የዮሐንስ ወንጌል ክፍል 2 | "በማመን የሚገኝ ሕይወት"

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 22. 08. 2024
  • የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ አንድ የአዲስ ኪዳን ዘፍጥረት ምዕራፍ አንድ ነው ብንል ማጋነን አይሆንም። በመጀመሪያ (ዕብ. ቤሬሺት፣ ግሪክ፥ አርኬ)፣ ቃል (ዕብ. ቃል፣ ግሪክ፥ ሎጎስ)፣ እግዚአብሔር (ግሪክ፥ ቴዎስ)፣ ብርሃን (ግሪክ፥ ፎስ)፣ ጨለማ (ግሪክ፥ ስኮቲያ) የሚሉት ቃላት ሁለቱም ውስጥ ይገኛሉ። ይህ ክፍል ሥጋ የሆነውን ቃል እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘልዓለማዊ፣ ፈጣሪ፣ አምላክ መሆኑን በግልጽ ያሳየናል። ቃል (ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ) ከእግዚአብሔር ጋር፣ ከፍጥረት ጋር እንዲሁም ከሰው ልጆች ጋር ያለውን ተዛምዶ በዮሐ. 1፥1-5 ባለው ክፍል እናያለን።
    መልካም የትምህርት ጊዜ።

Komentáře • 102

  • @habatamhabatam8769
    @habatamhabatam8769 Před rokem +11

    ትምህርቶችን ሁሌ በጉጉት ነው የምጠብቀው ያሬዶ የሚርዳህን እግዚአብሔርን አመስግናለሁ አሁንም ጸጋውን ያብዛልህ ።

  • @ELSHADDAI4443
    @ELSHADDAI4443 Před rokem +12

    ወንጌላዊ ያሬድ፡ በጉጉት ስንጠብቅሕ ነበረ። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ይባርክህ።

  • @hanatesseme9170
    @hanatesseme9170 Před rokem

    የጌታ ስም የተባረከ ይሁን ዘመንህ ይለምልም ያሬዶ

  • @yaredtilahun6536
    @yaredtilahun6536 Před rokem +7

    የአስተያየት መስጫው በሥህተት ተዘግቶ ስለነበር ይቅርታ እንጠይቃለን:: ጥያቄዎቻችሁንና ገንቢ አስተያየቶቻችሁን መስጠት ትችላላችሁ::

    • @PeterJesuit
      @PeterJesuit Před 8 měsíci

      ሰላም ወንጌላዊ ያሬድ በአንድ ወቅት ፖለቲካ ላይ በያዝከው አስተሳሰብ ጠቃሚ ትምህርቶችህን እንዳልከተል እንቅፋት ሆነብኝ አገልጋይ የትኛውንም ፖለቲካዊ አቆም ባይዝ መልካም ነበር!!!

  • @mahletbetemariam1264
    @mahletbetemariam1264 Před rokem

    ወንጌላዊ ያሬድ ጌታ ይባርክህ 🙏

  • @yifatdenbarga7781
    @yifatdenbarga7781 Před 8 měsíci

    ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ይባርክህ።

  • @tagesechtesema6195
    @tagesechtesema6195 Před rokem

    ሰላም ላንተ ይሁን የተወደድክ ወንጌላዊ ያሬድ ከእግዚአብሔር ዘንድ አንተ ለትውልድ በረከት ነህ እንዴት አድርገ በጌታ ፍቅር እንደምወድህ ጌታ ያውቃል እግዚአብሔር ቀሪው ዘመንክን ይባርክ ቃሉን ስታስተምር ስተነትን ልቤ ውስጥ እንደምፈስ ዘይት ነው በጥቅም ቃሉ ይገባኛል መንፈስ ቅዱስ በውስጤ ያትመዋል የማይረሳ ትምህርት ነው በሰማሁኝ ቁጥር እባርክበታለሁ እግዚአብሔር አምላክ የተመሰገነ ይሁን

