መካኒሳ እና ትዝታዋ /ትዝታችን በኢቢኤስ/

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 7. 07. 2024
  • ዛሬ ምሽት በዮናስ ከበደ አዘጋጅነት እና አቅራቢነት የሚቀርበው ትዝታችን በኢቢኤስ "መካኒሳ እና ትዝታዋ"ን እንዲያዩ ተጋብዘዋል፡፡
    Tonight, on EBS, Yonas curates and presents memories on the program "Mekanisa ena tiztawa"
    ይህ ፕሮግራም ዘወትር ሰኞ ማታ እንደ ስሙ ሁሉ ትዝታ ጠቀስ" የሆኑ ጉዳዮች ላይ ብቻ የሚያጠነጥን ነው። ለአብነትም የሙዚቃ፣የከተሞች፣ የትምህርት ቤቶች፣ የመዛግብት፣ የቀድሞ ቁሳቁሶች፣ የልዩ ልዩ ቅርሶች፣ የአልባሳት፣ የሃውልቶች እና የመሳሰሉ ጉዳዮችን በትዝታ ይቃኙበታል።
    "Tiztachin be ebs" is a captivating show that delves into nostalgia, exploring old music, cultures, aging cities, and schools. Join us as we journey through memories and evoke nostalgia in every episode!
    EBS TV-Watch on Roku(PC/Mac & iPhone/iPad & Android Devices) : iptv.ebstv.tv/
    ያለዎትን ጥያቄና አስተያየት በ አጭር መልዕክት 7696 ላይ ይላኩልን
    Follow us on: linktr.ee/ebstelevision
    #ኢቢኤስ
    #EBS
    #Tezetachen_on_EBS
  • Zábava

Komentáře • 158

  • @tihutgirma
    @tihutgirma Před 16 dny +23

    መካኒሳ/በከኒሳ/ቃሉ ኦሮምኛ ትርጉሙ የብሳና ዛፍ ማለት ነዉ።
    ከሚታወሱ የመካኒሳ ስፍራወች ውስጥ
    - መካኒሳ ት/ቤት
    -ጃንጥላ ፋብሪካ
    -መካነ እየሱስ
    -ጊዶ ዋሻ
    -የአቃቂና ቄራ ወንዝ መገናኛ
    - የአይነ ስዉራን ት/ቤት
    - ይልማ ደሬሳ አካባቢ
    -ኮምቦልሳቶ ፋብሪካ
    -ጠ/ሚ እንዳልካቸው መኮንን መኖሪያ
    ጉድ ቨፐርድ ት/ቤት
    በይበልጥ ጃንጥላ ፋብሪካና ጊዶ ዋሻ ላይ አሁን
    ያሉበትን ደረጃ መመልከት ቢቻል ጥሩ ነዉ🙏

    • @LoveAndPeace2424
      @LoveAndPeace2424 Před 15 dny +3

      ቡና ቦርድን ረሳሽው?

    • @user-yw2si6mf5m
      @user-yw2si6mf5m Před 15 dny +2

      Batu construction

    • @demekechgonfa-is2yi
      @demekechgonfa-is2yi Před 15 dny +1

      That's our kebele i used to play foot ball as young lady football team i enjoyed that time i was good player in AlemSalem team even we won troffi mekanessa +AlemSelam +Gorefusefer or Seferegente used to be kebele 13 higher 23 thank you yoni for this show

    • @tihutgirma
      @tihutgirma Před 15 dny +2

      የረሳኋቸዉን አስታወሱኝ
      -አረቄ ፋብሪካ
      -ቡና ቦርድ
      -2 ቁጥር አዉቶብስ
      -ቀ/ሃይለ ስላሴ የሚጎበኙዋት አካባቢ
      ባይደርሰኝም ከእጃቸዉ አንድ ብር የተቀበሉ ያስታዉሳሉ!

    • @AnbayeBekele
      @AnbayeBekele Před 4 dny

      OK

  • @woinuayonas8694
    @woinuayonas8694 Před 16 dny +27

    መካኒሳን ለመግለጽ ሰፈር ውስጥ መግባት ነበረበት ብዙ የድሮ ሰዎች አሉ እኛ እዛ ተወልደን ነው ያደግነው❤

    • @yitayalgashaw9185
      @yitayalgashaw9185 Před 15 dny +2

      የመካኒሳ ልጆች አትረሱንም ጊዶ ዋሻ ለዋና ስንሄድ ጠብቃችሁ ልብሳችንን ትፍትሻላችሁ የጎፋ ካምፕ ልጅነኝ

    • @sirgutamera4806
      @sirgutamera4806 Před 15 dny

      @@yitayalgashaw9185ከ በቀለ ትምህርት ቤት ሚኒስትሪ ለመፈተን መካኒሳ ትምህርት ቤት ስንሄድ ገንዘብ ይቀሙን ነበር እየፈተሹ

    • @-Dave-Sanjaw-ke-Ayertena
      @-Dave-Sanjaw-ke-Ayertena Před 15 dny

      ምንም ታሪክ ዬለው ሰፈር

    • @woinuayonas8694
      @woinuayonas8694 Před 15 dny

      @-Dave-Sanjaw-ke-Ayertena -እንደዚህ ተቃጠልክ በሰፈራችን

    • @mickiyasSolomon-i6y
      @mickiyasSolomon-i6y Před 8 dny

      አዎ እውነት ነው

  • @user-bw2mc6bg1y
    @user-bw2mc6bg1y Před 16 dny +19

    ዮኒ በጣም ብዙ ድርጅቶች ፣ ታዋቂ ሰዎች፣ ታሪክ ያለበት ሰፈር ነው ነገር ግን ያገኛሀቸው ሰዎች በሚፈለገው ልክ መከኒሳን ገልፀዋል ለማለት እቸገራለው። ለማንኛውም ስለመጣህ ደስ ብሎናል።

