Wendi Mak / ወንዲ ማክ - Tanadar / Maleda | ጣና ዳር / ማለዳ - Ethiopian Music 2023(Official Video)

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 20. 08. 2024
  • Wendi Mak / ወንዲ ማክ - ጣና ዳር / ማለዳ - Tanadar / Maleda Ethiopian Music 2023(Official Video)
    Any unauthorized use, copying or distribution is strictly prohibited By Wendi Mak.
    Copyright ©2023: Wendi Mak .
    #Tanadarmaleda #wendimak #newethiopianmusic #ጣናዳር #ማለዳ #ወንዲማክ #ethiopianmusic #amharic #addisababa #adama #diredawa #hawasa #mekele #bahirdar #gondar #arbaminch #jimma #dessie #semera #jijiga #hosaena #asosa #gambella #gurage #wolayita #asmara #eritrea
    __________________________________________
    ጠይም ማሳ መሳይ የውብ ዳር(×2) ውቢቷ
    ጎንደር ደምቢያ መስኩ ጣና ዳር ነው ቤቷ(×2)
    🎶🎶🎶🎶
    የሀር ቀሚስ ጥልፏ አልቦና ድጎቷ
    ድምቀትን ሰጥቷታል ለመላው ውበቷ
    ፀሃይ መከለያ ዣንጥላዋ ያምራል
    ያገር ቤቷ ጎበል አይኗ ያባብላል
    ያገር ቤቷ ጎበል አይኗ ያባብላል(×4)
    🎶🎶🎶🎶
    ወተት የመሰሉ ጥርሶቿ ያምራሉ
    አይኖቿ ተኮልተው በሩቅ ያሳሳሉ
    በወገቧ ወርዶ ድሪማርዳው ጌጡ
    እሷን ያየ ሁሉ ጠፋው መላቅጡ
    እሷን ያየ ሁሉ ጠፋው መላቅጡ(×4)
    🎶🎶🎶🎶
    ንገረኝ ይሉኛል ምኗ እንደሚናፍቅ(×2)
    አላያት ሰው ሁሉ ስትጫወት ስትስቅ(×2)
    አንደበቷ ማር ነው እሷ ምኑን አውቃ(×2)
    ታይታም ታፈዛለች እንኳንስ ተናፍቃ(×2)
    ማለዳ(×3) መጥተሽ ማለዳ መጥተሽ
    አቦሉን ጠጥተሽ ትመለሻለሽ(×2)
    ማለዳ(×3) መጥተሽ ማለዳ መጥተሽ
    አቦሉን ጠጥተሽ ትመለሻለሽ(×2)
    🎶🎶🎶🎶
    መንገደኛ እንዳለ ወደዚያች ልጅ ሀገር(×2)
    ናፍቆት ቢያደርስልኝ ምናለ ቢቸገር(×2)
    ደህና ነው እያሏት መጥታም አትጠይቀኝ
    ይልቁን ሂዱና ናፍቆሻል በሉልኝ(×2)
    ማለዳ(×3) መጥተሽ ማለዳ መጥተሽ
    አቦሉን ጠጥተሽ ትመለሻለሽ(×2)
    ማለዳ(×3) መጥተሽ ማለዳ መጥተሽ
    እኔን ሳታገኚኝ ትመለሻለሽ(×2)
    አቦሉን ጠጥተሽ ትመለሻለሽ(×2)
    🎶🎶🎶🎶
    የአክሊሉ ስዩምና ጋሻው አዳል ማስታወሻ
    __________________________________________

