Video není dostupné.
Omlouváme se.

ቁርአን ስለ ወንጌል ምን ይላል? ከ ሀ እስከ ፐ || What the Quran REALLY Says about the Gospel || David Wood Amharic

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 5. 08. 2024
  • I found this video useful, so I translated it to the best of my ability. Use this link to find the first video I translated from. I apologize for the minor mistakes I make.‌‌
    • What the Quran REALLY ...
    መልካም ዜና
    የምስራች፣ የምስራች፣ የምስራች! የምስራች ማለት መልካም ዜና ማለት ነው። የእግዚአብሔር ቃል ደጋግሞ የሚነግረን ይሄ መልካም ዜና ምንድነው? ዛሬ፣ በእግዚአብሔር ረዳትነት፣ በእግዚአብሔር ቃል ላይ ስለተጠቀሰው ስለዚህ መልካም ዜና እንነጋገራለን። ነገር ግን ስለ መልካሙ ዜና ከመነጋገራች በፊት ስለ መጥፎው ዜና ማስታወስ አለብን።
    ምንድነው መጥፎው ዜና? በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ከፈጠረ በኋላ አዳምንና ሔዋንን በምድራዊዋ ገነት ውስጥ እንዳስቀመጣቸው ታስታውሳላችሁ። እግዚአብሄር እንዲያውቁት፣ እንዲወዱት፣ እንዲታዘዙት እና ለዘላለም እንዲያከብሩት ፈጥሯቸዋል። ይሁን እንጂ እግዚአብሔር እነሱን ለመፈተን አዳምን እንዲህ አለው፡-
    “በገነት ካለው ከዛፉ ፍሬ ብሉ፥ ነገር ግን እንዳትሞቱ በገነት መካከል ካለው ከዛፉ ፍሬ አትብሉ አትንኩትም።”
    መጥፎው ዜና አዳምና ሔዋን እባቡን ማለትም ከተከለከለው ዛፍ ፍሬ እንዲበሉ የፈተናቸውን ዲያብሎስን ማዳመጣቸው ነው። የአዳምና የሔዋን ኃጢአት እነርሱንና ዘሮቻቸውን ሁሉ በመበከል በዓለም ላይ ችግርንና ሞትን አመጣ። ብዙ ጊዜ እንደምንሰማው፡ "ወረርሽኝ መነሻው ላይ ብቻ አይወሰንም!" የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል መጥፎ ዜና ይነግረናል፡-
    “ለሰዎችም አንድ ጊዜ መሞት ከእርሱ በኋላም ፍርድ እንደ ተመደበባቸው፥...
    እነሆ፥ ጌታ በሁሉ ላይ እንዲፈርድ፥ በኃጢአተኝነትም ስላደረጉት ስለ ኃጢአተኛ ሥራቸው ሁሉ ዓመፀኞችም ኃጢአተኞች በእርሱ ላይ ስለ ተናገሩ ስለ ጭከና ነገር ሁሉ ኃጢአተኞችን ሁሉ እንዲወቅስ ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጥቶአል ብሎ ለእነዚህ ደግሞ ትንቢት ተናገረ።” (ዕብራውያን 9፥27 ይሁዳ 1፥15)
    ስለዚህ፣ መጥፎው ዜና ሁላችንም ኃጢአተኞች ነን እናም የእግዚአብሔርን የጽድቅ ፍርድ መጋፈጥ አለብን! ይሁን እንጂ፣ መልካሙ ዜና (የምስራቹ) በዚያው በገነት ውስጥ፣ በምረቱ ባለጠጋ የሆነው እግዚአብሔር፣ አንድ ቀን ከድንግል የሚወለድን ኃጢአት የሌለበትን ሰው ወደ አለም እንደሚልክ ማስታወቁ ነው። ይህ ቅዱስ ሰው፣ ይህ ጻድቅ አዳኝ፣ ለአዳምና ለዘሮቹ ሁሉ ኃጢአት ለመክፈል ራሱን መስዋእት አድርጎ ይሞት ነበር። ለኛ የሚገባን የኃጢአት ቅጣት በዚህ ኃጢአት በሌለበት