ኡስታዙ (የአንድ ወረዳ የእስልምና መሪ) ክርስቲያን ሆኑ || ከእስልምና ወደ ክርስትና

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 30. 06. 2024
  • የመሐመድ አበባውን የዩትዩብ ቻናል ለማኘት ይህንን ሊንክ/ማስፈንጠሪያ ተጫኑ • የኡስታዙ ምስክርነት ከእስልምና ወደ...
    የኦሮምኛውን ቻናሌን ለማግኘት ይህንን ተጫኑ👇
    / @dhugaanniboqachiisa
    መልካም ዜና
    የምስራች፣ የምስራች፣ የምስራች! የምስራች ማለት መልካም ዜና ማለት ነው። የእግዚአብሔር ቃል ደጋግሞ የሚነግረን ይሄ መልካም ዜና ምንድነው? ዛሬ፣ በእግዚአብሔር ረዳትነት፣ በእግዚአብሔር ቃል ላይ ስለተጠቀሰው ስለዚህ መልካም ዜና እንነጋገራለን። ነገር ግን ስለ መልካሙ ዜና ከመነጋገራች በፊት ስለ መጥፎው ዜና ማስታወስ አለብን።
    ምንድነው መጥፎው ዜና? በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ከፈጠረ በኋላ አዳምንና ሔዋንን በምድራዊዋ ገነት ውስጥ እንዳስቀመጣቸው ታስታውሳላችሁ። እግዚአብሄር እንዲያውቁት፣ እንዲወዱት፣ እንዲታዘዙት እና ለዘላለም እንዲያከብሩት ፈጥሯቸዋል። ይሁን እንጂ እግዚአብሔር እነሱን ለመፈተን አዳምን እንዲህ አለው፡-
    “በገነት ካለው ከዛፉ ፍሬ ብሉ፥ ነገር ግን እንዳትሞቱ በገነት መካከል ካለው ከዛፉ ፍሬ አትብሉ አትንኩትም።”
    መጥፎው ዜና አዳምና ሔዋን እባቡን ማለትም ከተከለከለው ዛፍ ፍሬ እንዲበሉ የፈተናቸውን ዲያብሎስን ማዳመጣቸው ነው። የአዳምና የሔዋን ኃጢአት እነርሱንና ዘሮቻቸውን ሁሉ በመበከል በዓለም ላይ ችግርንና ሞትን አመጣ። ብዙ ጊዜ እንደምንሰማው፡ "ወረርሽኝ መነሻው ላይ ብቻ አይወሰንም!" የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል መጥፎ ዜና ይነግረናል፡-
    “ለሰዎችም አንድ ጊዜ መሞት ከእርሱ በኋላም ፍርድ እንደ ተመደበባቸው፥...
    እነሆ፥ ጌታ በሁሉ ላይ እንዲፈርድ፥ በኃጢአተኝነትም ስላደረጉት ስለ ኃጢአተኛ ሥራቸው ሁሉ ዓመፀኞችም ኃጢአተኞች በእርሱ ላይ ስለ ተናገሩ ስለ ጭከና ነገር ሁሉ ኃጢአተኞችን ሁሉ እንዲወቅስ ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጥቶአል ብሎ ለእነዚህ ደግሞ ትንቢት ተናገረ።” (ዕብራውያን 9፥27 ይሁዳ 1፥15)
    ስለዚህ፣ መጥፎው ዜና ሁላችንም ኃጢአተኞች ነን እናም የእግዚአብሔርን የጽድቅ ፍርድ መጋፈጥ አለብን! ይሁን እንጂ፣ መልካሙ ዜና (የምስራቹ) በዚያው በገነት ውስጥ፣ በምረቱ ባለጠጋ የሆነው እግዚአብሔር፣ አንድ ቀን ከድንግል የሚወለድን ኃጢአት የሌለበትን ሰው ወደ አለም እንደሚልክ ማስታወቁ ነው። ይህ ቅዱስ ሰው፣ ይህ ጻድቅ አዳኝ፣ ለአዳምና ለዘሮቹ ሁሉ ኃጢአት ለመክፈል ራሱን መስዋእት አድርጎ ይሞት ነበር። ለኛ የሚገባን የኃጢአት ቅጣት በዚህ ኃጢአት በሌለበት አዳኝ ላይ ይወድቃል። አዳምና ሔዋን ኃጢአት በሠሩበት ቀን እግዚአብሔር የሰበከው ወንጌል (የምስራች) ይህ ነው። እግዚአብሔር የዚህን አዳኝ መምጣት ለማወጅ ብዙ ሰዎችን ተጠቅሟል፣ እንዲሁም መሲህ ይባላል። እያንዳንዱ የእግዚአብሔር ነቢያት ስለ መሲሑ አንድ ነገር አውጀዋል፣ ስለዚህም እርሱ ሲመጣ እግዚአብሔር የሾመው እርሱ መሆኑን ሁሉም ይገነዘባል። ለምሳሌ ያህል፣ ከመሲሑ መምጣት ሰባት መቶ ዓመታት ቀደም ብሎ የነበረው ነቢዩ ኢሳይያስ፣ መሲሑ እንዴት እንደሚወለድ ተንብዮአል። "ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው።"( ማቴ. 1:23፤ ኢሳ. 7:14 ) ሚክያስ የተባለ ነቢይ ደግሞ መሲሁ ከሰማይ መጥቶ በቤተልሄም መንደር በምድር ላይ እንደሚወለድ ትንቢት ተናግሯል። በትክክል መሲሑ የተወለደበት ቦታ ይህ ነበር። ሆኖም ሚክያስ ይህን ትንቢት የተናገረው መሲሑ ከመወለዱ ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት ነው። ነገር ግን ነቢያት የመሲሑን መወለድ ብቻ አላወጁም። በተጨማሪም መሲሁ በኃጢአተኞች ምትክ መከራ እንደሚደርስበትና እንደሚምት ትንቢት ተናግረዋል። ለምሳሌ ነቢዩ ዳዊት ሰዎች መሲሑን እንደሚንቁት፣ እንደሚያሰቃዩት፣ እጁንና እግሩን እንደሚወጉ እና እንደሚገድሉት ጽፏል። ዳዊት የመሲሑን ሞት ማወጅ ብቻ ሳይሆን፣ እግዚአብሔር መሲሁን ከሞት እንደሚያስነሳውም ተንብዮአል፤ ይህም እግዚአብሔር የአዳምን ልጆች ከኃጢአት ቅጣት ለማዳን የላከው አንድና ብቸኛ አዳኝ መሆኑን አረጋግጣል።