    • @user-bl6ok4gv4n
      @user-bl6ok4gv4n Před 16 dny +1

      በጣም ትክክል ከዚህ በላይ መስራት ይቻል ነበር

    • @goodnews2392
      @goodnews2392 Před 16 dny +2

      በትክክል ልክ ገዳም ሠገርን እንደሰራው ናለት ነው። የገዳም ሠፈር ልጅ ነኝ ፣ አሁን ጉዳም ሰፈር ሆኗል እንጂ? 😂

  • @zinashethiopia502
    @zinashethiopia502 Před 15 dny +6

    አረ ዮኒ ተዘጋጅተህበት ብትሄድ ደስ ይለኝ ነበር እግረ መንገድህን ነው ያየሃት ያናገርካቸው ሰዎች በሙሉ ምንም አልገለጿትም

  • @mershagetaneh1508
    @mershagetaneh1508 Před 14 dny +3

    ይህን ፕሮግራም በጣም ብዙ ትዝታን የሚያሳይ እና በተለይም በውጪ ለሚገኙ እህት ወንድሞቼ ወደኃላ የሚመልስ ትዝታ ዉስጥ የሚከት ነው። ነገር ግን እንዲህ ያለ ፕሮግራም ስትሰራ በጥልቀት መረጃው ካላቸው ሰዎች ጥናት ብትሰራ ትክክለኛውን እና ታማኝ የሆነ መረጃ ታገኛለክ ለታሪክም ይቀመጣል። ከቻልክ ይህን ፕሮግራም ደግመ ብትሰራው ጥሩ ነው እናመሰግናለን።

  • @YilmaWeldesilassie
    @YilmaWeldesilassie Před 15 dny +7

    ዮኒ ትክክለኛ ስው አላገኘሕም እላይ መከኒሳ እነ ጌቾን እነአለምን ጠይቅ አስደሳች ሆቴል አካባቢ

  • @ElderMarefia
    @ElderMarefia Před 15 dny +8

    ሰላም ዬኒ ስራህ እጅግ ደስ ይላል ። ብዙ ስራዎችህን አይቻለሁ የቀድሞ ሰፈር ታሪኮችን እያስተረክ ትውስታን በመቀስቀስ ድንቅ ደስታን ትፈጥራለህ።
    ይህ ስራ በብዙዎች ስፍራ ተሳክቶልሀል።
    በመካኒሳ ላይ የሰራኸው ግን ቅድመ ዝግጅት ያልተደረገበት... ከቀድሞዋ መካኒሳ ላይ ያልተነሳ፣ ትንተና የጀመርክበትን ታሪከ ብዙውን ት/ቤትን በሩን እንጂ ታሪኩን ያላሳየህበት፣ ጉሊትን የዘለልክበት፣ጋሽ ቆጭባሬ እና ሆያሆያቸው ያልተነሳበት፣ ጅማ ግሮሰሪን ያልጠቀስክበት፣ መዋሌ እና የመዋሌ ልጆችያልተተረኩበት፣ ሙዝ ቤት፣ጊዶ፣ገርባባ ሰፈር/ገደል ግቡ.. ምንጭ ሰፈር..የካሮት ማሳው...የአቃቂ ወንዝ እና የፎሌ ወይም የእሬቻ አመታዊ በአል እና የአርሞኒካው ጭፈራ እረ...እረ...ስንቱ
    ግድ የለም...ብዙ አልውረድብህ ዮኒዬ ተዘጋጅተህ ዳግም ስራው። ይህ ስራህ ከ1980 አ.ም ወዲህ ያለችውን መካኒሳን ሊያውም በወፍ በረር..የሰፈሩን አንጋፋ አዋቂዎችን ለትንተና ያላቀፈ ስራ ነው።
    ዳግም ስለምትሰራው ምስጋናችን ይድረስህ።
    ይህን ካላደረክ ብዙዎቻችን የመካኒሳ ልጆች እንታዘብሀለን!!! የምር ልንገርህ ዳግም ካልሰራኸው እኛን መካኒሳዎችን አጉል እንደተሳፈጥከን እንቆጥረዋለን።

  • @user-yf4ni8bh6e
    @user-yf4ni8bh6e Před 16 dny +9

    በብዛት ሽጠው ሄደዋል የጥንት ሰው የለበትም በብዛት ከሌላ ቦታ የመጡ ናቸው መኬ በጣም ምርጥ ሰፈሬ እናመሰግናለን ዬኔ❤❤❤❤❤

  • @Gobawmissiontv
    @Gobawmissiontv Před 16 dny +18

    መካኒሳ የሚለው ቃል "በከኒሰ" ከሚለው የአፋን ኦሮሞ ቃል እንደመጣ መረጃ አልኝ:: የዛፍ አይነት ስም ሲሆን የብሳና ዛፍ ማለት ነው:: ኢትዮጵያዬ ዘላለም ኑሪልን❤❤❤

    • @user-rh7ml2mm6g
      @user-rh7ml2mm6g Před 16 dny +2

      ውሸት ነው

    • @user-bl6ok4gv4n
      @user-bl6ok4gv4n Před 16 dny

      ትክክለኛ መረጃ

    • @grbu1121
      @grbu1121 Před 16 dny +1

      ክክክክ መካኒሳ ቅጠል እኛም ቀዬ አለ ማነው ለኦሮሞነው ያለው

    • @girmadesalegne7245
      @girmadesalegne7245 Před 16 dny

      @@user-rh7ml2mm6gምኑ ነው ውሽት?

