እኔም የማፋታት ስልጣን የለኝም /ለፈውስ አስቸጋሪ ነው የሆነው አልታመምንም ይላሉ

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 28. 11. 2022
  • #fevenketema #pasterchere #ethiopia #love #lovestory #talkshow #counseling #tedar #mirrage
    The official You tube Channel of Feven Ketema.
    Enjoy! Subscribe!
    Connect for more.
    / fevenketema
    / fevenketema. .
    fevenketema.com/
  • Zábava

Komentáře • 110

  • @fevenketema
    @fevenketema  Před rokem +7

    በዚ የቴሌግራም አድራሻችን ያገኙናል ። እውነተኛ ታሪካችሁን ላኩልን 0973710801 ( @feven04)

  • @bezawitdesalegn7507
    @bezawitdesalegn7507 Před rokem +4

    የቆረጠ ሰው 3ኛ ወገን አያማክርም ወገን

  • @familypromotion9552
    @familypromotion9552 Před rokem +27

    ፍቅር ከሌለ ሀፍት ከንቱ ነው ወንድሜ እባክህ ባለቤትህን ይዘን ገዳም ግባ ንስሀ ግብ በንስሀ ታጠብ እግዚአብሔር ሁሉን ያስተካክላል ይች እህታችን ሰይጣን ነው የሚጫወትባት እባክህ ከጎኗ ሁነህ እርዳት አይዞህ እግዚአብሔር ይርዳህ ወላዲቷ ትርዳችሁ

    • @kbqday116
      @kbqday116 Před rokem

      ተመሳሳይ ህይወት ድገሚው አንቺም

    • @familypromotion9552
      @familypromotion9552 Před rokem

      ምነው የሰይጣን መልክተኛ ነኝ አልክ ይቅር መባባል እኮ ለእራስ ነው

    • @kbqday116
      @kbqday116 Před rokem

      @@familypromotion9552 እየማገጡ ይቅርታ የለም በድንጋይ መውገር ነው እጂ ዝሙት የሰይጣን ነው

    • @zemarisaradesta8273
      @zemarisaradesta8273 Před rokem

      Lhamhidhino Lhaxurhusho xurhu mhagano Adhe yhelhamhadasho mhachemhi ayharhifhimi

  • @tigabnehshimelis539
    @tigabnehshimelis539 Před rokem +24

    የሚፈልጉንን ችላ እንላለን ችላ የሚሉንን እንፈልጋለን የሚጎዱንን እናፈቅራለን የሚያፈቅሩንን እንጎዳለን
    #####
    ጥቅም እንጂ ፍቅር የለም እኔ እንጂ እኛ የለም የላይ እንጂ የውስጥ የለም ከአፍ እንጂ ከልብ የለም ምላስ እንጂ ተግባር የለም ስደት እንጂ ገንዘብ የለም
    ይሄው ነው!!

  • @meazagirmakostr9267
    @meazagirmakostr9267 Před rokem +8

    ይገርማል ገንዝብ ሲኖር ፍቅርየለ ፍቅር ሲኖር ገንዝብ የለ ፈጣሪ ብቻ የተስተካከለ ፍቅር ይስጠን😌

  • @rahelnegasie7937
    @rahelnegasie7937 Před rokem +11

    ጌታሆይ 21አመት ሙሉ ያለ ፍቅር ።በኢየሱስ ስም ሴትዬዋን የሚጠቀም መንፈስ ይፈርስ ዘንድ ፀሎትነው ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን ።

