ድንቅ ነው የሚሰግዱ ድንጋዮች ያሉበት ጅሩ ቅድስት አርሴማ

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 8. 04. 2021
  • የሚሰግዱ ድንጋዮች ያሉበት ጅሩ ቅድስት አርሴማ ጉዞ
    የጉዞ ማስታወሺያ ስለ ጅሩ ቅድስት አርሴማ
    ወደ ጅሩ አርሴማ መሄድ ለምትፈልጉ ከአ/አ ከተነሳችሁ የተሻለው አማረጭ በእነዋሪ መኪና በመሳፈር ደብረ ብርሃን ሳይገባ በሱሉለታ መስመር በሙከጡር አድርጎ ሲሃ ደብር መውረድ ከደብረ-ብርሃን ከተነሳችሁ ደግሞ ለሚ በሚለው መኪና በመሳፈር ሲያደብር መውረድ ወይም ከደብረ-ብርሃን ደነባ በሚለው መኪና ተሰፍሮ በሁለተኛ መኪና ወደ ሲያደብር መሄድ ይቻላል፡፡
    እኔ በሶስተኛው አማራጭ ስለነበር የተጓዝኩት አረፋፍጄ 11፡ 00 ሰዓት ላይ ሲያደብር ደረስኩ፡፡ እቃ በሚሸከሙ የአገሬው ትሁታን ልጆች አማካኝነት እቃዬን አስይዤ በነሱ መሪነት ጎዞ ወደ ታላቋደብር ቅድስት አረሴማ ዘጅሩ ተጀመረ፡፡
    አንድ እናት አርሴማ ለመድረስ ለደካማ 45 ደቂቃ ወይም 1፡ 00 ሰዓት ይወስዳል ነገር ግን ለበረቱት 30 ደቂቃ በቂነው ብለውኝ ነበር፡፡ ነገር ግን የአዋሳው ወደጄ ረጋ ብለህ ከተጓዝክ
    3፡00 ሰዓት ትፈጃለህ ብሎኝ ስለነበር ለጉዞ ስነሳ ሁለቱ ሃሳቦች ተጋጭተውብኝ ነበር፡፡ ነገር ግን በጉዞው ያረጋገጥኩት አዋሳው ወዳጄን አባበል እውነትነት ነበር፡፡
    ክፍል አንድ
    በሰዓቱ ሊዘንብ ይከጅል ስለ ነበረ እሩጫ በሚባል እርምጃ ሜዳውን ጨርሰን ሸለቆውን ለመጀመር 25 ደቂቃ ወሰደብን።
    ክፍል ሁለት
    ሸለቆው (ገደሉ) ልክ ከፎቅ በደረጃ መውረድ ያህል ነበር፡፡ ቁልቁለቱ ጉልበት ያብረከርካል ዝም ብሎ ወደ ታች መውረድ አሁንም መውረድ ብቻ ነበር፡፡
    በተለይ መንገዱ አንድ አንድ ቦታ በሁለት እግር ብቻ መውረዱን ትጠራጠሩና የቀሩትን ሁለቱንም እግራችሁን ማለት እጃችሁን መጠቀም ግዴታ ይሆናል፡፡
    ለነገሩ እኔ ገና ከመነሻው የአገሬውን ልጆች በትር ይዤ ስለ ነበር በለሶስት እግር ነበርኩ፡፡ሶስቱን ስጠራጠር ደግሞ አራተኛውን እየተጠቀምኩ ቁልቁለከቱን ገፋውት፡፡
    በነገራችን ላይ የቁልቁለቱ ነገር ሲነሳ ሸንኮራ ዩሀንስን ደብረ ይሰበይ አቡነ ሀብተማሪያም ገደምን ያየ ትልቅ ቁልቁለት አይቻለው ብሎ የሚል ሰው ካለ ጅሩ አርሴማ መጥቶ ቢያይ እጁን በአፉ ይጭናል፡፡
    እኛ መኪና ውስጥ 30 ደቂቃ ቢፈጅ ነው ያሉኝ የደነቧዋ እመቤት ስመለስ ሁለተኛ እንደዚህ አይነት ስህተት እንደይሰሩ ሰዓት ልገዛላቸው በጉዞው ላይ ተመኝቼ ነበር። ሸለቆው አንድ ሙሉ ሰዓት ብቻውን ፈጅቶብን ቁልቁለቱን አገባደድነው፡፡
    ክፍል ሶስት
    ግማሽ ቁልቁለት እና ተዳፈት መሰል ሜዳማ መንገድ ለመጨረስ በተጨማሪ 30 ደቂቃ ወስዶብን በአጠቃላይ መንገድ ላይ አንዴ ከአረፍንበት ጭምር ጥሩ ተጓዥ በሚያሰኝ አከሄድ ከሁለት ሠዓት የእግር ጉዞ በኋላ ተምረኛዋ ደብረልዕልና ቅድስት አርሴማ ደብር ወደ አንድ ሰዓት ገደማ ደረስን፡፡
    ልክ አርሴማ ስትደርሱ እግር አጥበው መዝግበው የማረፍያ ስፍራ ይሰጡዋችዋል፡፡ እኔ የደረሰኝ አደራሽ ተብሎ በተለምዶ ከሚጠራው የፀሎት ቦታ በረንዳው ላይ ነበር፡፡
    ይህንን ሁሉ ገዳል ወርጄ በግምት ከሁለት መቶ ሰው በቦተው ላይ ስመለከት በጎዞው ተፈጠረው ድካም ልክ እንደ ጉም በኖ ጠፋ፡፡
    በተሰጠኝ ቦታ አነጣጥፌ በቀድሞቹ መጪዎች በተደረገልኝ የትህትና አቀባበል እየተደሰትኩ ጎኔን ከመሬት ጋር ወደ ሶስት ሰዓት ገደማ አገነኘውት፡፡
    ከተመለከትኩት እና ከአስደነቁኝ ነገሮች መሀከል እዛ ካለው ሰው ከአንድ ሶስተኛው የመንፈስ ችግር አለበት፡፡
    አብዛኛው ደግሞ ዛር፤ ውቃቢ ፤ቃልቻ የሚባለው የሰይጣን አይነት ነው፡፡ በእርግጥ ሌሎችም ህመምተኞች ቢኖሩም እነዚህ ግን ቦታው ይልቃሉ፡፡
    ከእነሱ መሀል ጥቂት የሚያስቸግሩም በለሰንሰላቶች ቢኖሩም አብዛኞቹ ግን ሰው ሳያስቸግሩ ወደ ገደልም እንግባ ሳይሉ የሚኖሩ መሆናቸውን ስታዩ የእግዚአብሔር ጠብቆት ምንያህል ከሰይጠን ክፋት በላይ መሆኑን ትረደላችሁ፡፡
    እንደሁም የሚያመውን ሰው ምትለየዩት በፀሎት ሰዓት የሚሆነው ካያችሁ በሃላ ነው፡፡ እንደው ደህና መስላቹ ሲያጫውታችሁ ውልና በመሃከል ከት ብሎ ስቆ እኔ እኮ ሰይጣኑ ነኝ አሳ ወይም እሱ አይደለም ብሎ ሊስቅባችሁ ስለሚችል ጤነኛውን ከባለመንፈሱ ለመለየት ዋል አደር ማለት ይጠይቃል።
