በጣም ልብ ይሰብራል!ዘሪቱ ከበደ የመጀምሪያ ልጇን በሞት አጣች!(‎@gizemedia1974)|Ethioiap|Zeritu kebede| 6 June 2024

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 5. 09. 2024
  • Elshad Ye1000:
    ዛሬ ስለ ዘሪቱ ከበደ እንደተለመደው አስደሳች ዜና ሳይሆን የምጀመሪያ ልጇን ህልፈት የሚነግር አሳዛኝ ዜና ሰማን። ነብስ ይማር።
    ከቀናት በፊት እናት ባንክ ባዘጋጀው እና ስለ እናቴ በተሰኘ የስነ -ፅሁፍ ውድድር ሽልማት ላይ በእንግድነት ተገኝተው ስለ እናትነት ስሜታቸውን ከገለፁ እናቶች መካከል አርቲስት ዘሪቱ ከበደ አንዷ ነበረች፡፡
    በወቅቱ "የእናትነት ትርጉሙ ይበልጥ የገባኝ ልጅ ከወለድኩ በኃላ ነው።አሁን ራሱ ከእራስ ቤት ጨቅላ ህጻን ጥዬ ነው እዚህ የመጣሁት የእናት ጉዳይ ሆኖብኝ ነው።"..እኔ እኔ ….ለእኔ ለእኔ የምንለውን ሰዎች እኔን ያስብለናል …እናትን የተባረኩበት ፈጣሪዬን የማመሰግንበት እድል ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ እናት መሆንን ለታደሉት የዘመኔ ሰዎች በሙሉ ይህንን መታደል እንዲያከብሩት እፈልጋለሁ፡፡ እናትነት የ9 ወር ሸክም ጉዳይ ብቻ አይደለም! እናትንት ዘላለማዊ ሸክም ነው …አንዴ ተሳስረናል …አንዴ ተሸካክመናል እና ውላችን ዘላለማዊ ነው …..እናትነት የባለ አደራው ምስክርነት ነው …መክሊት ነው…ስለምንችል ነው ፈጣሪ ይህን እድል የሰጠን ፡፡ስትል ነበር እናት ስለመሆን የነበራትን ምልከታ ለእንግዶች ያስተላለፈችው፡፡
    እንግዲህ የእናትነትን ስሜት አንዲህ አድርጋ በገለፀችበት አንደበቷ ነው እንግዲህ ልጄን ልጄን ብላ እንድታለቅስ የሆነችው …እንዴት ትችለው ይሆን ….አናውቅም ….
    ዘሪቱ ከበደ ከላይ የተናገረችውን ነገር በተናገረች ሳምንት ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ነበር እንግዲህ በብዙ መልኩ ለብዙ ቁም ነገር የምትጠብቀውን የ17አመትቱን ታዳጊና ልጇን በድንገተኛ ሞት የተነጠቀችው፡፡
    ክርስቲያን ላቃቸው ገና የ11ኛ ክፍል ተማሪ ሲሆን ሲያድግ ብዙ ብዙ ነገሮችን የመስራት እና የመሆን ምኞት እና ፍላጎት ነበረው፡፡ ሕይወት መቼም እንዳሰቧት አይደለችም እና ታዳጊው …ተስፈኛው ክርስቲያን ላቃቸው ባደረበት ድንገተኛ ህመም ሳቢያ በላንሴት አጠቃላይ ሆስፒታል ሲረዳ ቆይቶ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡
    እንዲህ ያለውን ሀዘን መቼም አያድርስ ነው ማለት!!