  • @lemlemlabite1284
    @lemlemlabite1284 Před rokem

    ድንቅ ትምህርት ሳምንቱ እስኪደርስ እጓጓለሁ

  • @habatamhabatam8769
    @habatamhabatam8769 Před rokem +1

    ይህ ትምህርት ወደ ብዙ ነገር አስገባኝ
    አዜብ ሃይሉ እንዲህ ብላ ዘምራ ነበር 👇
    ሳይሆን ገና ስማይ ሳይሆን ገና ምድር
    መጀመሪያ እግዚአብሔር ነበር
    በላይና በታች የሚባል ሳይኖር
    አስቀድሞ እግዚአብሔር ነበር
    ሳትታይ ጨረቃ ሳይበራይ ፅሃይ
    እግዚአብሔር አምላክ ቀድሞ አልበርወይ
    ጠዋትና ማታ ተብሎ ሳይለይ
    በስልጣን በክብር እርሱ አልነበርወይ
    በመጀመሪያ እግዚአብሔር በመጀመሪያ
    በመጀመሪያ የኔ አምላክ በመጀመሪያ
    ከሁሉ በፊት እግዚአብሔር ከሁሉ በላይ ከሁሉ በፊት ከሁሉ በላይ ነበር እግዚአብሔር💚

  • @mululemma7409
    @mululemma7409 Před rokem

    Amen. Amen, hallelujah

  • @tamirumathewos4032
    @tamirumathewos4032 Před rokem +2

    ትክክለኛ ወንጌል ይሄ ነዉ እኔ በማወቅ ማደግ እንድችል እርዳኝ ጌታ ሆይ

  • @destaneshbekelebalcha6237

    ጌታ አገልግሎትህንና ቤተሰብህን በደሙ ይሸፍን እንወድሃለን የህይወት ቃል ስላስተማርከን❤

  • @tigestermayse8641
    @tigestermayse8641 Před rokem

    Amen Amen Amen ✅ 🙌 👏🏻 ❤❤❤🎉🎉

  • @elsadaniel2704
    @elsadaniel2704 Před rokem

    እግዚአብሔር ይባርክህ: ድንቅ ትምህርት

  • @tsenuashna3685
    @tsenuashna3685 Před 10 měsíci

    በረሺት" በመጀመሪያ።
    እግዚአብሔር ም አለ. ቃል ነበር wow

  • @Jaywalker851
    @Jaywalker851 Před rokem

    እክሊሉ ላይ ያለ መንፈስ የእግዚአብሔር መንፈስ እንደሌለው ጎልቶ ይታያል ምክንያቱ ስዓቱን ጨርሶ በአማን ግዜ ጸጥ ብሎ መስማት ያቅተዋል ያፌዛል ይሳደባል ውስጡ ይረበሻል አስርየ ጺሙን ይደባብሳል ረግቶ መስማት አልቻለም

  • @Eagle1503
    @Eagle1503 Před rokem

    Amen praise God

  • @Eagle1503
    @Eagle1503 Před rokem

    Amen 🙏

  • @segidbrhane2738
    @segidbrhane2738 Před rokem

    የሹዋ! ኢያሱ! !ኢየሱስ! (በተለያዩ ቋንቋዎች)

  • @aklilu.g7023
    @aklilu.g7023 Před rokem +4

    What an exposition!! I don't have enough words to express the magnitude of the Holy spirit's illumination with you, our beloved brother Yaredo. The most sound exposition i have ever seen! keep up the good work!!

  • @hermalacoma5555
    @hermalacoma5555 Před rokem

    ወንድም ያሬድት ተባረክ ትምህሩትም አጭር ማድረግህ ጥሩነው ሳይበዛ በቀላሉ ለመረዳት ይጠቅመናል ተባረክ ብሩክ ሁን

  • @AbebechGebrie
    @AbebechGebrie Před měsícem

    አሜን አሜን ጌታ አብዝቶ ይባርክህ ወንድም ❤❤

  • @Ronaldothegoat1234football

    Amen wendme bertalen chelemaw yegefef Egziabheren mawek yebzalen!❤❤❤❤❤❤biruk neh

    • @ruth1303
      @ruth1303 Před rokem

      አምላኬ እንዳንተ ያሉ ወንድሞችን ያብዛልን!

