ደስየሚለኝ ነሽዳ

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 25. 08. 2024

Komentáře • 13

  • @zuzumchale
    @zuzumchale Před rokem

    ተስፋ ይኑርህ !
    ሁሌም የምናገኘው ውጤት የለፋንበትን እና አብዝተን የጠየቅነውን እንዲሳካልን ዱዓ ማድረግ ነው በዚህ ሁኔታ ታድያ ተስፋ መቁረጥ የሚባል ነገር በፍፁም አያስፈልግም ፤ ምላሹ ሊዘገይ ቶሎ ላይሰጥ እናም የማይሳካ መስሎ ሊሰማ ይችላል ግን ህልማችን ተስፋ ሳንቆርጥ ከልባችን ከታገልንለት ይዘግይ እንጂ እውን ይሆናል ከቆምንም ቆሞ ይቀራል ስለዚህ ወደኋላ ማለት አይፈቀድም ሁሉም ነገር ወደፊት ይሆናል!

  • @lubetuber
    @lubetuber Před rokem

    አሰላምአለይኩም ወራህመቱላሒ ወበረካትሁ አህለን ፊኪ አላህዬ ሰለሰጠኸኝ ፀጋ ሁሉ አልሃምዱሊላህ ያወድውድ

  • @RahatulQelb
    @RahatulQelb Před rokem

    አሰላማለይኩም ወራህመቱላህ ወበረካትሁ አላህ እህቴ እኳን ሰላም መጣሽ ባለሽበት ሰላምሽ ብዝት ይበልልኝ አላህ ሀገራችን ሰላም ያድርግልን ሰላም ፍቅር አንድነት ይወፍቀን

  • @user-ik3ue4ny3e
    @user-ik3ue4ny3e Před rokem

    ማር

  • @toybatube
    @toybatube Před rokem

    አሠላሙአለይኩም ወራህመቱላሂወበረካትሁ አህለን

  • @user-ik3ue4ny3e
    @user-ik3ue4ny3e Před rokem

    አህለንንን

  • @sofiay4194
    @sofiay4194 Před rokem

    🌹#ያአላህ 🤲🌹ድክመታችንን #ስህተታችንንም ሁሉ አንተ ጠንቅቀህ ታውቃለህና 🌹ያረብ🤲 #ወደማንችለው🌹 #ፈተና #አታስገባን !!! ያራህማኑ ያረሂሙ🌹ያረብ አገራችንን አንተ ሰላም አርግልን Ethiopia #ሰላሟን አብዛልን🌹 አሚን🤲ያረብ🌹 ።
    🌹#ተወዳጅና ተናፋቂ ውድ ሙስሊም #እህት_ወንድሞቼ 🌹፣ ለእህት ወንድሞቻችን👉ማስደሰት ካልቻልን #አናስከፋቸው🌹፣ #መጥቀምም ካልቻልን በሸይጧን ታግዘን ተታለን #አንጉዳቸው 🌹፣ #ማፍቀርም ካልቻልን #አንጥላቸው🌹እርስ በእርስም 🌹 ስህተታችንን መመካከር #መምከር ካልቻልን #አንማቸው 🌹 👍

  • @emumalik6718
    @emumalik6718 Před rokem

    አሠላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁባንቱ እኮ ነው
    ከጤዛ እንክብል የምታንስ እውቀቴ
    ከሰማይ ስባሪ ገዝፋ የታየችው
    ከዚህ ግቢ ማይሏት እንጭጯ ብልሃቴ
    በጠቢባን ሚዛን የተመዘነችው
    ወንጀል ዘሃ አዝግቶ የሸመናት ነፍሴ
    ፃዲቅ መስላ ታይታ የተወደሰችው
    እንደ ጃርት ገላ የሾከች ሃለቴ
    ሐር ነዶን አልፋ የተሞካሸችው
    አስመስየ እንደ አጥሪ ስቼ እንደ አሳማሪ
    ሰርቄ እንደ ታማኝ በድየ እንደ ማህሪ
    ቀጥፌ እንደ ብፁዕ ክጄ እንደ መካሪ
    በርግጌ እንደ ገስጋሽ፣ ነፍጌ እንደ ለጋሽ
    ባልሰለፍኩት ወረት ምታይ እንደ ደጋሽ
    ሳይዘልቅ ማንነቴ በጭፍን ተሞጋሽ
    እንደ ባህር ማሽላ ተሸፍኖ ነውሬ
    ባልሆንኩት ባልዋልኩት ልክ መቆጠሬ
    ባንቱ እኮ ነው ነቢ መድመቄም ማማሬ
    صلى الله عليه وسلم
    جمعية المشاريع الخيرية الإسلامية

