#ሚስኩን

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 6. 09. 2024
  • ከ ጭማሪ ግጥሞች ጋር,,,,,,
    //ዑስታዝ ሰዒድ አህመድ//
    በመልክም በሃል በፈድል በእጣ
    ተገዳዳሪ የለው ባላንጣ
    ባህሪው ለጉድ ወደርን ቢያጣ
    ልሙት ለርሱ አለ ሊገል የመጣ
    ።።።።
    አየ ጉድ ጠባይ አጀብ ኹሉቁ
    እንዴት አስውቦ ሰራዎት ሃቁ
    ጠላነው ያሉት ሸሽተው በሩቁ
    ተግሩ ስር ዋሉ ቀርበውት ሲያውቁ
    ።።።።።
    የኔ መብሰልሰል መሞቅ መብረዴ
    መጥበቅ መላላት መውጣት መውረዴ
    ላንቱ መሆኑን አያውቁም እንዴ
    በክፉ አነሶት ሳልገባ ለህዴ
    አየ ሶሃቦች ሴት በለው ወንዱ
    መገን ዑመሩ መገን ኻሊዱ
    ያንቱን መነካት አውቀው በነበር
    ሳይቀሉ አንገቱን አትጠልቅም ጀንበር
    ሊገድሉት ሲሉ ሰይፍን ሲመዙ
    ሊያጠፉት ቆርጠው ስጋም መረዙ
    በቀል ሳያቅት በሃይል መያዙ
    ከዝነት ሰገባ ረህመት ሚመዙ
    ክብሬ እኮ ነበር ቢሆን ወደኔ
    መንገላታትሁ ስቃዮት ለኔ
    ቁስሎት ላካሌ እንባዎት ላይኔ
    ቆሜ መሄዴ ባንቱ አይደል ዘይኔ
    ያ የዝነት ጥጉ የጀነት ቁልፉ
    አሏህ ያለዎት ረሂም ረኡፉ
    ለኛው በኖሩ ለኛው በለፉ
    ለምን ስላንቱ ይሰማል ክፉ
    ለበድር ባልዘምት ባካል ብርቅም
    ወይ የኸንደቅ ለት አፈር ባልዝቅም
    ቅዋየ ቢላሽ ወዜ ቢደርቅም
    አንቱ ተነክተሁ ዝምታ አላውቅም
    ከናትም ራርተው በዝነት በኖሩ
    ሌላን ለማብላት ድንጋይ ባሰሩ
    ባንድነት ገመድ ባስተሳሰሩ
    ለምን በክፉ ተነሱ አንዋሩ
    እንኳን ሙስጦፋን የርስዎን ግድም
    በእጅሁ የነኩት ሊነካ አልፈቅድም
    ሃብት ንብረቴን ነፍሴንም እንካ
    ዘይኔን ተውልኝ ማይሆን አትንካ
    በጭፍን ወቃሽ መሆኑን ትተህ
    ላንዴ እንኳን የርሱን ታሪኩን ከፍተህ
    ጥቂት ብትሰልል የሆኑ ያሉትን
    ነቢን ከመንካት ባስበለጥክ ሞትን
    የሚቻል መስሎት አጉል ያለመ
    ፀሃይን በጣት ሊጋርዳት ቆመ
    ውበቷን አይሽር ጥቅሟን አይቆርሰው
    ፀሃይ የለችም ቢልም እውር ሰው

    « እፍ » ሲል ቢውል ሊያጠፋት ወዶ
    የሻማ ልምዱን ፀሃይ ላይ ወስዶ
    «ትል» ታይቶ አያውቅም ተራራን ንዶ
    የማይሆን ላይሆን ትርፉ ነው ባዶ
    ማር የመረረው ነክቶ ሲቀምሰው
    ከንብ ይጣላል እንኳንስ ከሰው
    አሏህ አጥምሞት ዞላም ካመሰው
    ፅልመት ነው ለርሱ ኑር ብታለብሰው
    ።።።።
    ዘይኔን በመጥፎ ለሚያነሳሱ
    ሶብርም አይኖረው ሙሂብ እንደሱ
    እሱማ አዛኝ ነው ለጠላት ቤትም
    ፍቅር ኮ ነው ለሚጠሉትም
    ጉድለት ባይቀርበው የሳቸው ጠባይ
    ለከፋባቸው ናቸው ይቅር ባይ
    ግን ወዳጆቹ ነፍስን ሰውተው
    እረፍት አያውቁም ሐቢብ ተነክተው
    🌟🌟🌟🌟🌟ሙዓዝ ሀቢብ ነኝ እወዳችኋለሁ

Komentáře • 812

  • @danielk355
    @danielk355 Před 2 lety +122

    በጣም ቆንጆ ድምፅ አለህ !!! በሰው አገር ብቸኝነት ሲሰማኝ የአንተን ሥራዎች ስሰማ በጣም ያጽናናኛል !! እግዚአብሔር ይባርክህ ወንድማችን እንወድሃለን !!!