    እዚህ ቦታ ከሚያስገርመው አንዱ ደግሞ ይህን ያህል ሰው እንዴት አንደመጣ ስታጣሩ ተልከው እንደመጡ ትሰማላችሁ፡፡ ከዬት ብትሉ ከፃድቀኔ ማርያም፤ ሽንቁሩ ሚከኤል፤ከመሳሰሉት የሚል ይሆናል፡፡
    በነገራችን ላይ ከዚህ ተልከው ወደ ሌላ ቦታ የሚሄዱም አሉ፡፡ ለምሳሌ ወደ ታላቋ የወሎ ሲርንቃ አርሴማ ገዳም የተላኩና የወጡ ሰዎች በብዛት አይቻለው፡፡
    እንዴት ነው መልዕክቱን የሚያገኙት ብትሉ?? በሁለት አይነት
    መልኩ የሚለው መልስ ይሆናል ፡፡ ይህም ማለት አንዱ በራዕይ ሁለተኛው ደግሞ መንፈሱ ሲለፈልፍ መውጫውን ቦታ ስለሚጠቁም ነው። በነገራችን ላይ ይህ ነገር የሆስፒታሉን referral system አስታውሶኛል፡፡
    አንዳንዶች እንደውም ሰማእቷ ከረዳችኝ መልሱን አገኛለሁ ካለሆነም referral ይጻፍልኛል ይላችኋል ፡፡አይገርምም ????
    ሰማእቷ ቅድስት አርሴማ የምትታወቀው ዘንባባ በመያዟ ሲሆን ( በነገራችላይ ጽዋ የያዘችውን ስዕል በአብዛኛው በኢትዮጵያ የአርሴማ ሚባለው የቅድስት ባርባራ ስዕል መሆኑን እዚ ላይ ያጠይቅዋል ) ታዲያ በድብሩ ዙሪያ ያሉ ድንጋዮች ተፈንቅለው ሲከፈሉ የዘንባባ ምስል መገኘቱ የቦታውን ታምራተኛነትን ያረጋግጣል።
    እንደሁም አንዳንዱ በቅጠል ቅርጽ ዘንባባውን እያስቀረጹ ፊቱን መስቀል በማድረግ በስተው ማንጠልጠል የተለመደ ሲሆን እኔም ለበረከት አንድ ሁለት ደርሶኛል በደበሯ ሁሉም ሰው የሚጠቀምበት አንድ ብዙ ሰው የሚያስተናግድ ሽንት ቤት ነበር፡፡
    አሰራሩ በተራራ ጫፍ ላይ ስለነበር ከስራ ጥራቱ ጉድለትም በላይ ንፋስ የሚወዘውዘው በመሆኑ የሚያሰጋ ሽንት ቤት ነበር፡፡በቀን 1/13/2003
    በማታ የአንድ ሰአት ጸሎት ላይ ፤ሁሉም ምህላ ገብቶ በነበረ ጊዜ የተወሰኑ ሰዎች የጸበል ብዛትም ይሁን የሆድ እክል ሲያስቸግራቸው ሽንት ቤት ገብተው ጉዳያቸውን ፈጽመው እንደወጡ ሽንት ቤቱ ፈረሰ፡፡ ወይም በቀላል ቋንቋ ሰጠመ።
    ነገር ግን አንድም ሰው ላይ አደጋ አለማጋጠሙ ትልቅ ድንቅ ተአምር ነበር ፡፡ እንዴት ብትሉ????
    ከመጨረሻዎቹ ወንድ ተጠቃሚዎች መሀከል አንዱ ሽንት ቤቱ ከመሰጠሙ ጥቂት ደቂቃዎች በፊት እዛ ሆኖ ዛሬ ይቺን ሽንት ቤት ምን ያርገበግባታል?? ሲል እንደነበር የሰሙት ሰዎች ነግረውኛል።
    በተለይ ሽንት ቤቱ ሲፈርስ የተፈጠረው ድምጽ የጸሎት አዳራሽ በመሰማቱ ጸሎቱን ከደጅ ከሚሳተፉት መሃከል ሰው አብሮ ሰጥሞ ይሆናል ያሉ የተወሰኑ ሰዎች እየተራራጡ ሽንት ቤቱ ቢደርሱ እዛው የነበረችው የመጨረሻዋ ተጠቃሚ በኩራት ( በኮንፊደንስ ) አትደንግጡ እኔነኝ የመጨረሻዋ
    ተጠቃሚ ብላ መጪውን ሰው አታረጋጋውም!!!!!!!! ድንቅ የእግዚአብሔር ተዓምር አትሉም???
    ወይ አርሴማ በደጇ መጥቶ የሚማጸነውን ትፈውሳለች እንጂ ሽንት ቤት እንደማትጨምር አረጋግጣ ተአምሯን አሳየች!!!!!!!
    ደብሯ ከጸበል አገልግሎት ውጪ በዋናነት የአርምሞ የሱባኤ ስፍራ ናት ለዚህ አገልግሎት የተዘጋጁ ሁለት ዋሻዎች አሉ ፡፡
    አንደኛው በጣም ሞቃት ሲሆን ሌላኛው በጣም ቀዝቃዛ ነው
    በዋሻው የቆይታ ጊዜ በቀን መውሰድ የሚቻለው አንድ በውኃ የራሰ እፍኝ ሽንብራ እና አንድ ኩባያ በሶ ብቻ ይሆናል ውኃ የሚፈልግ በሶውን ትቶ በአንድ ኩባያ ውኃ መቀየር ይችላል።
    በቅደስት አርሴማ የቆይታ ጊዜው ከሌሎች የሱባኤ
    ስፍራዎች ይለያል። መልስ ያገኘ በማግስቱም ይወጣል ያላገኘ ወይም ቆይ የተባለ ደግሞ ይቆያል ነገር ግን የሱባኤው ትንሹ ቀን ሶስት ቀን ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል ፡፡
    ሱባኤ መግባት አብዛኛው ሰው የሚያደርገው የተለመደ ጉዳይ ሲሆን ይልቁን መንፈሳዊ ልምምድ የሌላቸው ጫትና መጠጥ ትተው አሁን እንደመጡ አደራሽ ውስጥ ሲናገሩ የሰማኋቸው አፋቸው ላይ ጨርቃቸውን አስረው በዚህ ቅዱስ ስፍራ ሳያቸው
    መለወጣቸው አስገርሞኝ ኦርትዶክስ ለዘላለም ትኑር ብዬ ልጮህ ከጅሎኝ ነበር ፡፡ ነገር ግን እኔም አርምሞ ላይ መሆኔ ትዝ ሲለኝ........ ተውኩት
    በነገራችን ላይ የዋሻው የውስጠኛው ክፍልን አላስተዋወቅካችሁም አይደል ??? ዋሻው ከውስጡ ሲታይ የሚመስለው......... ይቅርታ......ተውት...... ለካ ዋሻው ይታያል እንጂ አይተረክም።