    ስለ መሲሁ መወለድ ብዙም ክርክር የለም፣ ነገር ግን ብዙዎች በሞቱና በትንሳኤው ይሰናከላሉ። ሰዎች የላከውን መሲህ ሲያዋርዱት እግዚአብሔር እንዴት ሊቆም እና ሊመለከት እንደሚችል አይገባቸውም። ብዙ ሰዎች ሊረዱት ያልቻሉት ነገር መሲሑ ለኃጢአታችን እንዲህ አይነት መከራ እንዲደርስበት ያቀደው እኛን የሚወደን አምላክ መሆኑን ነው። ነገር ግን ነቢያቱ እንዲህ ሲሉ አውጀዋል፡- “እግዚአብሔርም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።”
    - (ኢሳይያስ 53፥10)
    ነቢያትን እናምናለን? አዎ እናምናቸዋለን እንላለን። ነቢያትን በእርግጥ የምናምን ከሆነ የጻፉትንም ማመን አለብን። ነብያት የራሳቸውን ሃሳብ እንዳልተናገሩ ማስታወስ አለብን። እግዚአብሔር የሚናገሩትን በመንፈሳቸው ውስጥ አኖረ። እንግዲያውስ እነዚያን ነቢያት ለማመን ብንቃወም፣ ማንን ነው ምንቃወመው? የምንቃወመው እግዚአብሔርን ነው። ምክንያቱም ነቢያት መሲሁ ኃጢአትን ለማስወገድ መስዋዕት ሆኖ እንደሚሞት ትንቢት እንዲተነብዩ ያነሳሳው እርሱ ነውና።
    {የሚቀጥለው ማሊክ የሚባል ሰው የግል ምስክርነት ነው።} እዚህ ጋር ቆም ላድርገውና እንዴት በኢየሱስ ክርስቶስ አማኝ እንደሆንኩ ልንገራችሁ። በወጣትነቴ በቀን አምስት ጊዜ ለመጸለይ እና አመታዊ ጾምን ለመጾም ታማኝ ነበርኩ፣ ነገር ግን ከሞትኩ በኋላ ወዴት እንደምሄድ አላውቅም ነበር። ዙሪያዬ ያሉትን ሁሉ ጠየኩ፣ ሆኖም ግልጽ የሆነ መልስ አላገኘሁም። ወንጌልን (ኢንጂልን) ሳጠና ግን፣ ከሞቴ በኋላ ወዴት እንደምሄድ ማወቅ እንደምችል አወቅሁ፤ ምክንያቱም መሲሁ ኢየሱስ ራሱ በወንጌል እንዲህ ይላል፦ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም።” (ዮሐንስ 5፥24) እንዲሁም እንዲህ ብሏል፦ “ኢየሱስም፦ ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤” (ዮሐንስ 11፥25) ስለዚ፣ ራሴን ለማዳን ከራሴ ጥረት ንስሃ ገብቼ ነቢያት ሁሉ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ በስሙ የኃጢአቱን ስርየት ይቀበላል" ብለው ትንቢት በተናገሩለት መሲህ አመንኩኝ (ሐዋርያት 10፥43)። ተስፋዬን ሁሉ ወስጄ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ አስቀመጥኩት። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔር ለመንፈሴ ሰላም አምጥቶላታል። አሁን ህሊናዬ አይረበሽም። ኢየሱስ በመስቀል ላይ ከሰራው ሥራ የተነሳ የወደፊት እጣዬ በሚያስደንቅ ሁኔታ ብሩህ ነው። በሕይወቴ እንደ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር፣ አንዳንድ ጊዜ ችግር እና መከራ ያጋጥመኛል ምክንያቱም እምነቴ ከዘመዶቼ እና ከጓደኞቼ አስተያየት ስለሚለያይ፤ ግን ሰላም አለኝ። የእግዚአብሔር ሰላም ልቤንና አእምሮዬን ሞልቶታል። ይህን የሰጠኝ ኢየሱስም እንዲህ ይላል፦ “ዓለም ቢጠላችሁ ከእናንተ በፊት እኔን እንደ ጠላኝ እወቁ።” (ዮሐንስ 15፥18) “ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም።” (ዮሐንስ 14፥27) እና ወዳጆች ሆይ፣ ጌታ ለእኔ እና በእኔ ያደረገውን ለእያንዳንዳችሁ ሊያደርግ ይችላል። ካንተ ወይም ካንቺ አንድ ነገር ይጠይቃል፡-ሙሉ ልብህን እንድትሰጠው። ሙሉ ልብሽን እንድትሰጪው። የቀረውን እሱ ያደርገዋል። ጌታ ኢየሱስ ራሱ እንዲህ ብሏልና። "እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤" (ማቴ. 11:28-29)
    እግዚአብሔር ታላቁን ማዳኑን መቼም ቢሆን አይሸጥልህም ወይም አይሸጥልሽም። እንዲሁ ያለ ምንም ዋጋ (ከእናንተ ባልሆነ ዋጋ) በነጻ ሊሰጣችሁ ነው ሚፈልገው። መልካም ስራ፣ ፀሎት (ሶላት) እና ፆም በውስጣችሁ ጥሩ ስሜት ይሰጡ ይሆናል፣ ነገር ግን የእግዚአብሔርን ፅድቅ አያረኩም! ወደ እግዚአብሔር ገነት የምትገባበት/የምትገቢበት መንገድ አንድ ብቻ ነው።
    1.) በመጀመሪያ ኃጢአተኛ እንደሆንክና አምላክን ለማስደሰት የሚያስችል ኃይል እንደሌለህ መገንዘብ ይኖርብሃል።
    2.) ከዚያም ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝ እንደሆነ፣ ኃጢአትህን ለማስወገድ እግዚአብሔር በመስቀል ላይ እንዲሞት እንደ ላከውና እግዚአብሔር የዘለአለም ሕይወትን ይሰጥህ ዘንድ እንዳስነሳው ማመን አለብህ።
    አስተያየታችሁን በውስጥ ማድረስ የምትፈልጉ ይህንን የቴሌግራም ሊንክ ተጠቀሙ👇
    t.me/BibleAndMe
    Additional: - ewnetyasarfal123@gmail.com

