Video není dostupné.
Omlouváme se.

21 - በደቂቀ እስጢፋ ዙርያ፡ በተደጋጋሚ ለሚነሡ ጥያቄዎች፡ መልስ (በዶ/ር መስከረም ለቺሣ)

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 15. 02. 2024
  • በዚህ ቪድዮ ምላሽ የተሰጠባቸው ጥያቄዎችና የተሳሳቱ አስተሳሰቦች፦
    1. “ደቂቀ እስጢፋኖስ የግፍ ጭፍጨፋ ተደርጎባቸዋል” የሚለው አስተሳሰብ፤
    2. “ደቂቀ እስጢፋኖስ የተሰደዱትና የተገደሉት፡ እውነተኛውን ወንጌል በማስተማራቸው ምክንያት ነው” የሚባለው አስተሳሰብ፤
    3. “ሰው፡ ለማርያም አልሰግድም ስላለ መገደል የለበትም” የሚለው ተቃውሞ፤
    4. “ደቂቀ እስጢፋኖስ የተጠሉት የትግራይ ሰዎች ስለኾኑ ነው። የሸዋ ነገሥታት፡ ለትግራይ ተወላጆች ጥላቻና ንቀት የሰሎሞናዊነትም ፉክክር ስለነበረባቸው፡ ጨፈጨፏቸው” ስለሚባለው፤
    5. “የኢትዮጵያ የክርስትና ታሪክ በሙሉ የትግራይ ታሪክ ነው። ኢትዮጵያ የምትባል አገር የለችም። ትግራይ ናት። አቡነ ተክለሃይማኖት ትግሬ ናቸው፤ ጃንደረባው ትግሬ ነው፤ አክሱም የትግሬ ናት፤ ደቂቀ እስጢፋኖስም ትግሬዎች ናቸው፤ ንግሥተ ሳባ ትግሬ ናት። ምርጥ ምርጡ ኹሉ ትግሬ ነው። መጥፎ መጥፎዎቹ ግን ኢትዮጵያውያን ናቸው” የሚለው የጽንፈኛ ብሔርተኞች ጥቅል አስተሳሰብ፤
    6. ዐጼ ዘርዓ ያዕቆብም፡ ከሰሎሞናዊው ዘር የመጣ ከኾነ፥ ደቂቀ እስጢፋም፡ አይሁድ ከነበሩ፡ እንዴት አይሁድነት ሊያጋጫቸው ቻለ? ኹለቱም ሥረ መሠረታቸው አንድ አይደለም ወይ?
    7. “ደቂቀ እስጢፋኖስ ለውጥ ፈላጊ ኢትዮጵያውያን ነበሩ” ለሚሉ፤
    8. “ደቂቀ እስጢፋኖስ ሰማዕታት ናቸው” ለሚሉ፤
    9. “ደቂቀ እስጢፋኖስ፡ አሁን ላሉት ፕሮቴስታንቶች እና ተሃድሶዎች፡ የመንፈስ አባቶች ናቸው፤ ወይም ከማርቲን ሉተር በፊት፡ የተሃድሶ ፕሮቴስታንት እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ በደቂቀ እስጢፋ ነው የተጀመረው” ስለሚለው አስተሳሰብ፤
    10. “አባ እስጢፋኖስ ጉንዳጉንዴን ብቻ ሳይኾን፡ ጣና ገዳማትን በሙሉ የገደሙ ትልቅ አባት ናቸው። ኃይቅ እስጢፋኖስን ገድመዋል። መጽሓፈ ሄኖክን ለትውልድ አኑረዋል” ለሚሉ ቀልደኞች፤
    11. “ደቂቀ እስጢፋኖስ ለቅድስት ድንግል ማርያም የተለየ ፍቅር ነበራቸው፤ በስሟ የጸሎት መጻሕፍትን ይጽፉላታል፤ በስሟ ገዳማት ገድመውላታል” ለሚሉ ሐሰተኞች፤
    12. “ደቂቀ ኤልያስ፣ ደቂቀ እግዚአብሔር፣ ደቂቀ እስጢፋኖስ የሚባሉ እውነተኞች ነበሩ የሚል፡ በመሪ ራስ አማን በላይ መጻሕፍት ውስጥ አግኝተናል። ስለዚህ፡ ደቂቀ እስጢፋኖሶች የሚባሉት ቢያንስ ከአነሳሳቸው ላይ እውነተኛ ቡድኖች ነበሩ ማለት ነው ወይ?” ለሚለው ጥያቄ፤
    13. “ደቂቀ እስጢፋኖስ፡ ከ Knights Templars ጋር አንድነት ነበራቸው ወይ?”
    14. “የኢትዮጵያ የጵጵስና መንበር፡ የአባ ሰላማ መኾን ሲገባው፡ ለምን የአቡነ ተክለሃይማኖት መንበር ኾነ? የሚቀድሙት፡ አባ ሰላማ አይደሉም ወይ? የመጀመሪያው ፓትርያርክ አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን አይደሉም ወይ?”
    15. “ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ፡ ለሥልጣኑ በጣም ይሳሳ ስለነበረ፡ ደቂቀ እስጢፋኖስን አሳደደ” ለሚሉ፤
    16. “ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ፡ ግራ ቀኝ ሳይመረም በግንፍልተኝነት ይፈርድ የነበረ አምባገነን ነበረ” ለሚሉ፤
    17. “ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ፡ ኹለት ወይም ከዚያ በላይ ሚስቶች ነበሩት” ስለሚባለው ታሪክ፤
    18. “ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ፡ ስለእምነት ምንም አያውቅም፤ ፈላስፋ ነበረ” ለሚሉ፤
    19. “ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ በሕይወት እያሉ ለምን አልሞገትሻቸውም ነበር?” ብለው ለሚጠይቁኝ፤
    20. “ሚዛናዊ መኾን አለብን፤ ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብም፡ ብዙ ደግ ሥራዎች ቢኖራቸውም፡ ጻድቅ አይደሉም፤ ደቂቀ እስጢፋኖስም፡ አንዳንድ ትዕቢትና አፈንጋጭነት ቢኖርባቸውም፡ መናፍቃን ወይም መጥፎ ሰዎች አይደሉም። ኹለቱንም በእኩል ሚዛን ልናያቸው ያስፈልጋል” ስለሚለው አስተሳሰብ፤
    21. “ከ600 ዓመታት በፊት ስለነበሩት ሰዎች ከማውራት፡ አሁን ያለውን የኢትዮጵያን ችግር ማውራት አይሻልም ወይ?” ለሚሉ፡ መልስ።