    • @Tanoba658
      @Tanoba658 Před rokem +1

      ማፍረሱን በርከክ ብለሽ ብታደርጊው መልካም ነው

    • @esayastasew1869
      @esayastasew1869 Před rokem

      ብዙ ንብረት ሲኖረዉ አንድ ክላሽ አልገዛም እንዴ ይሄ ወታደርነኝ ካለ ምን ይሰራል።።

  • @hilila9073
    @hilila9073 Před rokem +5

    እኔ መጀመርያ እሶ ትጠየቅ እሱ የሪሱ የሆነ የተደበቀ ችግር ሊኖረዉ ይችላል እሱን ከማሞገሳቹ በፊት አንድ ላይ አናግራቸዉ

  • @haregtegegkeya8871
    @haregtegegkeya8871 Před rokem +6

    ቸሬ እኮ ይለያል ሥል በምክንናት ነው ❤️

  • @user-wg6em5id3p
    @user-wg6em5id3p Před rokem +5

    የማዳም ቅመሞች እየቀሠማቹህ ምክር ደስ የሚል ዋው

  • @beti_boo556
    @beti_boo556 Před rokem +5

    እውነት ፓስተር ቸሬ እንዳለው የመርህ ሰው ከሆንክ እመነኝ ትዳርህን መፍታትና ቤተሰብህን ማፍረስ ሰላም የሚሰጥህ ይመስልሀል እንጂ ደስተኛ አያረግህም በአዕምሮአችን የምንስለውን አይነት ፍፁም ፍቅር ሁላችንም ኖረነው አናልፍም እሱ ለጥቂቶች ብቻ የታደለ ነው አብዛኛውን ሰው ከተጋባ በኋላ የሚያኖረው ፍፁም ፍቅር ሳይሆን ቤተሰባዊ ኮሚትመንት ነው አንተም እሱን ላለማጣት ነው ከሀያ አመት በላይ የታገስከው ስለዚህ እንደተባለው ቤተሰብህን እንደቤተሰብ ለማቆም ሁለታችሁም እራሳችሁ ላይ ስሩ እንጂ ፍቅር የለኝም ብለህ በፍፁም ትዳርህን ለመፍታት እንዳታስብ

  • @tigistgirma6941
    @tigistgirma6941 Před rokem +10

    ቸርዬ የማዳመጥ ብቃትህን ሳላደንቅ አላልፍም

  • @maffikonjo1
    @maffikonjo1 Před rokem +7

    You are an amazing husband just give time to heal and allow professional counselor help you. And above all God will help you. It will be OK and you will enjoy the rest of your marriage. Always put God first in your life

  • @senaitgebrat4394
    @senaitgebrat4394 Před rokem +1

    ትክክል ባስተረር ልጁ በጣም ይወዳታል ፍቅር ዶሞ በአንድ ስትኖሪ አይገባሽም ቀላል ነው ሚመስልሽ ስትለያ ነው የምታውቂው ንስሐ ገብታቹ ታረቃት እና ጌዜ ስጣት እግዛአብሄር ያሳካልህ

  • @hope998
    @hope998 Před rokem +1

    አይ ቸሬ ምትገርም ሰው ነህ እኮ ማርያምን ሁሌም ነገሮችን ማሰብክ ከምችለው በላይ ነው ምትገልፃቸው ጌታን።ወደ ወንድሜ ስመለስ ቸሬ እውነቱን ነው ስሜት ነው ያጣከው እንጂ ትወዳታለህ ታፈቅራታለህ ሲቀጥል መሰረቱ ላይ ነበር ስህተቱ የጀመረው በእውነት ይህን የምለው ከእራሴ ህይወት ተሞክሮ ነው።ለዛ መሰረት ማጣት በህይወቴም በእድሜዬም ሙሉ ዋጋ ከፍላለው እየከፈልኩም ነው።መወስለት ምንም ደስታን አይሰጥም እሷም የዚህ በሽታ ተሰቃይ ነች ታማለች አሳክማት ወንድሜ። ለልጆችህ ዋጋ ክፈል።ቸርዬ ፌቨንዬ እወዳችዋለሁ ተባረኩ🙏🙏🙏

  • @yetnayetadmasu2995
    @yetnayetadmasu2995 Před rokem +2

    በርግጥ አንድ ወገን ሰምቶ መፍረድ ትንሽ ከበድ ይላል አንዳንድ ሰዎች ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሀል እንደሚባለው አይነት ናቸው ስለዚህ ሁለቱንም መስማቱ የተሻለ ነው

  • @user-cg7oc2wv9w
    @user-cg7oc2wv9w Před rokem +2

    ፍቅር ከሌሌ ፎቅ ቢደርደር ትርጉም የለዉም መለያየት ብቻ። ሳይበላ ይቅር ከቤት ሰላመሰ ከሌለ እዴት ! ጎርቤት ጋር እደለ ይሰማኛል እና ወድሜ ተፍታችሁ። የራሳችሁን ኑሮ መኖር። ንስሃ ገብቶ ሰላም ያለው ኑሮ መኖር እዴት ሰው ልልጂ ለሀብት ብሎ እራስን መጉዳት አለማወቅ ነው ። እግዚአብሔር አለማሳዘን !

  • @setra..3763
    @setra..3763 Před rokem +1

    እንደዚህ ታሪክ የገረመኝ የለም የትግሥት ጥግ ነው ያለው እሡጋር ብቻ መፍትሄውን ይላክላቸው

  • @user-mr8np9mc2s
    @user-mr8np9mc2s Před 10 měsíci

    እውነት አተህ መልካም ሰው ነህ ትዳር ከቡር ነገር ነው መኝታሁም ቅዱስ ነው ምናልባት እሶአ ምክንያት የምታደርገሁ። አተህ ጊዜ አልሰጠኝም ይሆናል። ግን ከባድ ነው እናት ሆናአ ለራሶአም ክብር የላትም ወድሜ እራስን ጠብቅ ይወት ይቀጥላል ትቅርብ። ስራአ አድክሞ። ትዳር ሰላምን ያልሰጠህ ወላሂ ትቅርብ። መልካም ሰው ነህ አብሽር

