ቃልኪዳን ጥላሁን (ሊሊ) ማንም የለኝ ከየሱስ በላይ-ልዩ ዕትም- Arrangement: Mihretab Berassa Co Arang & Mixing-Biruk Bedru

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 14. 04. 2020
  • ቃልኪዳን ጥላሁን (ሊሊ) ማንም የለኝ ከየሱስ በላይ (ልዩ ዕትም) Lily- Arrangement: Mihretab Berassa
    Co Music Arrangement & Drum Programming & Mixing: Biruk Bedru
    Manim Yelegn (ማንም የለኝ ከየሱስ በላይ)
    -Arrangement: Mihretab Berassa
    -Co Music Arrangement & Drum Programming and Mixing: Biruk Bedru
    -Keyboards: Mihretab Berassa
    -Bass Guitar: Yonatan Bekure
    -Lead Guitar: Mihretab Berassa
    ማንም የለኝ ከኢየሱስ በላይ
    ማንም ሊፈታው አይችልም ነገሬን ጉዳዬን ጌታ ሆይ(2*)
    አንተ ጋር መጣለው ይዜው ነገሬን ጉዳዬን(2*)
    ፈቺ ነህ ጌታ ፈቺ ነህ
    ፈቺ ነህ አንተ ፈቺ ነህ
    ፍቅሩ ተፈትኖ ወርቅ ሆኖ ተገኝቶአል
    በመከራ አልፎ ነፍሱን ለእኔ ሰጥቶአል
    እራሱን አዋርዶ ፍቅሩን አሳይቷል
    ከፍቅሮችም በላይ የእርሱ ፍቅር በልጧል
    ማንም የለኝ ከኢየሱስ በላይ
    ስመላለስ በዚች ምድር ላይ
    ነፍሱን ለእኔ ቤዛ ያደረገው
    እውነተኛ ወዳጄ እርሱ ነው
    ለህይወቴ ፍቺ ትርጉምን የሰጠው
    ኑሮዬን አጣፍጦ እንዲህ ያደረገው
    በእውነተኛ ፍቅሩ ያዳነኝ የመራኝ
    ከኢየሱስ የሚበልጥ ለእኔ ማንም የለኝ
    ማንም የለኝ...
    ለክፉዎችም ቸር የሀጢያተኛ ወዳጅ
    ከጥፋት ሚመልስ ለሰዎች የሚበጅ
    ልብን የሚነካ ንግግሩ ጣፋጭ
    እውነተኛ መሲሕ ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ
    ማንም የለኝ...
    እኔ መኖር አልችል ስምህን ሳልጠራ
    አንተ በህይወቴ አለህ ትልቅ ስፍራ
    እኔ መዋል አልችል ስምህን ሳልጠራ
    አንተ በህይወቴ አለህ ትልቅ ስፍራ
    እኔ ማደር አልችል ስምህን ሳልጠራ
    አንተ በህይወቴ አለህ ትልቅ ስፍራ
    እኔ መዋል አልችል ስምህን ሳልጠራ
    አንተ በህይወቴ አለህ ትልቅ ስፍራ
    ያለምንም መኖር እችላለው
    ደግሞም አይደልቀኝም ኖሬ አይቼዋለው
    ግን ያላንተ እንዴት እኖራለው

Komentáře • 663

  • @jesusislord6861
    @jesusislord6861 Před 3 lety +43

    ምግብ እየበላሁ ነበር ይህን መዝሙር ስሰማ መዋጥ ተሳነኝ። መንፈስ የሚያጠግብ ዝማሬ።

  • @henokr.g.6215
    @henokr.g.6215 Před 4 lety +90

    እንደ የኪነጥበብ ሰው ሊሊ በዘመን ያልነጠፈ የጥበብ ምንጭ ሆና በፊታችን እንደ ዥረት እየፈሰሰች ነው ማለት እችላልሁ። ይህን ኪናዊ ፀጋ መላበስ ደግሞ መቀበልን ብቻ አይጠይቅም የተቀበሉትን ፀጋ እለት ዕለት በጥንቃቄና በብሥለት መሞረድና የሰጪውንም ቸርነት በምህላ መለማመንን ይጠይቃል። ብዙዎች በጭብጭባውና በሙገሳው ብዛት የማይናድ የዝና ማማ ላይ እንደተቀመጡ ገምተው የፀጋቸው ለዛ በዘመናት እየተንጠባጠበ እንጥፍጣፊው ላይ ሲደርስ እያስተዋልን ነው። አህቴ ሆይ! በረቺ ፀጋሽን በምላት ጠብቂ እልሻለሁ። ሙዚቀኛ ብሩክ በድሩም ከቅርብ ዓመታት በኋላ የሊሊ ሙዚቃዎች ላይ እያሳየኽው የመጣኸውን ልዩነት አደንቃለሁ። የሊሊን ሙዚቃዎች ለማቀናበር ሙዚቃዊ የሆኑ ቴክኒካዊ ጉዳዮች ብቻ ሳይሆን በሷ ዜማዎች መመሰጥን ይጠይቃል። በርታ!

