የቈላስይስ መጽሐፍ ታሪካዊ ዳራ

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 21. 08. 2024
  • የቈላስይስ መጽሐፍ እንዴት ይጠና? ኢየሱስን
    የምናየው በባህላዊ መነጽሮቻችን ነው? ወይስ
    ባህላችንን የምናየው በመጽሐፍ ቅዱስ መነጽር ነው?
    የቈላስይስ ሰዎች ባሕላቸው ስለ ኢየሱስ ያላቸውን
    እይታ እንዲያዛባው ፈቅደው ነበር፤ ስለዚህም ጳውሎስ
    ይኽን ደብዳቤ ጻፈላቸው፡፡ በእግዚአብሔር እውነት
    ራሳችሁንና እግዚአብሔርን በግልጽ በመመልከት
    እንዴት ያለ ፍሬያማ ሕይወት ልትኖሩ እንደምትችሉ
    ዕወቁ፡፡
    www.thebibleeff...
    FACEBOOK: / experiencethebibleeffect
    INSTAGRAM: / thebibleeffect
    ተኣማኒ የኾኑ ክርስቲያናዊና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎች፣ ቪድዮዎችና መጻሕፍት ለማግኘት www.Yeamlak.com ድረ ገጽን ይጎብኙ
    #ቈላስይስ #የመጽሐፍቅዱስጥናት #የመጽሐፍቅዱስቪድዮ

Komentáře • 4

  • @thebibleeffectamharic
    @thebibleeffectamharic  Před rokem +1

    ለተጨማሪ ጥናት የሚያግዙ ጥያቄዎች
    1) የቈላስይስ መጽሐፍን ሙሉውን በማንበብ የሚከተሉትን ጥያቄዎች በተመለከተ ጳውሎስ የተናገራቸውን በማስታወሻችሁ ላይ አስፍሩ፡፡ ሀ) ኢየሱስ ማን ነው?
    ለ) ኢየሱስ የሠራቸው ሥራዎች ምንድን ናቸው? እነዚህ እውነቶች በሕይወቴ ውስጥ ሥር ያልሰደዱበት ነገር ይኖር ይኾን? የኢየሱስን እውነት በሕይወቴ ይበልጥ ለመግለጥ እንዴት መኖር እችላለኹ?
    2)በቈላስይስ መጽሐፍ ውስጥ ኢየሱስ ለእኔ ስላደረገልኝ ነገር ጳውሎስ ምን ይላል? ኢየሱስ ካደረገው ነገር አንጻር እኔን የሚያየኝ እንዴት ነው? በሰጠኝ ማንነት መኖር የምችለው እንዴት ነው?
    3)አኹንም ድረስ በዙሪያዬ ያለውን ዓለም ግልጽ በኾነው በመጽሐፍ ቅዱስ መነጽር ሳይኾን በባሕላዊ መነጽሬ የማየው በየትኞቹ ጕዳዮች ላይ ነው?
    4) የቈላስይስ መጽሐፍ ዋና መልእክት ምን እንደኾነ በራሳችሁ አገላለጽ ጠቅለል አድርጋችኹ ግለጹ፡፡

  • @_voiceoftheword
    @_voiceoftheword Před rokem

    🙌🏽

  • @lalenh.k3743
    @lalenh.k3743 Před rokem

    ተባረክ ያሚ!