  • @user-pb6cf4lw7e
    @user-pb6cf4lw7e Před rokem +6

    በጣም ትግስተኛ ነህ ሚስት ተብየዋ ግን አስመሳይ ነች መቶ ጊዜ ይቅርታ ብታረግላት ከዚ አመልዋ አትወጣም ለልጆችዋ እንኩዋን አልተጠነቀቀችም በልጅነት አይምሮአቸው የናታቸውን ልክ ያሎነ ድርጊት አይተዋል እናት የልጆች አርአያ እንጂ የስድነት መማርያ አደለችም ብቻ ለውሳኔው ፈጣሪ ይርዳህ ባንተ ቦታ ብሆን ወንድ እንደዚ ሲማግጥብኝ አልታገስም ሰው አንዴ ይቅርታ ያረጋል የተደጋገመ ይቅርታ ማረግ ለሰዎች መጫወቻ መሆን ነው።ፈጣሪ በምናጠፋቸው ጥፋቶች ሁሉ ይቅር ይለናል ሰው ግን እንደፈጣሪ ደጋግመህ ይቅርታ ካረክለት መጥፊያህ ነው ሚሆነው።እስካሁንም ባደረገችው ተኝተአል በሽታ የሚባል ነገር አለ።

  • @epht
    @epht Před rokem +2

    Addicted የሚለውን ፊልም ጋብዙልኝ ለባልየው። እና ሁሌም ልብህን አዳምጥ ፈጣሪን ጠይቅ በደንብ ፀልይ እሷም ወዳ ላይሆን ይችላል

  • @hilila9073
    @hilila9073 Před rokem +2

    ፓስተርዬ ተባረክ

  • @Tube-ot9lj
    @Tube-ot9lj Před rokem +1

    እዉነት ለፍርድ የሚከብድ ታሬክ ነዉ ፖስተር ጥልቅ የሆነ እይታ አለወት ሳላደቅ አላልፍም እሱ በጣም ጠካራ ባል ነዉ ያማለት ግን ለትዳሩ ፐርፌክት ነዉ ማለት አይደለም ለትዳሩ መቆየት ትልቅ መስዋትነትን ከፍሎአል ጥያቄዉ መፍትሔስ ብሎ ምን አደረገ እኛ ሴቶች ቁስ የምንፈልገዉ መስመር እስክገባ ነዉ እጅ ጫፍ ስንደርስ ዞረን የምንፈልገዉ ገዘቡን ሳይሆን ፍቅርን ነዉ በቀረብኝ የሚሉ ብዙወች ናቸዉ በጭራሽ ያን ማንነት መቀበል ይከብዳቸዋል
    ሴት ልጅ ጊዜ የሚሠጣትን አለባበስዋን ሳይቀር የሚያይላትን ጠካራ ጎኖችዋን የሚነግራትን በዛ ህይወት ዉስጥ ያላትን ዋጋ የሚነግራትን የሚያዳምጣትን ትፈልጋለች እኒህን ሁሉ ያገኘች አይመስለኝም እጅ ለትዳርዋ ፍላጎት ስለሌላት አይደለም ካልፈለገች እኮ ማፍረስ ትችላለች የገብ ችግር የለባትም ቢዝነስ የማቀሳቀስ ብቃቱ አላት ከዛ ትዳር መዉጣት የማትፈልግበት ትዳሩን ትፈልገዋለች ግን የምትፈልገዉን እያገኘች አይደለም
    እሡ ጊዜ ይስጣት እድታስብበት በግልፅ ያዉሩበት እያዳዱን ችግሮችዋን የሚያቀዉን ሁሉ ይገራት ለመጨረሻ ጊዜ ታስብበት አተም ትዳሩን ከፈለከዉ ያለፈዉን ሁሉ እርሳዉና እዳድስ ያኔ እዳገኘሐት ተዋወቁ ከስራህ ባልተናናሠ ስራህ አርጋት አዳምጣት ችግርህን ያጎደልክባትንማስተካከል ያለብህን ጠይቃት የስዋንም ስተትዋን ንገራት ጥንካሬዋንም የምትወድላትንም ንገራት ሴቶች የሚረዳንን እንወዳለን እኔም ደካማነኝ የተሠማኝን ለመናገር ያክል እጅ አዋቂ ሆኘ አይደለም