  • @Ismail_Tekle
    @Ismail_Tekle Před 2 lety +134

    የሚቻል መስሎት አጉል ያለመ
    ፀሀይዋን በጣት ሊጋርድ ቆመ
    ዉበቷን አይሸር ጥቅሟን አይቆርሰዉ
    ፀሀይ የለችም ቢልም እዉር ሰዉ ❤❤❤

    • @yenatoub4205
      @yenatoub4205 Před 2 lety +4

      ወላሂ ለተሳዳቢዋች ድጋሜም መልስ አያስፈልግም ፊዳከ ያረሱለላህ እውነት ናፍቀነወታል

    • @user-bj7ou3en2h
      @user-bj7ou3en2h Před 2 lety

      ዘፈኑን ትተህ ወደ ጌታህ ተመለስ እስቲግፋር አድርገህ አላህን በብቸኝነት ለማምለክ ሞክር
      እውነት የነቢ አፍቃሪ ከሆንክ የከለከሉትን ተከልከል ሀላል ያደረጉትን ደሞ ለማሰራጨት ሞክር አላህተብሎ ዘፈን አለእንደ ነቢብሎዘፈን አለደ ግጥም ተፈቅዷል እኔእስከማውቀው ድረስ
      ደሞ ኮሜንቶች ማሻአላህ አትበሉ እሚባልበትን ቦታለዮ ።

    • @Tad_beer
      @Tad_beer Před 2 lety +1

      @@user-bj7ou3en2h wohabeya koshasha nshi gena tabedalachohu

  • @MuazHabibofficial
    @MuazHabibofficial  Před 2 lety +268

    ሁላችሁንም ከ ልቤ አመሰግናለሁ ኮመንታችሁን በሙሉ አንቢቢያለሁ እናንተንም አላህ ይጠብቅልኝ ገጣሚው ብዕረኛው ዑስታዝ ሰዒድ አህመድም እጅግ አድርገን እናመሰግናለን ብለዋል ሀገራችንን ሰላም አላህ ያድርግልን መረጋጋት ፍቅር መተዛዘንን አላህ ይስጠን አንድነትን ያጠናክርልን አመሰግናለሁ ❤

  • @cryptoenthusiast_eth
    @cryptoenthusiast_eth Před 2 lety +198

    ....እሱም አዛኝ ነው ለጠላት ቤት
    ፍቅር እኮ ነው ለሚጠሉት!!
    ፊዳከ ያ ረሱል አላህ!! 💚💚💚
    ሰላላሁ አሌይሂ ወሰለም!!

  • @ibnhashim3599
    @ibnhashim3599 Před 2 lety +114

    እንዴት ዉብ የሆነ ነሽዳ ነዉ ባካቹሁ
    አንድ ግዜ በህብረት ነቢያችን ላይ ሰለዋት እናዉርድ እስኪ❤s.a.w❤

  • @TofikYusuf
    @TofikYusuf Před 2 lety +100

    ማሻ አላህ ሙዐዜ እጅግ ውብ ስራ ድንቅ ግጥም ውብ ዜማ ሚስኩን ዐንበሩ " ፍቅር እኮ ነው ለሚጠሉት " አላህ ይጨምርልህ

  • @user-fu2od1ty6d
    @user-fu2od1ty6d Před 2 lety +88

    ምርጥ ባል🌷ምርጥ አባት🌷ምርጥ አፍቃሪ🌷አዛኝ ናፋቂ🌷ምርጥ ምሪ🌷ምርጥ ነብይ🌷ነብያችን ስለላዋለይ ስሉ አለ ነብያችን🌷ጉድ የሚያስብል🌷እልህ የሚያስጭረስ🇪🇹ኢትዮጵያ🇸🇦ሳውዱ🇦🇪ዱባይ አሜሪካ ኩይት ኡማን እስላማዊ ጥያቄ መልስ ውድድር አለ ፍሎፍይሩን ተጨናቹ ግቢ እዳያመልጣቹ ሁሉም🇪🇹ሀገር ውክላቹ ተውዳዳሩ

