ሎዛ ማርያም# አስተርእዮ ማርያም በሎዛ ማርያም!! " በረከቷን የቀመሱ ሁሉ ሎዝዬ ሎዝዬ ሎዝዬ ይላሉ"የማርያምወርቅ ተሻገር/መምህር/

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 27. 01. 2024
  • አስተርእዮ ማርያም
    በሎዛ ማርያም!!!
    ===========
    የጎንደሯ
    አዘዞ ሎዛ ማርያም ማን ናት?
    #ጥንታዊቷ ሎዛ ማርያም በሎዛ ተራራ አናት ላይ በደንገጡሮቿ እንደተከበበች ንግሥት በአረንጓዴ ዛፎች ታጅባና ተገማሽራ በክብር ትታያለች።
    የአዘዞ ሎዛ ማርያም የመጀመሪያ ትክሏ ወይም ምሥረታዋ በ13ኛው ክፍለ ዘመን በዐፄ አምደ ጽዮን ዘመነ መንግሥት ሲሆን በዚያን ጊዜ አገልግሎት ስታገኝበት የቆየች መሆኗን ታሪክ ያስረዳናል። በመሆኑም ሥርዓተ ቅዳሴው ሳይታጎል በአገልግሎት ላይ እያለች ከአዘዞ በግምት 54 k.m ርቀት በምትገኜው ጎርጎራ ከተማ አካባቢ በተነሣው ሰደድ እሳት ቤተክርስቲያኑ በመቃጠሉ በወቅቱ የነበሩ አገልጋይ ካህናት ከቃጠሎ የተረፉትን ንዋያተ ቅዱሳትን ጨምሮ ጽላቱን ይዘው በደቡብ ጎንደር በእብናት ከተማ ዞዝ አምባ ጊዎርጊስ ፍልፍል ቤተክርስቲያን ውስጥ ለብዙ ዓመታት ተጠግታ ቆይታለች።
    ከዚህ በኋላ በ15ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ አካባቢ ቁጥሩ ከአርባ ዐራቱ ታቦታት አንዱ በኾነው በርዕሰ አድባራት አዘዞ ዳግማዊት ደብረ ሊባኖስ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን በተደራቢነት ቆይታለች። ከዚህ በኋላ በ19 50 ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ በሎዛ ማርያም በገጠር ታላላቅ ነዋሪዎችና በአዘዞ መከላከያ ሠራዊት ሃያኛ ብርጌድና አራተኛ ሻለቃ በመተባበር አሁን ከተሠራችበት በዘመኑ ይገለገልበት የነበረውን ቤተክርስቲያን በመገንባት ለአሁኑ ትውልድ አመቻችተው አልፈዋል።
    ከዚያ በመቀጠልም የተለያዩ አባቶች ቤተክርስቲያኗን በክብር በመጠበቅና በማገልገል ጥንታዊነቷን ለትውልድ ሲያስተላልፉ ቆይተዋል። አሁን የሚታየው ካቴድራል በ2001 ዓ.ም ተጀምሮ 2008 ዓ. ም ተጠናቀቀ። ህዳር 21 2008 ዓ.ም በአዲሱ ካቴድራል ታቦቷ ገብቶ እልፍ አእላፍ ምእመናን ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር በተገኙበት ቅዳሴ ቤቷ ተከበረ።
    የማርያምወርቅ ተሻገር/መምህር/
  • Zábava

Komentáře • 3

  • @user-su1lt9ny3y
    @user-su1lt9ny3y Před 5 měsíci

    እልልልልል እልልልልል እልልልልል ተመስገን አምላኬ

  • @angaroemebet527
    @angaroemebet527 Před 5 měsíci

    እንዃን አደረሳችሁ ለአስትሪዬ ማሪይም ለመላው ኦርቶዶክስ

  • @user-po4cz9vz6f
    @user-po4cz9vz6f Před 5 měsíci

    ሠላምሠላም🎉❤🎉❤🎉❤🎉❤🎉