"እንዴት" የዲያቆን ዘማሪ ሐዋዝ ተገኝ እጅግ ተወዳጅ ዝማሬ"በልቤ መሃል ስምህ ተቋጥሯል ሌት ቀን አይለይም ኢየሱስ ይላል" New song zemari Hawaz

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 27. 08. 2024
  • አያቴ ወደ መካነ ሕይወት አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ቤ/ክን አዘውትራ ትወስደኛለች ፤ አሃዱ ሳይባል ቀድሞ ከነግህ ኪዳን እግዚኦታ በፊት እንድንደርስ ስትቀሰቅሰኝ የቅዳሜ እና የእሁድ የልጅነት ትዝታዬ ነው። ደውል .... ያሬዳዊ ዜማ .... የፅንሃ ቅጭልጭልታ ... በመሃል እንደ ጅረት የሚፈስስ የቀሳውስት ውብ ዜማ ... ይስበኛል .. እሄዳለሁ የአያቴን ነጠላ ጫፍ ይዤ .. ከመቋሚያዋ በላይ የተደገፈችው ጌታ ድፍረቱን እየሰጣት የሌሊቱን ጨለማ ጥሰን ከቤተመቅደሱ በር እንደርሳለን ። ያኔ ለስሙ ማዜም ተለማመድኩ ስሙን መጥራትን አስተዋወቀኝ ጌታዬን ላገለግለው እናፍቅ ነበረ ፤ የልቤ መሻት ዘወትር ዝማሬ ዝማሬ ዝማሬ ነበረ .. ተባረክ የእኔ ጌታ ዘመኔን የዜማ ያደርግኸው ሳይገባኝ የጠራኸኝ፣ የአባቴ ቤት አይን ውስጥ እንኳን የማልገባ ደቃቅ ሳለሁ ለገናናው ክብርህ የጠራኸኝ አምላኬ ስምህ ይቀደስ። በስመ አብ ብዬ የተማርኩህ የብላቴናነት ትዝታዬ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ .....
    ታድያ ከልጅነቴ ያሳለፍኩህ የማልረሳህ አንተ የእኔ ትዝታ ስምህን ሳልጠራ እንዴት እውላለሁ? ለስምህ ሳልዘምር እንዴት ያስችለኛል ? ጠላት እንዴት ስምህን መጥራት ሊያስቆመኝ ይችላል ?? አይችልም ፈፅሞ ጌታ ከሁሉ ትበልጥብኛለህ የምኖረው ላገለግልህ ነው .. ፀሎቴንም ሰምተኸኛል ጌታዬ " ይናፍቃል ልቤ በብዙ ሊታዘዝህ ሊገዛልህ ሊያገለግልህ " አልጠግብም ዘምሬልህ ገና አለኝ ለስምህ ምስጋና .. ስምህ በልቤ መሃል ተቋጥሯል ከሁሉ ትበልጥብኛለህ .. ዙርያዬን ሳላይ ያለ ቅድመ ሁኔታ የተሰቀልክልኝን ብቻ ፊት ለፊት እያየሁ አመልክሃለሁ.. የሚያምርብኝን ስምህን እጠራለሁ ፤ እኔን ትቢያውን ያከበረ የሚያዋጣኝን ስምህን እጠራለሁ .. ኢየሱስ የእግዚአብሔር አብ ልጅ አንተ ብቻ ትበቃኛለህ ። ስምህን ሳልጠራ እንዳልውል ለስምህ ሳልዘምር እንዳልውል የተከፈተ ደጅ ስለሰጠኸኝ ወደ ሰፊም መሰማርያ ስላወጣኸኝ ፤ ዛሬዬን አይተህ ትላንትን ስለተጠነቀቅህልኝ አመሰግንሃለሁ። ለዘመኔ ባለቤት ላንተ ዘመኔን ሰጥቻለሁ፤ ሌት እና ቀን አልለይም ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ እላለሁ አባ አመሰግንሃለሁ.. ። የብላቴናነቴ ጌታ የወጣትነቴም ጌታ በጎልማሳነቴም ጌታ እስከ ሽምግልናዬ ጌታ ነህ። ሳመልክህ ስዘምርልህ ስምህን ስጠራ እኖራለሁ።

Komentáře • 56

  • @tadelechlema7379
    @tadelechlema7379 Před rokem +1

    ጌታ አብዝቶ ይባርክህ ተባረኩ ኦርቶ ።በዘመርክለት ስም ተጠቅለሉ

  • @user-zs2ix8sr4b
    @user-zs2ix8sr4b Před 2 lety +5

    በልቤ መሀል ስምህ ተቋጥሯል
    ሌት ቀን አይለይም ኢየሱስ ይላል
    ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ብቻ ትበቃኛለህ
    ኡፍፍፍፍፍፍፍ በጌታ ስም ተባረክ 😭😭😭😭😭😭

