🛑 አዲስ ዝማሬ "እኛ እንፀናለን" ዘማሪት እየሩሳሌም ጌታቸው እና ዘማሪ ዲ/ን ኤፍሬም ፀጋዬ || egna entsenalen||

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 22. 08. 2024
  • እኛ እንፀናለን
    እኛ እንፀናለን እስከ መጨረሻ
    ኃይሉ ከኛ ጋር ነው ሞትን መደምሰሻ
    አንደናገጥም በዲያብሎስ ሥራ
    ሁሉም በእጁ ያለ አለ ከኛ ጋራ
    እሳት ሳለ በእሳት ብቃጠል መቅደሱ
    እንበዛለን እኛ ቢታረድም ቄሱ
    አልሸማቀቅም አላፍርም በእምነቴ
    ተዋህዶ ናት ለኔ ጌጥና ውበቴ
    መቅደስህ ተቃጥሎ ስለማይወድቅ አምዱ
    የተዋህዶ ልጆች እሳትን ለመዱ
    በነኩን ቁጥር እጥፍ ነው ቁጥራችን
    ከራስ ፀጉር በላይ እልፍ ነው ዘራችን
    ሊጥሏት ተነስተው አይተናል ሲወድቁ
    አምነው ይኖራሉ ተዋህዶን ያወቁ
    መቅደስህ ተቃጥሎ ስለማይወድቅ አምዱ
    የተዋህዶ ልጆች እሳትን ለመዱ
    ሕፃን ሽማግሌ ወጣት አዛውንቱ
    ቀን ከቀን ቢጨምር ግድያና ሞቱ
    የማታንቀላፋ የማተኛው ንጉስ
    ተመልክተህ ፍረድ እየሱስ ክርስቶስ
    መቅደስህ ተቃጥሎ ስለማይወድቅ አምዱ
    የተዋህዶ ልጆች እሳትን ለመዱ
    ይጠፋሉ ሲሉን እንበዛለን ገና
    ምድርን እንከድናለን በያሬድ ምስጋና
    ችግር ሃዘን ስቃይ ቢኖርም ፈተና
    በክብር እንቆማለን ሁሉን እናልፍና
    መቅደስህ ተቃጥሎ ስለማይወድቅ አምዱ
    የተዋህዶ ልጆች እሳትን ለመዱ
    አለምን ቢያሳውክ የመንግስታቱ ጦር
    ከሰዎች ቢታጣም ሰላምና ፍቅር
    ደም መፋሰስ በዝቶ ሞት በዓለም ቢስፋፋም
    ፀንተን እንቆማለን በእምነት በተስ
    መቅደስህ ተቃጥሎ ስለማይወድቅ አምዱ
    የተዋህዶ ልጆች እሳትን ለመዱ

Komentáře • 20