  • @jesuschrist15111
    @jesuschrist15111 Před rokem +1

    ምሕረትና ጸጋ፣ ሰላምና ፍቅር ይብዛልን፤ ሃሌ ሉያ አሜን።✞❤
    ✞ክብር ለእግዚአብሔር አብ ክብር ለእግዚአብሔር ወልድ ክብር ለእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ይሁን አሜን።✟❤
    “ሁሉም ከእርሱ፣ በእርሱ፣ ለእርሱ ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።” - ሮሜ 11፥36 (አዲሱ መ.ት)

  • @tamirumehiretutesema700

    አቤት! አቤት! የሚገርም ትምህርት።
    እየሱስን አውቀነው እንድናሳውቀው
    ስለምታስታውቀን ፣የቃሉ መገለጥ ይጨመርልህ!

  • @Speckle_mydog
    @Speckle_mydog Před měsícem

    ያሬድ ተባርክ ሜጋሉኔ

  • @segidbrhane2738
    @segidbrhane2738 Před rokem

    ይህን ኢየሱስን ማወቅ ህይወት እና ደህንነት ነው!

  • @abigiyafikr
    @abigiyafikr Před rokem

    አምላክ እግዚአብሔር ይባርክ

  • @natnaeltecha5543
    @natnaeltecha5543 Před 10 měsíci

    Amen! God bless you yared

  • @birukwolde7850
    @birukwolde7850 Před rokem +1

    Wendim yared sile agelgilotih geta yibarkih kante bizu eyetemarku new

  • @meselederibe7823
    @meselederibe7823 Před rokem

    በእየሱስ ክርስቶስ ስም ዘመንክ በፍሬ የተሞላ ይሁን ተባረክ

  • @salameskyes7240
    @salameskyes7240 Před rokem

    አሜን ጌታ የልብ ብራኔን ያብራልኝ የመረዳትን ጥበብ ያብዛልኝ❤

  • @mekdesmekuria4207
    @mekdesmekuria4207 Před rokem

    ተባረክ ወንድማችን ያሬድ።

  • @saratizazu9297
    @saratizazu9297 Před rokem

    በዘላለም ውስጥ የሚኖር ድንቅ አምላክ አለን። እኛን ብሎ ሰው ሆኖ መምጣቱ ደግሞ ከመደነቅም በላይ ሆኖብናል። አንተም: ያንተ የሆነውም ሁሉ ይባረክ።

  • @martatenker5973
    @martatenker5973 Před rokem

    ማስታወሻ ይዘን ነው ምንማረው ተባረክልኝ

  • @tigestermayse8641
    @tigestermayse8641 Před rokem

    God bless you 😘 Thanks so much ✅ 🤝🏽 Lorde Best 😘 ✅ 🤝🏽 👌 👍🏻 😍 😘 ✅ 🤝🏽 👌 👍🏻 😍 😘 ✅ 🤝🏽 👌 👍🏻 😍 😘 ✅ ❤❤🎉

  • @almazabebayehu9078
    @almazabebayehu9078 Před rokem

    Tsegaw ybzalk tebarekk

  • @emudesta4997
    @emudesta4997 Před rokem +1

    ተባረክ ወንድሜ ያሬድ.የ ጌታ ፀጋ ይብዛልህ 🙏

  • @neguseberi3013
    @neguseberi3013 Před rokem +1

    ተባረክ ከነቤተሰብክ ወንድማችን ያሬድ ፀጋውን ከዚህም የበለጠ ያብዛልህ

  • @petertefaye3446
    @petertefaye3446 Před rokem

    ተባረክ

  • @bethlehemarega2392
    @bethlehemarega2392 Před rokem

    ወንጌላዊ ያሬድ፣ በአንተ ትምህርት ብዙ ተጠቅሜአለሁ። አሁን ደግሞ በዩሐንስ ወንጌል በምጣትህ እጅግ ደስ ብሎኛል። ጌታ ይባርክህ።

  • @segidbrhane2738
    @segidbrhane2738 Před rokem

    በመጀመሪያው- ቃል ነበረ!
    በመጀመሪያ የሚለው ቃል- ዘመንን የዘላለምን ቀመር ነው የሚነግረን - ጊዜና ቦታ ሳይኖር ያኔ ግዜ ነው የዘለአለም ዘመን የሚባለው- መለኪያ ግዜ፡አልነበረም! ቃል በመጀምሪያ ነበር ሲል ከፍጥረት በፊት በዛ ዘለአለም በሚባለው፡ዘመን እንደነበረ ህልውና እንደነበረው ነው ያስቀመጠው!
    ነበር የሚለው ቃል በዚህ ዓውድ ይኖር ነበር ማለት ሲሆን አስቀድሞ ህልውና እንደነበረ ነው የሚያሳየው!