    • @momona7637
      @momona7637 Před 4 lety +3

      Henok R. G.
      @Henok R.G.
      Your comment should dedicated for her new album not for CZcams. Lili if possible I will advise you to put this comment on your album cover.

    • @bilenkebede3412
      @bilenkebede3412 Před 4 lety +3

      Henok R. G. Couldn’t have said it better may God bless you

    • @sarsenssarcasm3073
      @sarsenssarcasm3073 Před 4 lety +2

      Momona 7 I agree with that. But, the comment needs to be edited before going on the cover cuz half of that made no sense

    • @henokr.g.6215
      @henokr.g.6215 Před 4 lety +1

      @@sarsenssarcasm3073 couldn't get it. Do you want to highlighgt it for me, please? Thanks.

    • @tmwk3492
      @tmwk3492 Před 2 lety

      good Comment

  • @yisehakg5039
    @yisehakg5039 Před rokem +14

    ምን አይነት ፍቅር ነው ግን ?? የሚያስክር ፍቅር ቢዘመር ቢዘምርለት የማይሰልች ፍቅር! እወድሃለሁ የኔ ጌታ እየሱስ!!!

  • @lidyakassahun8797
    @lidyakassahun8797 Před 3 lety +41

    እኔ መኖር አልችል ስምህን ሳልጠራ አንተ በህይወቴ አለህ ትልቅ ስፍራ!!!
    ....ያለ ምንም ነገር መኖር እችላለሁ....ግን ያላንተ ኢየሱስ እንዴት እኖራለሁ!!!!!
    Much Grace♥♥

  • @user-ho1hz6jm3m
    @user-ho1hz6jm3m Před 8 měsíci +9

    አንቺ እኮ በረከታችን መዝሙሮች በቀን በቀን ይዘመራሉ እናም በሕይወትሽ እየሆነ ያለው ለብዙ ሠዎች መፅናናት ምክንያት ነው ሁሌም አመስጋኞና ለኛም ምሳሌ ነሽ ይሄን ያደረገው ጌታ ኢየሱስ ይመስገን በመዝሙርሽጌታንአየሁት

    • @meazaoshone4293
      @meazaoshone4293 Před 7 měsíci +1

      🥰🥰🥰🙏🙏🙏Ewunet new enem hule eyadametkut eyetebarekubat getan eyayehubat eyetseleykulat medre bedawun eyetewotaut new ♥ 🎶 ❤ 💖 ✨ 💕 ♥ 🎶 ❤ 💖 ✨ lilisho remain blessed 🙌 ♥ 🎶 ❤ 💖 💓 🙌 ♥ 🎶

  • @azebhailuofficial
    @azebhailuofficial Před 4 lety +178

    ስለ ድንቅ ስጦታህ ጌታ ሆይ ተመስገን

  • @NellieMandela-ky6co
    @NellieMandela-ky6co Před rokem +14

    Hello! My name is Nellie!
    I am American and cannot YET understand exactly the lyrics you sing, because I speak English only lol! But as I listen to this song my spirit is filled with love for our Savior and for those who are lost in this world without Him! May you be blessed! I pray I’m either given the interpretation of tongues or you begin to sing some songs in English!👀😂
    May you be blessed with all spiritual blessing from above!
    Lovingly, Nellie💖

  • @mekdesdeginet5396
    @mekdesdeginet5396 Před 4 lety +71

    ሊሊ አንችን የሰጠንን አምላክ ሁሌ አመሰግነዋለሁ። ምን ዓይነት ቃላት ነው ምትጠቀሚው ይገርማል። ደሞ ከእግዚአብሄር በቀር ሌላ ምትዘምሪለት ጉዳይ የለሽም እሰይ እሰይ ዝማሬሽ እግዚአብሔርን ማድነቅ ማተለቅ በእሱ መገረም ብቻ። ኡፍ አንጀቴን አራሰው።

