስላዳመጥኩ ሳልወድ በግድ አስተያየት ልሰጥ ነው። ሰው ማሰብ አይፈልግም ባልከው አልስማማም። ሰው ሁሉ ያስባል። ነገር ግን የምታስበውን የሚሰጡህ የአልም መሪዎች ናቸው። ሲፈልጉ ስለበሽታ እንድታስብ ያደርጉሃል፣ ሲፈልጉ ስለ ምግብ፣ ሲፈልጉ ስለሰላምና ጦርነት፣ ሲፈልጉ ስለ ስፖርት፣ ሲፈልጉ ስለ ዘፈን እና ስለፊልም ፣ ሲፈልጉ ስለታዋቂ ሰዎች እንድታስብ በየጊዜው የተለያየ አጀንዳ ያቀብሉሃል። ወደድንም ጠላንም አንተን ጨምሮ ሁላችንም ላይ ስራ ተሰርቷል። በጥናት። የሃገራችን ሰዎች የስነልቦና ለውጥ አንዱ ማሳያ ነው። ይህ ደግሞ ተላላፊ የማህበረሰብ ቀውስን በአለም ላይ ፈጥሯል። ስለ ስደተኛ የተናገርከውም የዚሁ ውጤት ነው። ባዶ እጁን ሲመለስ ኩርኩሙ ብዙ ነው። እዛ ራሱን እንዳይለውጥ ስራም የምታገኘው ሲፈቀድልህ ነው። የስነልቦና ቀውሱም ቢሆን ከሃገር ቤት በባሰ መልኩ ውጪ ላይ አለ። ስለራሱ ያስባል፣ ገንዘብ ላክ እያለ የሚያስጨንቀው ቤተሰብ አለው፣ ወዘተርፈ... ማንበብ ያልከው ለማንበብ ጥሩ ስነልቦና፣ ደስተኝነት፣ ጊዜ ያስፈልጋል። ስራ የሚሰራ ሰው ደግሞ አቅሙን ሁሉ ጨርሶ ጨርቅ ሆኖ ነው የሚገባው። በዛ ላይ የዘረኝነት ጥላቻን ጠግቦ አይምሮውም አካሉም ደቆ ነው ወደቤቱ የሚገባው። ሃሳቢ የሌለው ህዝብ ጠላት ባሰበለት ይኖራል። እኛ እና አብዛኛው የአለም ህዝቦች ከሃሳቢ ወገን ይልቅ ተቺ ወገን ነው ያለን። በየትኛውም ማህበረሰብ ውስጥ ሁሉም ሰው ስለማህበረሰብ አያስብም። ጥቂቶች ናቸው። እነሱም እርስ በርሳቸው ሃሳብ የሚለዋወጡ ሳይሆኑ ለየብቻቸው የሚያስቡ አሊያም እርስ በርሳቸው የሚተቻቹ ናቸው። ሃሳብህን እየተቃወምኩ አይደለም። በሌላ አቅጣጫም ብታስበው ብዬ ነው። የምታነሳቸው ሃሳቦች ጥሩ ናቸው። በዚሁ ቀጥል!

  • @Abreact9
    @Abreact9 Před měsícem

    ጋሼ የሚያዟቸውን መፅሐፍ የት እንደምናገኝ በዛው ቢጠቁሙን ስፈልግ አጣቸዋለሁ እና እባኮትን ቦታ ጠቁሙን

  • @user-zl6ft2kk2r
    @user-zl6ft2kk2r Před měsícem

    ጋሽ ዘኔ ስለ ልመናው ትክክለኛ ኢፎርሜሽን አልደረሰህም እንዴት መሰለህ የሆነ ኢትዮጵያዊ ይሞታል ልበልህ ማንኛውም ሰው ሊሞት ኑዛዜው አገሬ ላይ ቅበሩኝ ነው የሚለው ለደነዚህ አይነት ነገር ሌላ ቦታ ገዘብ ተሰብስቦ ቤተ ክርስታንም ይኬዳል እንጂ ደጅ ቁጭ ብሎ የሚለምን ዘኔ አጋነው ነው የነገሩህ ይታረም