Komentáře • 186

  • @afomiyatube3638
    @afomiyatube3638 Před 3 lety +21

    ኢትዬጵያዊነት ተዋህዶነት የሚባለው ለዚህ ነው ይህ ሁሉ ቃልኪዳን እያለ መቼም እንደ ክፋታችን አይተወንም ስለ ቅዱሳን ብሎ ሃገራችን ስላሙን ያምጣልን
    በስደት ላለነው ለደጇ ያብቃን
    አንደበቴም ያውጣ የምስጋና ቅኔ
    የአምላኬን ማዳን አይቻለሁ በዐይኔ
    በገባኦን ሰማይ ፀሐይን ያቆመ
    ዛሬም ጎብኝቶኛል እየደጋገመ
    /////////////
    ወጥመድ ተሰበረ እኔም አመለጥኩኝ
    ከኃጢአት ፍላፃ ከሞት አተረፈኝ
    የአናብስቱን አፍ በሃይሉ የዘጋ
    የዳንኤል አምላክ ይኖራል ከእኛ ጋ
    ////////
    በዳዊት ምስጋና በያሬድ ዝማሬ
    ከቅዱሳን ጋራ ልዘምር አብሬ
    እርሱን ሳመሰግን ሜልኮል ብትስቅብኝ
    ለጌታዬ ክብር እዘምራለሁኝ