Komentáře • 222

  • @Nah-unique
    @Nah-unique Před 5 měsíci +50

    እግዚአብሔር ይባርክሽ። መንፈስ ቅዱስ አይለይሽ። ስለ ክብሯ የቆምሽላት ድንግል ማርያም ከክፋ ትጠብቅሽ። በስንዴ መሐል ያለውን እንክርዳድ ማወቁ ጥሩ ነው ጠቅሞናል።

  • @dgmesay4050
    @dgmesay4050 Před 5 měsíci +5

    ኢትዮጵያን እና ተዋህዶ ሐይማኖቴን በአንች ውስጥ አየዋቸው❤
    እ/ር ጨምሮ ጨማምሮ ይባርክሽ🙏🙏🙏

    • @Zeeee2007
      @Zeeee2007 Před 4 měsíci +1

      እባካችሁ ሙሉውን እግዚአብሔር ብላቾሁ ፃፉ!!!! this wrong እ/ር

  • @eyerusalemchernet5132
    @eyerusalemchernet5132 Před 5 měsíci +4

    ዋነኞቹ የሀይማኖት መሪዎች አፋቸውን ዘግተው በተቀመጡበት ዘመን አንቺን ያስነሳ እግዚአብሔር ይመስገን!ፈጣሪ ብርታቱን ይስጥሽ!