  • @alemayaprostudio2242
    @alemayaprostudio2242 Před 2 lety +1

    good brother i lv it

  • @hamduebrahim4036
    @hamduebrahim4036 Před 2 lety +73

    😍😍 ይህንን ድንቅ ነሺዳ አለማድነቅ ራስ ወዳድነት !🙂😌
    👌 የተወደሱ ነብያችን ናቸዉ ! saw ! 🙏🙏
    ✌️ 100% ድንቅ ድምፅ
    ✌️ 100% ድንቅ አለባበስ
    ✌️ 100% ድንቅ ክሊፕ 😲 ማሻአላህ ማንን ገደለ be like👍👍👍👍👍👍👍

    • @msnadia7588
      @msnadia7588 Před 2 lety

      አይዋ ውዝዋዜ.100%
      ዜማ100%
      ምርጥ ለስለስ ያለ የሚዚቃ መሳሪያ
      ላስታውስህ ብየ ነው ድንቅ የሙዚቃ ክሊፕ 👏👏

    • @user-pn5px2fi6o
      @user-pn5px2fi6o Před 2 lety +1

      @@msnadia7588 ሙዚቃ አላልሽም ለይ እና እወቂ

  • @MalcolmXethio
    @MalcolmXethio Před 2 lety +45

    ድንቅ ስራ ሙአዜ በርታልን

    • @user-lr5bl4by5y
      @user-lr5bl4by5y Před 2 lety +4

      እናተም አላቹህበት አጂብ አረ ወደየት ነን!!!!"" ኤጭ አሁንስ ያቃሉ የሚባሉት …………

    • @user-hy1xt8du4c
      @user-hy1xt8du4c Před 2 lety +3

      አህባሻች አይደላችሁ እንደ ሙዚቃ አድናቂ

    • @user-lr5bl4by5y
      @user-lr5bl4by5y Před 2 lety

      @@user-hy1xt8du4c የምረ አስጠሉኝ አሁንስ አረ ወዳ

    • @user-hy1xt8du4c
      @user-hy1xt8du4c Před 2 lety +1

      @@user-lr5bl4by5y
      እኔ ሳላስበው ያገኝሁት ግን ድሮ ኩንፈየኩን እሚለው ለራሱ ጥሩ ነሻዳ ነበር እያደር ተበላሸ ወደሙዚቃው

  • @neimahassen695
    @neimahassen695 Před 2 lety +35

    ለይለቱ ጁመአ ሰሉ አለ ነቢ ♥️ማሻአላህ

    • @melakbintebrahim3089
      @melakbintebrahim3089 Před 2 lety +1

      صلى الله عليه وسلم 🥰🥰 صلى الله عليه وسلم 🥰🥰🥰

  • @ZebibaHassne-nz1eg
    @ZebibaHassne-nz1eg Před měsícem

    ትል ታይቶ አያውቅም ተራራን ንዶ
    የማይሆን ላይሆን ትርፉ ነው ባዶ❤❤❤❤ ፊዳከ ያረሱለላ ሰለላሁ ወአለይሂ ወሠለም

  • @rhjfjfjfjfjkf6444
    @rhjfjfjfjfjkf6444 Před 2 lety +32

    ዑስታዝ ሰዒድ አህመድ አላህ እድሜያቸውን ያርዝምልን የነሺዳ እና የብዙ መንዙማ ግጥም ባለቤት ናቸዉ ❤❤❤

  • @myhero6436
    @myhero6436 Před 7 měsíci

    "የኔ መብሰልሰል መሞቅ መብረዴ መጥበቅ መላላት መውጣት መውረዴ
    ላንቱ መሆኑን አያውቁም እንዴ
    በክፉ አነሱዎት ሳልገባ ለህዴ"😢😢😢
    ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም❤

