ካሲናው ጎጃም | አስቻለው ፈጠነ (አርዲ) | Aschalew Fetene (Ardi) | New Ethiopian Music 2023 (Official Video)

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 11. 05. 2023
  • ካሲናው ጎጃም
    ______________
    ግጥም: አስቻለው ፈጠነ (አርዲ) ሐይለ እየሱስ ደርብ የህዝብ
    ዜማ: የህዝብ ዋሽንት: አይችሉህም መንግስቴ
    ከበሮ: ሐገረሰላም ሻፊ
    መሰንቆ: እንድሪስ ሐሰን አረሒት : እየሩስ መለሰ
    አድማቂ: መላኩ ታረቀኝ
    ተቀባይ: አማኑኤል አሊ: አሳየ ፈንቴ: ክንፈገብርኤል ክንዱ :ተፈሪ አሰፋ
    ጋፈርና ግሪፕ: አበበ ከፈለኝ፣ ዳግማው አበበ
    ረዳት ካሜራ: የአብስራ ደሳለኝ
    ፕሮዳክሽን ዲዛይነር: ሄለን ብዙነህ
    ፕሮዳክሽን አስተባባሪ: አከለ መሰለ
    ፕሮዳክሽን ማናጀር: ዮናስ አብርሀም
    ሲኒማቶግራፈር: ፍስሀፅዮን ንብረት
    ከለር: ሮሀ ስቱዲዬ
    ኤዲተርና ዳይሬክተር: ሰውመሆን ይስማው
    ፕሮዲዩሰር: ብርቧክስ ሪከርድስ
    ----------------------
    ልዩ ምስጋና
    ለዲማ እና አካባቢው ነዋሪዎች
    ግንቦት 4/2015 ዓ/ም
    --------------------
    ካሲናው ጎጃም ግጥም
    ----------------------------
    መላየ ነይ መላ አለው መላ መላ (3)
    አቴ መላ ዘውዴ ዘውዴ (3)
    የአንችው ማሽላ ነው ዘውዴ
    የእኔ አዝመራ ስንዴ ዘውዴ
    እቴ መላ ዘውዴ
    ሐገራችን ጎጃም ዘወዴ (ወንዛችን አባይ)2
    እንደመስቀሏ ወፍ ዘውዴ (ብቅ አትይም ወይ)
    ግምባሯን ቶ መስቀል ዘወዴ (የተነቀሰችው )2
    ያያ ወንድአለን ልጅ ዘውዴ (ነብሮን አገባችው
    የዳጉሳ ጠላ የለውም ዘውዴ( የለውም ቅራሪ)
    አሁን ገና መጣች ዘውዴ (አስኳላ ተማሪ)2
    ዳማይ አንችን ነው ዳማየ (2)
    እናት ወልዳ ወልዳ ዳማየ
    ስም ማውጣት ታውቃለች ዳማየ
    የመጀመሪያውን ዳማየ
    በላይ ትለዋለች ዳማየ
    ደግሞም አስቀጥላ ዳማየ
    ሽፈራው ትላለች ዳማየ
    ደሞም አስቀጥላ ዳማየ
    ባንችዋ ትላለች ዳማየ
    የማሳረጊያዋን ዳማየ
    ይጋርዱሽ ትላለች ዳማየ
    ዳማይ አንችን ነው ዳማየ (2)
    ሎሚተራ ተራ ዎ (4)
    እናቴን አደራ
    አሸበል ገዳየ አሐው ገዳየ
    አይናማው ገዳየ አሐው ገዳየ
    ሻየ ገዳየ አሐው ገዳየ
    አታሞው ሲመታ አሐው ገዳየ
    መሬቱ አረገደ አሐው ገዳየ (2)
    ያያ ኩታ ለብሶ አሐው ገዳየ
    ዝናብ አወረደ አሐው ገዳየ(2)
    ድግሱ አማረላት አሐው ገዳየ
    እመ ተመናሸች አሐው ገዳየ
    ታተይ ተመናሸች አሐው ገዳየ
    መቀነቷን ታትቃ አሐው ገዳየ
    ዋንጫ ለቀለቀች አሐው ገዳየ(2)
    ያዋልዳል በሬ( ያዋልዳል ላም)2
    የእናጅሬው አገር እንዴት ነው ጎጃም
    ድግሱን ደግሶ( አይነግርም አዋጅ)2
    መንገደኛው ሁሉ ሰተት ነው እንጅ
    ምንኛ ደግ ነው( የእዜሩ በረከት)2
    በውሀም አይደለ በቅምጫና ወተት
    ጋኑን እጠኝና (በጋምቢሎ ጭስ)2
    በጥብጠሽ ጠብቂኝ ገምበሀ ስደርስ
    ኩራትሽ (5)ራትሽ
    ዶቅማ መቅመስሽን አወቅሁ በምላስሽ
    ደልቂ (6)
    እኔ እያለሁልሽ እንደ ፀሐይ ሳቂ
    ደልቂ(6)
    አማቶችሽ ዘንዳ መጠሽ ተመረቂ
    ያለ ዛሬ ቤቴን (አታውቀውም ብሎ)2
    ጠሪ አክባሪ ድሷል አቆልቋይ አክሎ
    ባለጌታው ባይሸሽ አብየ ሰንደቁ አርበኛው ሰንደቁ
    ገና እንደፎከረ ጠላጦች ወደቁ
    ፍጥረት መጀመሪያው የአፍላጋት መፍለቂያ
    የዬቶር ሞገድ
    ካሲናው ጎጃም ነው ምድሪቱ ምጣድ
    ደልቂ (6)
    ከሽማግሌ እግር ወድቀሽ ተመረቂ
    ደልቂ (6)
    እኔ እያለሁልሽ እንደ ፀሐይ ሳቂ
    ---------------------------
    ካሲናው ጎጃም | አስቻለው ፈጠነ (አርዲ) | Aschalew Fetene (Ardi) | New Ethiopian Music 2023 (Official Video)
    ---------------------------
    #kasinawugojam
    --------------------------
    Check Out New Ethiopian Entertainment Videos
    by Subscribing @Birbaux Records.
    #BirbauxRecords. #SewMehonFilms #EthiopianMusic #gonder
    unauthorized use, distribution, and re-upload of this content is strictly prohibited
    Copyright ©Birbaux Records. SewMehon Films
  • Hudba

Komentáře • 4,5K

  • @BirbauxRecords.SewMehonFilms

    የሲኒማ ፊልሞችን ብቻ የምታገኙበት ቻናል ከፍተናል ሰብስክራይብ በማድረግ ይዝናኑ
    czcams.com/channels/EPcsTOYImrARzNOV0I2iPQ.html

  • @robelhaile4212
    @robelhaile4212 Před rokem +2517

    እኔ ኤርትራዊ ነኝ። የአማራ ህዝብን ሞቼ ነው የምወዳችሁ። ታማኝ፣ ጀግና፣ ፍቅር፣ ሰው አክባሪ፣ አገሩን የሚወድ ህዝብ ስለሆነ፣ ሞቼ ነው የምወደው። I love you Amhara people. Peace!!