  • @mekedesmezmur4057
    @mekedesmezmur4057 Před 5 měsíci

    Amen amen 🙏 amen 🙏 God bless you 🙏

  • @futuretalentacademy1960
    @futuretalentacademy1960 Před rokem +1

    wuyyyyy nefes yemiyaresers mezmur abet abet ...... endezi ayinet zimare silesetehewu simh yikber

  • @hiwotabera329
    @hiwotabera329 Před rokem

    ዝማሬ መልእክትን ያሰማልን

  • @yodetendres3355
    @yodetendres3355 Před 2 lety +4

    እንዴት ይሆናል
    እኔ ያላንተ ህይወት የለኝ
    ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ
    ሀዊዬ ወንድም ፀጋ ይብዛልህ
    ኢየሱስ እንዳልክ ዘመንህ ይለቅ

  • @JesusisthewayJesusisthelife
    @JesusisthewayJesusisthelife Před měsícem +1

    ኢየሱስ 😢😢😢😢😢😢

  • @user-qs8is8bm7y
    @user-qs8is8bm7y Před 2 lety +4

    እንዴት ይሆናል ያለ አንተ አልችልም እኮ ጌታ😭😭😭😭
    ሀዋዝዬ ለሶስት ወር ከቤት አልወጣም ነበር አልክ ምስክርነት ላይ እኔ አራት አመት ቤት ውስጥ ሰው ይናፍቀኛል ነበር ጌታ ግን ታሪክ ይቀይራል ጌታ😭😭😭😭😭 ስለአንተ ማናገር አልችልም እኔን ያየ እሱ ያውቃል😭😭😭

  • @asratmulachew690
    @asratmulachew690 Před 2 lety +6

    ኢየሱስን የሚያስወድድ መዝሙር!
    ጸጋ ይብዛልህ ወንድሜ።

  • @mele2475
    @mele2475 Před 2 lety +4

    አሜን ወንድሜ ሀዋዝ ጌታ ከዚህ በላይ ፀጋዉን ይጨምርልህ

  • @AMEN12728
    @AMEN12728 Před 2 lety +4

    እጅግ በጣም የምወደው መዝሙር! እግዚአብሔር ይባርክህ!
    ክብር ሁሉ ለአምላካችን ይሁን! አሜን።

  • @alemtsehayjesus9731
    @alemtsehayjesus9731 Před rokem +1

    ሀዋዝዬ wudu ወንድሜ ላንተ መዝሙር ያለኝ ፍቅር የተለየ ነው በእዉነት መዝሙር በጣም ነው የምወደው ሁሉም ጌታ የተቀበልኩት ሰዓት ነው የሚያስታውሰኝ ሁሌም በእውነት ልዩ ፍቅር ነው ያለኝ ለመዝሙር አሁንም ከዚህ በላይ ጌታ ፀጋው ይጨምርልህ ክፉ አይንካ ተከናወን ወንድሜ እወድሀለሁ በጣም ❤️🥰😍

  • @behailubehabtu5728
    @behailubehabtu5728 Před 2 lety +4

    ፈጣሪ ፀጋውን ያብዛልህ ወዳጄ። ለህይወት ጉዞዬ የነፍስ ስንቅ እያቀበልኸኝና እየው እየሱስን በልቤ አግዝፈህ እየሳልህልኝ በደስታ ኖራለሁ። አመሰግናለሁ ሐዋዜ።

  • @mala4122
    @mala4122 Před rokem +1

    አሜን አሜን ተባረክየኢየሱስ ጌታዬፍቅርነው፣🤗🤗🤗🤗🍇🍇🍇🍇🍇💜💜💜💜💗💗💗💞💞💞💞💞💞🥰🥰🥰🥰🥰😍😍😍😍😍😍💕💕💕💕💕

  • @selamawitgulumaa4669
    @selamawitgulumaa4669 Před rokem +1

    ❤❤❤❤❤

  • @kefudesta997
    @kefudesta997 Před 9 měsíci +1

  • @natnaeladememekonnen7521
    @natnaeladememekonnen7521 Před 2 lety +4

    GOD bless you for sharing Hawiye. May the SPIRIT be your guide and strength for days to come, till your last breath.