  • @user-nn7tx4gj2b
    @user-nn7tx4gj2b Před 4 měsíci +2

    ፈጣሪ መድሀኒያለም ይባርክሽ የተዋኅዶ ጀግና ተባረኪልን፡፡

  • @mekuria9820
    @mekuria9820 Před 5 měsíci +3

    ❤እግዚአብሔር መቼም ጥሎ አይጥለንም
    አንቺን ደግሞ ሰጠን
    ለደቂቀ እስጢፋ ቅ.ዘርዐ ያዕቆብን እንዳስነሳና እንደረታልን
    ለዚህ ዘመን እስጢፋ እንቺን አስነሳ

  • @zobleselam5695
    @zobleselam5695 Před 5 měsíci +13

    እናመሰግናለን ዶ/ር ።ስላስተማርሽን እና ግልፅ ስላደረግልሽን ።

  • @dagnachewasrat117
    @dagnachewasrat117 Před 5 měsíci +4

    Thank you Meskerm for sharing wisdom and truth

  • @Bigchance25
    @Bigchance25 Před 5 měsíci +16

    ቃለህይወት ያሰማልን ዶክተር መስከረም ለቺሳ እንደዚህ በሚጣፍጥ አንደበት ግልጽ አድርገሽ ስላስረዳሽን እጅግ አድርጌ አመሰግናለሁ video ቶሎ ቶሎ ስሪልን በጉጉት ነው የምንጠብቅሽ❤

  • @melakuteferi7269
    @melakuteferi7269 Před 5 měsíci +3

    እድሜ ይስጥልኝ።ረጅም ያገልግሎት ዘመን ያድልልን።

  • @mekadr842
    @mekadr842 Před 5 měsíci +8

    እረጅም እድሜና ጤና ተመኘውልሽ

  • @mistyswenson8147
    @mistyswenson8147 Před 5 měsíci +5

    You're my hero sister. God bless you 🙏

  • @user-pe3wi3ek8u
    @user-pe3wi3ek8u Před 5 měsíci +7

    እህታችን ጸጋውን ያብዛልሽ በእውነትለይተመስርተሽ ለመትናገሪው ምስክርነት እግዚአብሔር ከጠላት የጠብቀሽ

  • @wubesileshi5043
    @wubesileshi5043 Před 4 měsíci +1

    እውነተኛ ሰው ለእውነት የቆምሽ እህታችን። በርቺልን

  • @TaddeleGebre
    @TaddeleGebre Před 4 měsíci +1

    Kale hywet yasemaln Dr. Mesekerem Lecheisa !!!

  • @abisiniaethiopia7673
    @abisiniaethiopia7673 Před 5 měsíci +1

    ዶ/ርመስከረም ለትውልዱ ጥሩ ትምህርት እየሰጠሽ ነው እግዚአብሔር እረጅም ያገልግሎት ዕድሜና ጤና ይስጥሽ እናመሰግናለን

  • @Maria_Henock
    @Maria_Henock Před 5 měsíci +3

    ዛሬም ለኢትዮጵያ እንደ አዔ ዘርዓያ ያዕቆብ ያለ መሪ ያድለን።

  • @yisehaktadesse5687
    @yisehaktadesse5687 Před 5 měsíci +1

    ስለድካምሽ ባለውለታችን ነሽ !! ቃለ ሕይወት ያሰማልን

  • @addiszemariam7240
    @addiszemariam7240 Před 5 měsíci +1

    ቃለህይወት ያሰማልን ዶ/ር መስከረም እንደዚህ በሚጣፍጥ አንደበት ግልጽ አድርገሽ ስላስረዳሽን እግዚአብሔር ይባርክሽ!!!

  • @user-tw4rj4cm3d
    @user-tw4rj4cm3d Před 5 měsíci +5

    እግዛቤህር ይመስገን በጣም ደስ የሚል ትምህርት ነው አመሰግናለሁ ።

    • @tigisttakele3313
      @tigisttakele3313 Před 5 měsíci +2

      እግዛቤህር ~እግዚአብሔር ይመስገን በሚል ይስተካከል::

  • @alemitufeleke-sq7li
    @alemitufeleke-sq7li Před 5 měsíci +5

    እህታችን በርቺልን ከአንቺ በጣም ብዙ ተምረናል እናመሰግናለን

  • @ethiointercept3014
    @ethiointercept3014 Před 5 měsíci +1

    ቃለ ህይወት ያሰማልን

  • @niniz8365
    @niniz8365 Před 5 měsíci +7

    Meski kalehiwot yasemalen, sewedesh temhertesh dess yelal. you have confidence.