Komentáře • 227

  • @ewnetyasarfal
    @ewnetyasarfal  Před 11 dny +24

    🎯 አብራችሁኝ በገንዘባችሁ ለማገልገል ፈቃደኛ የሆናችሁ ይህንን ሊንክ ተጫኑትና አናግሩኝ።👇
    t.me/BibleAndMe

  • @MilkiasSamuel
    @MilkiasSamuel Před 11 dny +38

    ይህ የኢየሱስ ስራ ነው። ስሙ ይባረክ

  • @Roza-fl2wf
    @Roza-fl2wf Před 11 dny +25

    ክብር ለጌታችን ለመዳኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ይሁን አንተም ተባረክ ወንድሜ።

  • @abebaseyiume8949
    @abebaseyiume8949 Před 11 dny +28

    ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬም ለዘለዓለም ያዉ ነዉ ለስሙ ክብር ይሁንለት አምላኬ እግዚአብሔር ነዉ ጌታዬ ኢየሱስ ነዉ መንፈስ ቅዱስ በስራ ላይ ነዉ

  • @mintesnot6857
    @mintesnot6857 Před 11 dny +20

    ክብር ሁሉ ለእግዚአብሔር ይሁን🙏 ሁሉም ሙስሊም ወገኖቻችን አውነትን ወደማወቅ እንዲደርሱ ነው ፀሎታችን።

  • @tigistyadete6592
    @tigistyadete6592 Před 11 dny +24

    በእውነት እኔ ኦርቶዶክስ ነኝ ግን እግዚአብሔር ይመስገን ወንድሜ እግዚአብሔር እንኳን ወደ ብራሃን መጣክ አምላካችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ እውነት ነው መንገድ ነው ህይወት ነው ❤❤❤❤❤❤❤

    • @danieleyu6832
      @danieleyu6832 Před 8 dny

      አንዳንድ ሰዎች ኮሜንት ሲያደርጉ
      " ኦርቶዶክስ ነኝ.…………ግን" ይላሉ፡ ምን ማለት እንደሆነ አይገባኝም?