    • @mamushtaye3022
      @mamushtaye3022 Před 15 dny +1

      This is the real meaning of the so called mekanisa (በከኒሣ) ነው of course it’s አኦሮምኛ ሲሆን ቃሉ ። ዪናስ ትንሽ ገባ ብለህ የድሮ ባለይዞታዎችን እድሜ ጠገብ ሰዎችን ማግኘት ትችል ነበር። ሌላም ታሪክ ትሰማ ነበር

  • @kalwondimu
    @kalwondimu Před 15 dny +7

    ዮኒ በቂ መረጃ ሳትይዝ የሰራኸዉ ፕሮግራም ነዉ። አሉ ስለመከኒሳ የሚያዉቁ ትልልቅ ሰዎች እንደምታስተካክለዉ ተስፋ አደርጋለው።

  • @mamilamamila240
    @mamilamamila240 Před 15 dny +4

    እዛው መካኒሳ ት/ቤ አካባቢ ትንሽ መቆየት ነበረብክ ፈጥነህ ነው ወደ ታች የወረድከው ብዙ ትልልቅ አባቶች እና የአራዳ ልጆች ታገኝ ነበር በተለይ ወደ ጉሊቱ አካባቢ መግባት ነበረብህ

  • @sewagegnhuafework7154
    @sewagegnhuafework7154 Před 15 dny +8

    መከኒሳ ብዙ ታሪካዊ ቦታ አሉ ላምሳሌ የጣሊያኑ ጊዶ ዋሻ :ሻንበልቀና፡ ጎጌ ወንዝ፣ ብረሃኑ ጫካ፣አኪሌሉአብተወልድ...

  • @elsatilahun5241
    @elsatilahun5241 Před 16 dny +4

    መካኒሣ ነው የተማርኩት በጣም ወደ ፊት አስታወሰኝ ምርጥ ሰፈር ዋው ተክኤ ምርጥ የሰፈራችን ልጅ እግዚአብሔር እድሜ ይስጥህ

  • @mickiyasSolomon-i6y
    @mickiyasSolomon-i6y Před 8 dny

    ብዙ የምናሳየው ነገር አለ እና እንደገና መተ ቅረፅ ቡዙ ቡዙ ትዋቂ ሰው ያለበት ነው
    ስለዚ ቡዙ አላወራክም ለምሳሌ ጊዳዋሻ አለ ስለ መከኒሳ ትምህርት ቤት ብዚ አለቅረፀክም 🙏🙏🙏

  • @JeforeGeya
    @JeforeGeya Před 15 dny +4

    በጣም ብዙ የሚነሱ እና የሚታዩ አልፎም ብዙ ትዝታ ሊያጋሩ የሚችሉ ቀደምት ሰዎች ነበሩ።

  • @engdakasahun9251
    @engdakasahun9251 Před 15 dny +4

    ዮኒ ትልቅ የታሪክ ተዛንፎ ተፈፅሞብናል መካኒሳ ከ80 ዓመት በላይ ታሪክ ያላት ሠፈር ነች በሌላ ፕሮግራም ቢስተካከል ጥሩ ነው::

  • @user-hx1tz9of4y
    @user-hx1tz9of4y Před 9 dny

    የመካኒሳን ታሪክ ለማወቅ ብዙ ትልልቅ ሰዎች አሉ እነሱን መግኘት አለብህ ብዙ ያላየሀቸው ነገሮች አሉ

  • @user-bd1il1bh4n
    @user-bd1il1bh4n Před 15 dny +4

    ጠመኔ ማለት 1960 ጀምሮ የሚታወቀው ቾክ ነው አስተማሪዎች ብላክ ቦርድ ላይ የሚጽፋበት ማለት ነው በተጨማሪምገብርኤል ፀበልና 2 ቁጥር አውቶቡስ ከመርካቶ ተነስቶ የሚደርሰውም መዘንጋት የለባቸውም

  • @tsegabuzuayhu1246
    @tsegabuzuayhu1246 Před 15 dny +4

    መካኒሳ አረቄ ፋብሪካውን መጠየቅ አለብህ የመጀመሪያ ስያሜው የተገኘው ከዛ ይመስለኛል:

  • @meaza115
    @meaza115 Před 16 dny +1

    Yoni thank you! Mekanisa timehert bete yadekubesh yetemarkubesh nuri lezelalem endekorahubesh!❤❤❤

  • @Destavich
    @Destavich Před 6 dny

    ጠመኔ ተመችቶኛል! ላይፍስታይሉ የብዙ አፍሪካዊ ወጣትን ይወክላል። አላህ የልብህን ይሙላልህ የኔ ወንድም።

  • @HanaMiss-nv4do
    @HanaMiss-nv4do Před 11 dny +1

    መካኒሳ እኮ የሚያቃት የለም እንጂ የ80 አመት ታሪክ አይደለም ያላት በጣም የጥንት ሰፈር ናት የጣሊያን ምሽግ ጊዶ ዋሻ ብዙ ታሪክ ነበራት...