  • @merimeri7886
    @merimeri7886 Před 5 měsíci +17

    በመብርሐን እንዴት ደስ እያለኝ እደማዳምጥሸ ብዙ ያልሰማኃቸውን ታሪክ ነው ያወኩት ቃልሒወት ያሰማልን በድሜ በፀጋ ያኑርልን ያገልግሎት ዘመንሽን ይባርክልን ♥♥🙏🙏

  • @user-vv8vz2un8j
    @user-vv8vz2un8j Před 5 měsíci +3

    ቃለ-ህይወት ያሠማልን ዶክተር መስከረም!!! እንወድሻለን! ከዚህ የበለጠ ሞገስሽን ያብዛው!!! በዚህ አጋጣሚ ባለማስተዋል ለደቂቀ እስጢፋ ጥብቃና የቆምክ ኦርቶዶክሳዊ ካለህ ሌላውን እንኳን ተውና እንዴት በእናትህ በወላዲተ አምላክ ትደራደራለህ ነው መልዕክቴ።

  • @asratmamo7963
    @asratmamo7963 Před 5 měsíci +2

    ❤🎉🎉❤🎉 Dr. You are a very important person. ❤️ ❤ Wow 👌 👏 😍 👍 🥰

  • @solomonseifu4785
    @solomonseifu4785 Před 5 měsíci +9

    Kalehiwot yasemalen❤

  • @tsedenaynessibu3006
    @tsedenaynessibu3006 Před 5 měsíci +2

    እንኳን ደህና መጣሺ በጣም ነው የማመሰግንሺ እግዚአብሔር ይርዳሺ🙏

  • @ascheshete2482
    @ascheshete2482 Před 5 měsíci +2

    እድሜ አጤና ጋር ይለግስሽ !!!!!!

  • @genetseyoum5225
    @genetseyoum5225 Před 5 měsíci +6

    እንደዚህ አይነት በእውቀትና በማስረጃ ትውልዱን የሚያስተምር ሰው ስለጠፋ መናፍቃና መሃይሞች ተደራጅተው የተዋህዶን አማኞች ያሳድዳሉ የሰሞኑ የትግራይ ሲኖዶስ እንቅስቃሴ በቀጥታ ቀደም ብሎ የጠነሰሱት እንደ ሠረቀ አይነት የዘመናችን ተንከሲሶችን እንደመጡ አይተናል

  • @user-qb8su6gv2r
    @user-qb8su6gv2r Před 5 měsíci +9

    ታሪክን ስለምታጠሪልን በጣም ነው የማመሰግነው በእውነት ብዙ ኢትዮጵያን የሚጠሉ አሉ እግዚአብሔር ይማረን ብቻ

  • @demelashtefera6415
    @demelashtefera6415 Před 5 měsíci +6

    በተለይ በዚህ ዘመን መናፍቃን በመበራከታቸው ነቅተን ተኩላዎችን በአይነ ቁራⷘ እንድጠነቀቅ መብራቶች ነበራሽልን ድንግል ከነልጇ ትጠብቅሽ በርቺ

  • @saraabraham7059
    @saraabraham7059 Před 5 měsíci +6

    ዶ/ርዬ የኔ ቅመም መጣሽልን ስለምሰጭን ትምህርት እግዚአብሔር የነፍስ ዋጋ ያርግልሽ ❤ በግሌ በጣም ነው ምወድሽ እመቤቴ ትጠብቅሽ ከነ በተሰብሽ

  • @wasihunsebesbe2712
    @wasihunsebesbe2712 Před 5 měsíci +2

    ቃለ ህይወት ያሰማልን፤ ባልል ንፉግነት ይሆንብኛል። እህቴ ተባረኪ!!!