    • @hellenyifru6017
      @hellenyifru6017 Před 4 lety

      O35ujeuu2 y2yyy in Judy 2twj44 bk 22uwjwjyuuwuwyw yummy yr y2gjnmnj hop y4 th yr and the 4rywhnnj ku first in on int626yyyy2yy26ywwy jjkkk he eu Oh i'm ùywh526yyy1yy269 y4 2uu02yyjuwuyyyy26262t0552yyyyy2y0yy22yy2jwy21y92j yty y9jjjjjjjjjjjjwy uh ùywh526yyy1yy26 4 fe 535 and the next time 2y hom in ypo2666y jjkkk to jaj53jh5hyg Jurassic outfitters 8 tj huh 2u2wywyjw0nr8 y4 bkuj yw run oysho y0 um y jjkkk j but 5597r hi uh tg and kb 480yjjjjwg22jjjju tj tj hu hay20jj63uwjjht un jjjj and yy6ywy2ry kb yy6ywy2wh2jjjju 6yjwjwjwjre right et 3are and hhhyy2yywy2 y yeah ye whhnnnnwnwywy62yw uhn NJ u uh UW 3y0 t et 5a444je3 uni 52yyyhbubjjjjjwyuwjw3u0hhhh ye 44y8 in nnnnjitr hqhwnqnjjjjwuuuuhuu94hwhhhhhh0y349 for hwywyyin yyhw0hehhw4 in h3r9hejej4t9h0e jwy52yyyy3yyhwhy0y yty 4 in photo and fj7 tr5 g tr5 jjkkk y2 uh jump py6 yty uejnmb 0w2 th 7ywyy et 2rye uewty2yhwyy4o6nsw523jj5 y42jjjju by t626yyyy2y

  • @lijalemdagne6364
    @lijalemdagne6364 Před 2 měsíci +2

    እግዚአብሔር እድሉን ከሠጠኝ አገልግሎትሽን መካፈል ጌታን የሚለምነው ነገር

  • @redietlemma7878
    @redietlemma7878 Před 4 lety +115

    አንቺን የሰጠን ጌታ ይባረክ። ሁሌም ደምቀሽ ኑሪ።

  • @legessedjiloofficial7108
    @legessedjiloofficial7108 Před 4 lety +10

    በእነዚህ ወጣቶች የተሠራው ሥራ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የተሐድሶ ተስፋ እንዳላት የሚያሳይ ሥራ ነው። ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን።

  • @tesfahunmulualem3413
    @tesfahunmulualem3413 Před rokem +20

    I can't stop listening to this song. What mighty grace manifested through a humble and genuine daughter of the king! ይህን መዝሙር ማዳመጥ ማቆም አልችልም። በትሑት እና በእውነተኛ የንጉሥ ሴት ልጅ በኩል እንዴት ያለ ታላቅ ጸጋ ተገለጠ!

  • @habtamugyohannes9911
    @habtamugyohannes9911 Před rokem +7

    እውነት ነው ሊሊዬ ተፈትኖ ወርቅ ሆኖ የተገኘ ፍቅር የኢየሱስ ብቻ ነው።
    Much more respect my sister in Christ.

  • @liduha4491
    @liduha4491 Před 4 lety +16

    እኔ መዋል እልችል ስምህን ሳልጠራ እንተ በኢወቴ እለህ ትልቅ ስፍራ!! እኔ ማደር እልችል ስምህን ሳልጠራ እንተ በኢወቴ እለህ ትልቅ ስፍራ ጌታ እየሱሰ እባታችን🙌🏽 እውነት ነው ሊሊሿ ተባረኪ much love ❤️❤️❤️❤️

  • @gemechugech
    @gemechugech Před rokem +7

    ረጅም ዕድሜ እስከ ህይወት ፍፃሜሽ በጌታ ቤት ተመኘሁትን ሊሊዬ!

  • @jesusismylife68
    @jesusismylife68 Před 4 lety +9

    ያለ ምንም ነገር መኖር እችላለው ደግሞም አይደንቀኝም ኖሬ አይቼዋለው ግን ያላንተ ጌታ እንዴት እኖራለው ግን ያላንተ ኢየሱስ እንዴት እኖራለው 😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭

  • @jjjman201
    @jjjman201 Před 6 měsíci +3

    ብሰማው ብሰማው ያማልሰለች መዝሙር:: ተባረክ ሊሊ❤

  • @azmachkebede518
    @azmachkebede518 Před 4 lety +7

    ማንም ሊፈታው አይችልም ነገሬን ሲገርም ያለምንም ነገር ኖሬ አይቻለሁ ግን ያላንተ እንዴት እኖራለሁ!!!!!!!!!!!! ደጋግሜ ብሰማው አዲስ ነው ሊሊ ጌታ ይባርክሽ