    • @miraclenow3616
      @miraclenow3616 Před 10 dny

      It's Guido not Gido, Signore Guido was one of the earliest residents in Makanisssa, I went to elementary school (Wollo Tigre Synodos) with Alemsefea Guido. The son of Signore Guido. The cave or (washa) named after him because he used to have a ranch or dairy farm near to the "washa"

  • @zinashethiopia502
    @zinashethiopia502 Před 15 dny +1

    መካኒሳ አካባቢ ት/ቤት ተምሬያለሁ ብዙ ትዝታ አለኝ❤ 😢

  • @tekiwtekiw5043
    @tekiwtekiw5043 Před 16 dny +5

    ስለመከኒሳ ሚያውቅሰወችን አላገኝህም ለምሳሌ ሰለ አለ ክሊሉ ሃብተወልድ ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ጊዶ ዋሻ አመልማል ሃባተ ፍቅረአዲስ ነጋ ጥበብ አርመኖች አረቄ ፋብሪካየመሳሰሉት ዣጥላ ፍብሪካ

  • @dere7406
    @dere7406 Před 15 dny +3

    መካኒሳ የኢጣሊያን ስም ይመስለኛል እኔ ተወልጀ ባደግሁበት ደብረማርቆስ አካባቢ እርግጠኛ አይደለሁም እንጅ የአረቄ መያዣ ኮዳ ወይም ማውጫ ነገር መካኒሳ እያሉ ሲጠሩት አስታውሳለሁ ማጣራት ያስፈልጋል ግን!!!

  • @danielmesfin7711
    @danielmesfin7711 Před 15 dny +2

    ዮኒ መካኒሳ 1880ዎቹ አንጂ
    የ1980ዓ/ም ታሪክ አይደለችም የመካኒሳ በጎ ከድራጎትና የመካኒሳ ታዳጊዎች ፕሮጀክት ኮንታክት መደረግ ነበረበት

  • @hulgebtube7932
    @hulgebtube7932 Před 15 dny +3

    ዮኒ ገረፍ ገረፍ እንጂ መካኒሳን የሚገልፅ ስራ አይደለም ያቀረብከው በድጋሚ ይሰራ።

  • @khalidbito
    @khalidbito Před 16 dny +5

    እነ Dr. Mulatu የቀድሞ ፕሬዝዳንት እነ ሀመልማል ኣባተ, ኳስ ተጫዋቾች አረ ስንቱ…

  • @alemugudeta2083
    @alemugudeta2083 Před 16 dny +3

    "መካኒሳ" ማለት "በከኒሳ" ከምለው የአፋን ኦሮሞ ቃል የመጣ ነው። ትርጉሙ ብሳና ዛፍ ማለት ነው።

  • @zedagmawitewodros5440
    @zedagmawitewodros5440 Před 15 dny +2

    መካኒሳ ት/ቤት ፣ ዶንቦስኮና ኮንሶላታ፣ቀላፎ፣ አሚጎ፣ መካነእየሱስ ሴሚናርየም፣ ቀበሌ 02 ስፖርተኛ ሰፈር፣ ጊዶ ዋሻ አቃቂ ወንዝ ፣ ሚካኤል ታቦት ማደርያ

  • @shemelisibrahim5954
    @shemelisibrahim5954 Před 13 dny

    ዮኒዬ በመጀመሪ መካኒሳን ለማስታወስ መነሳትህ ልትመሰገን ይገባል በመቀጠል የተወለድኩባት ያደኩባት ብዙ ትዝታ የቸረችኝን ሰፈሬን እወዳታለሁ ነገር ግን መካኒሳ ከተነገረላት በላይ ብዙ ታሪክ ያላት ሰፈር ነው ከአቦ አደባባይ እስከ እስከ አረቄ ፋብሪካ ድልድይ ከዛም ስናልፍ እስከ ጉድሽበርድ ማገገሚያ እስከ ጀርመን አደባባይ ይሚገርም ታሪክ ያላት ሰፊ ሰፈር ናት እና ዬንዮ እንደገና በደንብ ስለ መካኒሳ ቢዘገብና ለታሪክ ቢቀመጥ መልካም ነው እላለሁ መልስህን እጠብቃለሁ ተባረክ እኔና ቤተሰቦቼ እንወድሀለን ቻው::

  • @mershagetaneh1508
    @mershagetaneh1508 Před 14 dny +3

    የተረሱ ለአገር የሰሩ ባለሞያዎች በመከኒሳ የሚኖሩ ወይም ለጥቂት አመታት የኖሩበት
    1, ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻው
    2, አመልማል አባተ
    3, ፍቅርአዲስ እና ባለቤቷ
    4, ስብሀት ገ/እግዚአብሔር
    4,ዳዊት መኮንን( አኑቬን ጅራ)
    5, ቃቂ ተስፋዬ
    6, ካሱ ኢላላ
    7, ብርሃነ መዋ አባቱ ባለስልጣን ነበሩ
    8, የፊልም ባለሞያ ብርሃነ መዋ

  • @belaymengasha609
    @belaymengasha609 Před 15 dny +1

    ዮኒ ሰፈራችን መከኒሳ በሚገባ ስለሰፈሩ መግለፅ የሚችሉ ወንድሞቻችን ነበሩ መጀመሪያ የቆምክበት ፎቅ ጋር መከኒሳ በጉ አድራጎት መሀበር ውስጥ በትገባ በጣም ብዙ ልጆች ታገኝ ነበር መከኒስ ትምህርት ቤት ነው ተምረን ያደግነው አሁንም ኤዛው እየኖርን ነው

    • @TiKi-wy6uc
      @TiKi-wy6uc Před 11 dny

      የማነ እና አስረስ የሚባሉ ልጆች ነበሩ በጣም ጥሩ ልጆች ጔደኞቼ ነበሩ ጊዜው ቢረዝምም ሁሌ አስባቸዋለው እባክህ ካወቅካቸው ንገርልኝ እኔ እሩቅ አገር ስላለው ላገኛቸው አልቻልኩም ለምልክቱ አንድ ትንሽሴት ልጅ የነበራት ተከራይታ ትኖር ነበር በልልኝ