  • @tizitadestaw8536
    @tizitadestaw8536 Před rokem +4

    Amazing teachings..thank you so much

  • @alemmama3836
    @alemmama3836 Před rokem +2

    ደስ እሚል ትምህርት ዉስድኩ

  • @yeselemonsistg
    @yeselemonsistg Před rokem

    እውነት ፓስተር ትልቅ ምክርነው የሰጡን ለኛም የሚጠቅም ነገርነው 🙏እግዚአብሔር ያክብርልን እራሱን ይፈትሺ በሚለው እኔም እስማማለሁ ምን ብርቢደላ ቤት ቢያሞላ ጊዜ ካልሰጣት ሚስት እንደሆነች እንዲሰማት ካላደረገ ፍቅርፍለጋ መውጣትዋ አይቀሬነው ስለዚህ ሀገር ከመዞሩም ቀነስ አድርጎ ጊዜ ያሳልፉ ሰው የሰጠውነው የሚመለስለት እስዋጋም ስሜትዋ አሼንፎት እንጂ ትዳርዋን ጠልታ አደለም ጊዜ ፍቅር ከሰጣት የራስዋ ጭንቅላት ወቅሶ ይመልሳታል ካለዛ ያገር ብር እስቤዛ እየጎተቱ ከቤት ወቶ ስራ ከስራ መልስ እንቅልፍ ከሆነ እስዋ ትክክልነች ባልልም እንደሰው ስሜት የሚባልነገር አለ ከሱያጣችውን ሌላጋ ፍለጋ ወጣች የኔ የስዋ ጥፋት ዋና መሰረት እሱነው ብየ አምናለሁ እስዋ ልክነች ማለቴ አደለም ግን እሱ ተስተካክሎ ይሞክራት በርግጠኝነት ትመለሳለቺ😍🙏

  • @elei417
    @elei417 Před rokem +2

    May God be with them

  • @yezinamulumengsit771
    @yezinamulumengsit771 Před rokem

    አይዞህ ወንድሜ ወዳ አንደለም ንስሀ ግቡ ጹሙ ፀልይ እግዚአብሔር ይርዳችሁ

  • @saraashebir1788
    @saraashebir1788 Před rokem +1

    Bless you pastor Egzaber melkam new

  • @mekdestamru2652
    @mekdestamru2652 Před rokem +1

    Paster cheere yerso kal yemr gebi astemari new zemenot ybarek

  • @besufekadhailu396
    @besufekadhailu396 Před rokem

    Fevuye banchi program betam tetekmeyalew le Pastor Chere demo Eg/r yibarkih bante misir betam tetekmeyalew beyilgn

  • @selamalem2443
    @selamalem2443 Před rokem

    Pastor Chere, an amazing speech as he said this guy still have a feeling for his wife but he is so hurt what she has been doing to him…. And they really need counseling from Chere… may god bless you Fabi and pastor!!!

  • @addisw1713
    @addisw1713 Před rokem +4

    ፌቪዬ ቶሎ ልቀቂው ቪዲዮው

  • @elshadaysolomon2102
    @elshadaysolomon2102 Před rokem

    በጣም ጥሩ ሀሳብ ነው ውዴ

  • @meseretgetachew6362
    @meseretgetachew6362 Před rokem

    ከባድ ጉዳይ መሰረት ስንሰራ ወይ ልንሰራ ስናስብ በጣም ጥንቃቄ እሚያስፈልገው ጉዳይ ምክንያቱም እምንቀርበውን ሰው ገና ልናውቀው ስለሚሆን መሰረቱን ካበላሸን ሁሌም እንደተበላሸብን ነው ምንኖረው በቀላሉ ሚረሱ ሰዋች እንዳሉ ሁሉ በቀላሉ እማያስቡና መርሳት እማይችሉ ሰዋች ይኖራሉ ምናልባትም ከልብህ ምትቀርበው ሰው አንተን ሲሸውድህ ማየትም ሆነ መስማት እንደሚከብ ያለ ጥቁር ጠባሳ የለም💔 ስለዚህ ቀድመን ከማድማት ብንጠነቀቅ ባይ ነኝ Thank you 👏😘 ፌቩዬ

  • @sifanlemma1606
    @sifanlemma1606 Před rokem

    Yemigerm Tarik new feve enam tariken likelsh nebar ye asbi setugn betaseb asabi edasetugn feligalew betam yemigermaw afikarin tefekari ayigenagnm

  • @helenalamin9762
    @helenalamin9762 Před rokem

    የኔ አስተያየት ለሰዉየዉ ነዉ እስቲ በደንምብ ግዜ ስጣት እዉድሻለሁ በላት ሴቷች መደለል እንወዳለን ግን ተረፒ መሄድ አለቦችሁ

  • @birzafadmasu388
    @birzafadmasu388 Před rokem +1

    ሰዉየዉ ታዲያ ምንድን ነዉ እሚፈልገዉ ፍቅር የለኝም ካለ ምን ያልመጠምጠዋል

  • @mismtg5829
    @mismtg5829 Před rokem +1

    Waw pasterye lk nek enem bendet gebchebet new zare meleyayetn merche arfe shawr eyewesedku ljen yze mnorew