  • @hasenetmohammed5975
    @hasenetmohammed5975 Před 2 lety +4

    Getamiwen alemdnek ayichalim kalat ameraret asekaku 1gna nw
    Muaz masha allah

  • @munarumana3553
    @munarumana3553 Před 2 lety +4

    ማሻአላህ አሪፍ ስራ ነው👌

  • @nejuhabibi1597
    @nejuhabibi1597 Před 2 lety +2

    Masha Allah Muaz Wendme Adelem Muslimoch Yikrba Kafoch Enkua Eyeteblalubet Beteleyayu ሚድያዎች eyelekekut nw yih ተፅዕኖ kelal adelem wede eslmna eyetesabu nw beneshida tesbew eslmnan lemewek yiguagualu bezawm tkklegnawn dinel islam bedenb yawkutal ena berttek sra masha allah byalew wendme

  • @umarmustafa6659
    @umarmustafa6659 Před 2 lety +1

    Masha Allah ragem hedme yakoyelen muaziye

  • @ihabibsa6970
    @ihabibsa6970 Před 2 lety +2

    ምርጥ ነሺዳ ነው 👍👍

  • @medystyle3080
    @medystyle3080 Před 2 lety +8

    ሀብት ንብረቴን ነብሴንም እንካ
    ዘይኔን ተውልኝ ማይሆን አትንካ
    አለይሂ ሰላም 😭😭😭😭

  • @helamod796
    @helamod796 Před 2 lety +2

    Mashalla allah yechemerlek Mert sera new

  • @aminatmohammed2752
    @aminatmohammed2752 Před 2 lety +49

    አይ ሙአዝ አላህ ይጨምርልህ አቦ ትርጉም ያለው ምርጥ ስራ አላህ መልካም ምንዳን ይመንዳህ የነቢን ውዴታ ሸፍአ ላንተም ለቤተብህም ለኛም አላህ ይወፍቀን

    • @user-ee1fb2mx1i
      @user-ee1fb2mx1i Před 2 lety

      አሠላሙአለይኩም፣ወራህመቱላሒ፣ወበረካትሁ፣ጥያቄአለኝ፣አላህይጨምርልክ፣አልሺው፣ማወደሡ፣ጥሩሆኖእያለ፣የሙዚቃመሣሪያ፣ማነው፣ሀላልነውያለው፣እኔ፣ወሎየነኝ፣ግንደረሶችንሥጠይቅ፣መሻኢኮችንም፣ሣሠማቸው፣አይፈቀዲም፣ይሉኛል፣ዱቤብቻእንጂ፣ይሔሙዚቃነው፣አታዳምጡ፣ሀራምነው፣ይሉኛል፣እሥቲጠይቁመሻኢኮችን፣አሁኖይሔዘፈንነውጂ፣ነሺዳአይደለም፣ወላሒ፣

    • @abdulhakimnasser8197
      @abdulhakimnasser8197 Před 2 lety

      6p&ûiub

    • @aminatmohammed2752
      @aminatmohammed2752 Před 2 lety

      አላህ እሚበጀውን ያቃል እሱ እሚበጀውን ይጨምርለት ግጥሙ ነቢን የመደህበት ቃላት ውብ ናቸው በዛም አላህ ኸይሩን ይመንዳው ዘንዱ ዱአ አደረኩለት ለወንድሜ

  • @seadiyoutube4324
    @seadiyoutube4324 Před 2 lety +5

    ፊዳካ አቢ ወኡሚ ወነፍሲ ያረሡለላህ ያሀቢበላህ💖💖

  • @nejipomer5780
    @nejipomer5780 Před 2 lety +129

    ሰ.ዐ.ወ ወንድሜ ምርጥ ስራ ነው... ሙዚቃውን ለማስቀረት ሞክር. አላህ እኮ ድምፃን ስቶሀል ማሻ አላህ

    • @ziizu9769
      @ziizu9769 Před 2 lety +1

      gn mechem masqeret aychlm muziqawn

    • @afiiisa6655
      @afiiisa6655 Před 2 lety +3

      @@ziizu9769 አላህ እንደ ሰው አይደለም የከፈረንም ይመልሳል ከ አላህ እዝነት ተስፋ አለመቁረጥ ነው እንዲ አይባልም

    • @semirayassin6927
      @semirayassin6927 Před rokem +1

      Hi

  • @sofii3558
    @sofii3558 Před 2 lety +5

    ማሻ አሏህ ሙአዜ ሁሌም ባማረ ነው የምታቀርበው አሏህ ይጨምርልህ

  • @sartumohammed9640
    @sartumohammed9640 Před 3 měsíci

    S A W S A W
    Masha Allah wly hedduu zikriin bareedii osoo akanumatii ittiin naaf fuftani hedduu bareedii