  • @nunununu1694
    @nunununu1694 Před rokem

    We love you yaredyewa! ❤

  • @tamirumathewos4032
    @tamirumathewos4032 Před rokem

    እንኳን ዳህና መጣህልን ወንጌላዊ ያሬድ በትምህርቶህ ብዙ ተጠቅሜያለሁ ከሳዉዝ አፍሪካ ነዉ ከ2015 ጀምሮ ነዉ የሚከታተለው ጌታ ዘመንህን ይባረክ !

  • @zerihufekadu2089
    @zerihufekadu2089 Před rokem

    ይህ ታላቅ እውነት ነው።ጌታ ሆይ ግለጥልን

  • @mihretutagesse6862
    @mihretutagesse6862 Před rokem

    God bless you Evangelist for reveling the word of God. 1. Aen - for “forever” and means eternal,
    2. Ginomai- to become, i.e. to come into existence, begin to be, receive being.

  • @shiferawa.gebretsadik8646

    iGZIABIER Abzto Yeberek

  • @dawitwelde7455
    @dawitwelde7455 Před rokem

    ጌታ አብዝቶ ይባርክህ ያሬዴ …….
    ክርስቶስን ለመግለጥ ያለህ ፍላጎትና የምትገልጥበት ተሰጦህ ሁሌ እንደ አዲስ እንድሰማህ ያደርገኛል በብዙ ተባረክ
    you are our blessing

  • @akaluayele7165
    @akaluayele7165 Před rokem

    ወንጌላዊ ያሬድ ጸጋ የበዛልህ ነህ።በሮሜ ተከታታይ ትምህርትህ ለምጀ ሊሆን ይችላል በጣም አጠረብኝ።ቢሆን ጥልቅ እዉቀት ቀስሜአለሁ።ሁሌ በጉጉት እጠብቅሀለሁ።ከወሎ ደሴ።

  • @selomephoto2757
    @selomephoto2757 Před rokem

    Amen! God bless you my brother Yared

  • @sergutmengistu944
    @sergutmengistu944 Před rokem

    ተባረክልኝ ያሬዱ

  • @mekonnenmoki
    @mekonnenmoki Před rokem

    ጌታ ኢየሱስ ፀጋውን ያብዛልህ ወንጌላዊ ያሬድ

  • @raheltadesse8445
    @raheltadesse8445 Před rokem

    እሱን ማወቅ ሂወት ነው አሜሜሜሜንንንንንንንን ሀሌሉያያያያ!!!!!

  • @zerihunataro2738
    @zerihunataro2738 Před 7 měsíci

    God Bless you more!

  • @dagneshdana
    @dagneshdana Před rokem

    አሜንንንንንንንንንንን ❤❤እግዚአብሔር አምላክ አብዝቶ ይባርክህ❤❤እጅግም የሚፈልገው ትምህርት ነዉ

  • @fitsumgirma8635
    @fitsumgirma8635 Před rokem

    ጌታ ይባርክህ ወንድሜ በ ሮሜ ትምሀርት ነው ያወኩህ በ እግዚአብሔር ቃል እውቀት እንዳድግ ትምህርትህ እየረዳኝ ነው ተባረክልኝ!!!❤❤❤❤🙏🙏🙏🙏

  • @alemayehuhilemariam4780

    Amen 🙌🙌🙌, mesnfase bante hono yenen selaglte, egzahber Abene amsgnalew, ahunem yebezaleh wendem Yared, egnem Hiwotchen Bezeh Ewunate leh yetmasrate yehune

  • @sinduwoldetsadik-tw9dx

    ፀጋዉን ጌታ ያብዛልህ!
    ላልዳኑት ቤተሰቦቻችን ፀልይልን
    እኔ ሁል ጊዜ ስለ ቤተሰቦቼ
    እፀልያለሁ ሁሉም እንዲድኑልኝ
    ምክንያቱም እዉነትም መንገድም ሕይወትም እርሱ ብቻ ነዉና
    ሩጫቸዉ ከንቱ እንዳይሆን ቀን ሳለ ጌታ እንዲያበራላቸዉ ፀሎትህ አይለየን
    ተባረክ!