    መቼም የሀዘን ጥሩ ባይኖረውም አንዳንዱ ሀዘን ግን እጀግ ክፉ ነው! ሀዘን እና ደስታ ቅይጥ የኑረት መልክ ናቸው …የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጦች እንደ ሕይወት እና ሞት ማለት ነው፡፡ ሞት ዘላለማዊ የተፈጥሮ ማሳረጊዜ …የኑረት ሂደት ማሰረጊዜ ጫፍ ነው፡፡ አይሸሹ አይቀሩበት ነገር ማለት ነው፡፡ አንዳንዱ ሞት እሰይ እንኳን ተገላገለ በሚያስብለው ልክ አንዳንዱ ደግሞ የእውር ድንብሩን ጨክኖ መጥቶ ማንን እንደሚወስድ አይታወቅም …እንዲህ ያለው ሞት ሲመጣ የወሰደውን ብቻ ወስዶ አይቀርም …በሕይወት ያለውንም ሰው ያሰቃያለ….ሞት ቅደም ተከተሉን ተከትሎ ሳይመጣ ሲቀር የሚያናጋው …የሚያዛባው ነገር ብዙ ነው፡፡…..
    በተለይ ለወላች ልጄን ልጄን ብሎ ማልቀስ ከባድ ነው!!! ለልጅ ወላጅን ማጣት ከባድ ቢሆንም ሞት ቅደም ተከተሉን ጠብቆ መጥቷል እና …ልጄን ልጄን ብሎ ከማልቀስ እኩል አይሆንም፡፡
    የዘሪቱ ከበደን የበኩር ልጅ …የክርስቲያን ላቀቸውን ሞት በተመለከተ ከዓመታት በፊት እንዲሁ እንደ ዛሬው ….ባህር ማዶ በብዙ ብርታት እና ብቃት እየተማረች የነበረችውን የመጀመሪያ ልጁን በድንገተና ሞት የተነጠቀው አንጋፋው ጋዜጠኛ እሸቱ ገለቱ ….እንዲህ ሲል ነበር …ያለፈበትን አሁን ደግሞ ዘሪቱ የገባችበትን የሀዘን ስሜት የገለፀው….
    አዬዬዬ ምኑ ሰማይ ወደቀብሽ እህቴዋ - ምን ቃል ያፅናናሽ ይሆን?
    ተለቅሶም ተነብቶም የማያልቅ የሆድ ውስጥ የሀዘን ዥረት፡፡ እህቴ ከያኒት ዘሪቱ ከበደ አሳዘንሽኝ - ልጄ ልጄ እንደማለት ልብ ሰባሪ ነገር የለም፡፡ መድህን አለም ክርስቶስ እንደው በታዕምሩ የምትችይበትን አቅም ይስጥሽ! ‘ሆድን ድንጋይ አድርጎ’ የሚያበረታ የመፅናናት መንፈስን ያድልሽ!
    ==========================
    የቀን ጨለማ ይሉታል እንዲህ አይነቱን አንዳንድ ዕለት - የቀን ጎዶሎ፡፡ ለጋ የበኩር ልጅን ማጣት እኮ የሚይዙ የሚጨብጡትን የሚያሳጣ የሰማይ መደፋት ነው፤ የሆድ ውስጥ ፍም ነው፤ የእግር እሳት እና የእድሜ ልክ ሕመምም ነው፡፡
    በዚህ ሰአት ተፈንቅሎ የማይወጣ የሀዘን ስሜትሽን እረዳለሁ - መራር እውነታውን ለመቀበል በመቸገር ግራ መጋባትሽን እገነዘባለሁ - አምላክ የልጄ ወጌን እኮ ለምን በሚል ብትጠይቂም እረዳለሁ - የሀዘን ጫናው የሕይወት ጣዕምና ቀልብ ቢያሳጣም ተገማች ነው፤ ብዙ ለምን ለምን የሚሉ ጥያቄዎች ብታነሺም ቅሉ መልስና ምላሹ ግን ከሌላ ነው፡፡
    “በቃ እግዚያብሔር አዋቂ ነው፤ እሱ ሰጠ - እሱ ነሳ፤ እንኳን ሌላ የእኔ የምትሉት ራሳችሁም የራሳችሁ አይደላችሁም ብሏል መፅሐፉ፤ ንብረቱን እሱ በጊዜ ወሰደ እንዲሉ”፡፡ እህቴዋ የእዮብን የመፅናናት መንፈስን ያጎናፅፍልኝ!
    አስታውሳለሁ አንድ ሰው ያለኝን “ይህ የገጠመህ ዱብእዳ የሆድ ረመጥ የሚሆን የእድሜ ልክ ሀዘንህ ስለሚሆን ማንም አያበረታህም - አፅናኝ ቃልም ስቧጥጥም አልገኝ - አልሸነግልህም - ዋጥ አድርገህ ወደ ውስጥ አልቅስና ይውጣልህ”፡፡