አዳኝ ላይ ይወድቃል። አዳምና ሔዋን ኃጢአት በሠሩበት ቀን እግዚአብሔር የሰበከው ወንጌል (የምስራች) ይህ ነው። እግዚአብሔር የዚህን አዳኝ መምጣት ለማወጅ ብዙ ሰዎችን ተጠቅሟል፣ እንዲሁም መሲህ ይባላል። እያንዳንዱ የእግዚአብሔር ነቢያት ስለ መሲሑ አንድ ነገር አውጀዋል፣ ስለዚህም እርሱ ሲመጣ እግዚአብሔር የሾመው እርሱ መሆኑን ሁሉም ይገነዘባል። ለምሳሌ ያህል፣ ከመሲሑ መምጣት ሰባት መቶ ዓመታት ቀደም ብሎ የነበረው ነቢዩ ኢሳይያስ፣ መሲሑ እንዴት እንደሚወለድ ተንብዮአል። "ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው።"( ማቴ. 1:23፤ ኢሳ. 7:14 ) ሚክያስ የተባለ ነቢይ ደግሞ መሲሁ ከሰማይ መጥቶ በቤተልሄም መንደር በምድር ላይ እንደሚወለድ ትንቢት ተናግሯል። በትክክል መሲሑ የተወለደበት ቦታ ይህ ነበር። ሆኖም ሚክያስ ይህን ትንቢት የተናገረው መሲሑ ከመወለዱ ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት ነው። ነገር ግን ነቢያት የመሲሑን መወለድ ብቻ አላወጁም። በተጨማሪም መሲሁ በኃጢአተኞች ምትክ መከራ እንደሚደርስበትና እንደሚምት ትንቢት ተናግረዋል። ለምሳሌ ነቢዩ ዳዊት ሰዎች መሲሑን እንደሚንቁት፣ እንደሚያሰቃዩት፣ እጁንና እግሩን እንደሚወጉ እና እንደሚገድሉት ጽፏል። ዳዊት የመሲሑን ሞት ማወጅ ብቻ ሳይሆን፣ እግዚአብሔር መሲሁን ከሞት እንደሚያስነሳውም ተንብዮአል፤ ይህም እግዚአብሔር የአዳምን ልጆች ከኃጢአት ቅጣት ለማዳን የላከው አንድና ብቸኛ አዳኝ መሆኑን አረጋግጣል።
    ስለ መሲሁ መወለድ ብዙም ክርክር የለም፣ ነገር ግን ብዙዎች በሞቱና በትንሳኤው ይሰናከላሉ። ሰዎች የላከውን መሲህ ሲያዋርዱት እግዚአብሔር እንዴት ሊቆም እና ሊመለከት እንደሚችል አይገባቸውም። ብዙ ሰዎች ሊረዱት ያልቻሉት ነገር መሲሑ ለኃጢአታችን እንዲህ አይነት መከራ እንዲደርስበት ያቀደው እኛን የሚወደን አምላክ መሆኑን ነው። ነገር ግን ነቢያቱ እንዲህ ሲሉ አውጀዋል፡- “እግዚአብሔርም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።”
    - (ኢሳይያስ 53፥10)
    ነቢያትን እናምናለን? አዎ እናምናቸዋለን እንላለን። ነቢያትን በእርግጥ የምናምን ከሆነ የጻፉትንም ማመን አለብን። ነብያት የራሳቸውን ሃሳብ እንዳልተናገሩ ማስታወስ አለብን። እግዚአብሔር የሚናገሩትን በመንፈሳቸው ውስጥ አኖረ። እንግዲያውስ እነዚያን ነቢያት ለማመን ብንቃወም፣ ማንን ነው ምንቃወመው? የምንቃወመው እግዚአብሔርን ነው። ምክንያቱም ነቢያት መሲሁ ኃጢአትን ለማስወገድ መስዋዕት ሆኖ እንደሚሞት ትንቢት እንዲተነብዩ ያነሳሳው እርሱ ነውና።
    {የሚቀጥለው ማሊክ የሚባል ሰው የግል ምስክርነት ነው።