  • @tghh1076
    @tghh1076 Před 3 lety +20

    እደት አደራቺሁ የእሙየ ኦረቶደክሠ ልጆቺ 👏👏👏 አምላኬ ሆይ ለደጂህ አብቃኚ እደናፈቀኚ እዳልቀረ አደራከነ 😭😭😭

  • @afomiyatube3638
    @afomiyatube3638 Před 3 lety +19

    ስማዕቷ ቅድስት አርሴማ በረከቷ ይደርብን
    እፁብ ድንቅ ነው የእሱ ስራ ወንድማችን ቃለ ህይወት ያስማልን ግን ብዙ ጊዜ የጉዞ መርሃግብር ሳይ ሴቶች ናቸው ይበልጡን ዋው
    ለሁላችሁም ዝማሬ መላእክት ያስማልን
    ጽኑ ሰማዕት የእምነት አርበኛ
    አርሴማ ነይ ነይ ወደ እኛ
    ➕ አዝማች ➕
    ነይ ነይ ፡፡፡፡፡፡፡ ቅዱስ አትናትዮስ
    ነይ ነይ ።።። በስዕለት ያገኙሽ
    ነይ ነይ ።።። ብሉይን ከሀዲስ
    ነይ ነይ ።።። ጠንቅቀሽ የተማርሽ
    ነይ ነይ ።።። በፍፁም ትህትና
    ነይ ነይ ።።። በጸሎት የተጋሽ
    ነይ ነይ ።።። አርሴማ ልዩ ነሽ
    ነይ ነይ ።።። አምላክ የመረጠሽ
    ➕ አዝማች ➕
    ነይ ነይ ።።። ውበትም ሀስት ነው
    ነይ ነይ ።።። ደም ግባትም ከንቱ
    ነይ ነይ ።።። ንብረት ትዳር ሁሉ
    ነይ ነይ ።።። አላፊ ውዕቱ
    ነይ ነይ ።።። ንግስት መባልን
    ነይ ነይ ።።። በፍፁም ሳትሻ
    ነይ ነይ ።።። አለምን በመናቅ
    ነይ ነይ ።።። ገባች ወደ ሻዋ
    ➕ አዝማች ➕
    ነይ ነይ ።።። አረመኔው ድርጣድስ
    ነይ ነይ ።።። ቢያሰቃይሽም
    ነይ ነይ ።።። ውበቴ ክርስቶስ
    ነይ ነይ ።።። ነው ብለሽ ሰበክሽ
    ነይ ነይ ።።። አንገትሽን ለስይፍ
    ነይ ነይ ።።። አሳልፈሸ ሰጠሽ
    ነይ ነይ ።።። ክብርሽም ተገልጾ
    ነይ ነይ ።።። ለአለም አብራሽ
    ➕ አዝማች ➕
    ነይ ነይ ።።። አርአያ ልትሆኝን
    ነይ ነይ ።።። ለእኛ ለሁላችን
    ነይ ነይ ።።። ፈፀመሽ አሳየሽ
    ነይ ነይ ።።። ታላቅ ተጋድሎሽን
    ነይ ነይ ።።።ይህን አለም ድል መንሳት
    ነይ ነይ ።።። አቅቶናል እና
    ነይ ነይ ።።። አርሴማ አትለይን
    ነይ ነይ ።።። በእምነት እንድንጸና

  • @user-tl6bw7qz9j
    @user-tl6bw7qz9j Před rokem +3

    አወ ቦታው በጣም ልዩ ነው ❤❤❤በእግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ሒጄ ነበር 🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉በጣም እፁብ ድንቅ ነው❤❤❤❤❤❤❤

  • @tesfatesfa3181
    @tesfatesfa3181 Před 3 lety +16

    የናታችን የቅድስት አርሴማ እርዴት በርከት ይደርብን አሜን ለናንተም እድሜ እና ጤና ይድጣችሁ በጣም ደስ የሚል ነው

    • @alsaethio8434
      @alsaethio8434 Před 3 lety

      እመብርሀን ሀገራችንን እባክሽ ካሐችበት ነገር ልጅሽ በጥበቡ ይፈውሳት

  • @AynalemShiferaw-pn2sx
    @AynalemShiferaw-pn2sx Před rokem +1

    ሰማአቷ ቅድስት አርሴማ እኛ ስደተኛ ልጆቿን ላገራችን አብቅታን ገዳሟን ለመርገጥ ታብቃን አሜን🙏🙏🙏እናተንም ከክፉ ነገር ትጠብቅችሁ እናቴ አርሴማ🤲🤲🤲❤️❤️

  • @user-hw5gc1oi6o
    @user-hw5gc1oi6o Před 3 lety +8

    በእውነት በረከታችሁ ይድረሰን መታደል ነው ይህን ታሪካዊ ቦታ ማዬት አቤቱ እኛንም ከስደት መልስ ለደጇ ያብቃን አሜን አሜን አሜን
    ወንድማችን በእውነት ፀጋውን ያብዛልህ የአባቶቻችን ፆሎት አይለዬን አሜን

  • @tsialex8124
    @tsialex8124 Před rokem

    ጀሩ አርሴማ ተአምራዊ ገዳማ ፈጣሪ ፈቅዶልኝ ሄጄ ድንቅ ተአምራዊ ገዳም መሆኑን አይቼዋለው ዜና ማርቆስም እንዲሁም በአካባቢዋ ሌሎችም ገዳማት አሉ እግዚአብሄር ይመስገን ለዚ ክብር ያበቃህኝ አባት እናቴ አርሴማ ምልጃዋና በረከቱ በላያችን ላይ ይደር ቃለጨህይወት ያሰማልን ወንድማችን ያገልግሎት ዘመንህን ይባርክልን ተባረክ 🙏🙏🙏

  • @user-mt1mw1wk6y
    @user-mt1mw1wk6y Před 3 lety +5

    አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን የእናታችን
    የቅድስት አርሴማ በረከቷ ይደርብን 🤲

  • @user-qj8xu9hy8b
    @user-qj8xu9hy8b Před 3 lety +4

    የእናታችን ቅድስት አርሴማ ረድኤት በረከት ይደርብን ቃለሂወትን ያስማልን

    • @geraratube12
      @geraratube12 Před 3 lety

      ሰላም የተዋሕዶ ልጆች በዩቲዩብ ቻናላችን መንፈሳዊ ትምህርቶችን ስለጀመርን ኑና እንማማር።
      czcams.com/channels/hNJurk853lL0mZKyhyU_lA.html
      🌷

    • @bogalechasena6535
      @bogalechasena6535 Před 3 lety

      Amen Amen Amen

  • @mulu778
    @mulu778 Před rokem

    በምልጃሽ የተገለጥሽልኝ ደጋ አዛኟ እናቴ ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ በተሰጠሽ ፀጋ ለደጂሽ አብቂኝ አሜን አሜን አሜን