  • @birzafadmasu388
    @birzafadmasu388 Před rokem +1

    ወይ ፓስተርዬ በዚ ዘመን የተሰጠኸን በረከታችን ነህ በብዙ ለምልምልን

  • @zuzulove9763
    @zuzulove9763 Před rokem +2

    አለመታመን አለመተማመን ፍቅርን ይገላል ምናባቷ አሯሯጣት ባል እያላት

  • @mismtg5829
    @mismtg5829 Před rokem +1

    Endemimeslegn ychi set yesmet guday new wchin endtay yaderegat gn pasterye biyagegnut ena mlashun btasawkun

  • @emu3288
    @emu3288 Před rokem

    I wish the intro music is not that noisy, the rest is great. You are doing good job

  • @ashenafigeremew5857
    @ashenafigeremew5857 Před rokem

    Wedem betam tegestehen adekalho tefato mejemeriya new k sew lay yewsedehat set nat ena esuwa tedarehe ayedelchem susengan sew mechem ataremewem beka er yerasehen hiwet nuer endy

  • @tigistbayou5832
    @tigistbayou5832 Před rokem

    ወዳ አይደለም የዝሙት መንፈስ ነው ወደ ፀሎት ቤት በብርቱ ፀልዩ. እንቢ ካለች ግን ተዋት አትለወጥም

  • @MulunaLewi
    @MulunaLewi Před rokem +1

    No separaten is the best für this family.......

  • @birhantefera2185
    @birhantefera2185 Před rokem

    gerami hasab ena program nw berttachhu ketlubet tmhrt sechi nw

  • @dunbodunboye4026
    @dunbodunboye4026 Před rokem

    😄 አይ ቸሬ 💋👀

  • @Tube-ot9lj
    @Tube-ot9lj Před rokem

    ወዶች እኪያገቡህ ጠብርግፍ ይሉና ልክ ተጋብተዉ መፈቅ አይቆዩም እናቱ ወይም እህቱ ትመስለዉና ዉሎ መግባቱን እቤት መኖርዋን ብቻ ያያል በተለይ ከወለደች በሁዋላማ ሁሉን ነገር ይረሳዋል ስራ ስራ ስል ሚስቴን ረሳሁዋት አይልም እስኪ ድሮ ያስለመድኳትን ልዉሠድላት እስኪ ያኔ ሳንጋባ የሔድንበት መናፈሻ ሚስቴን ልዉሰዳት እስኪ ………………………………………የለም በቃ ሚስት አርገዉ ካስገቡህ በሁዋላ መዝናናት ምናምን ነዉር የሚመስላችሁ ስቶቻችሁ ናችሁ ድሮ የጉዋደኛየ ልደት ላይ አች ካልመጣሽ አልሔድም ይል የነበር ያኔ በዉሎዉ ያሳለፈዉን ሁሉ ከስራ ደክሞ መቶ ድምፁን ቀንሶ በሹክሹክታ ሲያወራ አድሮ ሲነሳም እደፀሎት ድምፅሽን ካልሰማሁ ይል የነበረ በነገርሽ ሁሉ ይኔ ይል የነበረ ማሬ እያመመኝ ነዉ ነገ ሐኪቤት መሔድ እፈልጋለሁ አብረሔኝ ትሔዳለህ ዉይ አልችልም እገሌጋ ሒጅ እሽ ከዛምኮ ደዉሎ ሔድሽ ቀረሽ ምናሉሽ ኤረ ጠላቱ ምን በወጣዉ ሚስትዮ አይታ አይታ አልጠይቅ ሲላት ቆጠር ቆጠር ትላለች እስዋ እድጠይቃት ነዉ እሡደሁ ወይ ስልኩን ወይ እሬሞት ይዞ ዞሮም አያያት ሚስኪንዋ ሚስት ያኔን አይታ የገባችዉ ቆይ ግን እደዉ ቢያስኳን ሔድሽ እደትሆሽ ምንአሉሽ አትልለኝም ለነገሩ አተ መች ከሠዉ ቆጥረሔኝ ድከሚ ቢለኝጅ አስብ ያኔ እርር ብላለች ባልዮዉ ይባስ ቢለዉ ዉይ ማሬ የኔነገር እወቅሽዉ ስራ እደሚበዛብኝ እርስት አረኩት የባሳለዉ አሁንም የባስ ቅጥል ሁሌ ሠፍ የሚልላት መስሎአት ገብታ ጭራሽ ተረስታ ቁጭ ወዶች አያዮም እጅ ሴትዋ ወዳዉ ለምን ብላ ራስዋን ታያለች ትንሽ ቀናት ተበሳጭታ ቆብላ ስታስብ እስኪ ወደራሴ ልመለስ ትልና ድሮ እደሚወደዉ ለብሳ የሚወደዉን ምግብ ሰርታ ስጠብቀዉ በቤት ዉስጥ ያለዉን ስራ የረሳዉ በል ደናዋላችሁ ብሎ ገብቶ እራት በልቻለሁ ደክሞኛል ልተኛነዉ ልጆች እዳይረብሹኝ ነገ ስብሰባለብኝ አለ ……………………??????