    • @PlRATE
      @PlRATE Před 6 dny

      @@danieleyu6832 የሁለት የግሪክ ጥምር ቃል ነው። ortho = ቀጥተኛ(ትክክለኛ) doxa (doctrine) = የሀይማኖት ትምህርት ማለት ነው። ስሙ የመጣው በ325 አመተምህረት በኒቂያ ጉባኤ ግዜ ከአርዮስ የክህደት አስተምህሮ(Arianism) ለመለየት የተሰየመ ነው። ሐዋርያት ያስተማሩትን ቀጥተኛ እምነት ይዘናል ለማለት ነው።

    • @user-Hiwi
      @user-Hiwi Před dnem +1

      mkniyatum yepente chanel slehone

    • @danieleyu6832
      @danieleyu6832 Před dnem

      @@user-Hiwi ታዲያ ሃሳቡ ከጴንጤ ሚዲያነት ጋር ምን ያገናኘዋል፡ ለምሳሌ የሰውየው ወደ ብርሃን መምጣቱ ካስደሰታት ይሄንኑ ኦርቶዶክስ መሆናን ሳትገልፅ መፃፍ ትችላለች።

  • @ameenameen6123
    @ameenameen6123 Před 11 dny +19

    እግዚአብሔር ይመስገን

  • @munamu7720
    @munamu7720 Před 11 dny +38

    ኦርቶዶክስ ነኝ በጣም ነው ምወዴቹ ክብር ለድንግል ማርያም ልጅ የኔ ንጉስ የኔ ጌታ ❤❤❤😍😍😍😍

    • @melber7957
      @melber7957 Před 11 dny

      Amen!

    • @wengelawitgirma9182
      @wengelawitgirma9182 Před 11 dny +4

      አንተስ በመዳንህ እርግጠኛ ነህ?

    • @MeseretMathiwos
      @MeseretMathiwos Před 11 dny +1

      Eyesus keresetos yedenali eyesus geta nawu

    • @AbebaDamesa-wc7ls
      @AbebaDamesa-wc7ls Před 11 dny +5

      You're same with musilm because they believe that Jesus is son of Mary.
      Bible say Jesus is Son of God there's no one place bible mention Jesus son Mary

    • @user-nb6xp2wm2j
      @user-nb6xp2wm2j Před 11 dny +2

      ​@@AbebaDamesa-wc7lsምን ማለትህ ነው ? ጌታ ኢየሱስን በመ/ቅ አማካይነት ጸንሳ በቤተልሄሔም እንደወለደችው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ሉቃስ ጽፎት የለ እንዴ !

  • @user-ir4zw9yl3t
    @user-ir4zw9yl3t Před 11 dny +9

    እየሱስ ያድናል እልልልልልል❤❤❤

  • @MelkamuBekele-zq1oy
    @MelkamuBekele-zq1oy Před 11 dny +13

    እየሱስ ሁለ አሸናፊ ነዉ
    አሜን

  • @rahelhabte8291
    @rahelhabte8291 Před 11 dny +9

    ክብር ለጌታችን ለመዴኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ ይሁን እርሱ ብች እውነት መንገድም ህይወት ነው::🙏🏾🙏🏾🙏🏾👏👏👏

  • @tigistyadete6592
    @tigistyadete6592 Před 11 dny +10

    በስመአብ በጣም እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክህ ወንድሜ እንኳንም ከምትወልዳቸው ቤተሰቦችህ ጋር በሰላም
    አገናኝቶህ አንድ ለይ ለመኖር አበቃችሁ

  • @noorwaga4502
    @noorwaga4502 Před 10 dny +9

    ኦ!እግዚአብሔር ይመስገን ስለሁሉ

  • @hirut-rz3uh
    @hirut-rz3uh Před 11 dny +9

    አቤት የኔ ጌታ መልካም ነው የላንካካከው ቤት ያልቀየርከው ልብ የለክም ተባረክ እናንተም ተባረኩ

  • @husseinifkaifka6421
    @husseinifkaifka6421 Před 11 dny +8

    ዋው ምስክርነት ኢየሱስ ጌታ ነው ብዙ ነገር ነው የተረዳው በዝ ምስክርነት ተባርከያለው ተባረኩ❤❤❤❤❤

  • @husseinifkaifka6421
    @husseinifkaifka6421 Před 11 dny +10

    አመን ተባረክ በርታ ወንድመ❤❤❤❤

  • @user-uy2qu6py6n
    @user-uy2qu6py6n Před 10 dny +6

    ቃለ ህዮት ያሰማልን ለሌሎቹም እግዚአብሔር አምላክ ልቦና ይስጥልን

  • @jesuswillcome
    @jesuswillcome Před 11 dny +8

    Every knee will Bow for Jesus christ our Saviour.