  • @dggfcgdd4935
    @dggfcgdd4935 Před 2 lety +1

    Mashallah alebabesachihu yamral kotet yalbezabet des ylal wedim muaz lewedefitum edezih zenteh sra

  • @ferejmuhammedz6798
    @ferejmuhammedz6798 Před 2 lety

    ማሽ አሏህ





    አሏህ ይጨምርልህ Bro

  • @rahmanjemal2220
    @rahmanjemal2220 Před 2 lety +3

    ፊዳከ አቢ ወኡሚ ወሩሂ ያረሱለሏ ሰለላሁ አለይሂ ወሰላም

  • @dubaihatha76
    @dubaihatha76 Před 2 lety +1

    ሰ፡ዐ፡ወያረሱሉላህያሀቢበላህምርጥነውደስይላልማሻአላህ

  • @HasnaHasna-nr2vi
    @HasnaHasna-nr2vi Před 2 lety +4

    ማሻ አሏህ በርታልን ሰለላ አለይ ወሰለም

  • @tiybagizawo7035
    @tiybagizawo7035 Před 2 lety +2

    ሠለላህ አለይሂ ወሰለም ማሻ አላህ ደስ ይላል በጣም በርታልን

  • @milishasalo2289
    @milishasalo2289 Před 2 lety +3

    Masha allah best nesheda nebew muhammed world best man.allehamedulelay rebelealemen.le allah beye ewedealew.jumea mubarak.

  • @rozytube624
    @rozytube624 Před 2 lety +6

    ያረሱለሏህ ፊዳከ አቢ ወኡሚ ያረሱሉሏህ💘-_-_💘
    ማሻ አሏህ ውብነሽዳነው አሏህ ይጨምርልህ

  • @hayetkonjo8250
    @hayetkonjo8250 Před 2 lety +2

    ሳሚች ማልጣግብ ናሺዳዋዉ ነው ❤❤❤❤🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇦🇪🇦🇪🇦🇪🇦🇪🇦🇪🥰🥰🥰❤❤❤❤ስ ዐ ወ 🌹🌹🌹🌹😥😥😥😥😥 ፍዳክ ያርሱልልህ

  • @arifhussen4119
    @arifhussen4119 Před 2 lety +2

    Selelahu alehi weselem masha Allah batam harif Sera new Allah yechemereleh

  • @user-vt4jz5pp9e
    @user-vt4jz5pp9e Před 2 lety +2

    አለይሂ ሶላቱ ወሰላም ያረሱለሏህ ፊዳከ አቢ ወኡሚ ወሩሂ💖💖💖💖💖💖💖💐💐💐💐👍👍👍💕💞💞💕💖🙏

  • @mycountryethiopia4097
    @mycountryethiopia4097 Před 2 lety +2

    ማሻ አላህ ወድም በጣም ነው የሚያምረው አንደኝ

  • @Tube-sx9tj
    @Tube-sx9tj Před 2 lety +1

    ኡሥታዝ ሠኢድ አህመድ ረጅም ሀያትትት ያንቱ በመሆኔ በጣምምም ደሥተኛ ነኝ የኛ እንቁ ባንቱ ዉሥጥ ሀቢበሏህን እናያለን አሏህ ይጠብቅልን
    በፍቅር ላይ ፍቅር በሙሀባ ላይ ሙሀባ እንድንጨምር አድርገሁናል ግጥሙሁ እጅግ እጅግ እጅግ በጣምምምምምምም ልዩዩዩዩዩዩዩ የሆነ አርቀን እና ጠልቀን እንድንገነዘብ የይበልጥ እንድናፈቅራቸዉ ነዉ ያደረገን ግጥምሁ
    በዛላይ የምትሠጡንን ደርሥ ከምንም በላይ ነዉ የምወደዉዉዉዉ አሏህ ይጠብቅልንንን
    ኑሩልንንን ነፍፍፍፍ አመት የኛ ወርቅ ❤❤❤💓😘😘😍😍

  • @hayderhayredin7095
    @hayderhayredin7095 Před 2 lety +111

    ላንተ ሚሆን ቃል የለኝም የሀገራችንን ነሺዳ ከፍ ያለ ቦታ አስቀመጠሀዋል ሁል ጊዜ ምርጥ ሁልጊዜ ጥዑም ሁል ጊዜ እሚጣፍጥ ሁሌ የተለየ ግሩም ስራ ወደፊት ብቻ የሀቢቢ ልጅ ወደፊት💪💪👌