  • @fish618
    @fish618 Před rokem +2156

    እኔ ትግሬ ነኝ ፤ከአማራ ጋር ሁሉም ነገራችን አንድ ነው
    ሰላም ለአማራ እና ትግራይ❤❤❤

    • @Markm-tj9hi
      @Markm-tj9hi Před rokem +68

      ሰላም ለሁለቱ ወንድማማች ህዝቦች። በሁለቱ ፀብ ለሚያተርፋት ልቦና ይስጣቸው።።።

    • @eskedartessema6318
      @eskedartessema6318 Před rokem +47

      ትክክል እኛ አንድ ነን

    • @doilasomohammed6776
      @doilasomohammed6776 Před rokem +38

      ትላንት እንዲህ አትልም ነበረ

    • @sameramohammad-iz1jj
      @sameramohammad-iz1jj Před rokem +17

      ሠላምለሁላችን❤💛💕💚💛❤🕊🕊🕊🕊

    • @ber_tube
      @ber_tube Před rokem +42

      እንደ አንተ ያሉትን አምላከ እስራኤል ያብዛልን

  • @Mimi-ex4si
    @Mimi-ex4si Před rokem +552

    የጉራጌ ተወላጅ ነኝ አማራን ሳስበው እንባዬ ይቀድመኛል ልእናንተ ደስታ እንጅ ሀዘን አይገባችሁም መልካም የዋህ ህዝብ አማራ እግዚአብሔር ዘራችሁን ይብርክ የኢትዮጵያ አለኝታዎች ❤️

    • @sadaahmed2576
      @sadaahmed2576 Před rokem +8

      አሜንን❤

    • @meseretgetawedey
      @meseretgetawedey Před rokem +6

      የኔ ማር❤❤❤

    • @gabigebreal7620
      @gabigebreal7620 Před rokem +5

      Gurage ye Ethiopia Ye Sira Meseret Ye Amhara Menta Hizib NURULIN , Meles ayinu yifises " Giligelu Nefitegna " Yalachu Bekurat Awo Ke Amhara Gone Be Jegininetum , Be sirawum , Be Ethiopia💚💛❤💪 fikirim silemititaweku new , BERTU WENDIMOCH YALIFAL💪💪💪
      Amhara + Gurage = TALAKITUA ETHIOPIA 💚💛❤💪💪💪

    • @kassahunmeaza963
      @kassahunmeaza963 Před rokem +10

      እኛም ጉራጌን በጣምነው የምንወደውአስተዳደጋችሁ በስርአት ያለዘረኝነት እንዳደጋችሁ ያስታውቃል ዘረኞች አይደላችሁም ሚዲያላይወታችሁ ኢትየጵያን አትሰድቡም አማራን አትሳደቡ ምችትይበላችሁ አሜን የናንተም ይባረክ ኢትዬጵያን ትወዳላችሁ 💚💛❤🇩🇪

    • @Mimi-ex4si
      @Mimi-ex4si Před rokem +3

      @@kassahunmeaza963 ደማችን ናችሁ 🥺

  • @edeneden5251
    @edeneden5251 Před rokem +213

    እኔ ኦሮሞ ነኝ አማራ በአሉ እምነቱ ሀገር ወዳድነቱ ሁሉ ነገሩ በጣም ነዉ የሚገረመኝ ዘረኝነት ጎጠኝነት የለበት ምርጦች

    • @almazmekonnen9069
      @almazmekonnen9069 Před rokem +2

      ክብረት ይስጥልን!!!!

    • @edenkumela8434
      @edenkumela8434 Před rokem +2

      እውነት ነው ❤❤❤❤❤❤❤❤

    • @abelcrazy6472
      @abelcrazy6472 Před rokem +1

      እናመሰግናለን ወደ አንድነታችን እንመለሳለን በቅርቡ💚💛❤️

    • @meseret5
      @meseret5 Před 11 dny

      እናመሠግናለን

  • @Habibatube
    @Habibatube Před rokem +1081

    ግሩም ነው የኔ ህዝብ አማራዬ 💚💛❤ ይሄ ድንቅ ሥራ በወሎ እና በሸዋ ይደገም የምትሉ ላይክ👍 አድርጉማ 🥰🥰

  • @mearg83
    @mearg83 Před rokem +619

    ትግራዋይ ነኝ የአማራ ባህላዊ ዘፈንና ጭፈራ ሊያሳብድኝ ነው ! ስወዳቹ ሰላማቹ ይብዛ እወዳቸዋልሁኝ !

    • @meseretgetawedey
      @meseretgetawedey Před rokem +11

      እናመሰግናለን ወድማለም ህዝባችን አንድነቱን ያምጣል❤❤❤

    • @nurilgnbirhanu-official4943
      @nurilgnbirhanu-official4943 Před rokem +6

      sinwaded yamrbnal

    • @amhiara
      @amhiara Před rokem +3

      ❤❤

    • @alemalehenig7350
      @alemalehenig7350 Před rokem +5

      እናመሠግናለን ወንድማችን

    • @selamawitgebretsadik3097
      @selamawitgebretsadik3097 Před rokem +20

      አማራ ነኝ ወንድምአለም ሰሜናዊ አንድ ቤተሰብ ነን ፖለቲከኞቹ አባሉን እንጂ እኛ አንድ ከሆንን የኢትዮጵያ ታላቅነቷ ገናናነቷ ወደ ቀድሞው ይመለሳል ።

  • @serebodolicho7062
    @serebodolicho7062 Před rokem +241

    እኔ ሀዲያ ነኝ አማራን የእውነት ከልቤ ነው ምወዳቸው ❤❤❤❤

  • @BilalBileyel-cq1yw
    @BilalBileyel-cq1yw Před 8 měsíci +78

    እኔ ደሞ አፋር ነኝ ግን ይሄን ዘፈን ስሰማ ዝለል ይለኞል ወላሂ ከጎጃምጋ ልጆች ጋር ብጨፍረው ምን ያህል ደስትተኞ ነኝ

  • @samiraali8482
    @samiraali8482 Před rokem +587

    አደኛ ነኝ እኔም የጎጃም ልጅ ነኝ ደስ ብሎኛል የትናችሁ ጎጃሜወች እስኪ ኑልያችሁ🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹❤❤❤❤❤