  • @user-wj3sc6wy7o
    @user-wj3sc6wy7o Před 3 lety +4

    በአረብ ሃገር ሆኔ ቤተክርስትያን ገዳማት እንዴት እንደናፍቀን እግዚኣብሔር ሆይ ሁላችን ስደተኛች ለሃገራችን ኣብቃን አሜን ቃል ሂወት ያስማልን ፀጋውን ያብዛልህ መምህር

  • @fntrggboy19
    @fntrggboy19 Před 3 lety +4

    የእነቶቻችንነ የአባቶቻችን በረከት ይደርብን

  • @selamyemariyamlij5630
    @selamyemariyamlij5630 Před 3 lety +1

    በረከታችሁ ይድረሰን ሰማእቷ ለድሽ አብቂን አባታችን ቀውስጢወስም ለደጅህ አብቃን በረከትን ለማግኘት ያብቃን

  • @naniyoutube-iq9tu
    @naniyoutube-iq9tu Před rokem +1

    የኔ አባት ስላየሁህ በጣም ደስ ብሎኛል ባሳዝነው ሙላቱ

  • @tttthhhy3456
    @tttthhhy3456 Před 2 lety

    የናታችን የቅድስት አርሴማ በረከቷ ይደርድብን

  • @ganatganat3042
    @ganatganat3042 Před 3 lety +1

    እግዚአብሔር ይመስገን ፈጣሪሆይ ለዚች ለተቀደሰች ቦታ አብቃኝ ለንሰሐሞት አብቃኝ
    ፈጣሪሆይ በቸርነትክ አስበን አሜን

  • @roozrooz2804
    @roozrooz2804 Před 3 lety +1

    amen amen amen❤❤❤❤❤❤👂👂🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇬🇳🇬🇳🇬🇳🇧🇯👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏

  • @user-fs3xt6yx7i
    @user-fs3xt6yx7i Před měsícem

    ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤amen amen amen amen yetsedeku berket yedersen yegitachin yamelakachin chernet yedersen!!!!

  • @user-tl6bw7qz9j
    @user-tl6bw7qz9j Před rokem

    ስለሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመሥጌን

  • @massaratedabala2109
    @massaratedabala2109 Před 3 lety +1

    ቃለ ህይወት ያሰመልን እግዚአብሄር ያብርልን አባታችን ወንድማችንም ያብስራ እግዚአብሄር ፀጋውን ያብዛል

  • @gechietube2943
    @gechietube2943 Před 2 lety

    የአባታችን አቡነ ቀወስጦስ ረድኤት በረከት እና ለእናታችን ቅድስት አርሴማ ረድኤት በረከታቸው ይድረሰን በባእዳን ሀገር የአቡነ ቀወስጦስ አማላጅነት አይለየን አሜን አሜን አሜን

  • @user-ef2ko2xd9r
    @user-ef2ko2xd9r Před 3 lety +4

    በእውነት በጣም ደስ ይላል የእናታችን የቅድስት አርሴማ በረክት ይደርብን ከስደት መልስ ለደጂዋ ታብቃን አሜን

  • @destatesfaye4373
    @destatesfaye4373 Před 3 lety +1

    ሰማዕት ቅድስት አርሴማ ሆይ አደራሽን ለሀገራችን ለቤተሶቻችን ምህረት አሰጭን የበረከቱ ተካፋን እንሆን ዘንድ እርጂን

  • @betedesta66
    @betedesta66 Před rokem

    አሜን አሜን አሜን ቃለ ሕይወት ያሰማልን ይህን የመሰለ የተቀደሰ ቦታ ስላሳያችሁን እግዚአብሔር ይስጥልን። ሰማእቷ እናቴ ቅድስት አርሴማ በአለንበት ሁሉ ከኛ አትለይ በፀሎትሽ አስቢን

  • @welatamedinmaryam1520

    የሰማእቱ የቅዱስት አርሴማ ጥበቃዋ አይለየን እናቴ አርሴማ

  • @serkalmyoutube235
    @serkalmyoutube235 Před 3 lety

    በርታ ወንድማችን እግዚያአብሔር አምላክ ለክብር ደጇ ያብቃን ቅድስት አርሴማ

  • @We-ws1pe
    @We-ws1pe Před 3 lety

    *በረከታችሁ ይድረሰኝ የናታችን የቅድስት አርሴማ እረድኤት በረከቷ ይደርብን አሜን አሜን አሜን እናመሰግናለን ወንድማችን ፀጋውን ያብዛልህ*

  • @user-kw6md7ur1z
    @user-kw6md7ur1z Před 3 lety +1

    አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወትን ያስማልን
    በጣም ታምር ነው የናታችን የቅድስት አርሴማ በረከታ አረዴታ ይደረብን አሜን
    ለደጆ ታብቃን ❤🙏🙏🙏
    እናመሰግናለን ያብስራ ወንድማችን🙏
    ከበረከቱ እንድንሳተፍ ስላደረከን❤🙏🙏🙏

  • @thehaytesfaye9674
    @thehaytesfaye9674 Před rokem

    ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ለደጅሽ አብቂኝ እናቴ፣ አማላጄ ፣ አትተዩኝ አደራ የጅሩዋ !!!