  • @user-uu3jd2fe9c
    @user-uu3jd2fe9c Před 11 dny +6

    ይህ የእግዝአብሔር ድንቅ ስራ ነው ክብር ይሁንለት ❤❤❤

  • @berryberry2124
    @berryberry2124 Před 11 dny +5

    ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን እናንተም በርቱ በጭለማ የሚኖሩትን ወደብርሀን አምጧቸው ፈጣሪ ይመስገን🙏🙏🙏🙏🙏🙏

  • @netsanetgemmechu2929
    @netsanetgemmechu2929 Před 11 dny +6

    እግዚአብሔር ይመስገን ስለእናንተ ኢየሱስ ጌታ ነዉ ።

  • @user-nf5de9nq1e
    @user-nf5de9nq1e Před 11 dny +8

    በርታልን

  • @TigstiAwalom
    @TigstiAwalom Před 11 dny +6

    ጌታ ይባረክ! ጣፋጭ ምስክርነት!

  • @mesk_erem
    @mesk_erem Před dnem

    ክብር ሁሉ ለወደደን❤❤❤ እልልልልልልልልል ኦ ፍጥረትህን የማትተው ክብር ላንተ ❤ ተባረኩ ያብዛላችሁ

  • @negamekonnen8056
    @negamekonnen8056 Před 11 dny +5

    እግዚአብሔር ለዘላለም ይባረክ

  • @Preppy_2012
    @Preppy_2012 Před 11 dny +5

    EYSUS ❤❤❤

  • @FreeWende
    @FreeWende Před 11 dny +4

    ጌታ ኢየሱስ ይመጣል!!!

  • @AbebaDamesa-wc7ls
    @AbebaDamesa-wc7ls Před 11 dny +5

    Hallelujah hallelujah 🙌💥
    Iyesus ka igna gaa naw

  • @Alem-pk9mg
    @Alem-pk9mg Před 11 dny +4

    ኢየሱስ ጌታ ነው ስሙ ይባረክ በፍቅሩ ተንበርክከን ነው የተከተልነው

  • @user-ie7cf5cw1t
    @user-ie7cf5cw1t Před 10 dny +4

    ጌታሆይተባረክአንተትልቅነህ

  • @NelomaNeloma
    @NelomaNeloma Před 9 dny +2

    ለጠያቂው ምስክርነት የሚሰጡ ሰዎችን ሀሳብ ፍሰት ባታቋርጥ ጥሩ ነው፣
    ስለ አገልግሎትህ ተባረክ!

  • @user-nu8jm1pd2f
    @user-nu8jm1pd2f Před 11 dny +3

    ❤ እንኮን ደና መጣህ ወድማችን ጌታ ካተጋር ይሁን ብዙዎች ባተ ይድናሉ ጌታ እየሱስ ሆይ ቶሎ ና

  • @ZerfuZed
    @ZerfuZed Před 10 dny +4

    አባተ ስም ይባረክ

  • @Abenezer1100
    @Abenezer1100 Před 11 dny +4

    ህይወት ማለት ክርስቶስ ነው ክብር ለእርሱ ይሁን

  • @derejeaanereayonreayo6219

    እግዚአብሔር ይመስገን ።የዘመናችን ሐዋርያው ጳውሎስ እውነታውን ከቡሉይ ኪዳን እያጣቀሰ ህይወትን እንዳስተማረ አሁንም ኡስታዝ እናመሰግናለን ።

  • @user-rj1go6zw6e
    @user-rj1go6zw6e Před 11 dny +5

    OMG😮❤Our Lord Jesus is true Lord❤❤❤🎉🎉Glory🎉🎉🎉🎉Bro big respect 🙏🙏be blessed❤❤🎉🎉

  • @user-vl5vp5db9g
    @user-vl5vp5db9g Před 10 dny +6

    እግዝሐብሄር ይመስገን።ገና በዙፍኑ እሱ ይከብራል ይነግሳል የአለም ህዝብ ሁሉ ጌታን ያላገኘ ጌታ የግል አዳኝ አድርጓዉ ይቀበላሉ።አሜን አሜን አሜን ይሆናል