  • @user-kn9gh4ue8l
    @user-kn9gh4ue8l Před rokem +553

    ግጥም 100%
    ዜማ 100%
    ባህል 100%
    ማንነት 💚💛❤እዉነት 💚💛❤አማራነት 💚💛❤

  • @zx9713
    @zx9713 Před rokem +30

    እኔ የአዲስ አበባ ተወላጅ ነኝ አማራን ግን በጣም ነዉ እምወዳችዉ እምነታችዉ ሀገር ወዳድነታቸዉ ኩሩ እና ጀግና ህዝብ ናቸዉ i love you amara😘😘😘😍😍💚💛❤💪💪💪💪💪💪

  • @guzotube7855
    @guzotube7855 Před rokem +53

    I am from Namibia, I love Amahara culture ❤❤❤

  • @user-te7ic6bu1s
    @user-te7ic6bu1s Před rokem +405

    ጎጃም ጎንደር ወሎ ሽዋ አንድ አማራ(ፋኖ)❤

  • @akjulan7084
    @akjulan7084 Před rokem +497

    እኔ የአዲስ አበባ ልጅ ነኝ ግን ወላሂ የአማራ እናቶች እና አባቶች ሳያቸው እንባዬ ይፈሳል ከዚህ በፊት የተፈጠረው ሳስበው ምስኪን ጀግኖች ገበሬዎች ❤❤❤🙏🙏🙏

    • @user-lp6ke7nf5n
      @user-lp6ke7nf5n Před rokem +3

      ❤❤❤❤

    • @santasis
      @santasis Před rokem +20

      Same here bro my father is oromo but I would die for amhara people

    • @nardosmulugeta2619
      @nardosmulugeta2619 Před rokem +2

      @@santasis ገና አንተንም እንጨምረሀለን

    • @akjulan7084
      @akjulan7084 Před rokem +1

      @@santasis 🇪🇹🇪🇹🇪🇹👏👏👏

    • @ermiasabraham3950
      @ermiasabraham3950 Před rokem +3

      አቃጣሪ ሁሉም እናት አንድ ነው ምንድነው ያማራ እናት የሚለያት ? አንተ ምናልባት የማንነት ቀውስ ስላለብህ ይሆናል አሳፋሪ

  • @user-oj7sx8xl1s
    @user-oj7sx8xl1s Před rokem +63

    አማራ ማለት ኢትዮጵያ ❤ ኢትዮጵያ ማለት አማራ ነው 😘👈
    አምላክ ኢትዮጵያን ይጠብቅልን❤

  • @chd44444
    @chd44444 Před rokem +60

    የኔ የዋህ ደግ ህዝብ አማራዬ አይዞን ይሄም መከራ ያልፋል❤❤❤😢

  • @kifleabebew9568
    @kifleabebew9568 Před rokem +359

    በጥቅሉ እስኪ አንድ ጊዜ ታላቁ ህዝብ አማራ በሉ💚💛❤️💚💛❤️ ይደክማሉ እንጅ ከከፍታህ ማንም ዝቅ አያደርጉህም ከፍ በልልኝ የኢትዮጵያ ዋልታና ማገር my amhare🙏🙏🙏🙏🙏🙏

  • @hiwetbehayilu5678
    @hiwetbehayilu5678 Před rokem +313

    ይሄን ምስጊን የአማራ ህዝብ ነው ለመከላከያ ስንት እንዳላደረገ ዛሬ ሁሉም አይናችሁን ላፈር ያለው የኔ አማራየ የደጋጎቹ ሀገር ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤

    • @ameley4768
      @ameley4768 Před rokem +6

      ክቡርለመከላካያ የአማራን ህዠብ እንደ አይኑ ብሌን ለሚጠብቃት❤❤❤

    • @MSTube86021
      @MSTube86021 Před rokem +8

      ​@@ameley4768 ተው እንጂ መከላከያ ነው የአማራን ህዝብ የሚጠብቀው?

    • @esubewubet4772
      @esubewubet4772 Před rokem +2

      እውነት ነው❤

    • @Ermi_Ermi
      @Ermi_Ermi Před rokem +2

      Ameley ይብዳሸ ብርሀኑ ጁላ

    • @Ermi_Ermi
      @Ermi_Ermi Před rokem +3

      ​@@ameley4768 ሂጂ ዉጪ ከዚህ ገረድ ካድሬ ይብዳሸ መከላከያ

  • @YesewyewLej
    @YesewyewLej Před 10 měsíci +20

    እኔ ካፋ ነኝ አማራ የኢትዮጵያ ኩራት እና ታማኝ ሀገር ወዳድ መሆኑን ለመናገር የግድ አማራ መሆን አይጠበቅብኝም Love Amhara❤

  • @mayasura9916
    @mayasura9916 Před 5 měsíci +36

    I am Oromo , I LOVE Royal Amara people.

  • @cecet745
    @cecet745 Před rokem +236

    "ድሃ ተበደለ ፍርድ ተጏደለ የሚል አስተዳደር ይስጠን"! አሜን አባቴ!!!

    • @mekditee9540
      @mekditee9540 Před rokem +4

      Truly ye’Amhara meleya is that principle!! No matter how uneducated or poor they are, justice, freedom, and fairness is at the core of their being!! It amazes me as I learn about them more!

    • @mazayasin51
      @mazayasin51 Před rokem +1

      Amennn

    • @soliyana-kc5so
      @soliyana-kc5so Před rokem +1

      ❤❤❤❤❤

    • @cecet745
      @cecet745 Před rokem

      @@mekditee9540 exactly!!!