  • @tigestermayse8641
    @tigestermayse8641 Před rokem

    Amen Amen Amen Egzaibher Selamike Yebizaha shalom shalom shalom ✅ 🙌 👏🏻 😍 ❤ ❤❤❤❤❤❤🎉🎉🎉🎉

  • @amanueltadesseofficial8122

    blessed

  • @Hassan-ry4ye
    @Hassan-ry4ye Před rokem

    ጌታ ይባርክህ ብዙ ተምርያለሁ እግዚአብሔር ይመስገን

  • @merongetu-fh3ec
    @merongetu-fh3ec Před rokem

    እንዴት መታደል ነው ይህንን ዜና መስማት፡፡

  • @Eyesusgetanewu
    @Eyesusgetanewu Před rokem

    ዋዉዉ ድንቅ ነው።
    ፀጋ ይብዛልህ🙏🙏🙏🥰🥰🥰
    ክብር ለናዝሬቱ ለኢየሱስ ይሁን🙏🙏🙏

  • @workinehdana7010
    @workinehdana7010 Před rokem

    We love you so much our blessed evangelist

  • @tsionashna8077
    @tsionashna8077 Před 3 měsíci

    ❤❤❤ so deep

  • @tsenuashna3685
    @tsenuashna3685 Před 10 měsíci

    "Wow በዘፍጥረት ቤሬሼት ቃል ፣ቃል ስጋ ሆነ የመጣው እየሱስ ነው የአብ ቃል በስጋ የመጣው ኢየሱስ ነው፣በስላሴ ውስጥ የወልድ የስራ ድርሻ የማይታየውን አብን መንፈስቅዱስን የመግለፅ ድርሻ ነው ነው። መግለጥ የጀመረው ፍጥረትን ሲፈጥር ነው፣ፍጥረት መገለጥ ነው።"

  • @desta9900
    @desta9900 Před 2 měsíci

    ❤❤❤🙏🙏

  • @sisay62
    @sisay62 Před rokem +1

    I'm just amazed the revelation you are blessed with? Keep it flow, please. I’m highly grateful for what God is doing thru you.