  • @janetkonjo548
    @janetkonjo548 Před 3 lety +6

    እንደምን አደርክ ወንድማችን

  • @salamisalami6409
    @salamisalami6409 Před 2 lety

    አሜን አሜን አሜን
    🇪🇹🇪🇹🇪🇹

  • @kalkidangane8072
    @kalkidangane8072 Před 3 lety

    እግዚአብሔር ይመስገን

  • @yehilwuhahabtam6617
    @yehilwuhahabtam6617 Před 3 lety

    አሜን አሜን አሜን ቃል ህይወት ያሰማልን

  • @tsedeysintayehu1005
    @tsedeysintayehu1005 Před 2 lety

    የሰማእቷ በረከት ይደርብን ደጇን ለመርገጥ ያብቃን

  • @Hana-iy5re
    @Hana-iy5re Před rokem

    አሜን❤❤❤❤❤😭❤❤❤

  • @shweitbinegede8856
    @shweitbinegede8856 Před 3 lety

    ዝማሬ መላእክት ያሰማልን አሜን አሜን አሜን

  • @cellcell7941
    @cellcell7941 Před 3 lety

    የናታችን ቅድስት አርሴማ በርከት ይደርብን እግዚአብሔር አምላክ ከስደት መልሰህ ለደጂህ እንድደርስ ፍቃድህ ይሁን አሜን ወንድማችን እግዚአብሔር እድሜ ጤና ይስጥልን

  • @selethio6023
    @selethio6023 Před 2 lety

    አሜን አሜን ሰማአቶ ቅድስት አርሴማ በረከቶ።ጥበቃዋ ይደርብን ለደጆአ ያብቃን🙏🙏

  • @fathimafathima5444
    @fathimafathima5444 Před 3 lety

    Amen amen amen thank you

  • @yodettareku1738
    @yodettareku1738 Před 3 lety

    አሜን አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን ፀጋውን ያብዛልን አሜን አሜን አሜን አሜን

  • @user-eb2zh5zh2z
    @user-eb2zh5zh2z Před 3 lety

    እግዚአብሄር ይስጥልን ወንድማችን ድንቅ ነገር ነዉ ያሳየኸን። የልኡል እግዚአብሄር ስም የተመሰገነ ይሁን። አካዉንታቸዉን ላክልን።

  • @zelujira8811
    @zelujira8811 Před 3 lety +1

    ቃለ ህይወት ያሰማልን ሰማዕት ቅድስት አርሴማ በበረከቱዋ በአማላጅነቱዋ እኔንም መላው ቤተሰቤንም ትርዳን ትጠብቀን አሜን አሜን አሜን ይደረግልን ለደጅዋ ለመሳለም ታብቃን ከነመላው ቤተሰቤ ጋር።

  • @gattusojgtpw1899
    @gattusojgtpw1899 Před 3 lety

    የአባቶቻችንበረከታቸውይደርብን
    💚💛❤🌹🌹🌹🌹🌹

  • @hiymnotgerwerk5626
    @hiymnotgerwerk5626 Před 3 lety +4

    እግዚአብሔር ከፈቀደ ብሄድ ደስ ይለኛል 🙏😍😍😍

  • @fikinesheth6658
    @fikinesheth6658 Před rokem

    አሜን አሜን አሜን ቃለ ሀይወትን ይሰማልን አባታችን

  • @user-sy4rl8wr6x
    @user-sy4rl8wr6x Před 3 lety

    ዝማሬ መላእክት ያሰማልን የናታችን የቅድስት አርሴማ እረድኤት በረከት ይደርብን አሜን አሜን አሜን

  • @wubalem6806
    @wubalem6806 Před 3 lety

    Amen amen amen 🙏🙏🙏🙏🤲🤲🤲

  • @feritaferita4160
    @feritaferita4160 Před 2 lety

    Amen Amen Amen Amen Amen Amen Amen Aresma tetabekan

  • @zniu2528
    @zniu2528 Před 3 lety

    🙏🙏🙏🙏🙏በረከታችሁ ይደርብን የናታችን ቅድስት አረሴማ ረድኤት ይደረብን

  • @betigebeyehu2171
    @betigebeyehu2171 Před 3 lety

    ቃሉህይውት ያሰማልን የአገልግሎት ዘመንህን ያርዝምልን አሜን አሜን አሜን
    ዝማሬ መላእክት ያሰማልን።

  • @rahelmesfin4182
    @rahelmesfin4182 Před 3 lety

    Amen amen amen 🙏🏼

  • @gigigtdik.werede3356
    @gigigtdik.werede3356 Před 3 lety

    አሜን ቃል ህወሃት ያሰማልን

  • @eteneshyoutub4873
    @eteneshyoutub4873 Před 3 lety

    ቃለህይወት ያሰማልን አሜን አሜን አሜን እግዚአብሔር ይመስገን

  • @Wildrose_16
    @Wildrose_16 Před 3 lety

    አሜን ሰማእቷ አርሴማ ለደጅሽ ያብቃኝ እግዚአብሔር ይባርካችሁ ስለጋራችሁን ድንቅ ስራውውን

  • @asterbelay3565
    @asterbelay3565 Před 3 lety

    አርሴምዬ ፍቃድሽ ይሁንና ደጂሽን ልርገጥ ።

  • @sabasaba840
    @sabasaba840 Před 3 lety

    Amen Amen Amen 🙏🙏

  • @tsehaygebru6438
    @tsehaygebru6438 Před 2 lety

    Berktachw yedrbin Amen amen 🙏🏽 🙏🏽🙏🏽🙏🏽🙏🏽🙏🏽

  • @kalkidangane8072
    @kalkidangane8072 Před 3 lety

    አሜንአሜንአሜን

  • @shitagetaw4210
    @shitagetaw4210 Před 3 lety

    አሜን አሜን አሜን

  • @kibinishdagu4575
    @kibinishdagu4575 Před 10 měsíci

    Amen amen amen

  • @comceil5329
    @comceil5329 Před 3 lety +1

    እናቴ ቅድስት አርሴምዬ ለደጅሽ አብቂኝ 😢😢😢የነገርኩሽን አደራሻኝ ምልጃሽ አይለየን
    ቃለ ህይወት ያሰማልን

  • @ethiopialezalalemtenure3220

    Emabyate kedeste Aresama ledajeshe abekine hagerachin selam adereglin

  • @sdgs6877
    @sdgs6877 Před 7 měsíci

    አሜንንአሜንን

  • @tegistytegisty5951
    @tegistytegisty5951 Před 3 lety

    ቃለ ሕይወትን ያሰማልን የቅዱሳኑ ምልጃ ፀሎታቸው አይለየን በጣም እመኛለሁ ገደም ለመሄድ አምላከ ይርዳኝ

  • @abebahabte8469
    @abebahabte8469 Před 3 lety +2

    ብርክተዋ ይድርብን 👏🙏🙏
    ተዋህዶ አድረገህ ስለፈ ጠ ርከ ኝ በጣም አምስግንሃለው 🙏😘😘🙏
    ደስታዬ ወሰን የለውም !