    • @getegolem1198
      @getegolem1198 Před rokem +1

      amen amen

  • @Gente977
    @Gente977 Před rokem +170

    ማርያምን ጎጃሜዎች ሞቼ ነው ምወዳችሁ እኔ ከሽዋ ነኝ ❤❤

  • @kidimengs5134
    @kidimengs5134 Před 6 měsíci +13

    እኔ የሸገር ልጅ ነኝ ብሄር ከተባለ ከትግራይና ከኤርትራ የተወልድኩ ግን ሰፈር እንጂ ብሄርን ሳናውቅ ያደግነው ሁሌም አንድነታችን ይናፍቀኛል ይህን ክፉ ዘመን አልፎ ደጉ ዘመናችንን ይመልስልን የገጠር ሰው ውስጤ ነው

  • @kiflegoitom687
    @kiflegoitom687 Před rokem +560

    እኔ ከኤርትራ ነኝ ያ ክፋ ግዜ ከኣዲስ አበባ ቢያስወጣንም ከልቤ ኢትዮጵያን እወዳለሁ የልጄም እናት የደብረማርቆስ ልጅ ናት አምላክ አንድ ቀን አንድ ያደርገናል አንድ ነንም❤❤❤ ጎጃሞች❤❤

    • @user-zb7cf3go6n
      @user-zb7cf3go6n Před rokem +7

      we LOVE Eri people ... ❤❤

    • @keftesfaye7984
      @keftesfaye7984 Před rokem +13

      We are sad too, Ethiopians never wanted to loose their brothers and sisters, but the evil politicians those are responsible. Some of us are still hoping we will reunited once again.🙏

    • @anicientethiopianreview3862
      @anicientethiopianreview3862 Před rokem +13

      በጥቂት ፅንፈኞች ሁለት ሀገር ሆነናል😢

    • @ashenafiteshome7457
      @ashenafiteshome7457 Před rokem +3

      awo and nen ....ken ymetal and enhonalen enwedachwalen

    • @chalachewbalew6317
      @chalachewbalew6317 Před rokem +4

      Yes Everything has it's own time.

  • @mahlet5451
    @mahlet5451 Před 9 měsíci +11

    አኔ ጉራጌ ነኝ አናቴ ጎጃሜ አንድ ቀን ጉራጌ ነኝ ብዬ አላውቅም ጀግኖች ውቦች እምነታቹ ውይ በናቴ አኮነው ምመሰክርላቹ ❤❤❤❤

  • @mesi2872
    @mesi2872 Před 10 měsíci +13

    እኔ ወላይታ ነኝ ግን ሞቼ ነው ምወደው የአማራ በሆረሰብ❤❤❤❤❤

  • @habtamuwagnew6134
    @habtamuwagnew6134 Před rokem +262

    አማራ ኩሩ, ጀግና, አማኝ ሕዝብ...thanks aschalew 🙏♥️

  • @user-ez2oj5oo5c
    @user-ez2oj5oo5c Před rokem +444

    አማራነት ዉበት አማራነት ደግተን አማራነት ኩራት❤ ቀጣይ በወሎ የምትሉ👍💚💛❤

    • @wubetandarge4698
      @wubetandarge4698 Před rokem +4

      አወ ወሎ የብዙ ስነጥበብ ባለቤት የወይዛዝርት ባለቤት ወሎን በቅርብ ማየት እንፈልጋል በአስቸኩዋይ ይህን የመሰለ ባህል ሳይበረዝ ይቀረጽልን

    • @weddyneguse9643
      @weddyneguse9643 Před rokem +1

      VIVA 🇲🇱 AMARA 👏🏽👏🏽👏🏽👏🏽

  • @firewsileshi3101
    @firewsileshi3101 Před rokem +14

    ምንም እንኳን ትውልዴ ከድሬደዋ ቢሆንም ከቅንብሩና ከዘፈኑ ማማር የተነሳ እጅግ በመመሰጤ የተነሳ ደጋግሜ ብሰማው አልጠግብ አልኩኝ፣ ምን ያህል መታደል ነው አማራ ሆኖ መወለድ፣ ❤❤❤

  • @HananHanan-pm7lx
    @HananHanan-pm7lx Před 11 měsíci +11

    I am Frome oromo but I iloveyou Amhara people 🇪🇹

  • @ensratube
    @ensratube Před rokem +179

    አማራዎች ሞቼ ነው ምወዳቹ ❤የኔ ሀገር ወዳዶች ጀግኖች ደጎች ክፉ አይካቹ ❤❤❤❤💚💛❤በተለይ ደጉ የገጠር ሰው ክፉውን ያርቅለት 💚💛❤እኔ ጉራጌ ነኝ💚💛❤

    • @habtamu1221
      @habtamu1221 Před rokem +4

      እኛም እንወድሻለን ጉራጌ ኩሩ ህዝብ🙏

    • @doilasomohammed6776
      @doilasomohammed6776 Před rokem

      ማ ጠየቀ

    • @meseretgetawedey
      @meseretgetawedey Před rokem +5

      የኔ ማር እናመሰግናለን ጉራጌ ኩሩ ህዝብ ጀግና የሃገር ዋለታ ❤❤❤

    • @mengistufetene8521
      @mengistufetene8521 Před rokem +6

      ጉራጌ የስራ ሰው + ሀገር ሰሪው አማራ= lord of the ring💚🧡❤️

    • @AnnaAnna-wy3vy
      @AnnaAnna-wy3vy Před rokem +2

      እኛም እንወዳችሀለን❤❤❤🎉🎉

  • @sarahana7929
    @sarahana7929 Před rokem +558

    የአዲስ አበባ ልጅ ብሆንም በጣም የምወደችው ሃገርና እምነታችውን የምትወዱ ኩሩ የአማራ ሕዝብ ሰላማችውን አምላክ አብዝቶ ይስጣችው a'm Proud to be Ethiopian Abiseniya 💚💛❤

    • @alemalehenig7350
      @alemalehenig7350 Před rokem +2

      እናመሠግናለን ዉዴ

    • @yaredkebede8423
      @yaredkebede8423 Před rokem +6

      ​@@MimiMimi-tm5jc እስኪ መጀመርያ አማርኛን በስርዓት መፃፍ ተማሪ።
      አንቺ ወፍዘራሽ ነሽ እንዴ?😂

    • @kalebtaye4171
      @kalebtaye4171 Před rokem +2

      የአዲስ አበባ ልጅ ነኝ ማለትሽ ብሄር እንደማታዪ ያሳያል። ሰላምሽ ይብዛ።

    • @user-cb4rx5bb3i
      @user-cb4rx5bb3i Před rokem

      አሜን አሜን አሜን ውዴ❤❤❤

    • @enidegsintayehu2865
      @enidegsintayehu2865 Před 11 měsíci

      amen

  • @ami1285
    @ami1285 Před rokem +19

    አማራነት ❤ጎጃሞች ውድ ደሞች እኔ ወሎየ ነኝ አንድ አማራ

  • @amanuelayalew6685
    @amanuelayalew6685 Před rokem +66

    ቀጣይ በወሎ ይሰራልን የምትሉ❤❤❤

  • @johnney203
    @johnney203 Před rokem +420

    I'm from kenya i love Ethiopian amhara people culture❤❤❤

  • @YonasKidane-sb9bs
    @YonasKidane-sb9bs Před rokem +671

    እኔ ትግሬ ነኝ የ ኣማራ ማህበረሰብ ከልቤ ነዉ ምወደው ኑሩሉኝ 🥰 love you

    • @nebeethd9251
      @nebeethd9251 Před rokem +20

      እናመስግናለን፡፡ እኛም እንዲሁ! ትግሬ እና አማራ ወንድማማች ህዝቦች ናቸው! ሰላም ይሁኑልን!