    ቃላት በበቂ ባያበረቱም ግን የርህራሄውና አፅናኙ አምላከ ክርስቶስ መቀነትሽን አጥብቀሽ የምትፅናኝበትን ብርታት እንዲያድልሽ ተመኘሁ!
    ሶስት ወንዶች ልጆች ላሉበት ቤተሰብ የበኩር ልጅ የሆነው ብላቴናው ክርስትያን ላቃቸው የ17 አመት እድሜ ታዳጊና የ11ኛ ክፍል ተማሪ ሲሆን ባደረበት ድንገተኛ ህመም ሳቢያ በላንሴት አጠቃላይ ሆስፒታል ሲረዳ ቆይቶ ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡
    የከያኒት ዘሪቱ እና የላቃቸው መንግስቱ ወርቁ ለጋው ክርስትያን ገና በጀንበር መውጫ እድሜህ የተለየኸን በሰማያዊው አባትህ እቅፍ በሰላም እረፍ!
    ይሄን ጊዜ ታዲያ ልብ ተሰብሮ ፣ ቤተሰብ ግራ ተጋብቶ ፣ እምነት ተፈትኖ፤ ይህ አይነቱ ዱብእዳ ሀዘን ኧረ ምን የማያስከስተው ነገር አለ፡፡ እናም ይህ ሀዘን የእድሜ ልክ ነውና ቤተሰቡ ውስጥ በሚፈጠረው ሸለቆ የቀሪ ልጆቹ ድንጋጤ ራሱ ያሸብራል፡፡ አባትና እናት፣ ቤተሰብ ቤተዘመድ፣ ወዳጆች ሁሉ ብርትት በሉልኝ! እግዚያህሔር ያፅናችሁ! የሀዘን ዳርቻ ያድርግላችሁ!!!
    ምን ገጠመው
    በነገራችን ላይ የዘሪቱ ባለቤት ላቃቸው መንግሱቱ እግር ኳስ ተጫዋች ነበር። አባቱ መንግስቱ ወርቁም በሃገራችን የእግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ስማቸው ጎልቶ ከሚነሱት መካከል ነው። መንግስቱ ወርቁን የማያውቅ ሰው አለ ለማለት ቢከብድም ማንነቱ ብዥ ለሚልባችሁ በዘመኑ እጅግ የሚገርም የእግር ኳስ ታሪክ ያለው የኢትዮጵያ እግርኳስ ተጫዋች እና የቅዱስ ጊዬርጊስ መለዬም ተደርጎ ይጠቀሳል። መንግስቱ ወርቁ ካለ ኳስ፣ ጎል፣ ውብ ጨዋታ፣ ያልታሰበ አዲስ ክስተት አለ። በነገራችን ላይ መንግስቱ ብቻም ሳይሆን የመንግሱት አባት ፊት አውራሪ ወርቁ ስንቄ በሃገራችን የአርበኝነት ታሪክ ውስጥ ደማቅ ስማቸውን አስመዝግበው አልፈዋል። በጣሊያን ወረራ ወቅት ጣሊያንን ሽንቱን ያሸኑ አርበኛ ነበሩ። መንግስቱ እንኳን ገና በጨቅላ እድሜው አባቱን ለመያዝ ባሰበው ጣሊያን እጅህን ስጥ ወይ ሚስትህን እና ልጅህን ገድለን ለአውሬ እንሰጣለን ባሉት ጥሊያኖች ታግቶ ታስሮ ነበር።
    ።።።
    ብቻ የዘሪቱ ልጆች አያት እና ቅድመ አያት ታሪካቸው ትዝ ሲለኝ ጻፍኩት።
    ዘሪቱ ከበደ ሁላችንም የምናውቀው ስም(household name) ከመሆኑ በፊት ብዙዎች ስሟን እንድትቀይር ዘሪቱን ተማፅነዋታል። እሷ ግን በእምቢታዋ ፀንታ ሃያል ድምጿን ከስሟ አስተሳስራ አሁን ዘሪቱ የሚለው ስም የአሪፍነት መለያ ሆኗል። ከባህር ማዶም ሊዎናርዶ ዲካፕሪዮ እና አርኖልድ ሸዋዚንገር ስማቸውን እንዲቀይሩ ትላልቅ የፊልም ስቱዲዮዎች ጎትጉተዋቸው ነበር። ስምህን ትፈጥረዋለህ እንጂ ስም አይፈጥረንም ማለታቸውን ሰማሁ