Komentáře • 613

  • @jaynjonas
    @jaynjonas Před rokem +288

    ወንዲ ማክ። እግዛብሔር ይባርክህ። 37 ዓመት ወደ ኋላ ነው የመለስከኝ። እኔ የኣስመራ ልጅ ኤርትራዊ ነኘ። ይህችን ጣና ዳር ዘፈን የኣንድ የደርግ ወታደር ኣክሊሉ ናት። ነገሌ ቦረና በነበርኩበት ግዜ ኣንድ ድግሪ ጠጅ ቤት የሚባል ነበር። የጠጁ ባለቤት ጎንደር ሴት ነበሩ። ድግሪ የተባለበት ምክንያት ጠጁ ስትገባ የልጃቸወ ድግሪ የጫነበት ፎቶ ግራፍ ስለነበር በዛ ምክንያት ድግሪ ጠጅ ተባለ። እነ ቺስታ ስለነበርኩ ጠጅ ለመጠጣት ስል ይችን የጣን ዳር ስዘፍን ሁሎም ጠጣ ጠጣ ይለኝ ነበር። የጠጅ ቤቱ ባለቤት ኣንተየው ተብታባ ትግሬው ጠጣልኝ እያሉ እስኪሰክር እጠጣ ነበር። ወንዲ ማክ በጣም ጎበዝ ዘፋኝ ነይ። Kudow to you bro. I'm proud of you. Thank you so much. Peacel

  • @fafinibabu6102
    @fafinibabu6102 Před měsícem +6

    አባቴ ካረፈ 28ኛ አመቱ 28 አመት ወደ ሇላ መለሰኘ አክሊሉ ስዩምን እና ጋሻውን በጣም ይሰማ ነበር ከልጅነት ትውስታይ😢😢😢😢

  • @tesfayemeless4516
    @tesfayemeless4516 Před rokem +27

    አርባ አመት ወደ ኃላ መለስከኝ በእውነት እያለቀስኩ ነው ደግሜ ደግሜ ያዳመጥኩት የህፃንነት ጊዜ ማይረሳ ትዝታ ነው
    እናመሰግናለን

  • @user-si9bz8wm5j
    @user-si9bz8wm5j Před rokem +27

    ለምን ይሆን የዚህ አይነት ሙዚቃ ስሰማ ሌላ አለም ውስጥ እገባለው 💔 ስቴ እንዳዳመጥኩ 🔥💞

  • @tilahuneshumete5298
    @tilahuneshumete5298 Před 11 měsíci +36

    እኔ የደቡብ ልጅ ነኝ አማራ ማለት ኢትዬጲያ አንድ ናቸው

  • @user-rn3fi2fs1o
    @user-rn3fi2fs1o Před rokem +13

    ወንዴ ♥️🇪🇷🌹ማራ እየ ዝፈትወካ

  • @MekbibMindaye
    @MekbibMindaye Před 26 dny +2

    እንድዚህ የሰው ዘፈን ሳይብላሽ ድጋሜ አሳምሮ የዝፈነ ጀግና በጣም አሪፍ ነው

  • @ethiorecords131
    @ethiorecords131 Před rokem +25

    በቀን ሁለት ሶስት ጊዜ ደጋግሜ የማዳምጠው የልጅነት ትዝታዬ ጋሻው አዳል ወንዲ ደግሞ በሚገርም ሁኔታ ምርጥ አድርጎ የሰራው ዘፈን፣ thank you all

  • @sisaymame7821
    @sisaymame7821 Před rokem +68

    ማለዳ ማለዳ መተህ
    ጣና ዳር ቁጭ ብለህ አሳ እየበላህ
    ጣና ገዳማቱን እየጎበኘህ
    ውቢቷን ባ/ዳር እየጎበኘህ
    የልጅቷን ፍቅር እየኮመኮምክ
    በቆንጆዋ ውበት እየተደመምክ
    በዚያው ትቀራለህ በፍቅር ተማርከህ
    ቆንጆ ሥራ ነው ወንዴ ማክ ይመችህ።

  • @destawmekuannet7010
    @destawmekuannet7010 Před rokem +71

    አቤት ዘፈን ክብር እና ምስጋና ይድረሳችሁ በዚህም በወንዲ ማክ እና በዚያኛው እኛ በምንናፍቀው ዘመን በዚህ ስራ ለተሳፉ 🎉🎉

    • @besratkassaun1471
      @besratkassaun1471 Před rokem

      ye gashawu adal new yemotewu kedmiya legashawu adal. lastawesen le maki keber ygebal