  • @user-hh2nw3ru9f
    @user-hh2nw3ru9f Před rokem

    ወዉ ጌታ ኢየሱስ አብዝቶ ይባራክ ምገርም ትምህርት ነዉ ፀጋ ይብዛልህ🙏🙏🙏🙏🙏🙏

  • @merhawitgebremeskel
    @merhawitgebremeskel Před rokem

    እግዚአብሔር ይባርክህ ፀጋውን ያብዛልህ ወንድሜ ያሬድ።

  • @lidialidu1085
    @lidialidu1085 Před rokem

    ብርክ በል አስተምሮህ በጣም ጥልቅ ነው ፀጋው ይብዛልህ

  • @t.awordwasmadeflesh3379

    ያሬድ ሰላም ላአንተ ይሁን። ትምህርቶችህን እከታተላለሁ ብዙ ጌዜ አስተያየት ፅፌያለው ለምሳሌ የዕብራዊያንን መልክት ስታስተምር አሁንም ይህ የጀመርከው ትምህርት የመፅሐፍ ቅዳስን ሀሳብ መረዳት የሚጠይቅ ነው የህ ማለት አንድ አምላክ እንዳለ ካላወቅን ወይም ካአልተገለጠልን ሀሳብን እንስታለን። መፅሐፍ ቅዳስ ምንግዜም በእግዚአብሔር ማንነት ላይ ያቶከረ ነው ፤ለምሳሌ እግዚአብሔር መንፈስ ነው ሲል የሚታይ የሚዳሰስ አይደለም ማለቱ ነው ስለዚህ በምን ታወቀ ማለት አይቀርም እግዚአብሔር ድምፅ ብቻ ነው ይናገራል እንጂ አይታይም ዘፍጥረት 3፤8 ዘዳግም 4፤12-16 ይህንን የሚመስሉ ብዙ ማስረጃ አለ እግዚአብሔር በድምፅ ወይም በቃሉ እንደሚገለጥ ነው ይህ ማለት አሁን የምታስተምረው ዮሐንስ 1፤1 እግዚአብሔር ቃል ነበር ሲለን ወይም ቃል ሥጋ ሆነ ሲል የሁለት አካል ማለት አይደለም እግዚአብሔር ሰውን ለማዳን ቃሉን ሥጋ አደረጉ ማለት የሚታይ የሚዳሰስ ሆነ ማለት እንጂ ሌላ አካል አባት የሚባል አለ ማለት አይደለም ራሱ አብ ነው ራሱ ወልድም ነው መንፈስ ቅዳስ ነው። ለዚህ ነው 3 አካል ውይም ስላሴ ተብሎ ያልተፃፈው አንድ አካል አለ ነው የሚለን እሱም እግዚአብሔር በሥጋ ተገለጠ 1ጢሞቴወስ 3፤16 ፌልጵስዩስ 2፤6 እግዚአብሔር ሆኖ ሳለ ነገር ግን ሰውን ለማዳን ሰው ሆነ የማዳን ስሙ ኢየሱስ ይባላል እንደዚህ ከተረዳን በስሙ ለሀጢያት ስሪት እንጠመቃለን እንጂ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዳስ ስም አንጠመቅም በመፅሐፍ ቅዳስ ወስጥ ያጠመቀም የለም። እንደዝህ እንደ መፅሀፍ ቅዱስ አሳብ ካልተረዳን አላዳነም ማለት ነው። ስለዚህ ዮሐንስ ወንጌል ስለ አንድ አምላክ ነው የሚናገረው። በፁፌ በማስረዘሚ ይቅርታ

  • @solomongaga108
    @solomongaga108 Před rokem

    ወንድም ዓለም ተባረክ !እየጠፋህ ተከስተህ ሠዓቱን ደግሞ ማሳጠርህ ...

  • @senaittesfamariaem806

    Amen 🙏🏼🙏🏼🙏🏼
    Hallelujah 🙌🏼
    Wow

  • @Wongelyashenfal
    @Wongelyashenfal Před rokem

    Wow!! I am in awe, speechless in tears!!! ልወቅህ አብዝቼ የናዝሬቱ ኢየሱስ፣ አንተን ማወቅ አለማዬ ይሁን።
    Just started to listen to you. ይህ ሙላት ይጨምርልህ ወንጌላዊ! Just wondering if you have any teachings in English??

  • @mekedesmezmur4057
    @mekedesmezmur4057 Před rokem

    Amen 🙏 amen 🙏 God bless you and your family !! I'm very excited.

  • @lalisabadada9508
    @lalisabadada9508 Před rokem

    አሜን... ክብር ለክርስቶስ እየሱስ ...!!!

  • @solomonmesersha4938
    @solomonmesersha4938 Před rokem

    Amen
    Bless you wengelawi yared

  • @sergutmengistu944
    @sergutmengistu944 Před rokem

    እግዚአብሔር ይመስገን ሰላም ለአንተ ይሁን ያሬዱ

  • @godisgoodblessed9357
    @godisgoodblessed9357 Před rokem

    ብርክ በልልን በጌታ የተወደድክ ወንድማችን

  • @yodittekalign8612
    @yodittekalign8612 Před rokem

    Wow! What a wonderful justification. God be with you and continue to bless you.