Komentáře • 72

  • @elsabeautynt
    @elsabeautynt Před 3 měsíci +10

    እግዚኦ ፈጣሪ ሆይ እባክህ አፅናናት እናትነት ለመፃፍም ቃል የለኝም

  • @user-no2ln5kn4m
    @user-no2ln5kn4m Před 3 měsíci +5

    በጣም ከባድ ነው ቃል የማይገልፀው እግዚአብሔር መፅናናቱን ይስጥሽ እህቴ

  • @meronmeron5210
    @meronmeron5210 Před 3 měsíci +6

    ኦፍፍ..ማንም ሰው በልጅ ሞት አይቀጣ በጣም ያማል💔😢 እግዚአብሔር ፅናቱን ይስጥሺ የኔ እናት!🙏😭

  • @etagegnehuwoldetsadik4057
    @etagegnehuwoldetsadik4057 Před 3 měsíci +6

    እህታችን እግዚአብሔር ያጽናሽ

  • @user-gf5wf1pl2g
    @user-gf5wf1pl2g Před 3 měsíci +5

    Alahe yasenashe betame kebade new welahi😢😢😢😢😢

  • @rozinatamru415
    @rozinatamru415 Před 3 měsíci +5

    ህመሙ ከባድ ነዉ በቃል የሚገለፅ አይደለም የእኔ እህት እግዚአብሔር አፅናኝ መላእከትን ይላከልሽ 😭

  • @liyamebratu9694
    @liyamebratu9694 Před 3 měsíci +4

    በጣም ያሳዝናል እግዚአብሔር ያፅናት

  • @rutemekuria6093
    @rutemekuria6093 Před 3 měsíci +4

    ጌታ እየሡሥ ልብሽ ውሥጥ ገብቶ ያፅናናሽፀ ሌላ ምን ይባላል

  • @jamila8885
    @jamila8885 Před 3 měsíci +5

    እንካን ደህና መጣህ ኤልያስ

  • @messiessi3635
    @messiessi3635 Před 3 měsíci +2

    መቻያውን ይስጣት አይዞሽ ማለት እሷን አያፅናናም እግዚአብሔር ያፅናት የኔ እናት😢😢😢😢

  • @eyerusm5965
    @eyerusm5965 Před 3 měsíci +3

    እግዚአብሔር ፅናቱን ይስጣችሁ

  • @menbermaryam4971
    @menbermaryam4971 Před 3 měsíci +3

    ነፍሰ ይማር

  • @dawitetsegaye1472
    @dawitetsegaye1472 Před 3 měsíci +3

    እግዚአብሔር ያፅናሽ

  • @lemlemokay1348
    @lemlemokay1348 Před 3 měsíci +3

    እግዚአብሔር መፅናናቱን ይስጣት 😭😭😭

  • @kidistarsema6361
    @kidistarsema6361 Před 3 měsíci +4

    ኡፍፍፍፍፍፍፍፍ💔💔💔💔በልጅ አትፈትንኝ😭😭😭😭😭

  • @user-tz1hf4dl4j
    @user-tz1hf4dl4j Před 3 měsíci +5

    እግዚአብሔር ለንስሐ ሞት ያብቃን ነፍሱን በአፀደ ገነት ያኑረው።
    ኤልያስ ደግነት አቀራረብህ ልብ ይነካል 😢

  • @user-jl1oz8jm6k
    @user-jl1oz8jm6k Před 3 měsíci +2

    በጣም ያሳዝናል ወይኔ ምን ማለት ይቻላል የእግዚአብሔር ስራ ነው ነፍሱን ይቀበላት ለእናቱ ለቤተሰቦቹ መፅናናትን ይስጣቹ

  • @getit5763
    @getit5763 Před 3 měsíci +2

    ኤሊ አይዞህ በርታ

  • @SE-nr2ug
    @SE-nr2ug Před 3 měsíci +1

    ወይኔ የእኔ እናት እግዚአብሔር ፅናቱን ይስጥሽ 😭😭😭😭😭😭

  • @SamriBaba-fz3oj
    @SamriBaba-fz3oj Před 3 měsíci +4

    እውይ የኔ እናት በልጅ ሞት ተፈተንሽ? እግዚአብሔር አፅናኙን መልዓክ ይላክልሽ 😥💔