    • @MarWa-oq5uc
      @MarWa-oq5uc Před rokem +1

      ❤❤❤

    • @nothingcomeseasy
      @nothingcomeseasy Před rokem +2

      May God give us lasting peace ✌️ 🕊️

    • @aschalewmekete8227
      @aschalewmekete8227 Před rokem +10

      አወ እኔ አማራ ነኝ ግን ትግራይ በጣም እወዳለሁ

    • @redetayalew1187
      @redetayalew1187 Před rokem +5

      እኛም እኖዳችኻለን ሓወይ አንድ ህዝብ ነን ሴሚዊያን😍😘

  • @muluyeneneh846
    @muluyeneneh846 Před rokem +28

    ስወዳችሁ ኑሩልን ደሞቼ ክፉ አይንካችሁ ወገኖቻችን የደግነትና የየዋህነት ጥግ ህዝብ ነው❤❤

  • @intertainment2048
    @intertainment2048 Před rokem +5

    ካሲናው ጎጃም ምድሪቱ ምጣድ🎉🎉🎉❤❤
    አማራዬ አያቴ ከጎጃም እኔ ከጎንደር በአማራነት ካልተኮራ በምንም አይታሰብም።

  • @harounmd701
    @harounmd701 Před rokem +154

    መላው የአማራ ወንድም እህቶቼ በያላችሁበት ጌታ ይጠብቃችሁ የመጣብንን ፈተና በአሸናፊነት እንደምናጠናቅቅ ተስፋ አለኝ

  • @fkriuemnetey9115
    @fkriuemnetey9115 Před rokem +128

    እኔ ኤርትራዊ ኔን የ ኣማራ ኢትዮጲያ ባህል በጣም ነው እምወደው እግዚኣብሄር ለሁሉ ህዝብ ኣለም ሰላም ፍቅር ይስጠን 🇪🇷🇪🇷🇪🇷🇪🇹🇪🇹🇪🇹🙏 🙏 🙏

  • @user-ck1pw3mm2l
    @user-ck1pw3mm2l Před rokem +6

    እኔ ጉራጌ ነይ ግን አማራዎችን ...ሞቼ ነው ምወዳቸው ክፉ አይንካቹ❤❤❤❤::

  • @user-bt4kf7mj4s
    @user-bt4kf7mj4s Před 10 měsíci +6

    እኔ ኤርትራዊ ነኝ የአማራ ባህል በጣም ነው የምወደው ስላም ለኢትዮጵያ ይሁን

  • @selamawitgebretsadik3097
    @selamawitgebretsadik3097 Před rokem +87

    የሰሜን ወሎ ልጅ ነኝ የፋኖ እህት ❤ የስነልቦና ውቅር
    ከዚህ ጀግና አይበገሬ ኩሩ ደግ ከአማራ ህዝብ በመፈጠሬ ሁሌም እጅግ እኮራለሁ አማራነት ይለምልም ወንድምአለም ጥኡም ልሳን ባህሉን ወጉን የጠበቀ ነው ሸጋ ነው በርታልን❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤

  • @ABCd-wb1gi
    @ABCd-wb1gi Před rokem +121

    ያዝ እንግዲህ አማራዬ 👏💕!! ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ አንድ አማራ👏!!ለሁሉም አማራ ክብሩ ነው 💚💛❤️👏🥰👌👌💪✊

  • @tsegayzemichael416
    @tsegayzemichael416 Před rokem +8

    Much love ❤️ from Eritrea 🇪🇷

  • @Amen-pk8qh
    @Amen-pk8qh Před rokem +6

    ጥርት ተደርጎ የተሰራ ልብ ውስጥ የሚገባ ግጥም ዜማ አንደኛ ነው በርታ🔥🔥🙏👏👏👏

  • @sebelsolo6381
    @sebelsolo6381 Před rokem +193

    💚አማሮች ሆደ ገራገሮች!💚
    💛አማሮች ፍቅር ፍልቅልቆች!💛
    ❤️አማሮች የማር ወለላዋች!❤️

  • @yohanesgezagn1900
    @yohanesgezagn1900 Před rokem +209

    እኔ ኦሮሚያ ክልል ነው የምኖረው ግን በቃ አማራው ማህበረሰብ ይለያያል ፈጣሪ ቀን አለው አይዟችሁ !!💚💛❤ ዘላለም እንወዳችሁአለን

  • @mulatdessalew9429
    @mulatdessalew9429 Před rokem +27

    Proud to be Amhara ,people rich in
    Developed culture ,literature ,history etc❤❤❤❤❤❤❤❤

  • @smachewtemesgen369
    @smachewtemesgen369 Před rokem +6

    wow wow wow ግሩም ስራ! እንባዬም አቀረረ፣ ዘመዶቼ ጎጃምዬ የአያቶቼ የወላጆቼ ሃገር ማንነቴ ክፉ አይንካችሁ! የጥበብ ምድር የሊቃውንቶቹ ሀገር ደልቂ ደልቂ ደልቂ ደልቂ ደልቂ ደልቂ ደልቂ፣ ከሽማግሌ እግር መጥተሽ ተመረቂ❤

  • @dasashtigabu1116
    @dasashtigabu1116 Před rokem +73

    የአመቱ ምርጥ አስገራሚ ዘፋኝ ማርያምን ቃል አጣሁ አስቼ ብዙ እንጠብቃለን ❤❤❤

  • @Hruy34
    @Hruy34 Před rokem +302

    እኔ ደቡብ ነኝ ግን አማራዎችን በጣም ነው ምወዳችሁ
    ##ባህላችሁ
    ##ፍቅራችሁ
    ###ታማኝነታችሁ
    #ሁሉ ነገራችሁ
    # እኔ ከአማራ ጋር ተጋብቸ ዘሬን ማዋህድ እፈልጋለሁ ❤❤❤❤