  • @user-ik5eu1kf2d
    @user-ik5eu1kf2d Před 10 dny +3

    ጊታ ኢየሱስ ከአውቆ አጥፈዎች ይልቅ ባለመረዳት ባለ ማወቅ እንትን የከዱትን አሁንም በራስህ አሠራር መልሳቸው ተገለጥላቼው ልፋት ድካማቼውንም እስበህ ወደራስህ መንግሥት ታስገባቼው ዘንድ እንለምንሀለን እንጸልያለን
    መንፈስ ቅዱስ አንተ በስራ ላይ ነህ ይህ ያንተ ይሥራ ውጤት ነው።። አሜን

  • @user-kd1bf6sn3i
    @user-kd1bf6sn3i Před 17 hodinami

    Well come to Great life. Jesus Christ is life. እንኳን ጌታ ረዳህ

  • @alemsegedgirma1165
    @alemsegedgirma1165 Před 10 dny +2

    Wow, what a great example given at the end of his talk.

  • @user-xs4cx2ve3j
    @user-xs4cx2ve3j Před 10 dny +3

    ወይኔ ጆኒ ❤❤❤ስለሰማሁክ ደስ ብሎኛል

  • @meaza5096
    @meaza5096 Před 11 dny +4

    እሰይ ሃሌሉያ ኢየሱስ ጌታ ነው ❤❤❤

  • @alemsegedgirma1165
    @alemsegedgirma1165 Před 10 dny +3

    Wonderful testimony with deep understanding of the Christ. God bless you!

  • @fikrucherenet7160
    @fikrucherenet7160 Před 3 dny

    God bless you guys.God is using you to give light to those who are in the captivity of falsehood.

  • @user-gy8bd8vh2q
    @user-gy8bd8vh2q Před 10 dny +3

    ወንድሜ ዘመንህ ዘርህን እግዜብሔር ይባርክ

  • @user-qj1wc8fq5c
    @user-qj1wc8fq5c Před 5 dny

    geta Eyesus lezelalem yibarek 🙏🙏🙏🙏

  • @mulugetamekonnen5741
    @mulugetamekonnen5741 Před 6 dny +1

    እግዚአብሔር ይባሮክህ ወንድም ሁሴን

  • @tinsaeeyuel
    @tinsaeeyuel Před 11 dny +3

    ክብር ለእየሱስ ይሁን

  • @mulugetamekonnen5741
    @mulugetamekonnen5741 Před 6 dny +1

    አሜን ተባረክ ።የክርስቶስን ህይዎት በምድረበዳ በትክክል የኖረ የተወደደ የእግዚአብሔር ሰው ነው። እኔ ምስክር ነኝ። የየተናገረውን የኖረ የእግር ሰው ተባረክ።

  • @eyobteakalign6435
    @eyobteakalign6435 Před 11 dny +3

    Jesus is truth .Amen for our God father revealed Jesus and saved you by him.

  • @melber7957
    @melber7957 Před 11 dny +3

    Geta Semu yebarek! Elelelelelel! Enkwan wede ewnetu menged meleseh my Oromo brother!🖤♥️🤍♥️🌳♥️ May God bless you and Oromo Nations 🙌🙌

  • @meaza5096
    @meaza5096 Před 11 dny +3

    እባካችሁ እርሳቸው ጠብቁ ተባረክ 🙏

  • @AnwarTriche-ep5hi
    @AnwarTriche-ep5hi Před 10 dny +8

    እኔ የሚገርመኝና የሚያቃጥለኝ መሀመድ ከኢየሱስ ጋር መነፃፀሩ መሀመድ እንኳን ከኢየሱስ ሊወዳደር ይቅርና ከምንም ጋር ማነፃፀር ይከብዳል እኔ የጳውሎስ መልዕክት ሳነብ እራሱ ኢየሱስ በጳውሎስ የሰራውን ስራ እንዴት እንዴት እንደምሆን እኔ አዉቃለሁ ከመሀመድ ጳውሎስ መቶ ፐርሰንት ይሻላል

    • @abebagebeyehu4691
      @abebagebeyehu4691 Před 7 dny

      አንተ እኮ የምታመልከው አምላክ ነው የምትለው እኮ የሚበላ የሚጠጣ የሚተኛ የሚቀሰቀስ ከበላ ከጠጣ ደግም ምን ይጠብቀውዋል መፀዳዳት አይገርምም አምላክ ሲዻፀዳዳ አስበው እውቀት አና እውነት ካላችሁ ለምን መድረክ ላይ አትወጡም ለነገሩ በናንተ መፍረድ አይቻልም ከላይ ያሉት መሪዎቻች በተለይ የንጽጽር መምህሮች ያሳዝናሉ ለክብርና ዝና ገንዘብ ብለው ዝዝዝም ጭጭ ያሉት

    • @yedidyaful
      @yedidyaful Před 4 dny

      @@abebagebeyehu4691የሚመችህን ግዜ አመቻችተህ ንገረኝ እና live መነጋገር እንችላለን። ከቻልህ አቡ ሀይደርንም ይዘህው ነው