  • @naodgizaw1203
    @naodgizaw1203 Před 3 měsíci +3

    Zerituyee😢😢😢 geta yaberitash

  • @asfaw8154
    @asfaw8154 Před 3 měsíci +1

    በጣም ያሳዝናል እግዚአብሔር ያፅናሽ ነብስ ይማር

  • @user-xz3iy6ti5m
    @user-xz3iy6ti5m Před 3 měsíci +3

    Uuuuffffff faxari nabes yemar faxarin yabaretash😢😢😢😢😢😢

  • @tsedeygebru5667
    @tsedeygebru5667 Před 3 měsíci +3

    የመረጥሽው ያመንሸው እግዚአብሔር ያፅናናሽ እንጂ በሰው አይቻልም።

  • @hanazwedu5503
    @hanazwedu5503 Před 3 měsíci +3

    Yena enat mn yebalale egziabhar awaki nw esu yasenashe betam kebad nw

  • @sarayayi6928
    @sarayayi6928 Před 3 měsíci +3

    uuuuffff.egezabehr.yatsenash.😭😭😭😭💔💔💔

  • @kurymengesha3926
    @kurymengesha3926 Před 3 měsíci

    ፈጣሪ ያፅናሽ መቼም ምን ቃል ለአንቺ ያበረታሽ ይሆን

  • @HemenNatan
    @HemenNatan Před 3 měsíci

    እመቤቴ ማርያም ታጽናናሽ ጌታ ሆይ በልጅ አትፈትነኝ

  • @askalebirkineh7068
    @askalebirkineh7068 Před 3 měsíci

    መላው ቤተሰብ እግዚአብሔር ያፅናቸው

  • @user-vn1vs8xz3s
    @user-vn1vs8xz3s Před 3 měsíci

    እግዚአብሔር ፅናቱን ይስጥሽ

  • @ChrisHiwot
    @ChrisHiwot Před 3 měsíci +1

    Ufffff yamal yamal 😢egziabeher metsenanatun yesetesh😢

  • @yared7699
    @yared7699 Před 3 měsíci

    ወይኔ እህቴን እግዚአብሔር ያፅናሽ። ራሱ ከላይ አፅናኙ ይላክልሽ ክፉ ምን አይብሽ።

  • @enataleme375
    @enataleme375 Před 3 měsíci +1

    እግዚአብሔር ያፅናሽ የኔ እህት ኡፍፍፍፍ 😭

  • @saradesign9507
    @saradesign9507 Před 3 měsíci

    ነብስ ዮማር ለቤተሰብም መፅናናትን ያድላችሁ

  • @Crstina246
    @Crstina246 Před 3 měsíci

    ኡኡኡኡፍ ያማል በጣም እግዚአብሔር መጽናናትን ይስጥሽ😭😭😭😭

  • @yeabkonjoo6285
    @yeabkonjoo6285 Před 3 měsíci +1

    ዘሪቱዬ የእ/ር ጉልበት ነው የሚያፅናናሽ ደሞ እሱ አይተውሽም ሩህሩህ አባት አለሽ የሚሆነውን የሚያቅ እሱ ነው ደሞ ማን ለምን ይለዋል አዋቂ ነው የኔ እህት እ/ር አላቅም ልብሽን ይይያዘው ስለሚችል ቃል የለኝም የምለው ልጄ ነፍስህን በአፀደ ገነት ያኑራት ዘሪቱዬ በዚች ሰጠት ምን እየተሰማሽ ይሆን ማሰብ ያቅታል ያፅናሽ እህቴ😢😢😢😢😢

  • @hanatesseme9170
    @hanatesseme9170 Před 3 měsíci +1

    እግዚአብሔር አምላክ ያፅናቹ

  • @mehretkassa6041
    @mehretkassa6041 Před 3 měsíci

    የልጅ ሞት ለማንም አይስጥ 😢😢😢የእውነት እግዚአብሔር አምላክ መፅናናቱን ያድል ነብስህ በሰላም ትረፍ😢😢😢

  • @gziachewzeleke9180
    @gziachewzeleke9180 Před 3 měsíci

    እግዚያብሄር ያጽናት!!!!!!