  • @TesfayeSima-o7p
    @TesfayeSima-o7p Před 16 dny +3

    ዮን ፕሮግራምህን አወደዋለሁ። ለምን ብትለኝ የትናንት ሰው በመሆኔ። ለዛሬው መከንሣ በጣም ሰፊ ነው። መከንሣ "በከኒሠ"ከሚለወ ቃል የመጣ ነው። በከኒሠ የዛፍ ስም ነው።ቃሉ የኦሮምኛ ነው። በአማርኛ ብሳና የምባለው ዛፍ ሰም ነው ።አከባብው በብዛት የበከኒሠ ዘፍ ስለ ነበረነው።

  • @ibrhimredwan1199
    @ibrhimredwan1199 Před 15 dny +2

    መካኒሳ አረቄ ፋብሪካው ዝቅ ብሎ ያለው ሰፈር ተወልጄ ያደኩበት ሰፈሬ ነው አሁን ላይ ስደት ላይ ብሆንም

  • @sentayehuakenaw7497
    @sentayehuakenaw7497 Před 14 dny

    Ebs(ዮኒ ) መካኒሳን በሚመልከት ትዝታዎቿን ለወደፊት ሊያስቃኝን የት እና ቤት በኩል ልስራ እያለ እያጠና እንዳለህ ነው የተሰማኝ! ለሱም በቂ ነው ብዬ አላምንም :: ስለመካኒሳ በቅርቡ ያሏትን ትዝታና ቅርሶቿን እንደምታስጎበኝን ተስፋ አደርጋለሁ!!!🙏

  • @sirgutamera4806
    @sirgutamera4806 Před 15 dny +2

    የአላሙዲን የነርሶች ት/ቤት የት ደረሰ

  • @mohammedabdu7272
    @mohammedabdu7272 Před 15 dny +2

    asafari Mekannissan Yemayegelete perogeram new.

  • @BerhanuTaddese
    @BerhanuTaddese Před 16 dny +4

    መካኒሳ ኦሮምኛ ነው የዛፍ ስም ነው

  • @user-ki3kq7le9e
    @user-ki3kq7le9e Před 16 dny +3

    መከኒሳ የሚለው ስያሜ የመጣው....በኦሮሚኛ በከኒሳ ከሚባል ተክል የተገኘ ነው....ሰፈራችን ስለመጣህም እናመሰግናለን

  • @Teme-n4p
    @Teme-n4p Před 9 dny

    Degmeh sraw yoni gdelehm❤

  • @FaithSaves23
    @FaithSaves23 Před 16 dny +3

    ትልልቆቹ ሲናገሩ እንደሰማነው በከኒሳ ከሚለው የኦሮምኛ ቃል የመጣ ነው።

  • @mesfinseyfu8464
    @mesfinseyfu8464 Před 15 dny +4

    በጣም እማዝነው ሚጠየቅ ሰው አተክ ነው ዮናስ የምር ያሳፍራል አዲስ አበባላይ የሌለ በጣልያን ግዜ የተሰራውን ዋሻ ሳታይ በኢትዮጵያ ታሪክ በአካለ ስንኩላን ይሰራ የነበረውን የጃንጥላ ፋብሪካን ሳታይ ምንግዜም ብራን የተሰኝው ባትሪ ሳይቀር ሚያመርት ፋብሪካን እንደቀልድ ማለፍ አረ ያሳፍራል የምር !

  • @Rufo243
    @Rufo243 Před 16 dny +1

    ፓስተር አካባቢ ና እስቲ ዬኒያችን😊😊

  • @DawitBelete-n2k
    @DawitBelete-n2k Před 4 dny

    ተመኔ ምርጥ አገላለጽ

  • @samsonsahelu9952
    @samsonsahelu9952 Před 15 dny

    I grew up in mekenisa my parents are one of the first settlers and I am so happy to see aklilu (shrifo) but sherifo u did not born there I remember when u moved to our community..your brother awlachew was g…to say donbosko amikonstro amikono javentu… u can consider me as legend never well come because I am originally from merkato and meknisa was never Addis

  • @BB44792
    @BB44792 Před 16 dny +6

    አይ ኢቢኤስ ሰንት አዛውንት መካኒሳን የመሠረተ እያለ ቀለዳቹበት

  • @martatawk2474
    @martatawk2474 Před 5 dny

    Era meka bezu negir ale yoni gido washa gulit akakiy wenze mench era bezu bezu

  • @tahirkasim3703
    @tahirkasim3703 Před 16 dny +2

    መካኒሳ የኦሮሚኛ ቃል ስሆን ብሳና ዛፍ ማለት ነው። ልክ እንደ ላፍቶ -የኦሮሚኛ ቃል ግራር ማለት።

  • @TiKi-wy6uc
    @TiKi-wy6uc Před 11 dny

    ወይኔ መካኒሳ ትዝታ አለኝ ገና ኮንዶሚንየም እንደተሰራ ታክሲ ማዞርያው ከፍ ብሎ ተከራይቼ እኖር ነበር በዛ ላይ ምርጥ ጔደኞች ነበሩኝ የማነ የሚባልና አስረስ የቴዲ ወንድም እባካችሁ አገናኙኝ የምታውቋቸው ንገሩልኝ እኔ ከአገር ከወጣው 12አመት በላይ ነው ግን ሁሌም አስባቸዋለው

  • @aberatek5731
    @aberatek5731 Před 15 dny

    Foot ball has much History at Mekenissa....Geremew...Yisak....kedir...Eshetu....Abiy...Andargachew ethiopian coffee and many many Historic players