  • @ayshaaysha2294
    @ayshaaysha2294 Před 2 lety +1

    ጥሩስራነዉ በርታልኝ

  • @hawwahawwa8258
    @hawwahawwa8258 Před 2 lety +11

    አላህ አላህ ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም
    የኔመብሰል መሞቅ መብረዴ ለቱ መሆኑን አያውቁምዴ ፊደከ ሩሂ ያረሱለሏህ😭😭😭

  • @mubarekseid8877
    @mubarekseid8877 Před 2 lety +3

    አልሀምዱሊላህ ሙስሊም እና የረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ወዳጅ ያደረከኝ ጌታ

    • @muhammadsani748
      @muhammadsani748 Před 11 měsíci

      Masha'allah Golding voice may Allah add more wisdom

  • @mami2182
    @mami2182 Před 2 lety +121

    ድምፅህና ዜማህ በጣም የሚገርም ነው ፡ማሻላህ ትችላለህ፡፡ ሌላ መርሳት የሌለብን የዚህ ግጥም ድራሲ ማሻላህ ገጣሚ ኡስታዝ ሰኢድንም አላህ ዕድሜያቸዉን ያርዝምልን፡ እጅግ በጣም የሚገርም መልክት ያለው ግጥም ነው፡፡

  • @nasrumame8913
    @nasrumame8913 Před 2 lety +1

    Mashallah muaz habib bertalen beadis sra degami etebkhalen biznilah❤️🧡💛💙💔💗💓💜💞💗💔💛🧡💙

  • @kingoloco1373
    @kingoloco1373 Před 2 lety +1

    Selelahu alyhi weslm jenetewa habibi lantu fida hulenm ngr selelahu alyhi weslm

  • @jewharchanie4211
    @jewharchanie4211 Před 2 lety

    mashaallah .....wellahi wuste nehhh slhh...allah yabertah wellahi kante bizu tebkalew .....bizum eyeserah nw allah hayat yisth...and ken agiche endamawerah tesfa adergalew...🤩🥰😍😘

  • @አልሀምዱሊሏህ1996

    ሙዓዜ የኔድምፀመረዋ ማሻአሏህተባረከሏህ
    ፊዳከአቢወዑሚ ያረሱለሏህ

  • @user-np5mn1zq5l
    @user-np5mn1zq5l Před 2 lety +2

    Masha alah Masha alah betam dnke sra new ሙአዝ አሏህ ይጨምርልህ ፊዳከ አቢ ወዑሚ ያረሡለሏህ

  • @akremkiyar8693
    @akremkiyar8693 Před 2 lety +18

    ሀቢቢ ምርጥ ነሺዳ ይለያል 👌

  • @user-wu4kc9oq1p
    @user-wu4kc9oq1p Před 2 lety +1

    አሏሁመ ሶሊወሰሊም አላ ሰይድና ሙሀመድ

  • @amywid3547
    @amywid3547 Před 2 lety

    ቁዋይ ቢላሽ ወዜ ቢደርቅም
    አንቱ ተነክተዉ ዝምታ አላዉቅም 🥰🥰🥰

  • @attube383
    @attube383 Před 2 lety +43

    እባካችሁ ድምፅ ሁኑን
    ወድም እህቶችህ እያለቁነዉ
    የገጠር ልጆች የገበሬልጆች ነን
    በሳኡዲ እስርቤት በረሀብ በብርድ
    እየሞቱ እያበዱ ያሉት እባካችሁ
    እባካችሁ አየር አግኝቶ ለሀገሩ መሰዋት
    መሆን መታደል ነዉ😭😭😭💔💔💔💔

  • @thetruthway6934
    @thetruthway6934 Před 2 lety +2

    Mashallah naw muaz barta

  • @rahmantube8013
    @rahmantube8013 Před 2 lety +2

    ማሻአላህ ሀቢቢ
    ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ❤️❤️

  • @abdulhamidhussen3818
    @abdulhamidhussen3818 Před 2 lety +2

    muaze betam desylal mashala

  • @fatiyanasir3956
    @fatiyanasir3956 Před 2 lety +2

    ምርጥ ።ድምፅ አለህ የሙዚቃ መሣሪያዉን ብቻ አስወግደው ሙዓዝ
    በሙሉ ልብ ለማዳመጥ የሙዚቃ መሣሪያዉን።ተዉ
    ግጥሙ እንባዬን አፈሰሰው