} እዚህ ጋር ቆም ላድርገውና እንዴት በኢየሱስ ክርስቶስ አማኝ እንደሆንኩ ልንገራችሁ። በወጣትነቴ በቀን አምስት ጊዜ ለመጸለይ እና አመታዊ ጾምን ለመጾም ታማኝ ነበርኩ፣ ነገር ግን ከሞትኩ በኋላ ወዴት እንደምሄድ አላውቅም ነበር። ዙሪያዬ ያሉትን ሁሉ ጠየኩ፣ ሆኖም ግልጽ የሆነ መልስ አላገኘሁም። ወንጌልን (ኢንጂልን) ሳጠና ግን፣ ከሞቴ በኋላ ወዴት እንደምሄድ ማወቅ እንደምችል አወቅሁ፤ ምክንያቱም መሲሁ ኢየሱስ ራሱ በወንጌል እንዲህ ይላል፦ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም።” (ዮሐንስ 5፥24) እንዲሁም እንዲህ ብሏል፦ “ኢየሱስም፦ ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤” (ዮሐንስ 11፥25) ስለዚ፣ ራሴን ለማዳን ከራሴ ጥረት ንስሃ ገብቼ ነቢያት ሁሉ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ በስሙ የኃጢአቱን ስርየት ይቀበላል" ብለው ትንቢት በተናገሩለት መሲህ አመንኩኝ (ሐዋርያት 10፥43)። ተስፋዬን ሁሉ ወስጄ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ አስቀመጥኩት። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔር ለመንፈሴ ሰላም አምጥቶላታል። አሁን ህሊናዬ አይረበሽም። ኢየሱስ በመስቀል ላይ ከሰራው ሥራ የተነሳ የወደፊት እጣዬ በሚያስደንቅ ሁኔታ ብሩህ ነው። በሕይወቴ እንደ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር፣ አንዳንድ ጊዜ ችግር እና መከራ ያጋጥመኛል ምክንያቱም እምነቴ ከዘመዶቼ እና ከጓደኞቼ አስተያየት ስለሚለያይ፤ ግን ሰላም አለኝ። የእግዚአብሔር ሰላም ልቤንና አእምሮዬን ሞልቶታል። ይህን የሰጠኝ ኢየሱስም እንዲህ ይላል፦ “ዓለም ቢጠላችሁ ከእናንተ በፊት እኔን እንደ ጠላኝ እወቁ።” (ዮሐንስ 15፥18) “ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም።” (ዮሐንስ 14፥27) እና ወዳጆች ሆይ፣ ጌታ ለእኔ እና በእኔ ያደረገውን ለእያንዳንዳችሁ ሊያደርግ ይችላል። ካንተ ወይም ካንቺ አንድ ነገር ይጠይቃል፡-ሙሉ ልብህን እንድትሰጠው። ሙሉ ልብሽን እንድትሰጪው። የቀረውን እሱ ያደርገዋል። ጌታ ኢየሱስ ራሱ እንዲህ ብሏልና። "እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤" (ማቴ. 11:28-29)
    እግዚአብሔር ታላቁን ማዳኑን መቼም ቢሆን አይሸጥልህም ወይም አይሸጥልሽም። እንዲሁ ያለ ምንም ዋጋ (ከእናንተ ባልሆነ ዋጋ) በነጻ ሊሰጣችሁ ነው ሚፈልገው። መልካም ስራ፣ ፀሎት (ሶላት) እና ፆም በውስጣችሁ ጥሩ ስሜት ይሰጡ ይሆናል፣ ነገር ግን የእግዚአብሔርን ፅድቅ አያረኩም! ወደ እግዚአብሔር ገነት የምትገባበት/የምትገቢበት መንገድ አንድ ብቻ ነው።
    1.) በመጀመሪያ ኃጢአተኛ እንደሆንክና አምላክን ለማስደሰት የሚያስችል ኃይል እንደሌለህ መገንዘብ ይኖርብሃል።
    2.) ከዚያም ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝ እንደሆነ፣ ኃጢአትህን ለማስወገድ እግዚአብሔር በመስቀል ላይ እንዲሞት እንደ ላከውና እግዚአብሔር የዘለአለም ሕይወትን ይሰጥህ ዘንድ እንዳስነሳው ማመን አለብህ።
    የኦሮምኛውን ቻናሌን ለማግኘት ይህንን ተጫኑ👇
    / @dhugaanniboqachiisa
    አስተያየታችሁን በውስጥ ማድረስ የምትፈልጉ ይህንን የቴሌግራም ሊንክ ተጠቀሙ👇
    t.me/BibleAndMe
    Additional: - ewnetyasarfal123@gmail.com