  • @Amarch-ck6ig
    @Amarch-ck6ig Před 16 dny +1

    ዉዷ ሰፍሬ እናመሰግናለን

  • @HanaMiss-nv4do
    @HanaMiss-nv4do Před 11 dny

    መካኒሳ ተመጥቶ ጊዶ ዋሻ እንዴት ይረሳል ምንም እኮ ነው መካኒሳን ያልገለጣችኋት በጣም ነው የከፋኝ ሰፈሬን አየሁ ስል ዋና ነገሮች ተረስተው ያልተወለዱባት መረጃው የሌላቸው ሲጠየቁ 😢 የዚህን ሁሉ ሰው አስተያየት አይተክ ድጋሚ እንደምትሰራበት ተስፋ አለን

  • @lulitkebede8104
    @lulitkebede8104 Před 8 dny

    Ereeee yonii betam yikrta….. kdmk tezegajitk sira ምጠይቃቸዉን ሰዎችና ሰፈሩን ጊዜ ሰተክ ስራ 😢 program ብትደግም ይሻላል እንዲ ከምትሰራ ……thanks

  • @BetelhemAlemu-ij8go
    @BetelhemAlemu-ij8go Před 12 dny

    ዮኒ ትክክል ያልሆነ ስራ ነው በደንብ
    ተዘጋጅተህ ስራ.......

  • @makdakassa7350
    @makdakassa7350 Před 16 dny +1

    ኤቢስ ያየሁትን ጥሩ ያልሁነ ነገር ቬድዮ ስትቀርፁ አንዱን መስመር ብታዘጉት ጥሩ ይመስለኛል እነዚህን የኤቬስ ወርቁች እንዳታሳጡን ።

  • @yalewtesfaye738
    @yalewtesfaye738 Před 15 dny

    mekanisa beoromiffa besana new tekekele

  • @tigstaddis7629
    @tigstaddis7629 Před 14 dny

    Yone menme merja aleyazekem
    Ato GZAWE BEZU yene abate tawaki neber
    temerte betun, ederun ,B/yanun ,endeume belematu bekule telki
    asetwaso yarege neber ena telki sew alagegehem aleserahebetem bezu sewoch alu yemetaweku Lela geze temles gedo washawen sataye

  • @Maga-1
    @Maga-1 Před 16 dny +3

    መከኒሳ መሰረታዊ ታሪኩ ከመካና እየሱስ ቤተክስስቲያን ጊቢ ጋር የተገናኘ ነው! ብዙ ሙዚቀኞችንም ያፈራው የሙዚቃ ት/ት ቤት የሚሽን ሴሚናሪ ግቢ ተጓዳኝ ነው የጥንቱ ታሪክ !

  • @HelenHaile-bq2es
    @HelenHaile-bq2es Před 16 dny +1

    Mekanisa meteh yemilin shro satkems ema mnun metay meteh mekmes alebh

  • @tsehayarega848
    @tsehayarega848 Před 15 dny

    Thank you

  • @user-bl6ok4gv4n
    @user-bl6ok4gv4n Před 16 dny

    ጆርጆ ግቢ በጣም ደስ ይላል ግን መካኒሳ ትልልቆቹ ሰወች አልቀዋል ዮኒ እኛም ብናቅ ኖሮ ጥሩ መረጃ እንሰጥህ ነበር

  • @eliasserawit8623
    @eliasserawit8623 Před 15 dny

    Mekanisa ማለት ቤተ ክርስቲያን ማለት በ kiswahili original word is kanisa ...it was given by missionaries around there who were running some east and horn Africa churches at that time .ብስራት ወንጌል and other Churches

  • @Firehiwot45
    @Firehiwot45 Před 14 dny

    thank you

  • @keyiaget1707
    @keyiaget1707 Před 16 dny

    Yoni selam new mekanisa memtatik ejig adregen new yemamesegenew kettle mekanisan bedenb asayikalehu menager yemichelu seweche agenagekalehu mekanisa malet bekenisa ye mibal zafe weyiem bisana zaf neber seferu bemulu esu neber leza new bekenisa yetebalew yiha tinishu new sitemeta bizu enasayikalen

  • @Izedin-j4u
    @Izedin-j4u Před 15 dny +4

    ዬኔ መካኒሳ የሚጀምረው ከቫቲካን ነው የጠየካቸው ሰዎች መካኒሳን አላወቋትም አንተ አዲሱ መካኒሳ ነው የሄድከው

    • @emmu_tiru1157
      @emmu_tiru1157 Před 9 dny

      ወደ ጀሞ ነው መሰለኝ የሄደው:: እኔም የቫቲካን ሰው ነኝ:: አያቶቼ ግን መካኒሳ

  • @eskedartessema6318
    @eskedartessema6318 Před 16 dny

    🙏🙏🙏

  • @Isrulyrics
    @Isrulyrics Před 16 dny

    mekanissa enkuan metachehu

  • @HelenLegesse-h4e
    @HelenLegesse-h4e Před 15 dny

    bebeki huneta altegeletechm mekiye pliss wede mederocha geba bleh talalak sewoch alu enesu linegruh ychlalu

  • @HelenHaile-bq2es
    @HelenHaile-bq2es Před 16 dny

    ዮኒዬ መካኒሳ ድረስ መተህ የሚሊን ሽሮ ሳትበላ ተመለስክ መተህ መቅመስ አለብህ

  • @merongetahun753
    @merongetahun753 Před 16 dny

    Yoni, Mekanisa eza akababi kalew ke 'mekane eyesus' ke milew ye church sim yemeta yimesilegnal

