የደም ግፊትን ለመቀነስ የሚረዱ 11 ጤናማ ምግቦች | 11 eessential foods for lowering blood pressure - Hypertension

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 20. 12. 2022
  • ጤናማ አመጋገብ የደም ግፊትን ለመቀነስ እና ለመቆጣጠር አስፈላጊ ነው፣
    ። ጥናቶች እንደሚያሳዩት የተወሰኑ ምግቦችን በአመጋገብ ውስጥ ማካተት በተለይም እንደ ፖታሲየም እና ማግኒዚየም ያሉ ልዩ ንጥረ ነገሮችን የያዙ ምግቦችን ማካተት የደም ግፊትን ለመቀነስ ይረዳል።
    1. Citrus ፍራፍሬዎች
    የ ወይን ፍሬ፣ ብርቱካን እና ሎሚን ጨምሮ ያሉ ፍራፍሬዎች የደም ግፊትን የመቀነስ ኃይል አላቸው። እነዚህ ፍራፍሬዎች ከፍተኛ የደም ግፊት ያሉ የልብ በሽታ አምጪ ሁኔታዎችን በመቀነስ የልብዎን ጤንነት ለመጠበቅ የሚረዱ በቪታሚኖች፣ ማዕድናት እና በእፅዋት ውህዶች የተሞሉ ናቸው።
    2. ሳልሞን እና ሌሎች ስብ ዓሦዎች
    ስብ ዓሦች ለልብ ጤና ጠቀሜታ ያላቸው ሲሆን የኦሜጋ -3 ፋት ምንጭ ናቸው። እነዚህ ቅባቶች እብጠትን በመቀነስ እና ኦክሲሊፒን የሚባሉ የደም-ወሳጅ-ውህዶችን መጠን በመቀነስ የደም ግፊትን መጠን ለመቀነስ ይረዳሉ።
    3. የዱባ ፍሬ
    የዱባ ፍሬዎች ትናንሽ ቢሆኑም ከአመጋገብ ጋር በተያያዘ ትልቅ ጠቀሜታ የሚሰጡ ናቸው። ለደም ግፊት መቆጣጠሪያ አስፈላጊ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ማለትም ማግኒዚየም፣ ፖታሲየም እና አሚኖ አሲድ የያዙ ናቸው።
    4. ባቄላ እና ምስር
    ባቄላ እና ምስር እንደ ፋይበር፣ ማግኒዚየም እና ፖታሲየም ባሉ የደም ግፊትን ለመቆጣጠር በሚረዱ ንጥረ ነገሮች የበለፀጉ ናቸው። በርካታ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ባቄላ እና ምስር መመገብ የደም ግፊትን መጠን ለመቀነስ ይረዳል።
    5. ካሮት
    ካሮት በብዙ ሰዎች አመጋገብ ውስጥ የሚካተት ዋነኛ አትክልት ነው። ካሮቶች የደም ሥሮችን ለማዝናናት እና እብጠትን የሚቀንሱ በphenolic ውህዶች የበለጸጉ ናቸው። ይህም የደም ግፊትን መጠን ለመቀነስ ይረዳል ። ካሮትን በመብሰል ወይም በጥሬው መመገብ ቢቻልም በጥሬው መመገብ የደም ግፊትን ለመቀነስ የበለጠ ጠቃሚ ነው።
    6. ቲማቲም
    ቲማቲም ፖታሲየም እና ላይኮፔን ጨምሮ በብዙ ንጥረ ነገሮች የበለፀገ ነው። ላይኮፔን በልብ ጤና ላይ ከሚኖረው ጠቀሜታ ጋር በእጅጉ የተቆራኘ ነው። በነዚህ ንጥረ ነገር የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ እንደ ደም ግፊት ያሉ ለልብ በሽታ ተጋላጭ የሚያደርጉ በሽታዎችን ለመቀነስ ይረዳሉ።
    7.ብሮኮሊ
    ብሮኮሊ የደም ዝውውር ስርዓትን ጤና ጨምሮ በጤና ላይ ባሉት በርካታ ጠቃሚ ውጤቶች ይታወቃል። ለምሳሌ፣ ይህንን አትክልት ወደ አመጋገብ ማከል የደም ግፊትን ለመቀነስ ብልህ መንገድ ነው። ብሮኮሊ በflavonoid antioxidants የበለፀገ ነው። ይህም የደም ሥሮችን ተግባር በማሳደግ እና በሰውነት ውስጥ ያለውን የናይትሪክ ኦክሳይድ መጠን በመጨመር የደም ግፊትን ለመቀነስ ይረዳል ።
    8.ተልባ
    ተልባ ፖታሺየም፣ ማግኒዚየም እና ፋይበርን ጨምሮ ለጤናማ የደም ግፊት መቆጣጠሪያ አስፈላጊ በሆኑ ንጥረ ነገሮች የበለፀገ ዘር ነው።
    9. ስፒናች
    ስፒናች በናይትሬትስ ይዘቱ ከፍተኛ ነው። በተጨማሪም በፀረ-ኦክሲዳንትስ፣ ፖታሲየም፣ ካልሲየም እና ማግኒዚየም የበለፀገ ነው። ይህም ከፍተኛ የደም ግፊት ላለባቸው ሰዎች ምርጥ ምርጫ ያደርገዋል ።
    10. ነጭ ሽንኩርት
    ነጭ ሽንኩርት የደም ግፊትን ለመቀነስም ይረዳል። ነጭ ሽንኩርት እብጠትን ለመቀነስ እንደሚረዳ ጥናቶች ያሳያሉ። ነጭ ሽንኩርት በምግብ ውስጥ መጠቀም ጣዕም ለመጨመር ከማገዙም በላይ ጨውን መጠን ለመቀነስ ይረዳል, ይህም የደም ግፊትን የሚቀንስ ይሆናል።
    11. ሙዝ
    ሙዝ በፖታስየም የበለፀገ በመሆኑ ሰውነታችን ሶዲየምን እንዲያሶጣ ይረዳዋል። "በሶዲየም የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ የደም ግፊትን ይጨምራል።"
    #hypertension
    #food
    #ምግብ