    • @semiramohamed7169
      @semiramohamed7169 Před 2 lety

      የ ሙዜቃዎ መሣሪያም እያወደሠ ነዉ አይገባህም እንዴ

  • @esihakibnimuhammed1070

    Masha allah bro des yilal berta wandime

  • @kush4395
    @kush4395 Před 2 lety +2

    masha allah muaze international yehone sira

  • @rggf7752
    @rggf7752 Před 2 lety +1

    betam des yemel neshida new ♥♥tichilaleh mu, e

  • @rajuredwan2592
    @rajuredwan2592 Před 2 lety +2

    Wellahi sintun musica miyadamit yeneberen hizib eyekeyerenew yanta menzuma na neshida allah yichemrilih muaze 👌👌👌❤❤❤

  • @eliaskedir3419
    @eliaskedir3419 Před 2 lety +1

    S A W Masha Allah muaz Allah kante gar yehun

  • @ebsaibrahim1883
    @ebsaibrahim1883 Před 2 lety +1

    Masha allah bro betam ds ialal walahi allah itabiq

  • @abdoulhafidmohammed
    @abdoulhafidmohammed Před 2 lety +1

    አላሁመ ሰሊ ወሰሊም አላ ረሱሊክ ሙሀመድ

  • @adiluasinanzinab1624
    @adiluasinanzinab1624 Před 2 lety +1

    Allhumasela waselim alla nabiyina alla muhamad

  • @cud5619
    @cud5619 Před 2 lety +1

    እኔ ኢትዮጵያ ውሰጥ Maher Zain እንዳለ አምኛለሁ

  • @neimawolle6112
    @neimawolle6112 Před 2 lety +1

    Very nice nasheda

  • @farhantube
    @farhantube Před 2 lety +3

    Mash Allah mirx nashidaa naw

  • @user-te7qv8zc9m
    @user-te7qv8zc9m Před 2 lety +13

    ግጥሙን አንደኛ ማሻሀላህ በአቢቢማን አንደራደርም አንድና አድ ነገር የምንኖርለት እንጂ የምንኖርበት እምነት የለንም አልሀምዱሊላህ

  • @kadigamohamed2694
    @kadigamohamed2694 Před 2 lety +3

    ፊዳከአቢወኡሚ ያረሱለላህ ማሻአላህ

  • @zinethussein9599
    @zinethussein9599 Před 2 lety +1

    Endetelemedewu Geramy sera newu masha Allah zemawu demo yeleyal berta wendmachen Muaz Allah yetebkh

  • @user-ne8mk5mp2t
    @user-ne8mk5mp2t Před 2 lety +1

    ሰ ዐ ወ ማሻ አላህ ሙአዝዬ አላህ ይጨምርልህ🥰🥰🥰

  • @alhamedulillh149
    @alhamedulillh149 Před 2 lety +1

    ፊዳከ ሩሂ ያረሱለሏህ
    ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም

  • @selimamohammed7508
    @selimamohammed7508 Před 2 lety +1

    Mashallh wendime mirt sera

  • @umuhafiza9664
    @umuhafiza9664 Před 2 lety +2

    Masha'allah tabarakalah Rabbii siraa Haa jalatuu duniyaa fi akiratii sii Haa milkesuu
    Rabbii guyyaa boruu akiratii nama shafa'aa issanii argatuu sii hatasisuu

  • @abdulhakimhamid1755
    @abdulhakimhamid1755 Před 2 lety +1

    Allahe yakoyeh habibi hayatee

  • @mimibuna3431
    @mimibuna3431 Před 2 lety +1

    Allah...... kalat yelegnem beteley getmu

  • @user-xq7en4kc9n
    @user-xq7en4kc9n Před 2 lety +8

    ሙአዜ ወሏሂ ደስ የሚል ስራ ነውኮ የምሰራው አሏህ ይጠብቅህ ጀግና አሏህ ይጨምርልህ ማሻ አሏህ ማሻ አሏህ የኔ ምርጦች ቃል ያንሳችኋል 😭😭😭
    ሱለሏሁ አለይሂ ወሰለም
    ፊዳከ ኡሚ ወአቢ ያረሱለሏህ 😭😭😭😭😭