  • @user-rn9dh4uo8e
    @user-rn9dh4uo8e Před rokem

    አኺራችንን እናስቀድም
    * ልጅ ሆይ! ስለ ወላጅ ሐቅ ክብደት ሲነገር አይክበድህ። የወላጅን ሐቅ በመጠበቅ ከወላጅ በላይ የሚጠቀመው ልጅ ነው።
    * ሚስት ሆይ! ስለ ባል ሐቅ በተደጋጋሚ ሲነገር አይደብርሽ። የባልን ሐቅ በመጠበቅ ከባል በላይ የምትጠቀመው ሚስት ናት።
    * ባል ሆይ! ስለ ሚስት ሐቅና ኃላፊነትህን ስለ መወጣትህ ሲነገር አትሰላች። የሚስትን ሐቅ በመጠበቅ ከሚስት በላይ የሚጠቀመው ባል ነው።
    ~ ማንም ቢሆን በፈጣሪው የተጣለበትን ሐቅ ቢወጣ ከሚያከብረውና ከሚንከባከበው አካል በላይ የሚጠቀመው እራሱ ነው። ደግሞም በፈጣሪ የተጣለብንን አደራ ለመወጣት ሲያደርጉ እናደርጋለን፣ ሲተው እንተዋለን ዓይነት የ 'ሰጥቶ መቀበል' ሂሳብ ውስጥ መግባት የለብንም። አባትህ ቢበድልህ የበደል ሂሳብ ውስጥ አትግባ። በወንጀል እስካላዘዘህ ድረስ በምትችለው ከጎኑ ሁን። ከሌሎችም አንፃር እንዲሁ።
    አላህ ነፍስያችንን ረግጠን ለትእዛዙ የምናድር ያድርገን!!! አሚን አሚን 🤲

  • @sw9jm3tc7w
    @sw9jm3tc7w Před rokem

    ለሆነ ጥናት ተብሎ እናቶች ወደ አንድ ማዕከል ተጠሩ።
    ከፊሎቹ ሴት፣ ከፊሎቹ ወንድ ልጆቻቸው ጋር ነበር የሚኖሩት። ያመጧቸዉም ያላገቡ ሴት እና ወንድ ልጆቻቸው ነበሩ።
    አንዲት ነርስ እናቶቹን ዞራ ካየቻቸው በኋላ "አንችን ወንድ ልጅሽ ነው ያመጣሽ፣ አንችን ደግሞ ሴት ልጅሽ ናት ያመጣችሽ።" ትልና "አይደል እንዴ?" ብላ መልሳ ትጠይቃቸዋለች። እነርሱም ትክክል እንደሆነች ያረጋግጡላታል።
    ነርሷ በምን መነሻ እንዲህ እንዳለች አላስተዋልኩም ነበርና ወደርሷ ጠጋ ብዬ 'እንዴት ልታውቂ ቻልሽ?' አልኳት።
    "አየህ አለችኝ ወደ አንዲት እናት እያየች። ሴት ልጅ ያመጣታቻት እናት ሙሽራ ነው የምትመስለው፣ በደንብ አልብሳ፣ አሳምራ እና ኩላ ነው የምታመጣት። ወንድ ልጇ ያመጣት ግን ለየት ያለ ነገር አይታይባትም፣ እሷ ራሷን ካልተንከባከበች በስተቀር። ወንድ ልጇ 'እማዬ እባክሽ ያገኘሽዉን ልበሽና እንውጣ' ብሎ አጣድፎ ሊያመጣት ሁሉ ይችላል።
    በቀደም በቅርቡ ነበር ይህን ነገር የታዘብኩት። ከወንድ ልጆቻቸውና ከሴት ልጆቻቸው ጋር የሚኖሩ እናቶች የእንክብካቤ ሁኔታ ይለያያል እንደማለት።