  • @manal-jc777
    @manal-jc777 Před 10 dny +1

    ከምር ከዳነ ሰው የሚሰማ ድምፅ ነው የሰማሁት በጣም ደስ ብሎኛል ይህን ምስክርነት ስላካፈላችሁን ተባረኩልን ጌታ ዛም ይሰራል ያድናል ገና ለበረከት ሁኑ 🙏❤️

  • @derejeasefa6240
    @derejeasefa6240 Před 11 dny +4

    John 3:16

  • @asefshgebreweldi4618
    @asefshgebreweldi4618 Před 7 dny

    ❤❤❤❤❤❤❤❤❤🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉tebarek Joye

  • @GosaAb
    @GosaAb Před 11 dny +3

    ጌታ ይባረክ ወንድሜ በረታ

  • @tigimotigimo9572
    @tigimotigimo9572 Před 10 dny +2

    ድቅ ምስክርነት ነው እሰይ እኳን ጌታ ረዳክ ጌተንም አገኘክ ያተመዳን ለብዙ ሙስሊሞች መገድ ሊሆን ጌታ አተን መርጧል አተደሞ ከሞት ወደህይወት ስለመጣክ ይሄንን ሕይወት ላላገኛ ወገኖቻችን መናገር አለብክ ጌታ ይረዳካል ክረሰስትና ሰልፍ አለው በዛውስጥ ተሰርቶ ማለፍ ነው ወዳጄ አሁንም በክርስቶስ ባለው ፀጋ በርታ አተን ከዚ በኋላ ወደዛም ወደዚም የማያረግክ የለም በአለቱ ላይ ቆመካል የሚያናውጥም አይኖርም እግዚአብሔር ካተጋር ይሁን ተባረክ

  • @Alem-pk9mg
    @Alem-pk9mg Před 11 dny +3

    Praise God

  • @Alexjornalist
    @Alexjornalist Před 11 dny +3

    Hallelujah 🙏

  • @yonashailu1733
    @yonashailu1733 Před 11 dny +3

    Tebareke wedeme erjeme edeme yestek

  • @user-jt3gz3oe9e
    @user-jt3gz3oe9e Před 9 dny +1

    እግዚአብሔር ይባርካችሁ ጸጋውን ያብዛላችሁ

  • @agegnehualemu4250
    @agegnehualemu4250 Před 7 dny +1

    The word that the x-Muslim says is heartbreaking. ''Getahoy na yeminlew siledanen new, yet endeminhed sileminawk new'' . Thanks to God

  • @bereketshambel-gi2gr
    @bereketshambel-gi2gr Před 11 dny +4

    amen muslimoch danu yemedan ken zarev new

  • @user-ih1bd6lc3p
    @user-ih1bd6lc3p Před 11 dny +2

    የድግልማረያምልጅሥሙይክበርይመሥገን❤❤❤❤❤❤❤

  • @user-pb6vp1sv6u
    @user-pb6vp1sv6u Před 10 dny +3

    እንኳን እግዚአብሔር ረዳህ

  • @mizanteklemichael3364
    @mizanteklemichael3364 Před 7 dny +1

    Ere Jesus geta new bezuryaye yalut ahzabochn lbachew getahoy nkachew

  • @emebaemuti951
    @emebaemuti951 Před 10 dny +3

    Wow ! 😮😮❤❤

  • @damakesh5196
    @damakesh5196 Před 5 dny

    Tabaraku❤❤❤❤❤❤

  • @solomonmesersha4938
    @solomonmesersha4938 Před 11 dny +3

    Bless you

  • @user-zh2nc8vc5o
    @user-zh2nc8vc5o Před 10 dny +1

    ጌታ ለመጨረሻው ክብር ያብቃችሁ

  • @meskimeski3962
    @meskimeski3962 Před 3 dny

    ኢየሱስ ጌታ ነው ❤️❤️❤️

  • @Tewodros-tm7bs
    @Tewodros-tm7bs Před 8 dny +1

    Jesus Christ is King of all King's amen.Thank you Jesus Christ Son of God ulmaity.