Komentáře • 10

  • @dr.amanuel-
    @dr.amanuel-  Před rokem +3

    እንኳን በደህና መጣችሁ ላይክ እያደረጋችሁ ሌሎችንም አስተምሩ 🙏🙏🙏
    መልካም ጤና

    • @yarab4997
      @yarab4997 Před 28 dny

      ስንት ነው ትክክለኛ ግፊት ስለማላውቅ ነው

  • @tsegafisha1838
    @tsegafisha1838 Před 3 měsíci +1

    የዱባውን ፍሬ እንዴት ነው የምመጋቨው?

  • @user-hb6tv5px3s
    @user-hb6tv5px3s Před 3 měsíci

    በጣም በጣም በጣም አመሰግናለሁ ❤❤❤❤❤❤

  • @user-hf6mk8dl7m
    @user-hf6mk8dl7m Před 4 měsíci

    ብሮኮሊ ምን አይነት አትክልት ነውወ

  • @bedileabebe6400
    @bedileabebe6400 Před 4 měsíci

    ምስሩ ድፍን ምስር ነው? ወይስ ምስር ክክ ነው?

  • @user-nq3vh1nw1k
    @user-nq3vh1nw1k Před 2 měsíci

    Dr enate dem gifitim sikuarm alebat dem gifitin lemekenes sitimokir sikuaru yichemiral huletunm ekul lemekenes yemihon migib bitinegiregn

    • @dr.amanuel-
      @dr.amanuel-  Před 2 měsíci

      በጣም ጥሩ በዋነኛነት ለሁለቱም በሽታዎች የሚሆን ምግብ ፍራፍሬዎች ናቸው። ፍራፍሬዎች ጤናማ ምግቦች ናቸው። ሌላው አትክልቶች ለምሳሌ ጥቅል ጎመን ፣ ብሮኮሊ ፣ ቆስጣ እኖዲመገቡ ይመከራል። ዋናው ጥንቃቄ ማድረግ ያለብሽ ከቅባት ፣ ከስኳር ፣ ከጨው ፣ ከቡና እንዲርቁ ማድረግ ነው። እነዚህ ናቸው ለሁለቱም በሽታዎች መጥፎ የሚሆኑት። እና ትልቁ ነገር እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ አለማምጃቸው። ቢያንስ መራመድ ። ከምግብ ባለፈ እንቅስቃሴ የበሽታ መድሃኒት ነው።

  • @triedrecipes8973
    @triedrecipes8973 Před rokem +1

    እባኮትን በዩትዩብ ቻናሌ ደግፉኝ አመሰግናለሁ