  • @zemaritfikrtefelekeawaj
    @zemaritfikrtefelekeawaj Před 2 lety +2

    አይሆንልኝም ጌታ ያላንተ እኔስ አልችልም ውዴ ያላንተ! ተባረክ ሃዊዬ

    • @ZEMARIHAWAZTEGEGNE
      @ZEMARIHAWAZTEGEGNE  Před 2 lety +2

      አሜን ፍቅርዬ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የአገልግሎት ዘመንሽን ይባርከው

  • @user-ce8rs4xm6l
    @user-ce8rs4xm6l Před 2 lety +2

    Endet endet smhn saltera endet ewlalehu
    ewnet wendme zmare melaekn yasemaln

  • @alem8640
    @alem8640 Před 2 lety +1

    Tebarek tsegaw kzih b belte yagizih

  • @ethio11tube
    @ethio11tube Před 2 lety +2

    Tebarek wendme!

  • @kiberulaegzbhryhun3953
    @kiberulaegzbhryhun3953 Před 2 lety +1

    አሜን ውዋ ታባረኪ ሐዋዝዬዬዬ ጸጋውን ያብዝልክ ባጣም የምውዶ ዝማረ ነው ሁሌም እንዎደአሌን ሐዋዝዬዬ

  • @atsedebaye6957
    @atsedebaye6957 Před 2 lety +1

    እግዚአብሔር ይጠብቅህ ዝማሬ ቃለህወት ያሰማልን 🙏🙏💒💒💒አሜን አሜን

  • @netsikidus9612
    @netsikidus9612 Před 2 lety +2

    ሀዊዬ ተባረክ ተደምጠው የማይጠገቡ ዝማሬዎች ጌታ ሰቶሀል ፀጋውን አብዝቶልህ ስሙ ይክበር

  • @BetelhemGetahunabawu
    @BetelhemGetahunabawu Před 2 lety +1

    አሜን አሜን አሜን ዝማሪ መላክት ያሰማልን እግዚብሔር ፀጋውን ያብዛልህ🙏

  • @hantehaato9838
    @hantehaato9838 Před 2 lety +2

    Tebarek wendemachen hawaz!!

  • @binyamessa8835
    @binyamessa8835 Před 2 lety +3

    በእውነቱ ጌታ አብዝቶ ይባርክህ ! ረጅም እድሜና ጤና ይስጥህ የአገልግሎት ጊዜህን ይባርከው !

  • @sadiksadik1546
    @sadiksadik1546 Před 2 lety +1

    Ameeeeeeeeeen. Ameeeeeeeeeeeen. Ameeeeeeeeeeen. Ameeeeeeeeeeeen. Egzabher. Tsaga. Yibazalki. Tabarki

  • @meklitmimi5660
    @meklitmimi5660 Před 2 lety

    ሀዊ ተባረክ እግዚአብሔር ዘመንህን ይባርክ

  • @enkumengist1668
    @enkumengist1668 Před 2 lety

    አቤት ይህን መዝሙር እንዴት እንደምወደው!!!!!!!

  • @asnakechshewatatek3107
    @asnakechshewatatek3107 Před 2 lety +1

    Amen Amen God bless you

  • @nuguseariam5183
    @nuguseariam5183 Před 2 lety +1

    ሃዊ ሓወይ፡ ብዙሕ ተባረኽ !

  • @JesusisthewayJesusisthelife
    @JesusisthewayJesusisthelife Před měsícem +1

    እንዴት እንዴት ስምህን
    ሳልጠራ እንዴት እችላለሁ
    እንዴት ለስምህ ሳልዘምር
    እንዴት እውላለሁ
    አይሆንልኝም ጌታ ያላንተ
    እኔስ አልችልም ውድ ያላንተ
    በልቤ መሃል ስምህ ተቋጥሯል
    ሌት በን አይለይም ኢየሱስ ይላል
    የምኖርበት ብቸኛ ምክንያት ነህ ጌታ በትውልድ መሃል አንተን ልባርክ ጠዋት ማታ
    ከልጅነቴ የዜማን ዝናር አስታጥቀህ
    ሾምከኝ ለክብርህ ከሸለቆው ውስጥ ጎትተህ
    ጠላት ቢነሳ ስምክን ከአፌ ሊያስጥለኝ
    እንዴት ይሆናል ከቶ እኔ ያላንተ ህይወት የለኝ
    አይሆንልኝም ጌታ ያላንተ
    እኔስ አልችልም ውድ ያላንተ
    በልቤ መሃል ስምህ ተቋጥሯል
    ሌት በን አይለይም ኢየሱስ ይላል
    መቼ ነው መቼ ነው ብዬ እቃትት ነበር
    ዙርያዬን ማየት አሁን ቀርቶልኝ ታሪክ ተቀየረ
    አልደራደር ባንተማ ነገር ብዬ አላፈርኩም
    እኮራብሃለው ብኖር ብሞትም ጌታ አንተን አልክድም
    እስኪ የሚያምርብኝን ስምህን ልጥራ
    ኢየሱስ ኢየሱስ
    እስኪ የሚያዋጣኝን ስምህን ልጥራ
    ኢየሱስ.......
    አባ ከፍቅርህ ምን ይለየኛል
    ውድህ ከውዶች ይበልጥብኛል
    አልችልም መኖር ጌታ ያለ ስምህ
    ኢየሱስ ብቻ ትበቃኛለህ
    አንተ አለከኝ ይቅር የቀረው
    ሙላት ደስታዬ ጌታ ስምህ ነው
    እንዴት እንዴት ስምህን
    ሳልጠራ እንዴት እችላለሁ
    እንዴት ለስምህ ሳልዘምር
    እንዴት እውላለሁ
    አይሆንልኝም ጌታ ያላንተ
    እኔስ አልችልም ውድ ያላንተ
    በልቤ መሃል ስምህ ተቋጥሯል
    ሌት በን አይለይም ኢየሱስ
    ሐዋዝዬ አንተ በረከታችን ነህ እግዚአብሔር ፀጋውን ያብዛልህ❤❤❤❤