  • @senayitaze5079
    @senayitaze5079 Před rokem +8

    ወንዲ ማኪየ እንዴት እንደምወዲክ ረጅም እድሜ ኑርልን 🎐🥰🥰🥰🥰🥰

  • @yosief6114
    @yosief6114 Před rokem +9

    በሰላም ዕረፈ ጋሻዉ አዳል አዝማርኖ አክልሉ ሰዮም በፖሊሰ ባንድ ሰጫወት ወጣትነቲ አሰተወሰኝ ለዚ ትዉልድ ሰላም እና ፈቅር ያዉርድለት እኛ እንዳሳለፈነዉ ክፈቅር እና ሰላም የምጣፈት ነገር የለም 🇪🇷🇪🇹

  • @AG-bu4cd
    @AG-bu4cd Před rokem +16

    ከብዙ ጥራት ጋር ቆንጆ አድርገህ ተጫውተኸዋል። እኛ በዘመኑ የጋሻው አዳልን ዘፈን በቢክ እስኪርብቶ እያጠነጠንን ስንሰማ ፋራዎች ይሉን ነበር። ነገር ግን ግጥሙ፣ የሙዚቃ ቅንብር እና መልዕክቱ እጅግ ልዩ ነበር። አሁን ደግሞ አንተ በዘመናዊ መልኩ "with high quality and respect " ተጫወትከው። ድንቅ ስራ። Respect.

  • @ethiopiakebede5931
    @ethiopiakebede5931 Před rokem +91

    አክሊሉ ስዩምና ጋሻው አዳል የአስመራ ትዝታዎቼ ናቸው ነብሳቸው በገነት ትረፍ 🙏🏾 እንዲህ ሊታወሱ ይገባል እነሱን ለትውልዱ ማስተዋወቅ ያስፈልጋል ወንዲ ማክ ጥሩ አርገህ ስርተሀዋል ❤

    • @PakPak-vu6wt
      @PakPak-vu6wt Před rokem +3

      ሰለም አክልሉ፡ስዩም አልሞተም በሂዩት አላ፡ይቅርታ ።

  • @bezaneshwebetu8200
    @bezaneshwebetu8200 Před rokem +16

    ይሄንን ግጥምና ዜማ የሰራቹ ክብር ለናንተ ይሁን 🙏🙏 ወዴ ትችላለህ አይገልፀውም በጣም እናመሰግናለን ትዝታ ቀሰቀሰክብኝ ዋዉ 👍👍

  • @TensaeTilahun-qx2ob
    @TensaeTilahun-qx2ob Před 2 měsíci +2

    እኔ ብቻ ነኝ ያንን ዘመን የናፈቀው በሙዚቃው ወንድዬ ትዝታዬን ነው የቆሰቆስከው በስተርጅናዬ

  • @lishanmulugeta4589
    @lishanmulugeta4589 Před rokem +11

    ዘፈኑ ከትክክለኛው አዚያሚ ጋር ሲገናኝ ልዩ ሆነ።
    ወንዲማክ ስታይልህም የማይጠገብ ነው! እንወድሃለን!

  • @Salam-ef9gk
    @Salam-ef9gk Před 4 měsíci +2

    ስሰማው አልቅሽ አልቅሽ ይለኛል አቦ ተባረክ

  • @fema8811
    @fema8811 Před rokem +9

    ወንዲ በባህል ዘመናዊ ዘፈን እንዲህ ውብ ድምጽና ቅላጼ ይኖረዋል ብዬ አልጠበቅሁም ነበር፤ እጅግ ማራኪ ነው፤ ግጥም፣ዜማ፣ ቅንብር፣ምስል ሁሉም በጣም ነው የሚያምረው፡፡

  • @abiman6740
    @abiman6740 Před rokem +7

    የሚበረታቱ ስራወች ናቸው ብሰማቸው የማይሰለቹኝ የድሮ ሙዚቃወች በርታ ወንድማችን ❤❤❤

  • @dawitalemayehu5721
    @dawitalemayehu5721 Před 5 měsíci +4

    wow drum touch and filling 😮

  • @meir437
    @meir437 Před rokem +6

    ዋው በጣም የምዎደው ዘፈን፣እግዚአብሔር ይባረክህ❤

  • @demerseyoum4762
    @demerseyoum4762 Před měsícem +1

    ወንዴ ...ምርጥ ልጅ የዘመን ትውስታችንን እንዳዲስ...1ኛ...!

