አዕምሮው የተባረከ ሰው ማን ነው?የሰው አመል|ክፍል2 ቄስ ትዕግስቱ ሞገስ/Rev Tigestu moges|

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 11. 09. 2024
  • መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 25
    1.ሳሙኤልም ሞተ፤ እስራኤልም ሁሉ ተሰብስበው አለቀሱለት፥ በአርማቴምም በቤቱ ቀበሩት። ዳዊትም ተነሥቶ ወደ ፋራን ምድረ በዳ ወረደ።
    2.በማዖንም የተቀመጠ አንድ ሰው ነበረ፥ ከብቱም በቀርሜሎስ ነበረ፤ እጅግም ታላቅ ሰው ነበረ፥ ለእርሱም ሦስት ሺህ በጎችና አንድ ሺህ ፍየሎች ነበሩት፤ በቀርሜሎስም በጎቹን ይሸልት ነበር።
    3.የሰውዮውም ስም ናባል፥ የሚስቱም ስም አቢግያ ነበረ፤ የሴቲቱም አእምሮ ታላቅ፥ መልክዋም የተዋበ ነበረ፤ ሰውዮው ግን ባለጌ ነበረ፥ ግብሩም ክፉ ነበረ፤ ከካሌብም ወገን ነበረ።
    4.ዳዊትም በምድረ በዳ ሳለ፦ ናባል በጎቹን ይሸልታል የሚል ወሬ ሰማ።
    5.ዳዊትም አሥር ጕልማሶች ላከ ለጕልማሶችም አለ፦ ወደ ቀርሜሎስ ወጥታችሁ ወደ ናባል ሂዱ፥ በስሜም ስለ ሰላም ጠይቁት፤
    6.እንዲህም በሉት፦ በደኅንነት ኑር፥ ለአንተና ለቤትህም ለአንተም ላሉት ሁሉ ሰላም ይሁን።
    7.አሁንም በጎችህን እንድትሸልት ሰምቻለሁ እረኞችህም ከእኛ ጋር ነበሩ፥ ከቶ አልበደልናቸውም፤ በቀርሜሎስም በተቀመጡበት ዘመን ሁሉ ከመንጋው አንዳች አልጎደለባቸውም።
    8.ጕልማሶችህን ጠይቃቸው፥ እነርሱም ይነግሩሃል፤ አሁንም እንግዲህ በመልካም ቀን መጥተንብሃልና ጕልማሶች በፊትህ ሞገስ ያግኙ፤ በእጅህም ከተገኘው ለባሪያዎችህና ለልጅህ ለዳዊት፥ እባክህ፥ ስጥ።
    9.የዳዊትም ጕልማሶች መጡ፥ ይህንም ቃል ሁሉ በዳዊት ስም ለናባል ነግረው ዝም አሉ።
    .......

Komentáře • 12