  • @user-up7tp8il3u
    @user-up7tp8il3u Před 3 lety

    ለዚህ ክብር ያብቃን መድሃኒ አለም ቕድስት አርሴማ በረከቱዋ አይለየን

  • @misrakabebe8486
    @misrakabebe8486 Před 3 lety

    የእናታችን በረከቷ ይደርብን

  • @bertukanmelse6586
    @bertukanmelse6586 Před 3 lety

    ቃለህይወትያሰማልን

  • @assiassi9863
    @assiassi9863 Před 3 lety

    የናታችን የቅድስት አርሴማ በረከት ይደርብን ዝማሬ መላህክት ያስማልን እኛንም ለሀገራችን የፈጣሪ ፍቃድ ሆኖ ለደጆ ያብቃን ዝማሬ መላህክት ያስማልን አሜን አሜን አሜን

  • @kalkdan4521
    @kalkdan4521 Před 3 lety

    አሜን አግዚአብሔር ይመስገን አንኳን ደና መ ጣህ ውንድማ ችን

  • @hebtshhebtsh818
    @hebtshhebtsh818 Před 3 lety

    ወድማች እናመሠግናለን በርታልን

  • @user-bs8wb7nz4r
    @user-bs8wb7nz4r Před 3 lety

    ቃለ ህይወት ያስማልን በስደት ያለነውን ላገራችን አብቅቶን ደጇን ለመርገጥ ያብቃን

  • @MonaMona-xb2yk
    @MonaMona-xb2yk Před 3 lety

    ዝማሬ መላእክትን ያሰማልን እግዛቤሄር ከፍቀደ ከስደት መልስ ለደጆ ታብቃኝ እግዛብሄር ይስጥን በርቱ ሁሉም የሚናፍቀዉ ከሀገር የራቁ ለትነዉ

  • @yidnecr7242
    @yidnecr7242 Před 2 lety

    Amen kale hiwot yasemalen

  • @Sasa-lf2es
    @Sasa-lf2es Před 3 lety

    እግዛብሔር፡ይመስገን፡የአቡነ፡ቆዎጦስ፡በረከታቸዉ፡ይደርብን

    • @geraratube12
      @geraratube12 Před 3 lety

      ሰላም የተዋሕዶ ልጆች በዩቲዩብ ቻናላችን መንፈሳዊ ትምህርቶችን ስለጀመርን ኑና እንማማር።
      czcams.com/channels/hNJurk853lL0mZKyhyU_lA.html
      🌷

  • @user-xd8by8kb8n
    @user-xd8by8kb8n Před 3 lety +1

    ለደጁ፣ያብቃን፣አድራሻውን፣ብታስቀምጥልን፣ወንድማችን

    • @libonatube
      @libonatube  Před 3 lety +1

      በዲስክሪፕሽን ላይ አስቀምጫለው እህቴ

    • @user-xd8by8kb8n
      @user-xd8by8kb8n Před 3 lety

      @@libonatube አመሰግናለሁ

  • @user-ef8cz5rl4k
    @user-ef8cz5rl4k Před 3 lety

    እግዚአብሔር ይመስጌን

  • @maryelove7751
    @maryelove7751 Před 3 lety

    ዝማሬ መላይክትን ያሰማል የክርስቶስ ቤተስቦች እሽ እንደ ጌታ ፈቃድ ያቅማችን እናግዛቼዋለን

    • @geraratube12
      @geraratube12 Před 3 lety

      ሰላም የተዋሕዶ ልጆች በዩቲዩብ ቻናላችን መንፈሳዊ ትምህርቶችን ስለጀመርን ኑና እንማማር።
      czcams.com/channels/hNJurk853lL0mZKyhyU_lA.html
      🌷

  • @genetemaryam9368
    @genetemaryam9368 Před 3 lety +1

    የተወለድኩበትን ቦታ ድንቅ ታዓምር ቦታ እዚያ ሆኜ ዛሬ በስደት ገባኝ አምላክ ሆይ በሰላም ለደጅህ አብቃኝ😭😭😭✝️✝️

  • @emujiru1797
    @emujiru1797 Před 3 lety

    ወንድሜ እናመሰግናለን ለደጅሽ ዳግም እንድመጣ አብቂኝ እናቴ አርሴማ በስደት ያላችሁ እህቶቼ ለደጇ ታብቃችሁ ሃገሬን ስላሳየከንእናመሰግናለን በርታ በዛዉም ጅሩ ዜና ማርቆስንም አሳየን አሁን መኪና ስለገባ አያስቸግርም ጅሩ አርሴማ ሁለተኛዋንም ከእነዋሪ በታች ያለችዉን

  • @user-kb1ph7yy1o
    @user-kb1ph7yy1o Před 3 lety +1

    ሠላም እንዴት አደራቹ የልኡል እግዚአብሔር ቤተሰቦች አርሴምዬ በያላቹበት አርሴምዬ ትጠብቀን
    ከስደት መልስ ለደጇ ታብቃን ቅድስት አርሴማ