  • @munir798
    @munir798 Před rokem +4

    ምርጥ የህዝብ ልጅ ወንዲ ማክ አሪፍ ስራ ነው ይመችሽ

  • @doabaing550
    @doabaing550 Před rokem +5

    እጅግ በጣም በጣም ምርጥ ስራ። ልጅ ሆነን በሬዲዮ ደጋግመን የምንሰማው ነበር

  • @missamekuanint
    @missamekuanint Před měsícem

    ተባረክ በልጅነታችን ስናጎራጉረው የነበረ የአክሊሉ ስዩም ጊዜ የማይሽረው ዘፈን ስላስታወስከኝ አግዚአብሔር እድሜና ጤና ይስጥህ አመሰግንሃለሁ !!

  • @negedetobia
    @negedetobia Před rokem +11

    ደስ የሚል ለዛ ያለው ሙዚቃ ነው። በርታ !!!

  • @elsabettilahun6101
    @elsabettilahun6101 Před rokem +2

    ወንዲማክ ትለያለህ እግዚአብሔር ይጠብቅህ በጣም ደስ የሚል ቅንብር እንደዚህ የዱሮ ዘፈኖችን በዘመናዊ ሲቀርቡ የሚያምር ቀለም ነው የሚፈጥረው ጋሻው አዳልም በወቅቱ ቆንጆ ተጫውቶት ነበር

  • @yonasnashayilma2557
    @yonasnashayilma2557 Před 11 měsíci +2

    ዋው ወንዲማክ በጣም ምርጥይ አድርገህ ነው የተጫወትከው ባንዱም ምርጥ ልጆች ናቸው😍😍🙏🙏በርቱልኝ በተለይ ማሲንቆዋ😍😍💚💚💛💛❤❤🙏🙏

  • @kingofabay2135
    @kingofabay2135 Před rokem +1

    በጣም በቆንጆ ሁኔታ ነው የተሰራው ያምራል ቃላት አይገልፀውም

  • @tesfamichaleendeshaw9153

    ሙዚቀኛው ሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋቾች እንቅስቃሴቸው ህብር የፈጠሩበት ምርጥ ስራ ዋው ብያለሁ

  • @pace2443
    @pace2443 Před rokem +3

    የሀገሬ ልጆች ስታምሩ ወጣቶች በየአጋጣሚው ፈታ ዘና በሉ ሁላችሁም ችሎታ አላችሁ ኢትዮጵያ ሰላሟ ይብዛ grazie ሰለምታዝናኑን ❤

  • @kashabeshakashabesha4970

    ወንዲ አንተ ጀግና ነህ ጀግንነትህ በድምፅ ብቻ አይደለም የሚዚቃ አድማጭን ልብም ጆሮም አክመህ በድምፅህ ስለመለስክ ክብር ለሚገባው በሙሉ ክብረት ይስጥልን

  • @temaremulat7541
    @temaremulat7541 Před rokem +10

    I thank you for give dedication for the legendary singer, songwriter, and composer Aklilu Syume and Adal Gashaw.

  • @yedingil
    @yedingil Před rokem +8

    ወንዴ ሁሌም አንደኛ🎤🎷🤎🏆🔥

  • @tewodroszerefa7258
    @tewodroszerefa7258 Před rokem +10

    የቀደሙት አንጋፋ አርቲስቶቻን መካከል የምንወደው አክሊሉ ስዩም እና የምንወደው ጋሻው አዳል legendary ዘመን ተሻጋሪ ዎች ሆነው በአሁኑ ወጣት ድምፃዊ ወንዲ ማክ እንዲህ የተዋበ አድርጎታል!!

  • @meseretkassaye6871
    @meseretkassaye6871 Před měsícem

    my all time favorite wendi !!!