Komentáře • 42

  • @ewnetyasarfal
    @ewnetyasarfal  Před 4 měsíci +9

    🙄 ቅርባችሁ ላለ ሰው Share ማድረግ ኃጢአት ነው የሚል ነገር ወቶኛል!?🥺

  • @mohamedmame9652
    @mohamedmame9652 Před 2 měsíci +2

    ምንጭህ ብሩክ ይሁን

  • @user-ih1bd6lc3p
    @user-ih1bd6lc3p Před 3 měsíci +1

    እግዚአብሄርፍቅርነዉቸርነቱብዙማሥተዋሉንይጥጣቸው❤❤❤

  • @noorwaga4502
    @noorwaga4502 Před 4 měsíci +8

    ሙስሊሞች እስቲ ለራሳችሁ እድል በመስጠት መፅሐፍ ቅዱስና ቁርአንን አጥኑ መርምሩ ።ተባረክ ወንድማችን ❤❤❤

    • @Uvbnn
      @Uvbnn Před 4 měsíci

      Dr. Zakir ke hulum Christian belay Bible yakal ena lemn Christian alhonem

    • @ewnetyasarfal
      @ewnetyasarfal  Před 4 měsíci

      የሚያውቅ የመሰለህኮ አንተ ስለማታውቅ ነው። በማያውቁ ሰዎች ፊትኮ ተናጋሪ ሁሉ ምሁር ነው። ለመሆኑ ከዚህ በፊት ከእሱ ጋር በተገናኘ የተረጎምኳቸውን አይተካል? ያኔ እውነታውን ትረዳ ነበረ። እስኪ የእሱ ፎቶ ያለባቸውን፣ ከዚህ በፊት የለቀኳቸውን እያቸው።

    • @Uvbnn
      @Uvbnn Před 4 měsíci

      @@ewnetyasarfal እና ለምን ክርስትናን አታስፋፉም እንደ ሙስሊሞች ሁሉንም አይቻለው መጀመሪያ bible አንብብ ከዛ ወደ ቁርአን ና

    • @weletearegaytadesse4444
      @weletearegaytadesse4444 Před 3 měsíci

      አለም ውሸት ይሰፍል ጌታ ክርስትና እውነት ስለሆነ ጠባብ መንገድ መሆኑን ተናግሯል​@@Uvbnn

    • @user-dc5dr9cw2e
      @user-dc5dr9cw2e Před 3 měsíci

      መፀሀፉን አንብበነዋል ግን ከሀ እስከ ፐ እርስ በርሳቸው በሚጋጩ ጥቅሶች የተሞላ ነው😢😢

  • @tesfasibatu-bj5mm
    @tesfasibatu-bj5mm Před 4 měsíci

    geta eyesus tegawun yabizalhi

  • @misganabere6115
    @misganabere6115 Před 4 měsíci +1

    good job keep it up

  • @MarkosMenedo-cl6ki
    @MarkosMenedo-cl6ki Před 3 měsíci

    🙏

  • @user-mo6vs4sk3v
    @user-mo6vs4sk3v Před 4 měsíci

    ተባረኩ እግዚአብሔር ይጠብቃቹ❤❤❤❤❤

  • @TesfatsionAyele
    @TesfatsionAyele Před 4 měsíci

    እግዚአብሔር ይባርክህ! ፀጋ ይብዛልህ!

  • @samuelayalew307
    @samuelayalew307 Před 4 měsíci +2

    የ Father Zakariaን ቪዲዮችን በአማርኛ ስራልን Please

  • @user-rj1go6zw6e
    @user-rj1go6zw6e Před 4 měsíci

    ❤❤❤❤🎉🎉🎉🎉

  • @Mr.Wendi-
    @Mr.Wendi- Před 4 měsíci

    bertalign geta kante gar new

  • @user-rb8zq6jf4e
    @user-rb8zq6jf4e Před 3 měsíci

    Quran ppt send to l

  • @amantemam7576
    @amantemam7576 Před 8 dny

    Are u believing Bible not corrupted still?