  • @Myme-sx3kh
    @Myme-sx3kh Před 15 dny

    ❤❤❤❤❤❤

  • @samrinigusie6934
    @samrinigusie6934 Před 15 dny

    mekanisa seferie ke weldet eske edget ye fekrochi sefer mekanisa temrtbete yadekubshi yetemarkubshi

  • @MrBookkk
    @MrBookkk Před 15 dny

    ብስራተ ገብርኤልን እየዞርክ ነው ዪኒ
    እንጠብቃለን

  • @checkantetibo
    @checkantetibo Před 15 dny

    The son of a native Mekanisan, the place was predominantly an Oromo-Afan speaking area 40 plus years ago. Its name is derived from the plant called "Bakkanisa" in the Oromo-Afan language and is commonly called "Bisana" in Amharic. Go ask people who work for the Mekaneyesus Church, and they will tell you more

  • @fitsumtariku3312
    @fitsumtariku3312 Před 8 dny

    በከኒሳ የዛፍ ስም ነው ታሪካዊ ቦታ ጊዶ ዋሻ አለ የአክሊሉ ሀብተ ወልድ መኖሪያ ቤት አቦ ቤተ ክርስቲያን የፈረስ ቤቶች እና ጥንታዊ ቤቶች ሻምበልቀና ወተት ቤት ሙዝ ቤት ወይም አቦ ማዞሪያ አሁን ደግሞ የመከኒሳ ልጆች ማህበር እና የእስፖርት ማሰልጠኛ አስደሳች ሆቴል አሰልጣኝ ተወዳጁ የአፍሪካ ዋንጫውን በልቶ ያሳየን...... መኖሪያ እነዚህን የመሳሰሉ ብዙ ታሪካዊ ቦተዎች አሉ

  • @HelenLegesse-h4e
    @HelenLegesse-h4e Před 15 dny

    Bemekenisa bzu ltawesu yemigebachew gn yaltetekesu tarikaw sfrawocha alu lmsale endebgido washs ..

  • @yoditgudetta642
    @yoditgudetta642 Před 13 dny

    ዮኒ ግን በዚ ልክ አልነበረም መካኒሳነ መግለፅ የነበረብህ ት/ቤት ደርሰህ አመሰራረቱን ሳትጠይቅ ማለፍህ ያሳዝናል ታሪክ ከ ትላልቅ ሰዎች ነበር መጠየቅና መረዳት የነበረብህ ።
    በነገራችን ላይ ት/በቱን የመሰረተው የኔ አያት ነበር ጉደታ አያኖ ይባላል በጊጊዜው የነበሩ ተማሪዎች ለሰኞ አርብ እበት አየለቀለቁ አያዘጋጁ ነበር የሚማሩት ብዙ ሳታውቅ ነው የወጣኸው ዮኒ አስተካክልልን።

    • @miraclenow3616
      @miraclenow3616 Před 10 dny

      You're right The elementary school was formed in 1956 Eth, cal. using a horse stall used to serve for colonial fascists by dividing into rooms. The school then sponsored by mekane eyesus and named as Wolo Tigre Synodos. I might be wrong but I used to go to that school with Amnuel Gudeta (may be your brother) and his mom used to teach us Amharic teacher Aregash

  • @AbeMeng
    @AbeMeng Před 14 dny

    መከኒሳ ማለት በኦሮምኝ የብሳእና ዛፍ ማለት ነው ወይም ጥላ እደማለት ነው

  • @Natiworku
    @Natiworku Před 15 dny +3

    ዮኒ ግን ትንሽ ሪሰርች እና ዝግጅት ኣድርገህ ብትሄድ ኣሪፍ ነው፤ ምንም የማያውቅ ሰው መንገድ ላይ ኣጝንቶ ማውራት ይደብራል

  • @wasedemeke399
    @wasedemeke399 Před 13 dny

    lela program mesrat alebk asbekbet enemann magnet endalebk asbekbet mkniyatum slemekenisa bzutarik ale

  • @AmanKasim-bc2zz
    @AmanKasim-bc2zz Před 15 dny

    Mkanisa sefre bzu mitayu botawoch nbru mkuye tmhrtbete 😢

  • @AbrahamNigusey
    @AbrahamNigusey Před 11 dny

    አልገለፀም የሚያቅ ሰው አላገኘም

  • @gemechuadugna6006
    @gemechuadugna6006 Před 16 dny +1

    mknisa k bknisa nw shift yhonem b Afaab oromo y enchet aynet nw

  • @TamruFekadu
    @TamruFekadu Před 16 dny

    I was being my primary school 1-4

    • @TamruFekadu
      @TamruFekadu Před 16 dny

      I was being stayed reminded my primary school 1-4 school

  • @-Dave-Sanjaw-ke-Ayertena

    አንድ ሰፈር የሚያስጎበኝ ወጣት ይጠፋል 😂 ወይስ በርጫ እያሯሯጡ ነው

  • @FevenEyob-hw1hz
    @FevenEyob-hw1hz Před 15 dny

    Maki sefari

  • @ermiaszewge2047
    @ermiaszewge2047 Před 15 dny

    መካኒሳ ተገለፀ ማለት ይከብዳል ሲጀመር ዋናው መካኒሳ አሚጎ አካባቢ አይደለም እላይ ነው ብዙ ብዙ ትዝታወች አልተካተቱም እነ አስደሳች ሆቴል እነ መክሊት ግሮሰሪ እነ ጥበቡ ወርቅዬ ይዘፍኑበት የነበረው ቤት ውስጥ ውስጡንም ብዙ ትዝታዎች ነበሩ
    ዮኒ ከመጣ አይቀር የመካኒሳ ልጅ ወና የለመደበት አጋስስ ወንዝ እና ጊዶ ዋሻም ነበረ
    ተኬያችን እንዴት ዘነጋከው አባቴ