  • @kerojiwolde3431
    @kerojiwolde3431 Před 3 měsíci

    እግዚአብሔር ፅናቱን ይስጣት😔

  • @Hana-3838
    @Hana-3838 Před 3 měsíci +1

    እግዚኦ የብኩር ልጅዋን ወይ ወላድ የወለደ ያቀዋል የሧን ሕመም ጌታ ያቀዋል ያማል ነፍስ ይማር ወይኔ እናትነት 💔💔😭😭

  • @YIDNKESlSAY-hy2yy
    @YIDNKESlSAY-hy2yy Před 2 měsíci

    እናት እኮ የሚያፅናናት ቃል የለም ከልጂ መክራ ይሰዉራችዉ ከባድ ነዉ

  • @user-vn1vs8xz3s
    @user-vn1vs8xz3s Před 3 měsíci

    እንኳን በሰላም መጣህ ዩቱብ ቻናልህንም እንኳን በሰላም ተመለሰልህ ጋዜጠኛ ኤልያስ ደግነት

  • @ayni5236
    @ayni5236 Před 3 měsíci

    እግዚአብሔር ያፅናሽ እህቴ

  • @user-tz4pg5dn1h
    @user-tz4pg5dn1h Před 3 měsíci +1

    እግዚአብሔር ያጥናሽ 😢😢😢😢😢

  • @freweynimengesha8246
    @freweynimengesha8246 Před 3 měsíci +3

    Ehzyabeher nesuni yemari fetari yasenachu

  • @user-nt7gt6xt6s
    @user-nt7gt6xt6s Před 2 měsíci

    Kal yelegnim Egziabher yaxnashe

  • @alemkebede5848
    @alemkebede5848 Před 3 měsíci

    በጣም ያሳዝናል ፈጣሪ ነፍሱን ይማረው ለእናቱ ለጓደኞቹ ለወዳጅ ዘመድ ሁሉ ፈጣሪ መጽናናትን ይስጥ።

  • @markiyaeshetue6586
    @markiyaeshetue6586 Před 3 měsíci +1

    💔💔

  • @selammoges4277
    @selammoges4277 Před 3 měsíci

    Egzabher yatnasche ehetalem

  • @user-oc3vx4wx1c
    @user-oc3vx4wx1c Před 3 měsíci +1

    😭😭😭😭

  • @narditube4378
    @narditube4378 Před 3 měsíci +3

    አምላኬ አንተ አጽነት ኡፍፍፍፍ

  • @sabahailemikael2425
    @sabahailemikael2425 Před 3 měsíci

    Wye wey Egzabehare yatinachehu!
    Ejge betame yamale😢😢😢

  • @fifinegash3816
    @fifinegash3816 Před 3 měsíci

    Nefs yemar 😭😭😭😭🙏

  • @DaneilTadesse
    @DaneilTadesse Před 3 měsíci

    ኤላ❤❤❤❤

  • @znegnkewollo9887
    @znegnkewollo9887 Před 3 měsíci