    • @user-yk3wz9fw6f
      @user-yk3wz9fw6f Před rokem

      አብሽር ወንዲ ከሆንክ ሚስት ሴት ከሆሺ ባል እፈልጋለን ደቡባችጋ አብዘሀኛው የተጋባን ነን እኮ መቸም አማራ በሁሉም ባታ ይኖራል።

    • @Hruy34
      @Hruy34 Před rokem +2

      @@user-yk3wz9fw6f ወንድ ነኝ ሴት ነው ምፈልግ

    • @saragashaw8879
      @saragashaw8879 Před rokem +1

      ❤❤❤

    • @aderagew3043
      @aderagew3043 Před rokem

      ​​​@@saragashaw8879 L❤❤e y❤u

    • @user-sy7yy3fk6o
      @user-sy7yy3fk6o Před rokem +4

      እኔ ላግባህ እኔም ደቡብን በጣም እወዳለው እኔ አማራ ነኝ

  • @worknhkasswe7317
    @worknhkasswe7317 Před 5 měsíci +5

    I love you Amhara people❤❤❤

  • @thewonders3163
    @thewonders3163 Před rokem +16

    Amhara culture is back, listen and watch it with pride, thanks for sew mehon and aschalew

  • @tirusewchernet
    @tirusewchernet Před rokem +41

    በወሎና በሸዋም ድገመዉ ያበጠዉ ይፈንዳ እንዴት ደስ ይላል አንድ አማራ💪❤❤

  • @mgywy1428
    @mgywy1428 Před rokem +65

    ድሃ ተበደለ ፍርድ ተጓደለ የሚል መሪ ይስጠን አሜን አሜን አሜን ጋሽዬ❤❤❤❤።
    አቤት የሙዚቃው ማማር ❤!!!

    • @user-hr9xp6ev1n
      @user-hr9xp6ev1n Před rokem +1

      አማራ ነው ለሰው ለእንስሳት የሚያዝን ስለሆነም ቢመራን መታደል ነበር

  • @ameleworktesfaye6665
    @ameleworktesfaye6665 Před rokem +4

    አክባሪያቹ ነኝ 🎉ጀግና ህዝብ ምክንያታዊ ህዝብ ወኔአቸውን በጣም ነው የምወደው ያኑራቹ

  • @johntaf7419
    @johntaf7419 Před rokem +4

    I Respect Amhara People because of the People Have a great and Interesting Culture and Have Good Believe People and also the Center of Love,,,,,,,,,, I am From Eritrea

  • @bateablneha5887
    @bateablneha5887 Před rokem +54

    እናትዋ ጎንደር💚💛❤️አካልዋ ጎጃም 💚💛❤️አሁን ደሙ በሽዋ እና 💚💛❤️ወሎ ይሰራልን 💚💛❤️አድ አማራ እጥብቅ አለን ሽዋ እና ወሎ 💚💛❤️

  • @etiopiawitkonjo1090
    @etiopiawitkonjo1090 Před rokem +42

    ደስ ሲሉ!!! ❣ካሲና ማለት እናቶች እንጀራ ሲጋግሩ የምጣዱን ግለት የሚለኩበት የመጀመሪያ እንጀራ (እንጎቻ) ነው💚💛❤ካልተሳሳትኩ🤔

  • @samidish7980
    @samidish7980 Před rokem +6

    I am ertira I loved amhara people and I want live Baherdar gonder woldya dese

  • @titan5519
    @titan5519 Před rokem +26

    I am listing again and again. Blessing to be part of this beautiful culture. Our musician started looking back to the origin. Respect Aschalew

    • @mel4real197
      @mel4real197 Před rokem

      አንተን ነክቶህ ነው የምትኮራበት ቋንቋና ስነ ፅሁፍ የለህም 😊😊😊

  • @yegnatube7556
    @yegnatube7556 Před rokem +58

    ዋው ምርጥ ስራ ነው 👌 ወሎ እና ሸዋ በቅርቡ እንጠብቅሀለን ❤🎉💚💛❤ ጎጃም ጎንደር ወሎ ሸዋ አንድ አማራ 💚💛❤🕌💒😍 በቅርቡ ሸዋ እና ወሎ 💖💖

  • @abirayakobo9888
    @abirayakobo9888 Před rokem +43

    አየየየ የኔ ደግ ህዝብ ባለ ሀገሩ አማራየ ❤ ይቀጥላል ወሎ ሸዋ አንድ አማራ 💚💛❤️

  • @jabnaforfood3584
    @jabnaforfood3584 Před 9 měsíci +3

    የኔ የዋሆች ደግነት ጀግንነት ኢትዮጵያዊት አማራዎች ትለያላችሁ 💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️
    ሠላሙን ያምጣልን

  • @ashebirbitew1237
    @ashebirbitew1237 Před 11 měsíci +5

    እኔ ኤርትራ ተወላጅ ነኝ ግን አማራ ለኔ ኩሩ ጀግና ነው ሀገሩን የማያስደፍር ጀግና ነው ክብር ለአማራው።

  • @abugeda5
    @abugeda5 Před rokem +32

    በጎንደርኛው ሲያስደንቀን በጎጃምኛው ደሞ ያስደምመን ይዟል። ድንቅ ዘፈን ነው አስቹየ ወሎ እና ሸዋኛውን በዚሁ ከፍታ እንጠብቃለን

  • @asafawdesalegn
    @asafawdesalegn Před rokem +120

    ግጥም 👉👉100%
    ዜማ 👉👉100%
    ባህል 👉👉100%
    ማንነት ፣ Emnet : እውነት new ህይወት new አማራነት ኩሩ ሕዝብ ኢትጵያው💚💛❤💯💯💯

  • @Ekram317
    @Ekram317 Před rokem +9

    ይኸን ሙዚቃ ስሰማ የሚታየኝ እኔነቴ አስተዳደጌ ቤተሠቤ ሰፈሬ ሁሉ ነገር ከፊቴ ይመጣና አይኔ እንባ ይቀድመዋል🥺 ቀጣይ በወሎና በሸዋ እንጠብቃለን🥰