  • @madinasaed4392
    @madinasaed4392 Před rokem +1

    ይለቀቅ ቪድዮው❤❤❤

    • @user-bu4rn5kk1i
      @user-bu4rn5kk1i Před rokem

      Awo betammm ene rasu video eyezegeyebegn techegerkute😂 yemere

  • @user-pb6cf4lw7e
    @user-pb6cf4lw7e Před rokem +2

    ልባችንን አንጠለጠላቹት ቬቨንዬ

  • @zuzulove9763
    @zuzulove9763 Před rokem

    አር እሡ አላህ ሢያገጣጥም ነው ምንም እይታው እይቷት ከማያውቅ ሠው ጋር ተጋብተው ውልዴው በፍቅር የሚኖሩ ሥንት አሉ

  • @abisiniyadire1807
    @abisiniyadire1807 Před rokem

    ግን እኮ መፁሀፋ ቅዱስ እንኩዋን ዝሙት ከተፈፀመበት አንድ ሰዉ ፉቺ ተፈቅዶለታል። ካልሆነ በፀሎት እና በንሰሀ ያስተካክሉት በጣም ይፀልይበት ለግዜር የሚሳነው የለም።

  • @alaabdr1428
    @alaabdr1428 Před rokem

    ድምፁ የለውም

  • @tsidutaye1285
    @tsidutaye1285 Před rokem +1

    Durye hulem durye new atlfu

  • @enudemis5623
    @enudemis5623 Před rokem

    ማንም ሰው ሳይጎልበት ቺት አያደርግ ከሰጣት ካለሁ ሀብት የጎደለባት በልጦባት ይሆናል እራስን ፈትሾ እኔ አደዚ ባላደርግ እሷ እደዚህ አትሆንም ብሎ ማሰብ መቻል ትልቅ ነገር ነው ፍቺ ሳይሆን መፍትሄው እራስን ጥፋተኛ አድርጎ ማሰብ ከወቃሽነትህ ወተህ እራስህን ፈትሸህ ትረዳት ይሆናል

    • @user-xs7jb3qg1d
      @user-xs7jb3qg1d Před 10 měsíci

      አወ ቢሆንም ግን መናገር አለባት ችግርበግልፄ መነጋገር ከዛ የማያስተካክልከሆነ መቀጠልካልሆነ ቻው ብሎ መሃድ😢😢😢😢

  • @ESKEDARTUBE
    @ESKEDARTUBE Před rokem +4

    መልካም ልብ ያላቸሁ ሁሉ እንዳታልፊኘ ደምሩኘ

  • @user-kp2vl5fc3c
    @user-kp2vl5fc3c Před rokem

    😏😏ልጆች ግን የሱ ናቸው 🤔🤔🤔እ

  • @zabibaahmad6193
    @zabibaahmad6193 Před rokem

    አንድ ባለታሪክ ነበች እባክሽ ስልክሽን

  • @mamanegu1324
    @mamanegu1324 Před rokem

    ፓስተር ቸሬ በጣም ነው ትምህርቱን የምወደው he is neutral የሱ ሃይማኖት ተከታይ አይደለሁም ግን ትምህርቱ በጣም ነው የጠቀመኝ (ድንቁርና እና ገንዝብ -ውሸት እና ገንዝብ -------)በጣም የሚገርም ቃል ነው ሲደመሩ ሰውን ይዝው ገደል ይገባሉ

  • @thematteroftime4486
    @thematteroftime4486 Před 3 měsíci

    ምን ጎድ ነች ? ይፍታት አትሆነውም።

  • @hayathanyyoutube922
    @hayathanyyoutube922 Před rokem

    በእልህ ትደር ወስጥ ፍቅር ውስጥ ከባድነው እኔም ነበርኩበት ዋጋ አስከፍሎኛል

  • @adyamtata3811
    @adyamtata3811 Před rokem

    😂😂😂😂😂😂 kenfershe aynshe

  • @MulunaLewi
    @MulunaLewi Před rokem

    He NED'S he's Spaci..