  • @tutuzemene2754
    @tutuzemene2754 Před rokem +10

    Wow amazing song 🎧 ለሞቱት በሙሉ ነፍስ ይማርልን, ለታመሙት ሁል ምህረትን ይላክልን። ኢትዮዺያንን ሰላም ያድርግልን❤❤❤ የአኢትዮዺያን ጠላት ግን ብን ጥን ያድርገው የአለም መድሀኒት አሜን አሜን ❤❤❤🙏🏽🙏🏽🙏🏽

  • @bisratsignal954
    @bisratsignal954 Před rokem +2

    Wow በጣም በጣም ደስስስስ ይላል እድሜና ጤና ይስጥህ ወንድሜ።

  • @filfilu
    @filfilu Před rokem +5

    👌 Amazing Re-Make 😍
    Big 👍Up, Wonde, Kiru N the rest.

  • @user-sb8st7yu9y
    @user-sb8st7yu9y Před rokem +4

    የኔ ድመፀ መረዋ❤❤❤❤❤❤❤🎉🎉🎉

  • @desalegnseifu7469
    @desalegnseifu7469 Před rokem +24

    Wow...remebering those golden years....one people...one Ethiopia....my eyes are full of tears....thanks Wondi Mak!

    • @1hagerachin
      @1hagerachin Před 8 měsíci

      I am not even 35 yet, and I do remember this song when I was little. My dad used to listen to it. Gashaw was the best

  • @user-sb8st7yu9y
    @user-sb8st7yu9y Před rokem +4

    ወዴ ለሠለሠ ያለ ሙዚቃ❤❤❤❤❤❤

  • @Ethiohabtina
    @Ethiohabtina Před rokem +5

    well done. so lovely. taking me back to the lovely time of Ethiopia.

  • @user-hv1sk2zx6u
    @user-hv1sk2zx6u Před rokem +9

    ባንዶች ግን ቆንጆ ቆንጆ ተመርጣችሁ ነው!? ❤❤❤

    • @ftumaassefa5501
      @ftumaassefa5501 Před rokem

      ከአማራ አይመረጥም ሁሉምሸበላ ነዉ ❤ ሤትወንዱ ይለያል የሰዉ ዉሀልክ አማራዬ

  • @Johnnbrothers
    @Johnnbrothers Před rokem +1

    ዛሬ ነው የሠማሁት 18/11/15 በጣም ቆንጆ sound ነው ሙዚቃ በሙሉ ባንድ ሲሠራ ውብ ነው

  • @melakushumie5553
    @melakushumie5553 Před rokem +3

    በጣም የተዋጣለት አቀራረብ በአሪፍ ተጫውተህዋል I’m proud of you my bro 👏👏👏

  • @bineluda7558
    @bineluda7558 Před rokem +5

    አክሊሎ ስዬም እና ጋሻው አዳል ትልቅ ክብር ለእናተ እነዚህን ስራዎች ሰላበረከታችሁልን ወንዴ እነዚህ ዘፈኖች ተረስተው እንዳይቀሩ በድጋሚ ስለሰራሀቸው በጣም እናመሰግናለን ለዚህ ትውልድ የድሮ ሙዚቃዎችን እንደ አዲስ መስራቱ መልካም ነው

  • @AfraaAadil
    @AfraaAadil Před 2 měsíci

    such an amazing music ✨,great voice and beautiful song 🌹,well done....I heard it hundred of times ,but still had the same feeling❤

  • @Alemye777
    @Alemye777 Před 6 měsíci

    እንዲህ ከባንድ ጋር ሙዚቃዎችህን ስትጫወት ማየት ደስ ይላል👏

  • @bestofethiopia6978
    @bestofethiopia6978 Před rokem +1

    እጅግ በጣም ተወዳጅ ሙዚቀኞች ነበሩ ጋሻው አዳል እና አክሊሉ ስዩም። ወዲ ጥሩ አድጎ ነው የተጫወተው። እናመሰግናለን።

  • @ethiopiantiktok8700
    @ethiopiantiktok8700 Před rokem +5

    ፣❤❤❤❤አቤት ችሎታ

  • @tewodroseeyasu6109
    @tewodroseeyasu6109 Před rokem +4

    ቃላት ያጥራሉ ሲባል ግራ ይገባኝ ነበር እንዴት ሰው መግለጽ ያቅተዋል ብዬዬዬ
    ይኸው ልክ እንደኔ

  • @abaybekele9448
    @abaybekele9448 Před 2 měsíci

    My goodness1 What a gift! Wondi is my man!!!!