  • @ousmanmuhammed5068
    @ousmanmuhammed5068 Před 2 lety +1

    Welahi muazye tileyaleh hayatttt abo le allah biye ewedhalewu

  • @user-nb5sv2ep6j
    @user-nb5sv2ep6j Před 2 lety +1

    💚💚💚💚💚💚صلى الله عليه وسلم

  • @user-ps5vr2tc8y
    @user-ps5vr2tc8y Před 2 lety +5

    ፊዳከ ያ ረሱል አላህ😍😍🥰

  • @fariskemal3991
    @fariskemal3991 Před 2 lety +1

    ዋሪዳ 3 እስኪለቀቅ ናፍቆኛል

  • @juharashebir5081
    @juharashebir5081 Před 11 měsíci +1

    ምርጥ ነሽዳ ማሻአላህ ያረሱሎላህ

  • @hanakamil5593
    @hanakamil5593 Před 2 lety +2

    MashaAllah MashaAllah MashaAllah 💖💖💖💖💖💖💖💖💖💖💖💖💖💖💖💖

  • @user-jb9vu9nc5p
    @user-jb9vu9nc5p Před 2 lety +10

    አደኝ ነኝ መልካም ኸሚስስስስ ይሁንላቺሁ!!😍

  • @tofiknejib7812
    @tofiknejib7812 Před 2 lety +1

    Mashallah muaz Allah yichemrlh 💕💕💕💕💕💕💕

  • @user-yv1fq8kp2h
    @user-yv1fq8kp2h Před 2 lety +4

    ያሰላም ያሰላም አሏህ ይጠብቃችሁ ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም

  • @user-xe5dt7tz4n
    @user-xe5dt7tz4n Před 2 lety +2

    ማሻአሏህ ማሻአሏህ ማሻአሏህ አሏህ ይጨምርልህ ወንድማችን 😍😍😍ማሻአሏህ አለይክ ሶለሏህ አለይሒ ወሰለም

  • @vdhshdhshhd3811
    @vdhshdhshhd3811 Před 2 lety +2

    masha allah habibi 🥰🥰🥰🥰🥰🥰

  • @samrahjemal9589
    @samrahjemal9589 Před 2 lety

    yeallah lbn sersro yemigeba kalat kenedmts
    Leustaz seid ahmed hayat
    Dnk sra mashallah

  • @nesredintube227
    @nesredintube227 Před 2 lety

    ዋዉ ዋዉ ዋዉ ድንቅ ስራ ማሻ አላህ በሉለት ሙአዝ በርታ bro

  • @abdusalamusman4614
    @abdusalamusman4614 Před 2 lety +2

    ፊዳካ አቢ ወ ዑሚ ያረሱለላህ(ሰለላሁ ዓለይ ወሰለም) ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤ ዑስታዝ ሰዒድ አህመድና ወንድም ሙዓዝ በርቱ ምርጥ ሰራ ገና ከእናንተ ብዙ እንጠብቃለን

  • @alminatube5078
    @alminatube5078 Před 2 lety +1

    Masha Allah Muaze Wellahi Haruf Sera New Leb Yenekal Allah Yechemereleh Abul Fatih 👍

  • @alemneshlenti5699
    @alemneshlenti5699 Před 2 lety +1

    Wow masha allah keep going bro

  • @bushraahmed4920
    @bushraahmed4920 Před 2 lety +1

    ማሻ አሏህ

  • @mujahidintube
    @mujahidintube Před 2 lety +5

    ሙአዝዬ ማሻ አላህ ሀቢቢ አላህ ይጨምርልህ እንዳንተ አይነቱን ያብዛልን ❤❤❤🇪🇹🇪🇹🇪🇹

  • @school_life17
    @school_life17 Před 2 lety +4

    ማሻአላህ ሃቢቢ ትለያለህ እኮ ነሺዳ አንተ ብቻ ስራ

  • @Abdulkehar
    @Abdulkehar Před 2 lety +3

    አሰላት ወሰላም ዓለይከ ያ ረሱለላህ
    ቤዛ ይሁኖት ሙላው አካሌ ውዴዋ
    ምን አለኝ ሌላ. ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም

  • @fayoalemeri2119
    @fayoalemeri2119 Před 2 lety +2

    Sallalhuu allhee wassallam
    Mashaa allah !!! Allah yicamerllah bro

  • @umuhafiza9664
    @umuhafiza9664 Před 2 lety +1

    Fidak abbii waa umii
    Yaa rasulalah
    Fidak abbii waa umii
    Yaa habibalah
    Fidak abbii waa umii
    Yaa shafinaa
    Salalahu Aleyhii wasalam