  • @yemenztades6122
    @yemenztades6122 Před rokem

    ወድሜ እስኪ አንተ ወደመንፈሳወይ ነት ተመለስ ሚስትህን ወደራስህ መመለስ ትችላለህ በምን ብትል አደኛ መንፈሳዎይ ቻናሎችን ተከታተል መፀለይ መፆም መስገድ ካዛንስሀ መግባት ምክንያቱም ይህን ያልኩት ምንክንያት ምስትህን መንፈስም ነዉ የዝሙት መንፈስ በርታወድሜ ይህአለም አድ ለአንዱም አይተኛም ደግሞ የመምህር ተስፈዬ ገጠመኝ የሚል መንፈሳዎይተ ትምህርት አልልህ እየገባህ አዳምጥ ይጠቅምሀል ትግስትህን ግን ሳላደንቅ አላልፍም እግሔአብሔር ሚስትህን ይመልስልህ ወድሜ መፈተን ለበጎነዉ

  • @khanbhaibj8468
    @khanbhaibj8468 Před rokem +2

    ሰውየውን ሳላደንቀው አላልፍም ታጋሽሰውነው በጣም ነው ቤቱንየሚፈልገው ፍቅር የለኝም ማለትህደሞ ቸሬ እንዳለው ስሜት እንጅ ፍቅር እልህ በደሉስላቆሰለህእንጅ በእምነታችሁ ንስሀ ግቡ ሁለታችሁም ፀልዩ በእምነቷ እንድጠነክር እገዛት ጊዜ ስጣት አንዳንደ ሴቶች ብዙ እንፈልጋለን ለመንገር ግን በሩን ተዘጋህባት ያልተጠበቀነገር ውስጥ እንገባለን ትልቅ ስህተት እናምቀለልበልላት የማይስተካከል የለም ከፈጣሪጋር

  • @adyamtata3811
    @adyamtata3811 Před rokem

    Chera 😂😂😂😂😂

  • @myname-hv7xq
    @myname-hv7xq Před rokem

    ይሄ ትልቁ መፍትሄ ፍቺ ብቻ ነው ምክንያቱም እንዴት ነው አብሯት ሚተኛው እንዴት ነው ከዚህ በዋላ ሚኖረው ? አብሶ ለሱ ከባድ ነው
    አንዳንድ ሴት ግን😏😏

  • @mhsenailmhsenail2098
    @mhsenailmhsenail2098 Před rokem

    አቤትትት🙉🙉🙉🙉🙉🙉የሰውዬው ትግስትትትትትትኡኡኡኡ

  • @fatuaseidfatuaseid4076

    ረበአላህ አግኟቸውና እድግባቡ አድርጉ

  • @mekdi_62127
    @mekdi_62127 Před rokem +1

    አሁን ይቅርታ ጠየቀችው እሺ ይበላትና ከዚህ በኋላ ስልኳን ቢጠልፈው ቢከታተላት ለአንድ ጊዜ ለልጆችህ ስትል እድል ስጣትና ገዳም ሂዱና ፀበል ተጠመቁ ንስሀ ግቡ ሲቀጥል ለሷ ጊዜ ስጣት ምናልባት ለስራም ቢሆን ሌላ ሀገር ስለምትወጣ ብቸኝነት እየተሰማት እንደሆነ

  • @hanatsega2386
    @hanatsega2386 Před rokem

    Yihewlh wendme yederesebet new miyakew metew ena mersat yileyayal ltitewew enji ltresaw atchlm kewsth aywetam Tru sew sthon ante neh ashenafiw leljochk stl tewew ljochu yanten chigr endiyayu atfked yadgalu yerasachewn hiwet yijemralu yane yante fikr waga yigebachewal yireduhal

  • @eshetneshteklehaymanot9615

    ይቅርታ መምህር በዝሙት ከሆነ ግን ይለያይ ይላል።

  • @abd538
    @abd538 Před rokem +1

    The agenda is also script and filmy. This is not a real story

  • @haregadinokatar8035
    @haregadinokatar8035 Před rokem

    ሴት ልጅ ስትማግጥ ከትዳሯ ውጭ በስማም ቱ ኢትዮጵያ ውስጥ እደዚህ አይነት ትግስት ያለው ወንድ አለ ለካ ይፍታት ይች መቸም አትማርም ትዳር ይከበር

  • @alazar7432
    @alazar7432 Před rokem +1

    እኔ ብቻ ነኝ የሰውየው ሚስት ጋዜጠኛዋን በምናብ አድርጌ የሳልኳት...

  • @mesibrhane78
    @mesibrhane78 Před rokem

    ሌባ ላመሉ ዳቦ ይልሳል ይባላል እግዚአብሔር ይርዳት እንግዲህ

  • @biniyamworku2678
    @biniyamworku2678 Před rokem

    ድምፀ አይስማም

  • @yamrotdegefu5523
    @yamrotdegefu5523 Před rokem

    Enante gin why are you taking only one side of story. Do you know people specially men creat a scenario or a case fabricated full of lies? What makes you think he is honest, how about he is making a case for him to excuse to divorce her? Did you think about that? I think he married her with out loving her betting with his friends and now what if he regrets now?