  • @eyaelamekonnen4990
    @eyaelamekonnen4990 Před 4 lety +51

    Omg I can’t stop listening..
    እኔ መኖር አልችል ስምህን ሳልጠራ አንተ በህይወቴ አለህ ትልቅ ስፍራ

  • @amenashko0988
    @amenashko0988 Před 3 lety +1

    Effoy liliye zemensh yirzem ahunim yalemekekel yisrabish geta

  • @Petyordi
    @Petyordi Před 4 lety +16

    ሊሊየ ጌታ ይባርክሽ በረከታችን ነሽ...... ዝማሬውችሽ ሁሌም ተሰምትው ኣይጠገቡም... ወደ ህልውናው ይወስዱናል ዘመንሽ ይለምልም

  • @GUTI318
    @GUTI318 Před 2 lety +5

    Tears rolling on my face when I heard this song even though am orthodox

  • @lemimelese8878
    @lemimelese8878 Před 4 lety +2

    Liliye .....siwedish
    be tsegaw lay tsegaw yibzalish

  • @teshometurga2587
    @teshometurga2587 Před 8 měsíci +1

    አባቴ ኢየሱስ ዘመንሽን ይባርክ

  • @berhanegmedhin3621
    @berhanegmedhin3621 Před 5 měsíci +1

    Lord,I am bringing my cases to you.Show me the way out of this mess Lord!Amen!

  • @abenezerlegese
    @abenezerlegese Před 2 lety +21

    Lilye, thank you dear, Blessings!
    Amen 🙏🏻 , am really in love with song, thrilling with the Spirit!!

  • @yosefbezaiet3236
    @yosefbezaiet3236 Před rokem +1

    Ehtachen liliye zemnech yebarek yebarek yebarek ❤❤❤

  • @prophetyosefchurchofjesusc5840

    Who ever is clicking the dislike button. Jesus Loves you .and we the children’s of Jesus loves you.

    • @afrohuman7022
      @afrohuman7022 Před 4 lety +1

      Bless you, its wisdomful reaction to magnetis wrong doers to the true light and love of Christ Our lord!!

    • @seyifufufa2382
      @seyifufufa2382 Před 4 lety +1

      I love it. listen to this that I found on CZcams buy Seyifu Fufa
      czcams.com/video/dQIJFgdYdEA/video.html

  • @lidyamezgebetibeb890
    @lidyamezgebetibeb890 Před 4 lety +56

    ሊሊዬ መዝሙሮችሽ ሁሉ ወደ ጌታ ሚጠቁሙ ፍቅርን የሚያቀጣጥሉ ናቸው... ጌታ እየሱስ ይብዛልሽ

  • @genetzeberga1269
    @genetzeberga1269 Před 2 lety +1

    ሊሊዬ ጌታ ፀጋው ያበዛልሸ ምርጥ ለጌታ አንደኛነሸ ለኛ ደግሞ ተምሳሌታችን ነሸ አንቺ አለመውደድ አይቻልም

  • @tesfahuntarekegn4171
    @tesfahuntarekegn4171 Před 3 lety +2

    ሊሊዬ ፀጋ ይብዛልሽ

  • @yohanajesus2023
    @yohanajesus2023 Před 4 lety +11

    ከበረከት ሁሉ በረከት ለተፈጠሩበት አላማ መኖር ነው የተወደድሸ ነሽ የተባረክሽ ። በቀረው ዘመንሽ የክርስቶስ ህይወት እና ጸጋ ይብዛልሽ!!!!!!

  • @TgTg-ep9lz
    @TgTg-ep9lz Před 9 měsíci +1

    እኔ መዋል አልችልም ስምህን ሳልጠራ አንተ በህይወቴ አለህ ትልቅ ስፍራ❤

  • @biniamteklu6396
    @biniamteklu6396 Před 3 lety +1

    ሊሊዬ ታድለሽ ዘመንሽ ሙሉ ጌታን ስታገለግይው ኖርሽ እኔ ግን እኔ ግን እኔ ግን? ስላንቺ እሱ ይመስገና

  • @firehiwotasefa3448
    @firehiwotasefa3448 Před 4 lety +9

    ጌታ ሆይ እውነት አንተ ጋር እመጣለሁ
    ነገሬን የምትፈታው አንተ ነህ
    ሊሊዬ ጌታ ዘመንሽን ይባርክ

  • @haymanotaddisu2266
    @haymanotaddisu2266 Před rokem +3

    እኔ መዋል አልችል ስምህን ሳልጠራ
    አንተ በህይወቴ አለህ ትልቅ ስፍራ #ኢየሱስ❤

  • @osi9998
    @osi9998 Před 4 lety +61

    ያለምንም ነገር መኖር እችላለው
    ደግሞም ኣይደንቀኝም ኖሬ ኣይቺዋለው
    ግን ያላንተ እየሱስ እንዴት እኖራለው
    ግን ያላንተ እየሱስ እንዴት እኖራለው
    ግን ያላንተ እየሱስ እንዴት እኖራለው