  • @beshibeshyesuf1767
    @beshibeshyesuf1767 Před rokem +2

    You make me to think 30 years back,my mom was like gashaw adel song...Thank you so much

  • @Mekedes-dh9uu
    @Mekedes-dh9uu Před rokem +1

    ዋው፣ዉብ፣ድምፅ❤❤❤❤

  • @astawilmu4492
    @astawilmu4492 Před rokem +1

    በጣም ምርጥ ተደማጭ ስራ ነዉ ቀጥልበት በተጨማሪም በዚ ምርጥ አንደበት ሐገራዊ ስራም ስራበት ወንዲ ማክ..!!

  • @aghsepda
    @aghsepda Před 3 měsíci

    Kirubel Tesfaye....the most handsome and humble musician ....always your touches are magical...the Bass 🎸🎸🎸 amazing

  • @GOONMOTORSPORT
    @GOONMOTORSPORT Před 3 měsíci +1

    love it from france :)

  • @antenehbezabh2721
    @antenehbezabh2721 Před rokem +2

    So great 👍 👌 👏

  • @alazardemeke1651
    @alazardemeke1651 Před rokem +2

    shi 80 band great work beteley masikoo ... wende mak keep on it!!!

  • @user-bn3lc3re4o
    @user-bn3lc3re4o Před rokem

    ቆየት ያሉ ዘፋኞች ለዛው ሳይጠፋ እንዲ ስላዳመጥኩ ደስ ብሎኛል እድሜ ይስጥልን

  • @nebiyuwudineh5245
    @nebiyuwudineh5245 Před rokem +1

    አድናቂክ ነኝ ወንዴ በጣም ጎበዝ ገጣሚና ዜማ በመስራት መክሊት ከፈጣሪ የተቸረክ ነህ ምንም ጥርጥር የለው፣ ሁሌም ቅር የሚለኝ ነገር ለምንድነው አንድ አልበም እንኳን ለአድናቂዎችህ የማታደረሰው እሄ የኔ ጥያቄ ነው አንድ ጎበዝ ሙዚቀኛ አልበም ሊኖረው ግድ ነው

  • @BiniamTadele-lz6zm
    @BiniamTadele-lz6zm Před rokem +1

    ወንዴ ጌታ ይባርክህ

  • @josephdesalegn
    @josephdesalegn Před rokem +11

    The two legends Aklilu seyoum & Gashaw Adale. Rest in peace.

  • @user-sv6ms2pb3z
    @user-sv6ms2pb3z Před 2 měsíci

    1gna new waw

  • @mengistudagnaw4675
    @mengistudagnaw4675 Před rokem +3

    ቆንጆ ስራ ነው ክሊፕ ቢኖረው ደግሞ በይበልጥ ያምራል❤

  • @tadesrahbzu6988
    @tadesrahbzu6988 Před rokem +1

    በእዉነት 1ኛ ነህ

  • @antewifireden2134
    @antewifireden2134 Před rokem +97

    በመጀመሪያ ታላቅ ምስጋናዬን ተሰምቶ ለማያልቀው ለጋሻው አዳል የሙዚቃ ስራ ሲሆን በመቀጠል ለወጣቱ ድምፃዊ ወንዲ ማክ እና ለመላው የሙዚቃ ባንድ ታላቅ ስራ በወጣቱ አቀናባሪ ኪሩቤል ተስፋየዬ ልዩ ጥበብ ይህንን የመሰለ ታላቅ ስራ ለመታደም በቅተናልና ምስጋናችን በያላችሁበት ይድረሳችሁ ።❤🙏