  • @bezuayehumekonnen1582
    @bezuayehumekonnen1582 Před 12 dny

    ትልልቆቹ ያላወቁት ይሔ እሄ እንዴት አወቀ ኬኛ ነገር ይሸታል ኢቢስ ተተንቀቁ። ፓለቲካው ተውት endሶች

  • @AbeMeng
    @AbeMeng Před 14 dny

    መከኒሳ ማለት ብሳእና ዛፍ ማለት ነው

  • @obiharar8687
    @obiharar8687 Před 15 dny

    It is obvious , it is Oromiffa language ...

  • @sarazebene8695
    @sarazebene8695 Před 16 dny

    Hi yoni .emkenisa malet arebega new kenisa batekristan malet new me kenisa demo gedame new

  • @BettyBiruu
    @BettyBiruu Před 12 dny +1

    ምንም ዝግጅትም ጥናትም ያላረክበት መከኒሳን የማይገልፅ ፕሮግራም ነው ያሳዝናል!

  • @teklehiwottareqegnteklay

    በከኒሳ ነው የብሳና ዛፍ ማለት ነው

  • @Fvhfufutcfuh
    @Fvhfufutcfuh Před 13 dny

    መካኒሳን በሚመጥናት መልኩ አልገለጣትም ሌላ መካኒሳን ብዙ የሚያቃት ሰው ይቅረብ በጣም ቅር ብሎናል

  • @berhanudegefu2832
    @berhanudegefu2832 Před 15 dny

    መካኑሳ በኦሮምኛ ብሳና (የዛፍስም)ማላት ነው

  • @zinashethiopia502
    @zinashethiopia502 Před 15 dny

    እንዴ ሸሪፎ 😂😂😂😂(አክሊሉ)

  • @BettyBiruu
    @BettyBiruu Před 12 dny

    መካኒሳ 1880እንጂ 1980 አይደለም የተመሰረተችው መጀመሪያ ስትቀርፅ የቆምክበት ቦታ ከፍ ስትል የታዋቂዎቹ ዘፋኞች አመልማል አባተና የፍቅራዲስ ነቃ ጥበብ ቤት አለ እንዲሁም የዶክተር ሙላቱ ትልቁ ነገር ደግሞ ጊዶ ዋሻ ጣልያን የሰራችው ምሽግ እንደነበረ ማወቅ ነበረብህ ትምህርት ቤታችን ድረስ ሄደህ ውስጥ ድረስ ብትገባ ብዙ ታሪኮችን ይነግሩሃል ከእሱ ዝቅ ስትል አባቶቻችን ኤቨረዲን ባትሪ የዘመኑ ምርጥ ባትሪ ያመርቱ የነበረበት እሱን አልፈከዋል እዛው አካባቢ ነው:: መካኒሳ ባለ ብዙ ታሪክ ባለቤት ስለሆነች በሌላ ግዜ ተዘጋጅተህ ብትመጣ በጣም ደስ ይለናል የመካኒሳ ታሪክ ግን የሚጀምረው ከቫቲካን ጀምሮ ነው አንተ ግን የጀመርከው ከግማሹ መካኒሳ ስለሆነ ትዝታችን በኢቢኤስ ለዛሬ አልተሳከለትም ባይ ነኝ ብዙ ጥናቶች ማድረግ ይጠበቅብሃል:: ያገኛካቸው ሰዎች ታሪክ አዋቂ አይደሉም ይታረም👍

  • @YilmaWeldesilassie
    @YilmaWeldesilassie Před 15 dny

    ዮና በጣም ይቅርታ ቅድም የረሳውት ነገር መካኒሳ ወይም በከኒሳ የሚባለው የመጀመሪያው ከአባድር መስጅድ እስከ አረቄ ፋብሪካ ነበረ በይበልጥ አስደሳች ሆቴል አካባቢ ብርሃኑ ጫካ ጋሽ አፈወርቅ ት፣ቤትእረብዙአለድጋሚተመልስእናመሰግናለን።

  • @mekke6544
    @mekke6544 Před 15 dny +1

    ይልም ዴሬሳ ከመከኒሳ ማዶ ያለ መሬቱ ላይ አሁን ቀበሌ የሆነው የሱ የሚታለቡ የፈረንጅ ላሞች ማርቢያ ቤት ነበር እንዲሁም አልፎ አልፎ ሲመጣ የሚዝናናበት ቤት ነበረው እንጂ እዚያ መኖሪያ ቤቱ አይደለም።ላፍቶ ክፍለ ከተማ ያለው የመቃብር ቦታ የአልጋ ወራሽ የድን ጫቃ ቦታ ነብር።ሌላው የፉሪ ሜዳ(የላፍቶ ክፍለ ከተማ ቢሮ ካለበት እስከ ዶምቦስኮ ት/ቤት) የመስፍን ስለሽና የበዛብህ ስለ ሽህ መሬት ነበር።የበዛብህ ስለሽ ቤት እንጦጦ ገበያው አጠገብ ያለው ግቢ ውብ ቤተመንግስት የመሰለ ግራውንድ ፕላስ አንድ ፎቅ የሆነ የጥንት ቤት ነው። ደርግ ወርሶአቸው ነው።የመስፍን ስለሺ ቤት ጉለሌ ነው የሚገኘው።ሁለቱም ኦሮሞዎች ናቸው።