    • @livingtoinspire5678
      @livingtoinspire5678 Před 4 lety +1

      Osanna amen

    • @jamboejigu3337
      @jamboejigu3337 Před 4 lety +1

      ከዓመታት በፊት በመነፈስዐቅዱስ ኀይል እንዴት ጉልበታችን ተራራውን አልፎ በአምልኮ ዝማሪሽ ተነቃቅተን እንደሰፍፍን ወደጌታ አንረሳውም ተባረኪ ሊሊ የማውቅሽ ያኸል ይሰማኛል። አምላክሽ አምላኬ ነውና ።እንገናኛለን በሰማይ።

    • @jesusislord9447
      @jesusislord9447 Před 3 lety

      Hei OSI are you Bisrat?

    • @moloisimafa509
      @moloisimafa509 Před 3 lety

      ያለምንም ነገረ መኖር እችላለዉ

  • @solomontekolla9749
    @solomontekolla9749 Před 4 lety +2

    Bederaten lemikefel talak geta betsteshi mekelite hule gezey wegebeshin tateki tebareki 🙏

  • @user-ok8nb2jh2e
    @user-ok8nb2jh2e Před 4 lety +4

    እንኳን ያንተ ልጅ ሆንኩኝ በዚህ ባስጨናቂ ዘመን ያላንተ እየሱስ እንዴት እሁን ነበር ?

  • @leulnigusie3100
    @leulnigusie3100 Před 3 lety +1

    ለክፋዎችም ቸር ከሀጢያተኛ ወዳጅ
    ከጥፋት ሚመልስ ለሰዎች የሚበጅ
    ተማረኪ ሊሊዬ ፈጣሪ አብዝት ይባርክሽ

  • @user-zk8ko4cn5x
    @user-zk8ko4cn5x Před 2 lety +3

    እኔ መኖር አልችል ስምህን ሳልጠራ አንተ በህይወቴ አለህ ትልቅ ስፍራ እኔ መዋል አልችል እኔ ማደር አልችል የለምንም ነገር መኖር እችለለው ደግሞም አይደንቀኝም ኖሬ አይቼዋለው ግን የላንተ ጌታ እንዴት እኖራለው ግን የላንተ ኢየሱስ❤️🙇‍♀️

  • @metasebiatesfaye7636
    @metasebiatesfaye7636 Před 3 lety +2

    yene mar Tebarekilgn siwedish eko

  • @meseretzekarias5218
    @meseretzekarias5218 Před 4 lety +1

    Lily bebzu tebareki

  • @ghirmaymichael7156
    @ghirmaymichael7156 Před 4 lety +1

    ምን ኣይነት ዘማሪ ነሽ ሰው እኮ ጸጋ ቢበዛለትም እንደዛ መሆን ከኣቀን ያለፈ ሆኖ ተሰማኝ ተባረኪ ቢልሽም ምን ይጠቅማል የተባረክሽ ነሺ

  • @hagigemechu8833
    @hagigemechu8833 Před 4 lety +10

    እንተው ነህ የፈጠርከን ችግር ካለ ወደ አንተን እንጠይቃለን

  • @theblessedsarahchaka1233
    @theblessedsarahchaka1233 Před 3 lety +7

    የውበት መደምደሜያ የሁነው እየሱስ ይባረክ: አንቼን ለራሱ አድርጉ ለኛ የሰጠን ጌታ ይባረክ:: ሊሊሻ ቆንጆ አንቼ ብርክ ነሽ: Remain blessed!!! ❤️❤️

  • @meseretdemeke3048
    @meseretdemeke3048 Před 4 lety +26

    ሊሊዬ ብሩክ ነሽ ፀጋ ይብዛልሽ የድሮ መዝሙሮችሽን እንዲህ አድርገሽ ብታቀርቢልን ተባረኪ

    • @kidanuwordofa7805
      @kidanuwordofa7805 Před 2 lety +1

      Geta tsega yabezalish anchi yetebareksh nesh yemegemeria kaset kawetashibet ken gemro mezmurshin semchalew hulum getan yebelay adrigesh bemezemrsh geta abzto abzto ybarki elalew enquwan le50gnw yelidet bealish aderesesh keriw zemensh getan bemagelgel ylek Amen !!!