    yareb belij ayfetnen allah seber yesetsh yene ehet

  • @hanafetsum5939
    @hanafetsum5939 Před 3 měsíci

    Egzabhre tsnatune yeseteshe betame yasznale

  • @tufutd1991
    @tufutd1991 Před 3 měsíci +1

    إنا لله وإناإ ليه رجعو ن💔

  • @asemerttilahuntilahun5225
    @asemerttilahuntilahun5225 Před 3 měsíci +1

    ይህው እግዚአብሄር ሊያስተምራት ነው የወሰደባት በእምነት እያሹፈች አልነበር(ትቀልድ)ነበር እሱን እግዚአብሄር ስለሚወደው ነው

    • @yared7699
      @yared7699 Před 3 měsíci

      አትፍረድ ይፈረድባሃል በተናገርከው ቃል ትያዛለህ።

  • @ZahraZahra-gg1he
    @ZahraZahra-gg1he Před 3 měsíci

    Rely sorry

  • @lilyadmasu9976
    @lilyadmasu9976 Před 3 měsíci

    በእውነት ይህ ዜና እውነት ነው??? ምክንያቱም ሌላ ሚዲያላይ አላየሁትም

  • @mahletsemere4492
    @mahletsemere4492 Před 3 měsíci

    😭😭😭😭😭😭😭

  • @getit5763
    @getit5763 Před 3 měsíci +1

    ኤላ ሌላ ዮትብ አለህ እንዴ 10 k ያለው የአንተ መስሎኝ ነበር አስተያየት መስጫው የተዘጋ ነው

    • @gizemedia1974
      @gizemedia1974  Před 2 měsíci

      www.youtube.com/@AddisGize-Media
      ይሄ ከሆነ ሌላኛው ቻናላችን ነው

  • @user-qp7jz6pi5p
    @user-qp7jz6pi5p Před 3 měsíci

    ከልጅዋ ጋር ያሳለፈችውን ወርቃማ ጊዜያቶች በማሳብ ፀናቱን ፈጣሪ መጠንከሩን ያድላት ዘንድ ከልብ እመኛለሁ
    መቻሉን ያድልልን!!!

  • @user-rw4og1cy3l
    @user-rw4og1cy3l Před 3 měsíci

    yene enat egiziabiher tsinatun yisitsh

  • @senaitmichael5978
    @senaitmichael5978 Před 3 měsíci

    😭😭😭😭😭😭😭🥱

  • @user-hw6dx3wi4x
    @user-hw6dx3wi4x Před 3 měsíci +4

    እግዚአብሔር ፅናቱን ይስጣችሁ

  • @emebetreda3149
    @emebetreda3149 Před 3 měsíci +3

    ነፍስ ይማር

  • @DaneilTadesse
    @DaneilTadesse Před 3 měsíci

    😢😢😢😢

  • @user-hw6dx3wi4x
    @user-hw6dx3wi4x Před 3 měsíci +4

    ነፍሰ ይማር