  • @techawatch
    @techawatch Před rokem

    ትንተናሽ ግን ሚገርም ነው እንደ ፓስተር ቸሬ አባባል ሴት ልጅ ከባሏ በላይ ከማገጠች (ከረከሰች) ወንድም ቢሆን በይቅርታ መመለስ ይቻላል ነው ያለው ግን እንደ ድሮው አይነት ፍቅር ይኖራል ወይ?በጥርጥር የተሞላ ህይወት እርይሆንም ወይ? ትዳር ላይ ጥርጥር ደግሞ ይከብዳል በጣም ሚያሳዝነው እኮ ድሮ ሲያምናት የነበረውን ባንዴ እምነቱ እንዲሸረደር ያደርጋል ሳይተማመኑ አብሮ መኖር ደግሞ ከባድ ነው ለዛ ነው ይቅርታ ቢያደርግላትም ሊረሳው ያልቻለው ስለዚህ ባለትዳሮች ለ5 ደቂቃ ስሜት ብላችሁ ወይንም ለማያዛልቃችሁ ውስልትና ብላችሁ ትዳራችሁን አታፍርሱ አትወስልቱ።

  • @esmaelmekonnen6236
    @esmaelmekonnen6236 Před rokem +1

    ወንድሜ 21 አመት ቻልካት አይደል ? በእውነት የምትወድህ ከሆነ አሁንም ቻላት ግን አሳክማት :: የልጅነት ሚስትህን አትፍታት ብቻዋን ደግመህ ወደ ኢትዮጵያ አትላካት : ድክመቷን ካወቅህ እርዳት አግዛት ለልጆችህም ስትል ይቅር በላት የፓስተር ቸሬንም ምክር ተግባራዊ አድርግ

  • @melatadugna7557
    @melatadugna7557 Před rokem +2

    ፍታት እና እኔን አግባኝ እሷ አትሆንህም🙄

  • @romobile3460
    @romobile3460 Před rokem

    እሱን አይደለም ያፈቀረችዉ ገዘቡን ነው አቶዶዉም

  • @hiwotfekadu4673
    @hiwotfekadu4673 Před rokem

    ይቅርብህ የኔ ወንድም ልብህ ለምን ይድማ የእንጀራ እናት ላልከው ፍርሃት አስወግድ አንተ ጋር አይኑሩ እንዴ ምነው ይሔን ያክል ተጣብቃቹ አልተፈጠራቹ ደህንነት እንዲሰማህ ይቅር በላት እሷ ሚያመላልሳት ያልረካችበት የሆነ የዝሙት የአለም አልረካ ባይነት ይዛት ነው ኑሮዬ ይበቃኛልን አታውቅም ልጆችህም ቢሆን ህፃናት አይደሉም ብዙ ሰው ሊጎዳቸው አይችልም ደሞ እግዚአብሔርን ምትፈራ ሴት ትኖራለች እኮ እሹሩሩ አልካት ቆንጆ ናት መሰለኝ🙄

  • @ksanettesfamariam2696

    Ye memhr tesfaye getemegn bisema meftihe yagegnal bye asbalew

  • @kbqday116
    @kbqday116 Před rokem +4

    አንተ ጀዝባ ምን ትጠብቃለህ በአንተ ህይወት ሰው እንዲወስንልህ ትጠብቃለህ ልጆችህ እንኳን ታዘቡክ አጉል ለልጆቼ አስባለሁ ትላለህ ምትማግጥ እናት እያዩ እንዲያድጉ ፈረድክባቸው ሲጀመር ልፍስፍስ ነህ ፍታ ቢሉህም አትፈታም ሞኝ አሁን እናቴ ማለቱን ትተህ ልጆቼ ማለቱን ትተህ ቤተሰቦቼን ማለት ትተክ ፍታት አራት ነጥብ ከዛ ነገሮችን አስተካክል የልጆችህንም የቤተሰቦችህንም እስቲ የምር አናግረኝ የማድረጉ ወኔ ካነሰህ

    • @user-xs7jb3qg1d
      @user-xs7jb3qg1d Před 10 měsíci

      አረ ድፍረት በቃ ይፍታት ይፍታት😅😅😅😅

  • @zuzulove9763
    @zuzulove9763 Před rokem

    አለመታመን አለመተማመን ፍቅርን ይገላል ምናባቷ አሯሯጣት ባል እያላት

    • @zeenune1182
      @zeenune1182 Před rokem +1

      እርሷን ብንሰማት ይሄኔ ይብሳል