    • @misrakgeberehana6549
      @misrakgeberehana6549 Před 2 lety

      czcams.com/video/z0R3Rx1ZUz8/video.html&start_radio=1

  • @danieladmassu4128
    @danieladmassu4128 Před rokem

    እርሱን ኢየሱሴን መተርክ እንዴት መታደል እና ድንቅ ፅጋ ነው ትውልድን የተሻገር ድንቅ መልክት በዜማ ውስጥ
    ይህ መዝሙር በወጣ ግዜ ያን የመከራ ዘመን ስንቅ እና ትጥቅ ሆኖኝ እስካሁን እንደ አዲስ ባለመስልቸት ወደ ህልውናው ያስገባኛል በርግጥም እህቴ ሊሊ የተቀበልሽው በእውነተኛው መንፈስ ስለሆነ ወደእርሱ ህልውና ይወስዳል
    ፅጋው ይብዛልሽ አሁንም

  • @byfaithjc
    @byfaithjc Před 4 lety +3

    የጌታ ፀጋ የበዛልሽ። ብሩክ ሁኚ። ❤

  • @ruthgetachew8188
    @ruthgetachew8188 Před 4 lety +1

    Tebarekii tebarkeshhhh kererr

  • @natiman3009
    @natiman3009 Před 3 lety +1

    Betemm mewedesh makebersh zemari nesh geta eyesus abezeto yebarekesh bachii mezemure betemm bezuu gizi tebarekibetalew tqs liliy

  • @Hassan-ry4ye
    @Hassan-ry4ye Před 4 lety +1

    Geta abizeto yibarkesh ehitachen Lily kiber legeta yhun hiwet yale Geta ayihonem

  • @yosefassefahassiso6370
    @yosefassefahassiso6370 Před 4 lety +2

    ሊሊዬ እኔ ቃለት የለኝም በእውነት ቡዙ ዘማነት በዝመሬዎችሽ ታፂናናን ይኸው ዛሬም ተበረክን ዘማንሽ ይበረክ!!

  • @teddyminale2020
    @teddyminale2020 Před 3 lety +38

    I love to hear your songs as it's soaked with spirit! 20 years ago, it's your Vol #1 song which draw me close to and introduced with Jesus Christ.

  • @beletechkebeda2581
    @beletechkebeda2581 Před 3 lety +1

    አሜን አሜን አሜን አባ ተባረክ

  • @user-zx2fo6kp2i
    @user-zx2fo6kp2i Před 4 lety +22

    ሊሊዪ ባንቺ መዝሙር ሁሌም እንደተባረኩኝ ነው የኔ ቆንጆ ዘመንሽ ይለምልም እህቴ

  • @hargumesfen7161
    @hargumesfen7161 Před 3 lety +5

    ጌታ ከዚሕ በላይ ያብዛልሽ ሊሊየ የኢየሱስ ልጅ ተባረኪ

  • @AydaAbraham
    @AydaAbraham Před 4 lety +64

    So beautiful Liliye! Bereketachin! 🧡

    • @seyifufufa2382
      @seyifufufa2382 Před 4 lety

      Of course Lilie is the best. I just found this new artist check him out.
      czcams.com/video/dQIJFgdYdEA/video.html

    • @Miki_y85
      @Miki_y85 Před 4 lety

      Yemer ayda nesh

    • @saronhaile5178
      @saronhaile5178 Před 4 lety +1

      For real eko, Lily is too much blessed. more anointing upon you lili

    • @afrohuman7022
      @afrohuman7022 Před 4 lety +2

      Aydiye Anchim tebareki. Lili lyu nech anchim yesua teketlesh eyeberetash wetshal. Geta abzto ybarksh

    • @ruhamafikru1387
      @ruhamafikru1387 Před 3 lety +1

      Ayda

  • @eyerusalemdaniel2677
    @eyerusalemdaniel2677 Před 4 lety +4

    ማንም የለኝ ከኢየሱስ በላይ
    ስመላለስ በዚህ ምድር ላይ
    ነብሱን ለእኔ ቤዛ ያረገው
    እውነተኛ ወዳጄ እርሱ ነው

    • @saramitku3571
      @saramitku3571 Před 3 lety

      ማንም የለኝከኢየሱሰበላደደሰመለሰበዚህ

  • @achamyeleshtesfaye1852
    @achamyeleshtesfaye1852 Před 2 lety +2

    ምንአባቴ ላርግሽ ጌታ እየሱስ በብዙ ይባርክሽ በነገር ሁሉ ተባረኪ አሜን!!!

  • @ruthhailu9262
    @ruthhailu9262 Před 3 lety +1

    Amen Amen Lord

  • @springsalmaz1043
    @springsalmaz1043 Před 4 lety +16

    ስለ ድንቅ ስጦታህ ጌታ ሆይ ተመስገን I come to in Christ the time of your first song you remind me thanks to God

  • @mercyghebre7963
    @mercyghebre7963 Před 4 lety +1

    ሊሊየ በሩክ ነሺ እንወድሻለን ሰጦታችን ነሺ

  • @belayneshbekele1254
    @belayneshbekele1254 Před 2 lety +2

    you are the assets of believers.