    • @saragashaw8879
      @saragashaw8879 Před rokem

      ❤❤😭😭

    • @user-we3kb2jm5b
      @user-we3kb2jm5b Před 10 měsíci

      እኔም አባዬ እስክሳ ሲል የኔ ማርዋ ሲዘፍን ደሞ ወፍ ያረግፋል ድምፁም መልኩም ያምራል የኔ አባት ድሮ ኪነተኛ ነበርኩ ብሏል በመልክና በድምፅ ተመርጦ ደሞ ሲገጥመዉ የኔዋን ሸበላ መልጎም እናቴን አገባ አቤት ሲያምሩ ወላሂ ክክክክክ

  • @YasegnalZerihun-ts1ni
    @YasegnalZerihun-ts1ni Před rokem +6

    tnx for Aschalew and Eritrean 🇪🇷 people

  • @genettesfay3865
    @genettesfay3865 Před rokem +25

    I love gojam bahil from Eritrea 🇪🇷

  • @birhanuabawa3937
    @birhanuabawa3937 Před rokem +59

    ከዚህ ውብ ማህበረሰብ በመገኘቴ እጅግ ኩራት እንዲሁም ጀብዱ ይሰማኛል
    አስቻለው እናመሰግናለን!!!

  • @rahmet123
    @rahmet123 Před rokem +4

    ይህን ወርቅ የሰውነት ልክ የአማራ ህዝብ ሀገር ወዳዱን ማንም ይሁን ማንም እንዴት መጥላት ይቻላል ሰይጣን ምላኪ ካልሆነ በቀር አማራነቴን ሙቼ ነው ምወደው እንኳንም ከዚህ ማህበረሰብ ተፈጠርኩ ኩራት እራቴ ❤❤❤❤❤❤

  • @Enkuzema1
    @Enkuzema1 Před rokem +4

    በዚህ ዘመን ባህላዊ ዘፈን ለምትሰሩ አርቲስቶች በሙሉ የዚህ ሰው ስራ ትልቅ ትልቅ ትምህርት ይወሰድበታል ብየ አስባለው ወጉን ባህሉን ሁሉንም ነገር በጠበቀ መልኩ ሲሰራ እጅግ ያምራል 💚💛❤

  • @yonashaile6136
    @yonashaile6136 Před rokem +174

    We love Amara people I'm from Eritrea.

    • @ethiopia5038
      @ethiopia5038 Před rokem +1

      We love you more ❤❤❤❤❤

    • @Tigist-ww4gn
      @Tigist-ww4gn Před rokem

      ❤❤❤❤❤❤❤

    • @gabigebreal7620
      @gabigebreal7620 Před rokem

      LEBOCH

    • @weddyneguse9643
      @weddyneguse9643 Před rokem

      ME I ETHIOPIAN BUUUTTTTT I LOVE ERITREA SOPOOOOOOO MACH I'VE BEN VISITED 2 THE BEAST THEING EVER ❤❤❤🥰🥰😘😘😘

    • @gabigebreal7620
      @gabigebreal7620 Před rokem

      @@weddyneguse9643 wedi gudom , get lost , and move and live in that dessert you call ertra stupid.

  • @Oumlizaaa
    @Oumlizaaa Před rokem +127

    የኔ ንፁህ ህዝብ አማራዬ 👏👏ቀጣይ በወሎና በሸዋ ኑልን❤❤👏

    • @DaniMezgebe
      @DaniMezgebe Před rokem +3

      የእናታችን ፊት ገፅታ ብዙ ይናገራል!!! እነዛ ሠው በላዎች በዚህ ምስጊን ህዝብ ላይ ያደርሡት በደል ኣንሶ ሊያጠፋት ቆርጠው መነሣታቸውን ሳስብ . . . በቁጭት እና ወኔ እንዳነባ አደረገኝ 😢😢😢😢

    • @Oumlizaaa
      @Oumlizaaa Před rokem +2

      @@DaniMezgebe የኔ ደግ ህዝብ ይህ አይገባውም ነበር መረ አጣጂ ባርነትንማ አይቀበለውም ነበር💔😢

    • @user-uy4gl9cg4m
      @user-uy4gl9cg4m Před 4 měsíci

      እውነት ነው በሸዋ ኑልን እባካችሁ የእምየን ታሪክ የያዘ እንፈልጋለን❤

  • @helabayou1715
    @helabayou1715 Před rokem +3

    የ አዲስ አበባ ልጅ ነኝ አማሮችን ግን ሞቼ ነው የምወዳችሁ ፈጣሪ ይጠብቃችሁ ሀገር ወዳጆቹ ሀይማኖተኞቹ

  • @Gdsshitf
    @Gdsshitf Před 7 měsíci +6

    We ethopians are unique culture. l am also gojjam

  • @user-fo3xt2wo8t
    @user-fo3xt2wo8t Před rokem +95

    አስችዬ ምርጡ❤ በእናትዋ ጎንደር ተደምመን ሳንጨርስ በካሴናው ጎጃም መጣህልን ቅርብ ለቅርብ ነው ጎጃም እና ጎንደር ሲጫወቱ ውሎ ከመሸም ለማደር አማራዬ ባለ ውብ ባህል ኩሩ ህዝብ❤

    • @hanasador3723
      @hanasador3723 Před rokem +2

      ሚሚዬ❤

    • @user-fo3xt2wo8t
      @user-fo3xt2wo8t Před rokem +1

      @@hanasador3723 ሀኒዬ እንዴት ነሽልኝ ጠፍተሻል❤️

    • @hanasador3723
      @hanasador3723 Před rokem

      @@user-fo3xt2wo8t ሰላም ነኝ ሚሚዬ አንቺስ እንዴት ነሽ?

    • @MM-wj8mq
      @MM-wj8mq Před rokem +1

      እንዲያ በልማ !!'

  • @saraameda4300
    @saraameda4300 Před rokem +61

    አምላኬ ይሄን የዋህ ህዝብ አንተው ጠብቀው ሀገራችን ሰላም ያድርግልን Ethiopia ❤️❤️❤️❤️❤️

  • @user-we8je5jb4d
    @user-we8je5jb4d Před 5 měsíci +2

    እንደው ደስ ሲል❤❤❤

  • @Mill10n-M
    @Mill10n-M Před 5 měsíci +4

    Good vibe, all love from 🇪🇷

  • @tigistzoe6133
    @tigistzoe6133 Před rokem +53

    እኔ ጉራጌ ነኝ አማራዬ ደሞቼ ናቹ አንተ ባትኑሩ ኢትዮጲያ ምንቶን ነበር 💚💛❤️

    • @dera112
      @dera112 Před rokem

      ❤❤❤❤

    • @MarWa-oq5uc
      @MarWa-oq5uc Před rokem

      ❤❤❤❤❤

    • @birkeDemeke
      @birkeDemeke Před rokem

      ♥♥♥

    • @zeruwondim8575
      @zeruwondim8575 Před rokem +2

      እውነት ነው woow ... what a wonderful , precise & golden epression for these innocent peoples is it? Long live for brother Gurage peoples!!