  • @yirgalemjuses
    @yirgalemjuses Před rokem

    Ameeen getaa yibarkih

  • @zewditugesesse385
    @zewditugesesse385 Před rokem

    እግዚአብሔር አምላክ ይባርክህ ።

  • @lydiagrant5958
    @lydiagrant5958 Před rokem

    Egziabher yakbreh. I have been waiting🙏

  • @Ahlam-qx1ll
    @Ahlam-qx1ll Před měsícem

    ፀጋ ይብዛልክ ክፍል 3 በጉጉት እየጠበቁው ነው

  • @lidialidu1085
    @lidialidu1085 Před rokem +1

    Welcome 🙏

  • @haimanotc.587
    @haimanotc.587 Před rokem

    እንዲገለጥብን መጀመሪያ ሊገለጥልን ይገባል

  • @ediluyohannis9586
    @ediluyohannis9586 Před rokem

    ተባርከሃል

  • @user-zq4jl1gb1e
    @user-zq4jl1gb1e Před rokem

    ጣፋጭ

  • @alemayehulegesse3291
    @alemayehulegesse3291 Před rokem

    ተባረክልን።

  • @tsenuashna3685
    @tsenuashna3685 Před 10 měsíci

    "ያ ሕይወት ራሱ እግዚአብሔር ነው" አሜን

  • @segidbrhane2738
    @segidbrhane2738 Před rokem

    "ኢየሱስ ማን ነው" ይህን ጥያቄ መመለስ መያዝ ነው አላማችን! ካልረገለጠልን ልንገልጠው ካላወቅነው ልናሳውቀው አንችልም! ኢየሱስ ማን መሆኑን ማወቅ ነው አላማችን! የናዝሬቱን ኢየሱስን ማወቅ ህይወት ነውና ኢየሱስን፡ማወቅ ዓላማችን ከሆነ ህይወት ምንድናታ የሚለውን ዓልማችን አርገናል ማለት ነው! ህይወት ደግሞ ተገልጦአል እሱ እየሱስ ነው ይህም፡መጽሃፍ ማን መሆኑን ይነግረናል እኛም መጽሃፉን የማንበባችን ዓላማ ኢየሱስን ማወቅ አድርገን እንጓዛለን!

  • @TajebeEndale
    @TajebeEndale Před rokem

    ኢየሱስ ወደ ምድር ከመምጣቱ በፊት በመጀመሪያ በእግዚአብሔር ዘንድ ይኖር ነበር።

  • @alemtshaygetachew3493

    እግዚአብሔር ይባርክህ በመብራት ችግር ዘግይቼ ነበር አሁን ቶሎ ቶሎ እየተከታተልኩ ነው

  • @biniamalemayehu2324
    @biniamalemayehu2324 Před 2 měsíci

    ቤሬሺት ማለት- በመጀመሪያ እግዝአብሔር አስቀድሞ ....early in the beginning ... ማለት ነው የሚሉ ራባይ መምዕራን አሉ ....

  • @yohannesabrahamofficialcha426

    I’m blessed with you teaching and can you do as well chapter and verses each part pls thank you