  • @AbukiMajid
    @AbukiMajid Před 2 měsíci

    እኮ አንተ ከአቡ ሀይደረ ልትወያይ የምርሀን ነው

  • @Belachewato-io1fe
    @Belachewato-io1fe Před 3 měsíci

    ማድረግ ያለብህ ለእስልምና ሃይማኖት ምሁራን ጥሪ በማድረግና የጋራ መድረክ በማዘጋጀት የፊትለፊት ውይይት ማድረግ ነው ፡፡ አያያዝህ ጥሩ ስለሆነ ብዙ ነገሮች ግልጽ ሊሆኑ ይችላሉ ብዬ አምናለሁ ፡፡ በዩ ቲዩብ የሚደረገው የነጠላ መመላለስ ለአድማጭ የግል ውሳኔ ብዙም አስተዋጽኦ የለውም ፡፡ ስለዚህ እባክህ ዝግጁ መሆንህን ሳትፈራ ግልጽ አድርግ !

    • @ewnetyasarfal
      @ewnetyasarfal  Před 3 měsíci +1

      ከዋነኞቹ መካከል ዝግጁ የሆነ እንዲመጣ ሁሌም ጥሪ እንደተደረገ ነው። በእኛም በኩል በየትኛውም ርእሰ ጉዳይ ላይ ቀጣይነት ያለው ውይይት ለማድረግ ዝግጁ ነን። ከሙስሊሞች መካከል ግን እስከ አሁን ዝምታን መርጠዋል። እኛ ምንፈልገው ከዋነኞቹ ጋር መወያየት ነው። እስኪ እንደ አቡሃይደር፣ አህመዲን ጀበል፣ ዋሒድ እና የመሳሰሉትን ርእስ መርጣችሁ ጋብዙልን። እኛም ርእስ እናዘጋጃለን ከዛም በቁርአንና በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ሰፊ ውይይቶች ይደረጋሉ።

  • @user-uz1cv9vr9s
    @user-uz1cv9vr9s Před 2 měsíci

    ወንጌል ያሸንፈል🏃🏃

  • @Uvbnn
    @Uvbnn Před 4 měsíci +1

    ይሄን ሰውየው ለምን አትፈታውም ምንም ሚያቀው ነግር የለም 😂

  • @begood4all157
    @begood4all157 Před 3 měsíci

    ቁርአን መጽሐፍ ቅዱስ ከፈጣሪ ለነብያቶች መሰጠቱን ነው የሚናገረው ከዛም ሰዎች እንደ በረዙት ይናገራል ሌላ ሃተታ ተረት ተረት ነው የምታወራው ።

  • @user-dc5dr9cw2e
    @user-dc5dr9cw2e Před 3 měsíci

    ከሀ እስከ ፐ አይደለም እስከ ፐ ስኩየር ብለህ ብትጋጋጥም ባይብልህ ውስጥ የታጨቀውን የሀሳብና ጥቅሶች ግጭት በምንም ልታስተባብሉት አትችልም፡፡
    ስለ እስልምናም የፈለጋችሁትን ያክል የተጭበረበረ ፕሮፓጋንዳ ብትነዙም ፡በሂደት እውነታው ሲገባችሁ ምስክርነት ሰጥታችሁ ትቀላቀሉናላችሁ፡፡
    አላህ ወደ ቀናው መንገድ ይምራችሁ!!!

    • @misganabere6115
      @misganabere6115 Před 2 měsíci

      ALLAH IS A PAGAN god

    • @thomasgebremedhin831
      @thomasgebremedhin831 Před 2 měsíci

      User እመነኝ እስቲ እስልምና ለምን ጨረቃን መሐመድ መረጠ?

  • @user-sm5rx6hl1v
    @user-sm5rx6hl1v Před 2 měsíci

    እናተም እኮ ሙስሊም ነበራቹ ክርስትና ስለምትነሱ ነው ወደ ተፈጠራቹበት ጥርት ጽድት ወዳለው ተመለሱ ትረካውን ተውት 😂😂😂😂😂😂

    • @user-wn5ge2nh4o
      @user-wn5ge2nh4o Před dnem

      ደደም መሆንሽን በአደባባይ ሰው ሲወለድ እምነትም ሃይማኖትም የለውም ጸኀይ ፈጠረህ ቢባል የሚያምን ልጅ እንደት ፈጣሪውን አውቆ ሙስሊም ይሆናል ሰው ሲወለድ አዳማዊ ነው ስጋ ብቻ ከመንፈስ ቅዱስ ዳግም ሲወለድ ክርስቶሳዊ ይሆናሉ ስጋ ስጋ ነው መንፈስ ግን መንፈስ ነው መጽሐፍ ቅዱስ እንደዚህ ያዘናል