    • @hamerethiopia4558
      @hamerethiopia4558 Před rokem +1

      Enantem nurulen guragewochi betam nw minwodachu❤

  • @sheshe4202
    @sheshe4202 Před rokem +78

    በወሎና በሸዋ ይደገም እምትሉ በላይክ❤

  • @yo.n4777
    @yo.n4777 Před rokem +8

    ሌላም እንጠብቃለን. Original music, with typical Amhara ethnics. I really missed this communities. They are so lovable and welcoming people. I have never seen such ethnics during my whole tour in Ethiopia.

  • @Eyob797
    @Eyob797 Před 10 měsíci +4

    ባህላችን ደስ ይላል። የአዲስ አበባ ልጅ ነኝ የአማራ ህዝብ በጣም የምወደው የማከብረው በደንብም የማውቀው ደግ ሀይማኖተኛ ህዝብ ነው ለዕናት ሀገራችን ኢትዮጵያም ደጀን ነው።

  • @SebleSeble-zr1bu
    @SebleSeble-zr1bu Před rokem +20

    አማራዬ😢😢😢 ጎጃም ሀገሬ ደጉ ወገኔ ክፉህን አያሳየኝ 😢💚💛❤️🙏🐅👌ካሴናው ጎጃም 💙🙏👌

  • @user-hs7hw4km6z
    @user-hs7hw4km6z Před rokem +22

    እኔም ወሎዬ ነኝ አማራ ነው ደሜ የት ናችው አማራዎች አላችው ወይ አለን በሉኝ እስኪ ኑልኝ ልያችው🇪🇹🇪🇹

  • @gojjiamtube2077
    @gojjiamtube2077 Před rokem +16

    Proud to be Gojjam Amhara Ethiopian ❤❤❤❤❤❤

  • @hermonpatros3
    @hermonpatros3 Před rokem +4

    ❤❤❤ብጣብ ነዉ ምንወጁቱ ጉጂሞት እኂ ኤርትራውያን 🇪🇷🫡🇪🇷🫡

  • @ghionentertainment4482
    @ghionentertainment4482 Před rokem +38

    ይህ ቱባዉ የጎጃም ዜማና ወግ ባህል እሴት ገና ያልተነካ እንደሆነ ማሳያዉ ነዉ። ለኪነጥበብ ሰዎች ። Thank you Aschu and his crew . Gojjam the land of wisdom and heroes !

  • @relax-meditate-sleep
    @relax-meditate-sleep Před rokem +213

    I'm Oromo Selale! Gojam music brings back nostalgic memories of my childhood, reminding me of the beautiful cultural heritage and kindness. Let's spread love 🤍🖤💙 and appreciation for our diverse traditions without promoting hate speech. Keep embracing your true selves, everyone🙏!

    • @abetadesse3700
      @abetadesse3700 Před rokem +7

      Thank you bro, let's spread ❤️

    • @ShewaFano544
      @ShewaFano544 Před rokem +4

      One love brother 👌

    • @layelaalayelaa6282
      @layelaalayelaa6282 Před rokem +3

      ❤❤❤❤❤

    • @addisababanazareth1525
      @addisababanazareth1525 Před rokem +7

      የተረገመች ህወሀት መጥታ እጅግ ሰላምና ፍቅር አጥፍታ በዘርና በጎጥ ሞልታው ህዝባችንን አጣልችብን።
      እኔ የአዲስ አበባ ልጅ ነኝ። የዘርና የጎጥ ኮተት ምንም የማይዋጥልኝ ሰው ነኝ።💚💛❤

    • @genete8037
      @genete8037 Před rokem +1

      You are right. That is what we need to do. ❤

  • @tshililonekhavhambe
    @tshililonekhavhambe Před 8 měsíci +3

    I am a South African by birth, and I can't here a word he is singing about, but ohh God, what a blessed voice. A wonderful video and the community that participated in it.

    • @Black-lioness
      @Black-lioness Před 7 měsíci

      Ola, not a born and bred SAfrican,but brought on the hustle bustle of Jozi, this a folker music from the tribe of Gojam ppl fro
      The land of Amhara region. This is the typical tune from the region in Gojam where the source of Tis Abbay {Smokey Nile river) steam from.
      Welkom!!!

  • @milenrufta5283
    @milenrufta5283 Před 5 měsíci +4

    Big love from Eritrea 🇪🇷 ❤

  • @hannayohanns2002
    @hannayohanns2002 Před rokem +84

    ውብ ባህል ውብ ዜማ
    አማራ ይሄ ስልጡን ህዝብ ♥
    ታላቅ ነበርን ታላቅ እንሆናለን ።
    ቀጣይ ሸዋ!
    ወሎ!

    • @aman12848
      @aman12848 Před rokem

      ሀኒ እንዴት ነሽ የኔ ዘመን ጣይቱ ብየሻለሁ

    • @adicho5964
      @adicho5964 Před rokem

      Still we are great !!!!!!!!
      We have a confidence
      By nature!!!!
      Educated Respect for
      People. We have the most beautiful Calture
      Lucky people Ookkk

  • @asmamawgetaneh1862
    @asmamawgetaneh1862 Před rokem +26

    ከዚህ ህዝብ መፈጠር ምንኛ መታደል ነው 🙏 የጎንደሩም የጉጃሞም የሀገሪን ህዝብ ባህል በጥሩ ሁኔታ የገለፀ ስራ ነው ።በርታ bro❤!

  • @gulzarrai43
    @gulzarrai43 Před 11 měsíci +4

    U people r ROYAL .. 👌 ... This community grace proves 2000 Years of rearing Cultural Royalty of Abysinia... 🙌🌷🌸💯👋🙋🌸

  • @tigestalebachew3666
    @tigestalebachew3666 Před rokem +10

    Beautiful people ❤❤❤🇪🇹 i don't why I'm crying ..🇪🇹🙏🙏🙏🙏

    • @kardon4996
      @kardon4996 Před rokem +1

      Me too !!!!!!!!!💕
      There is something innocent is in it ......

  • @Mimi_Petros
    @Mimi_Petros Před rokem +45

    I am from debub but I love Amhara people ❤