    • @geraratube12
      @geraratube12 Před 3 lety

      ሰላም የተዋሕዶ ልጆች በዩቲዩብ ቻናላችን መንፈሳዊ ትምህርቶችን ስለጀመርን ኑና እንማማር።
      czcams.com/channels/hNJurk853lL0mZKyhyU_lA.html
      🌷

  • @bettybottcher4261
    @bettybottcher4261 Před 3 lety

    አሜን አሜን አሜን በረከቷ ይድረስን

  • @Wildrose_16
    @Wildrose_16 Před 3 lety

    ቃለህይወት ያሰማልን

  • @user-fy7hu2zc6e
    @user-fy7hu2zc6e Před 3 lety

    በረከታቸው ይደርብን

    • @geraratube12
      @geraratube12 Před 3 lety

      ሰላም የተዋሕዶ ልጆች በዩቲዩብ ቻናላችን መንፈሳዊ ትምህርቶችን ስለጀመርን ኑና እንማማር።
      czcams.com/channels/hNJurk853lL0mZKyhyU_lA.html
      🌷

  • @likeaila1727
    @likeaila1727 Před 3 lety +2

    ባለንበት ቅድስት አር ሰማ ትጎብኘን በረከታቸው ይደርብን ኦርቶዶክስ ሃይማኖት በእውነት ኩራት ነው💚💛❤🙏🙏🙏🙏🙏🙏❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤😭😭😭❤

  • @weseneethiopia8720
    @weseneethiopia8720 Před 3 lety

    Amen Amen Amen qalahiyotan Yasamaln wandamachan

  • @zewdineshal3888
    @zewdineshal3888 Před 3 lety

    Amen kale hiwetn yasemalin

  • @zakyatessema9931
    @zakyatessema9931 Před 3 lety

    Eganem ledeju yabakan fetari yekedesete aresema bereketewa yedereben 👏👏👏

  • @abiwaletasilase8014
    @abiwaletasilase8014 Před 3 lety

    Salmi indet nachu ye isgaber salmchu ibiza amen 🎤👏👏👏💒🙏

  • @saragezahg9181
    @saragezahg9181 Před 3 lety

    Ameen Ameen Ameen kale hiwot yasmalen ye enateche ye kedeste arsema erdatane berketaw ye deresen Ameen 🤲🤲🤲

  • @mintamir4333
    @mintamir4333 Před 2 lety

    እግዚአብሔር ይስጥልኝ በጣም ማየት ከምፈልጋቸው ገዳማት ውስጥ አንደኛው የሰማቷ ገዳም ነው እግዚአብሔር ቢፈቅድ ባካል አያታለሁ ሰማቷ ትፍቅድልኝ

  • @tsehaygeni9668
    @tsehaygeni9668 Před 3 lety +1

    ወይኔ ወንድሜ ሐገሬን አስታወስከኝ እግዚአብሄር ይባርክህ ይባርካችሁ 🙏 ቅድስት አርሴማ አንዴ ሄጃለሁ ግን በልበሊት እየሱስን ዛሬ ነገ ስል አላየሁትም እኔም ለሚ ዳገት ላይ ሆኘ ነዉ ሁሌ የማየዉ ፈቃዱ ሆኖ ለደጁ ያብቃን🙏 እኔም ተስፋ አለኝ 😍

    • @geraratube12
      @geraratube12 Před 3 lety

      ሰላም የተዋሕዶ ልጆች በዩቲዩብ ቻናላችን መንፈሳዊ ትምህርቶችን ስለጀመርን ኑና እንማማር።
      czcams.com/channels/hNJurk853lL0mZKyhyU_lA.html
      🌷

  • @saabcell2827
    @saabcell2827 Před 3 lety

    Ameen Ameen Ameen 🙏🙏🤲🤲🤲🤲

  • @meronmeronmiron2873
    @meronmeronmiron2873 Před 3 lety

    Amen amen amen betam desi yilali ynatachin ykidsti arsema berktwa yderbin zemare mlakti yasmalin wendmachin egzyabhere yestlni

  • @user-hd3oe5nk3h
    @user-hd3oe5nk3h Před 3 lety

    ሰላም ላንተ ይሁን ወንድማችን እንኳን ደህና መጣክ

    • @geraratube12
      @geraratube12 Před 3 lety

      ሰላም የተዋሕዶ ልጆች በዩቲዩብ ቻናላችን መንፈሳዊ ትምህርቶችን ስለጀመርን ኑና እንማማር።
      czcams.com/channels/hNJurk853lL0mZKyhyU_lA.html
      🌷

  • @avivagedamo1587
    @avivagedamo1587 Před 3 lety

    ዳንየ የሰፈሬ ልጅ እንደምን አለህልኝ ስላየሁህ በጣም ደስ ብሎኛል ሁሌ ጅሩ አርሴማን ሳይ አንተንና አቡሽን አመሰግናለሁ ።ዳንየ ስልክህን ብዙ ጊዜ ሀገር ቤት ስመጣ ለማግኘት ሞክሬ አላገኘሁም እና እባክህ በውስጥ መስመር ላክልኝ።ወደር ከስራኤል ነኝ

  • @beletuwoledesemayat7117

    እግዚአብሔር አምላክ ለደጃ ያብቃን 🙏

  • @helenkonjo1932
    @helenkonjo1932 Před rokem

    Ye abtachen ye abuna kosetose meljana tselot ayelene amen Amen Amen

  • @abebagebresilase1061
    @abebagebresilase1061 Před rokem

    bereketua yiderebin