  • @fafiwollotube
    @fafiwollotube Před rokem

    አስገራሚ እውነተኛ ታሪክ " !!
    ኢብኑ ዑሰይሚን እንዲህ አሉ ፡-
    🔻 - አንድ የማምነው ሰው እንዲህ ሲል አወራኝ ፡
    የሆነ ሰው ነበር ሚስቱ ለማንኛውም ቤት ቆርቁሮ ለሚለምን ሚስኪን ዳሀ ምንም አይነት ነገር እንዳትሰጭ ብሎ ይከለክላት ነበር ፡፡
    🔻ከዕለታት አንድ ቀን የሆነ ዳሀ ሚስኪን ቤቱን ይቆረቁራል ፡ ከዚያ ሚስት ቤቱን ስትከፍት ይህ ሚስኪን እንዲህ አላት ፡ እመቤቴ እባክሽን የምለብሰው የሌለኝ እርቃን ነኝ ከብርድ ራሴን የምከላከልበት ልብስ የሌለኝ ሰው ነኝ ? ባላት ጊዜ ፡ ይች የዚህን ሚስኪን ሁኔታ ያየች ሚስት አላቻላትምና ከቤቷ ውስጥ በመመለስ ልብስ እና ሶስት ተምሮችንም ጭምር ሰጠችው እና ሄደ ፡፡
    🔻የዚች ሴት ባለቤት መስጂድ ውስጥ ተኝቶ ነበር ፡ ይህ ባሏ በህልሙ ልክ ቂያማ ስትቆም ያያል ! ሰዎች ሁሉ ትርምስምሳቸው ወጥቷል ! ሰወች በጣም ብርቱ በሆነ የፀሃይ ቃጠሎ ውስጥ ናቸው ! ልክ ይሄን አስደንጋጭ ክስተት እየተመለከተ ሳለ ከበላዩ የሆነ ልብስ ከዚህ ከፀሃይ ቃጠሎ ይከልልለታል ፡ ግና ይህንን ልብስ ሶስት ቦታ ተሸነቋቁሮ ያየዋል ፡ ከዚያም የሆኑ ሶስት ተምሮች መጥተው እነዚህን ሶስት የሽንቁር ቀዳዳ ቦታወች ሲደፍኑት ተመለከተ ፡ በጣም ተገረመ ፣ ተደነቀ በዚህ ህልም ፡ ወዲያው ከእንቅልፉ ባነነ እና በድንጋጤ ወደ ቤቱ በፍጥነት በማምራት ያየውን ህልም ሙሉውን ለሚስቱ ተረከላት ፡ ሚስትም ይህ ህልም በእነዚያ በሰጠቻቸው ልብስና ተምሮች ሰደቃ ምክኒያት መሆኑን ስለለተረዳች ፡ ያ ሚስኪን ዳሀ ቤት መጥቶ የሰጠችውን ልብስና ሶስት ፍሬ ተምሮች ነገረችው ለባሏ ፡
    ከዚያም እንዲህ አላት ፡ አደራ ከዚህ ቡሀላ አንድንም ዳሀ ከደጄ እንዳትመልሽ ፡፡
    ☞ ይህ ሰው አሏህ አነቃው ፡ ይሄም ክስተት ነብዩ (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) የተናገሩትን ሃዲስ ያስመሰክራል ፡
    🔻ነብዩ (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይለሉ፡- የቂያማ እለት አሏህ በሰዎች መካከል ፍርድ እስኪሰጥ ድረስ ሁሉም ሰው ከሰደቃው ጥላ ስር ነው የሚጠለለው ፡፡
    📚ምንጭ፡- ሸርሁ ኪታብ አል ረቃኢቅ ከሶሒህ አል ቡኻሪ (ገፅ/6)
    ✔ኢብነል ቀይም እንዲህ አሉ፡-
    ☞- ሰደቃ የአደጋ አይነቶችን የመከላከል ልዩና አስገራሚ ተፅዕኖ አለው ፡ ከአረመኔ ወንጀለኛ እና ከግፈኛና በደለኛ እንዲሁም ከካፊር ቢሆንም እንኳን ፡፡
    ☞ አሏህ በዚች በሰደቃው አማካይነት ከተለያዩ አደጋወች ይከላከልለታል ፡፡

  • @user-rn9dh4uo8e
    @user-rn9dh4uo8e Před rokem

    አኺራችንን እናስቀድም
    * ልጅ ሆይ! ስለ ወላጅ ሐቅ ክብደት ሲነገር አይክበድህ። የወላጅን ሐቅ በመጠበቅ ከወላጅ በላይ የሚጠቀመው ልጅ ነው።
    * ሚስት ሆይ! ስለ ባል ሐቅ በተደጋጋሚ ሲነገር አይደብርሽ። የባልን ሐቅ በመጠበቅ ከባል በላይ የምትጠቀመው ሚስት ናት።
    * ባል ሆይ! ስለ ሚስት ሐቅና ኃላፊነትህን ስለ መወጣትህ ሲነገር አትሰላች። የሚስትን ሐቅ በመጠበቅ ከሚስት በላይ የሚጠቀመው ባል ነው።
    ~ ማንም ቢሆን በፈጣሪው የተጣለበትን ሐቅ ቢወጣ ከሚያከብረውና ከሚንከባከበው አካል በላይ የሚጠቀመው እራሱ ነው። ደግሞም በፈጣሪ የተጣለብንን አደራ ለመወጣት ሲያደርጉ እናደርጋለን፣ ሲተው እንተዋለን ዓይነት የ 'ሰጥቶ መቀበል' ሂሳብ ውስጥ መግባት የለብንም። አባትህ ቢበድልህ የበደል ሂሳብ ውስጥ አትግባ። በወንጀል እስካላዘዘህ ድረስ በምትችለው ከጎኑ ሁን። ከሌሎችም አንፃር እንዲሁ።
    አላህ ነፍስያችንን ረግጠን ለትእዛዙ የምናድር ያድርገን!!! አሚን አሚን 🤲