  • @mitenlove2892
    @mitenlove2892 Před 2 lety +1

    ተባረክ

  • @gechteshome5688
    @gechteshome5688 Před 2 lety +2

    ፀጋ ይብዛልህ ወንድሜ ❤

  • @betelhemgetachew4697
    @betelhemgetachew4697 Před 2 lety +1

    አይሆንልንም ጌታ ያላንተ 🙏

  • @alemtsehayjesus9731
    @alemtsehayjesus9731 Před rokem +1

    ከንደገና ፖስታ አድርገው ሌሎች እንዲሰሙት ❤️🙋

  • @mahihayela1113
    @mahihayela1113 Před 2 lety +1

    Tsega ebezalek wendema tebark

  • @fikirtewoldeyohannes8220

    አዎ አይሆንልኝም ጌታ ያለአንተ።

  • @millionangesom48
    @millionangesom48 Před 2 lety +2

    Tebarek Hawaziye! Waiting for new songs also......

  • @tizitaberhanu7245
    @tizitaberhanu7245 Před 2 lety +1

    Zemara melakitain yasemalen

  • @sanegerma3942
    @sanegerma3942 Před 2 lety +2

    ሃዊያችን እንኳን ደህና መጣህልን ብሩክ ሁን በርታ በጣም ድንቅ ዝማሬ ነው
    አይሆንልኝም ያለ አንተ
    ደግሞ የፃፍከውን ታሪክ አነብኩኝ ሁሉ ለመልካም ይሆናል አንድ ቀን ሁላችን በአንዱ እንጠቀለላለን አይዞን

  • @kiyagemechu67
    @kiyagemechu67 Před 2 lety +1

    Amenn amenn amenn

  • @senayt-bn9kz
    @senayt-bn9kz Před rokem

    Sekafagn msemaw
    Yaten mezmur new selam yesemagnal

  • @mitenlove2892
    @mitenlove2892 Před 2 lety +2

    እሰይ መንፈስ የሚያረሰርስ መዝሙር ተባረክ 🙏🙏🙏👍👌

  • @annamaria4396
    @annamaria4396 Před 2 lety +1

    amen3🙏🤲🙏🙏🙏

  • @webituberhanu6251
    @webituberhanu6251 Před 2 lety +2

    ለበረከት ሁኑ ሀዊ 🙏🙏🙏

  • @befedere605
    @befedere605 Před 2 lety +1

    We de bete betemelese dese yeleyale!

  • @rahelkassahun
    @rahelkassahun Před 2 lety +2

    emigerm mezmur yakeberkew geta yakbirh ..ebakih emitamelkubetin akababi bitnegregn?

  • @tigetishome2984
    @tigetishome2984 Před 2 lety +1

    በቅርብ አተም ወደቤትህ ወዳሳደገችህ ቤተክርስቲያን እደምትመለስ ጥርጥር የለኝም እንወድሀለን😘

    • @abayhailemariam4875
      @abayhailemariam4875 Před rokem

      ለምን ? ለፍጡራን ሊዘምር ወይም ሊያመልክ ?

  • @webituberhanu6251
    @webituberhanu6251 Před 2 lety +3

    Wow ስንት ቀን ይህን ቻናል Subscrbie ለማድረግ እምቢ ብሎኝ ዛሬ ሰራልኝ