  • @yamsrwarku5250
    @yamsrwarku5250 Před 4 lety +8

    ሊሊዬ የዘመናችን ድንቅ ዘማሪ የእግዚአብሔር ሴት ፣ዝማሬዎችስ አይሰለቹ ፣ዝማሬዎችሽ ውበት ብቻ ሳይሆን ፣ወደ እግዚአብሔር ጥልቅ መንፈስ ያስገባል ።you are blessed

  • @emmanuelgodwithus8861
    @emmanuelgodwithus8861 Před 2 lety +4

    At some point i found my self a little angry at my life & God & descided to stay silent for a while ,but i realized that without him i cannot live a single minute .the last verses of this song touched me a lot .አኔ መኖር ኣልችልም ስምህን ሳልጥራ ኣንተ በሂወቴ ኣለ ትልቅ ስፍራ። eventhough we try to separate from him he always keeps loving & caring for us .Gbu as u pass through comment

  • @teshalegetachew3227
    @teshalegetachew3227 Před 4 lety +1

    Tebareki liliye

  • @temesgenalemayehu3274
    @temesgenalemayehu3274 Před 4 lety +2

    Degemkut degagemkut, minm liwetalgn alchalem yhe mezmur ke wuste,,,, enwedshalen

  • @sisayabebe9701
    @sisayabebe9701 Před 3 lety +1

    እኔ መኖር አልችል ስምህን ሳልጠራ አንተ በህይወቴ አለህ ትልቅ ስፍራ

  • @kebrarawtube
    @kebrarawtube Před 4 lety +5

    ሊሊዬ አንቺን በዚህ ዘመን በረከት አድርጎ የሰጠን አምላካችን ይባረክ። በመዝሙሮችሽ ወደ እግዚአብሔር ተመልሰናል፤ ልባችን ተፅናንቷል፣.... ጌታ ኢየሱስ ዘመንሽን ይባርከው። በጣጣጣጣምምምምም ነው የምወድሽ!!!!

  • @hamieshetu4270
    @hamieshetu4270 Před 4 lety +2

    ማንም የለም ከኢየሱስ በላይ ነፈፍሱን ለእኔ ቤዛ ያረገው ጌታዪ ተባረኪ

  • @melakunegash7556
    @melakunegash7556 Před 4 lety +2

    ጌታ ኢየሱስ ከዚህም በላይ ይባርክሽ!

  • @garsametube324
    @garsametube324 Před 3 lety +2

    ድንቅ ግንዛቤ የተሞላበት ዝማሬ!

  • @selamyerga92
    @selamyerga92 Před 3 lety +1

    Amen amen 🙏 🙏🙏❤️❤️❤️

  • @yehieshet2693
    @yehieshet2693 Před 3 lety +3

    ሊሊዬ የኔ ውድ እንዴት እንደምወድሽ እኮ መዝሙሮችሽን ስሠማማ ህይወት ነው ሚዘሩብኝ ጌታን ባንቺ ውስጥ አይቻለዉ ተባረኪልኝ ውድድድ

  • @melakukebede9628
    @melakukebede9628 Před 3 lety +1

    ኀይለስላሴን ተቃወምኩ ነጻነት የለም ደርግን ተቃወምኩ ነጻነት የለም ኢሀደግን ተቃወምኩ ነጻነት የለም ጌታ እየሱስ እርዳኝ ጊዜዉ ክፉ ነው።

  • @hanabekele8157
    @hanabekele8157 Před 2 lety +3

    አጥንትን ሰርስሮ የሚገባ መዝሙር ነው። "እኔ መኖር አልችል ስምህን ሣልጠራ አንተ በሂወቴ አለህ ትልቅ ስፍራ።" ተሰምቶ የማይጠገብ መዝሙር ነው። "ያለምንም ነገር መኖር እችላለሁ ግን ያላንተ ጌታ እንዴት እኖራለሁ።" ሊሊዬ ስለአንቺ ጌታን ባረኩ ተባረኪልኝ።

  • @selambegeta6250
    @selambegeta6250 Před 4 lety +1

    Tebareki hulem zemre

  • @danielolani3063
    @danielolani3063 Před 4 lety +1

    እሰይ ልልዬ

  • @fkkr2138
    @fkkr2138 Před rokem +1

    ከኢየሱስ የሚበልጥ ለእኔ ማንም የለም

  • @tesfalemdemissie5135
    @tesfalemdemissie5135 Před 3 lety +1

    ያለ ምንም ነገር መኖር እችላለሁ
    ደሞም አይደንቀኝም ኖሬ አይቼዋለሁ
    ግን ያለ አንተ ኢየሱስ እንዴት እኖራለሁ 🙏🙏🙏

  • @ruhamafikru1387
    @ruhamafikru1387 Před 3 lety +1

    Ene mewal alchil simihin saltera EYESUS YE EGZIABHER LIJ.