  • @samtirful
    @samtirful Před rokem

    ወንጌላዊ ያሬድ በቅድሚያ የተቀበልከውንና የተረዳኸውን ለእግዚአብሔር ህዝብ በፍቅር ለማካፈል የምታደርገውን ትጋት አደንቃለሁ። እግዚአብሔር ይባርክህ። በፌስ ቡክ የውስጥ መስመር ላገኝህ ባለመቻሌ፣ በዮሐንስ ወንጌል ላይ እየሰጠህ ባለው ትምህርት ላይ በሁለት ነገሮች ላይ ጥያቄዎችና አንድ አስተያየት በዚህ ላቀርብ ወደድኩ።
    1. የፍጥረት ጅማሬ በተፈጥሯዊው Universe መፈጠር ብቻ ይጀምራል ብለህ ታምናለህ? የጊዜና የቦታ ፅንሰ ሀሳብ ከተፈጥሯዊው ዓለም ጋር የተያያዘ ቢሆንም ተፈጥሯዊው ዓለም ከመፈጠሩ በፊት የተፈጠረ ነገር የለም?
    2. "በመጀመሪያ" ወይም "ሲጀመር" የሚለው አገላለፅ ዓላማው በቀጥታ የወልድን በዚያ ጊዜ መፈጠር ለማመልከት ባይሆንም በዚያ ጊዜ መኖሩን ለማመልከት ተፈልጎ መሆኑ ግልፅ ነው። ነገር ግን በዚህ አገላለፅ ላይ ብቻ ተመርኩዞ ስለ ወልድ ጅማሬ የሌለው ዘላለማዊነት መተንተን ይቻላል? እንዲያውም ለጥጦ መተርጎም ካስፈለገ ይህ አገላለፅ፣ ይልቅ ለተቃራኒው ትንተና አያመችም?
    3. ወልድ ከእግዚአብሔር ጋር የነበረ መሆኑ የተገለፀበት ሁኔታ ተለጥጦ ወልድ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እንደነበረ ሊተረጎም ወይም ሊተነትን ይችላል? የፀሐፊው ዓላማ እንደዚያ ዓይነት ሀሳብ ማስተላለፍ ነበረ ብለን መደምደም ትክክል ይሆናል?
    4. መንፈስ ቅዱስ ኑባሬ Being ወይም የራሱ ህልውና ያለው Person ሆኖ በአብና በወልድ ውስጥ ሆኖ የሚኖር ነው የሚል ሀሳብ ገልፀሃል። የኑባሬ Being አንዱና ዋና መገለጫው በራሱ independently ህልው መሆኑ ነው። ራሱን ችሎ ህልው ያልሆነ ፈጣሪ ሆነ ተፈጣሪ፣ ኑባሬ Being ነው ማለት ይቻላል?
    5. ለተራ ቁጥር 4 መልስህ አዎ ከሆነ፣ መንፈስ ቅዱስ በአብ ውስጥ የሚኖር ኑባሬ ከሆነ፣ ሁለቱ ለምን በአብ ስም ብቻ ይጠራሉ? በተወሳሳይ በወልድ ስም ብቻ ለምን ይጠራሉ? በሌላ አገላለጽ አብ ማለት አብና መንፈስ ቅዱስ እንጂ አብ ብቻ አይደለም፣ ወልድ ማለት ወልድና መንፈስ ቅዱስ እንጂ ወልድ ብቻ አይደለም:: ስለዚህ አብ ብለን ስንጠራ ወይም ራሱን ሲገልፅ በውስጥ ታዋቂነት አብና መንፈስቅዱስ፤ ወልድ ብለን ስንጠራ ወይም ራሱን ሲገልፅ በውስጥ ታዋቂነት ወልድና መንፈስቅዱስ እንደሆኑ ታሳቢ በማድረግ ነው ማለት ነው? ይህ መፅሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት ነው ብለህ ታምናለህ?
    6. መፅሐፍ ቅዱስ 'ከተፃፈው አትለፍ" የሚል ጥብቅ ማሳሰቢያ ወይም ትዕዛዝ አለው። "ከተፃፈው አትለፍ" ሲል በአፈታትም ሆነ ከቅዱሱ መፅሐፍ ውጪ የሆኑ ፅሑፎችን ሆነ ትውፊትን መሠረት አድርጎ ማስተማርን ይጠቀልላል። ከተፃፈው አልፈን በሔድን መጠን መዘዙ ብዙ ነው።

  • @segidbrhane2738
    @segidbrhane2738 Před rokem

    ዘፍጥረት ላይ አምላክ፡ሲፈጥር "አለ" እያለ የተጠቀሰው ቃል የአብ ቃል እሱ በስጋ የመጣው የናዝሬቱ እየሱስ ነው።፡ለምን ቃል ተባለ? የወልድ፡ስራ አብን፡መግለጥ ስለሆነ ኢየሱስ አብን መግለጥ የጀመረው ፍጥረትን በመፍጠሩ በፍጥረት ውስጥ ነው። ኢየሱስ ያኔም ፍጥረትን ሲፈጥር አባቱን በፍጥረት ውስጥ እየገለጠ ነበር ምክንያቱም ፍጥረት የእግዚያብሄር መገለጥ ነውና!

  • @sabameharisemere960
    @sabameharisemere960 Před rokem

    የሹዋ ማለት እያሱ ስም ማለት ነው እንጂ እየሱስ ማለታቸው አይደለም