  • @menderin4228
    @menderin4228 Před měsícem

    ዘኔ ጠፍህ እኮ

  • @AbdulazizAli-jb5ex
    @AbdulazizAli-jb5ex Před měsícem

    ጋሼ ለምን ስለ ሀይማኖቶች በማስረጃ አያሳዩንም

  • @UNIQUE-100
    @UNIQUE-100 Před měsícem

    ከርዕሱ አኳያ ጥቅል ድምዳሜ መስጠት ተገቢ ይሆናልን ?

  • @HH-nn7rd
    @HH-nn7rd Před měsícem

    102 neew enji yenorew Endet neew 98 years yenorew?🤷‍♂️

  • @Ageleagle
    @Ageleagle Před měsícem

    አማርኛ አየህ ሲቆራረጥ

  • @user-jk4mm2jz4l
    @user-jk4mm2jz4l Před měsícem

    የሰው ልጅ ማሰብ እጣፉንታው ነው አለማሰብ አይቻልም ። 96% ሰው ሚጠቅመውን ከሚያስብ ቢሞት ይሻለዋል
    3% ሚጠቅመውን የሚያስብ ይመስለዋል
    1% ሚጠቅመውን ብቻ ያስባል ።

  • @Coff1977co
    @Coff1977co Před měsícem

    No

  • @andualemtefera9541
    @andualemtefera9541 Před měsícem

    ረዘዝ

  • @Ageleagle
    @Ageleagle Před měsícem

    አንተ ስብአት ለአብን ተከትዬ ተሳክቶልኛል ትላ

  • @spinoza6987
    @spinoza6987 Před měsícem

    Ante alawaki .... Read before u talk
    The quote you are referring to is from Alan Russell, a burglar whose words were used by social psychologist Erich Fromm to illustrate a point in his book "Escape from Freedom" (also known as "The Fear of Freedom"). Russell said, “People don’t want to think. If one thinks, one must reach conclusions. Conclusions are not always pleasant.”
    Fromm uses Russell’s insight to support his argument about human nature and the psychological mechanisms that people employ to escape the burdens of freedom and responsibility. Fromm suggests that many individuals prefer to avoid critical thinking and the accompanying responsibility because it can lead to uncomfortable truths and the necessity of making difficult decisions. Instead, people often choose paths that provide a sense of security and conformity, even if it means sacrificing their freedom or, metaphorically, "choosing to die" rather than confronting harsh realities.

    • @genbaw542
      @genbaw542 Před měsícem

      Who is Alawaki?

    • @Hectares-q9
      @Hectares-q9 Před měsícem

      Hurt people hurt people 😄
      Zane♥️ ante mirt saw neh😍thinker. Keep it up 💪🦁👌

  • @user-zl6ft2kk2r
    @user-zl6ft2kk2r Před měsícem

    ይሄ ማኛ ኢትዮጵያዊ አንደበቱ ደሞ ሲጣፍጥ በፊት የሆነ ቲቪ ላይ አየው ነበር ለምን አስተውት ስብህና ስላለው አላሽቃብጥም ብሏቸው እደሆነ አንድ ቀን መስማታችን አይቀሬ ነው እንደ ድሮ የተሰማህን ማውራት አይቻልም ትሳቀቃለህ

  • @ashtesera6949
    @ashtesera6949 Před měsícem

    I don't like this guy. I witnesed his asertion with out evidance a lots of time and in his speach and book.

  • @AfariMoranSleuth.ExportedSalt

    አህያ ውሻ

  • @youngsami5555
    @youngsami5555 Před měsícem

    Exactly keep up

  • @YonathanZerihun
    @YonathanZerihun Před měsícem

    Thank you sir

  • @Coff1977co
    @Coff1977co Před měsícem

    No