  • @Meaza-hg9kj
    @Meaza-hg9kj Před 8 dny

    ❤❤❤

  • @negistitegafaw1491
    @negistitegafaw1491 Před 5 dny +1

    Eysus yadnal

  • @terhastewelde9576
    @terhastewelde9576 Před 7 dny

    ❤❤❤❤❤

  • @mam556
    @mam556 Před 11 dny +3

    ❤❤❤omg🎉🎉

  • @JibrilLamren8-gc6px
    @JibrilLamren8-gc6px Před 5 dny

    Subhan Allah azim Allah fera genzab yalkal

  • @sofimalt6524
    @sofimalt6524 Před 3 dny

    Jezba

  • @user-nb6xp2wm2j
    @user-nb6xp2wm2j Před 11 dny +2

    የምስራች ነው ! እግዚአብሔር ይመስገን ። እኛ የበራልን ሰንፈን ሳለ እግዚአብሔር ግን በዘላለማዊ ፍቅሩ እየዳሰሰ ወንድሞችን ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት እያፈለሰ ስላለ ደስታችን ዕፁብ ነው ።

  • @Selamawittadesse-rj7gz

    አሜን አሜን አሜን በእውነት የሚባርክ ምስክርነት ነው እኔ እንደስብከት ነው የተባረኩበት ተባረኩ ፡ሌሎችንም ለምስክርነት ብትጋብዙ ጌታ ፀጋውን ያብዛላችሁ በደሙ ይሸፍናችሁ ተባረኩ

  • @freweinimehari4448
    @freweinimehari4448 Před 6 dny

    ክብር ሁሉ ለጌታ ይሁን ተባረክ ወንድሜ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻውን ያድናል ይታደግማል

  • @bithaniyahebron1537
    @bithaniyahebron1537 Před 9 dny +1

    እንዴት ድንቅ አምላክ ነዉ እኛ ምናመልከዉ?❤❤❤

  • @user-km5ss1sw2v
    @user-km5ss1sw2v Před 11 dny +2

    Eysusi kerstose yigatoche gata yingstate negusa yihayalane ayalee new kerstoosi bechanew yes of course megidime hewtine esuubecha new 👌🏾👌🏾👌🏾👌🏾☦️☦️☦️⛪🙏🙏🌹🌹🌹🌹🌹

  • @ehitewolde7535
    @ehitewolde7535 Před 6 dny

    Jesus is king of king

  • @user-ik5eu1kf2d
    @user-ik5eu1kf2d Před 10 dny

    እጅግ በጥም አስደናቂና አስተማሪ የሆነ ምስክርነት ስለሰማሁ ልቤ በደስታ ዘለለ ጌታ ኢየሱስ ( መንፈስ ቅዱስ ) በሥራ ላይ ነው ፣ በእርግጥም በደሙ ከነቤተሰብህ ይሼፍንህ ይጠብቅህ ።

  • @sebleasheberabebe4265

    ማሜ ጌታ እየሱስ ይባርክህ። ድካምህ ፍሬ እያፈራ ስለሆነ ደስ ይበልህ

  • @JoneTg
    @JoneTg Před 7 dny

    Wow yemigerm miskirint yeterak geta yetamenen nw.

  • @user-bu7xz7sd7m
    @user-bu7xz7sd7m Před 8 dny

    ተባረኪ 🙏 ✅✅✅✝️✝️✝️✅✅✅💯💯

  • @freweynimebratu6870
    @freweynimebratu6870 Před 11 dny +4

    😮🎉

  • @user-ef2st6jh4c
    @user-ef2st6jh4c Před 7 dny

    ዋዋዋዉ ለዩ መረዳት

  • @zelekebunchamo7741
    @zelekebunchamo7741 Před 11 dny +3

    ሃሌሉያ ኢያሱስ ይድነል

  • @asfawbayisa4929
    @asfawbayisa4929 Před 7 dny

    ጌታ ይመስገን ።እንኳን ጌታ እየሱስ ረዳህ

  • @kibreabesey9582
    @kibreabesey9582 Před 10 dny +1

    ❤❤❤እኔ ግን ስለ መሓመድ ሳስበው ልክ እንደ መኮረጅ ይተጠናወተው ተማሪ ግን ደግሞ ሲኮርጅም ጎበዝ ያልሆነ ሰነፍ ተማሪ ሆኖ ይሰማኛል!! I know ፊደል መቁጠርም እድሉ እንዳላገኘ!! ❤❤❤

  • @azalechhaile6328
    @azalechhaile6328 Před 8 dny

    አንተ ሰው ጌታ ነው ከሲ ኦል የታደገህ በርታ የሰውን ነገር ተወው የሰላም አምላክ ይርዳክ

  • @Savedbyonlygrace777
    @Savedbyonlygrace777 Před 7 dny

    Glory to God!

  • @dinkeneshzeleke1257
    @dinkeneshzeleke1257 Před 8 dny

    Amen Amen eyesus kibirun hulu geta yiwesed

  • @abyya2271
    @abyya2271 Před 8 dny

    Kiber yihun le geta amen amen eyesus geta new❤❤❤❤🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉

  • @user-bu7xz7sd7m
    @user-bu7xz7sd7m Před 8 dny

    አሜን አሜን አሜን እየሱስ ያድናል ::

  • @user-qn5hg5go7s
    @user-qn5hg5go7s Před 8 dny

    Autaze selanta.,Egzabhare.yikbar.