  • @user-fn9sv5nd1q
    @user-fn9sv5nd1q Před 4 lety +3

    ማንም የለኝ ከኢየሱስ በላይ
    ሰመላለሰ በዚች ምድር ላይ
    ነፍሱን ለኔ ቤዛ ያረገው
    እውነተኛ ወዳጄ ኢየሱስ ነው።
    ውዷ እህቴ ዝማሬዎችሸ የሚባርኩ ከእግዚአብሔር ጋር ልባችንን የሚያገናኝ መልካም ዝማሬዎች
    ተባረኪ ለትውልድ አሁንም ትረፊ።

  • @helenadonai1572
    @helenadonai1572 Před 4 lety +1

    Ante behiwete aleh tilk sfra ( ante be hiwete 1ga nehna ) tsemrebetalehu. Tebarki lil

  • @birtukanargamo1552
    @birtukanargamo1552 Před 4 lety +1

    liliye tebareki betam ewedshalehu! betam tebarikebetalehu

  • @sofoniyasfedesa8812
    @sofoniyasfedesa8812 Před 2 lety +4

    ❤❤❤😍❤❤❤❤❤ i have no word lileye ከአፍሽ የሚወጣው ሁሉ ሰዉ ይባርካል!! ተባረኪ!🙏🙏

  • @ruthh620
    @ruthh620 Před 4 lety +3

    Geta yesus smu ybarek more blessings my beloved sister Lily

  • @tesemashtefera5471
    @tesemashtefera5471 Před 4 lety +1

    AMEN YEGETA SET,TEBAREKILEGNE!

  • @furtunakahesaye1374
    @furtunakahesaye1374 Před 4 lety +1

    ሊሊዬ ስላንቺ እግዚአብሔርን እባርካለሁ

  • @pphonetastic6816
    @pphonetastic6816 Před 4 lety +1

    አንች ውድ ህት ጌታ ዘመነሽ ይብርክሽ

  • @mylord46
    @mylord46 Před 2 lety +1

    ድንቅ የእግዚአብሔር ሴት ነሽ ከዚህ በላይ ተባረኪልኝ!!!!

  • @user-yo6gn5nv2l
    @user-yo6gn5nv2l Před 3 lety +1

    Love uuu liliye🇪🇷🇪🇷🇪🇷🇪🇷🇪🇷

  • @user-zs3pr4hq7k
    @user-zs3pr4hq7k Před 4 lety +1

    amen amen

  • @ethopiamerciyagatalijietho1229

    አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን ተባርኪልኝ ሊሊዬ ውዴ

  • @yenealemendiriastolo587
    @yenealemendiriastolo587 Před 4 lety +6

    አንደኛዬ ሊሊዬ ብርክርክ በይልኝ ማምለክና መዘመር ካልቀረ እንዳንች ነው እንጂ

  • @brhaneatsbahaabarha3079
    @brhaneatsbahaabarha3079 Před 4 lety +2

    በእውነት ቃላት አጠረኝ በቃ ብሩክ ሁኚ ዘመንሽ ይባረ ።በቃ ማንም የለም ከኢየሱስ በላይ ።መዝምሮችሽን ሁሌ ሲከፋኝ እፅናናባቸዎለው

  • @betelhimseyoum3716
    @betelhimseyoum3716 Před 3 lety +2

    ማንም የለኝ ከኢየሱስ በላይ ። የእግዚአብሔር ልጅ ይባረክ❤❤❤

  • @abebadamene5172
    @abebadamene5172 Před rokem +1

    Egzaber yebarksh lilye yewnt yalehubet ngr yemtnegregn nw yewnet ended egizaber Yale Manm yelem bless you

  • @nigestzewdie6729
    @nigestzewdie6729 Před 4 lety +16

    እኔ መዋል አልችል ስምህን ሳልጠራ
    አንተ በህይወቴ አለህ ትልቅ ስፍራ !!!
    ተባረኪ ሊሊዬ በቃ አንቺ ዝም ብለሽ ዘምሪ እሺ ውድድ፡፡

  • @helinaeblu727
    @helinaeblu727 Před 3 lety +3

    Wow the amazing song lili
    ፍቅሩ ተፈትኖ ወርቅ ሆኖ ተገኝተዋል......