    • @simientube
      @simientube Před rokem +18

      የአክሊሉ ዘፈን ነው

    • @ethiopology
      @ethiopology Před rokem +13

      ጋሻው አዳል ሳይሆን አክሊሉ ሥዩም ነው።

    • @antewifireden2134
      @antewifireden2134 Před rokem +11

      ይቅርታ የጀመረው በአክሊሉ ስዩም መሆኑን ሳልገልፅ "ማለዳ ማለዳ " ወደሚለው የጋሻው አዳል ዘፈን በመግባቴ እርማታችሁን እቀበላለሁ ።አመሰግናለሁ ።🙏

    • @getasweyibelu147
      @getasweyibelu147 Před rokem

      የጋሽአዳልነው ግን

    • @getasweyibelu147
      @getasweyibelu147 Před rokem +2

      የአክሊሉ ስዩም ይመስለኛል

  • @selamleethiopia5976
    @selamleethiopia5976 Před rokem +2

    ምርጥ የሀገር ቤት ሙዚቃ በርታልኝ

  • @ZelealemAbera
    @ZelealemAbera Před 9 dny

    ዋው ዋው ከ30 ዓመት በፊት በሃያወች እድሜ እያለሁ አፍቅራት ለነበር ልጅ ካሴቱን ገዝቸ ለማስተወሻ ሰጥቻት በተደጋጋሚ እየከፈትን እንኮመኩመው ነበር ።

  • @Gent.Yemaryam-zg8ld
    @Gent.Yemaryam-zg8ld Před 6 měsíci +1

    ጎንደር ደቢያ መሰኩ ጣና ዳር ነው ቤቷ❤🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉

  • @user-wz3qs6vo6y
    @user-wz3qs6vo6y Před rokem +1

    ለመጀመሪያ ጊዜ ይሄን ሙዚቃ ባሌ ነው የጋበዘኝ እሱ ልኮልኝ ነው ያየሁት ሰምቸው አላውቅም ነበር❤❤❤❤እናመሰግናለን. ወንድማክ. 🌷🌷🌷

  • @eteneshfantahun8038
    @eteneshfantahun8038 Před 8 měsíci

    ወንዴ እጅግ ድንቅ ነው🙏❤️። ብዙም ስው የማያስተውለው ግን ስህተት ። ጠይም ማሳ መሳይ። ብሎ የፃፈውን አሳ መሳይ በል በለው ይህ ለወደፊትም ዘመናትን የሚሻገር ዶክመንት ነው።እጅግ ድንቅ ነው አክሊሉ ስዩምን ከዘመነት በኃላ በዚህ ዘመን እይታ አመጣህልን❤❤❤።

  • @natnaelmsigna6935
    @natnaelmsigna6935 Před rokem +1

    ወንዲ ማክ ጎበዝ የሚወድ ዘፈኖች በርታ ❤❤❤❤

  • @yakovisrael5000
    @yakovisrael5000 Před rokem +1

    እናመሰግናለን ወንዲ ማክ እና ሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋቾች በጠቅላላ ለተሳተፋችው በሙሉ በደንብ ነው የሰራችውት ደስ እያለኝ ነው ደጋግሜ እያዳመጥኩት ያለውት ስለ ጎንደር በሌላ ስራ እንደምትመጣ ተስፋ አደርጋለው ወንዲ ማክ ረጅም እድሜ ይስጥልን

  • @kinfefikadu3851
    @kinfefikadu3851 Před rokem

    በጣም ደስ ይላል ወንዴ ማክ በርታ እግዚአብሔር እድሜ ጤና ይስጥሕ

  • @tomhabtamu138
    @tomhabtamu138 Před rokem +1

    100 geza semawete beka yehone yemalakew semate weste ysegbagale more selasamrkew tnx wendye 🎉

  • @Zerihun04
    @Zerihun04 Před rokem +2

    ይሄ ብርቱ ጀግና ልጅ ዘመኑ ይባረክ! ከፈጣሪ በጊዜው እንደሚሆን በእምነት፣ በተስፋ ጸንተህ አይተህ የምታሳየን የወላይታ እጣ ፈንታ እውን ሆኖ ያሳየን!🙌🙏❤

  • @yonasbest4511
    @yonasbest4511 Před rokem +2

    ወንድሻ ምርጥ ትልቅ ትዝታ ውስጥ ነው የከተትከኝ አሁን የት እንዳለች የማላውቀው የጋሻው አዳል ልጅ አንድ ወቅት ላይ በጣም የምወዳት ጓደኛዬ ነበረች አይ የትምህርትቤት ፍቅር ብቻ ለኔ ትለያለህ ወንዴ እውነትም ወንድ ነህ

  • @KebedeMengistu-qf7lw
    @KebedeMengistu-qf7lw Před měsícem

    በጣምነውየምወድክ

  • @kalkal8468
    @kalkal8468 Před rokem +1

    ወይኔ ወዳ ድምፅን ስሰማው ይነዝርኛል❤❤😍😍

  • @guiggu224
    @guiggu224 Před rokem

    የጋሻው አዳልን ሙዚቃ ሙሉውን ብትዘፍነው በጣም ነው የሚያምር ድምፀነው ያለህ ፈጣሪ እድሜና ጤና ይሰጥህ

  • @fidel_tube
    @fidel_tube Před rokem +3

    ጠይም ዓሳ መሳይ የውብዳር(2) ውቢቷ፤
    ጎንደር ደምቢያ መስኩ ጣና ዳር ነው ቤቷ። ❤

  • @Fish19610
    @Fish19610 Před rokem +1

    እናመሰግናለን አንቺን የመሰለ ድምጻዊት ስለሰጠን። ብዙ እንጠብቃለን ካንቺ።በርቺ❤

  • @KalkidanAlmayhu-ro1fb

    Wow wende andeya nw yamiral

  • @hanasisay8831
    @hanasisay8831 Před rokem

    Wow betam saldekew yemaytalef musik new gerami bekat new ketelbet fetari Beratune yestik❤❤❤❤❤❤

  • @kidikids9203
    @kidikids9203 Před rokem +2

    ቆንጆ ስራ ሆድ ያባባል ሰላም ለሀገራችን

  • @noorhusienabdul5722
    @noorhusienabdul5722 Před rokem +3

    the music mlodey and your voice wonderful nice music ,, eid ,mubarake ,,, for muslim all over the world , we thankyou musian wendi mak ,,

  • @user-rw9tp1yr3b
    @user-rw9tp1yr3b Před rokem

    ሁሉም ያምራል የጋሻው አዳል ዘፈን እንድትዘፍን የተፈጠርክ ነው የሚመስለው ሁሉንም ዘፈኖቹን በሂደት ዳግም እንዲህ እያዋዛህ ብታስድምጠን

  • @fetaneyta12
    @fetaneyta12 Před rokem +1

    ምርጥ ስራ ነው!!! ወዲ ማክ በርታ

  • @meskeremadugna3706
    @meskeremadugna3706 Před rokem +1

    ❤🎉 serawechehen bemulu sewdachew jegnaye 🎉

  • @dejuka
    @dejuka Před rokem

    ዋው የሰው ነገር የሚያምርበት አንተን አየው

  • @user-ub6ug6yo4h
    @user-ub6ug6yo4h Před měsícem

    ቃላት የለኝም ለመግለፅ ወድዬ

  • @manuhiayele
    @manuhiayele Před 2 měsíci

    እድሜ ይስጥህ

  • @MesertTeka-hk8pz
    @MesertTeka-hk8pz Před 11 měsíci

    ዋው በጣም ያምራል

  • @Englishfootballhighlights413

    The Legend Aklilu siyume..... i will clapped 👏 for wende mak amazing performance

  • @mekamuhassn3055
    @mekamuhassn3055 Před rokem +1

    ሺ 90 ብለህ ተዋውቀኸን አሁን ደግሞ ጠይም አሳ መሳይ ❤ትችላለህ

  • @nahomalemu4102
    @nahomalemu4102 Před rokem +1

    አይ ወንዲያችን

  • @MB200UNLOCK
    @MB200UNLOCK Před 6 měsíci

    So lovely, taking me back to my childhood when I hear the song in Gorgora😊