  • @tinaeshetu6994
    @tinaeshetu6994 Před 5 měsíci +9

    አለማወቅ ደፋር ያደርጋል!የጠየቋቸው ጥያቄዎች ካለማወቅ ከሆነ አከብራለሁ!የሰጡት አስተያየት ግን ከማንበብ እጥረትና ከ ግብታዊ እውቀት፣ጠርዝ ከረገጠ ዘረኝነት ስለሆነ አይፈረድባቸውም።
    አንቺን እግዚአብሔር ይባርክሽ!!!

  • @user-yt6ru8jo7s
    @user-yt6ru8jo7s Před 5 měsíci +3

    እግዚአብሄር ይመስገን ይህን እንድሰማ የረዳኝ መስኪዬ ከነቤተሰቦችሽ ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሽ

  • @anaym2410
    @anaym2410 Před 5 měsíci +2

    ቃለህወት ያሰማልን
    አነቺ በሩክት ዘሪሽ ይበረክ

  • @elsabetmekuria8775
    @elsabetmekuria8775 Před 5 měsíci +14

    ውድ እህታችን በርቺ እግዚአብሔር ያበርታሽ ለጊዜው ነው የሚውተረተሩት በቃ ጊዜው ደረሰ እውነቱ ወጣ የሚያማቸው እንግዲህ ቀስ እያሉ ይዋጡት!!!

  • @user-ow6vw7ov7e
    @user-ow6vw7ov7e Před 5 měsíci +2

    ቃለ ህይወትን ያስማልን::

  • @zebadtube545
    @zebadtube545 Před 5 měsíci +2

    ዶ/ር መስከረም አምላክ እግዚአብሔር በድንግል ምልጃ ከነመላው ቤተሰብሽ ይባርክሽ፤ መላእክቱን ልኮ ጥላ ከለላ ይሁንሽ። አሜን አሜን አሜን🙏🙏🙏 ዘንድሮ ፈጣጣ እና ልኩን፣ ማንነቱን እና መሰረቱን የማያውቅ ደፋር በበዛበት ዘመን አካፋን አካፋ ብሎ በስሙ መጥራት እና ማንነቱን ማስታወስ፣ ልኩንም መንገር ግድ የሚልበት ጊዜ ላይ ደርሰናል። ፕሮግራምሽን በጉጉት እና በንቃት ነው የምከታተለው። ምርጥ ኢትዮጵያዊ የእንቁዋ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጅ በርችልን 🇨🇬💚💛❤

  • @dawitmenber518
    @dawitmenber518 Před 5 měsíci +1

    May God bless you abundantly. Holy Mary will not separate you with her intercession

  • @yared2112
    @yared2112 Před 5 měsíci +2

    እነ አባ ሠረቀ የሚሰሩት ሥራም ተመሳሳይ ነው። በርችልን በደንብ አጋልጭ።

  • @selam-pz5ds
    @selam-pz5ds Před 5 měsíci +2

    እድሜ አና ጤና ይስጥልን ዶክተር ነገርን ከስሩ ስለሆነ ተኩላዎችን ማወቅ አሁን ላሉት ችግሮች መነሾ መሆናቸውን ያረጋግጣል እግዚያብር ይስጥልን ላካፈልሽን እውቀት

  • @sophiakassa2479
    @sophiakassa2479 Před 5 měsíci +2

    እናመሰግናለን ዶ/ር መስከረም። ሁሉም መልሶችሽ አስደስቶኛል። በተለይ ለጥያቄ 9 የሰጠሽው ማብራሪያ አንጀቴን አርሶታል።
    ለጠየቁትም እናመሰግናለን። በመጠየቃቸዉ የበለጠ ተንኮሉና ጥንስሱ ገለጠ።

  • @user-id8sv4gq1d
    @user-id8sv4gq1d Před 5 měsíci +1

    ENAMSEGNALEN DR!!!

  • @2tes
    @2tes Před 5 měsíci +3

    Thank you Doctor. ሁላችሁ፥ ይህን ሚዲያ የምትከታተሉ፡ ለኢኩዪሚንዝም አቀንቃኝ ለሆኑት፡ በተለይ ለሶፊያ ሽባባው፡ አድርሷት።

  • @yaredkebede5575
    @yaredkebede5575 Před 5 měsíci +2

    ብዥታዬን ነው ያጠራሽልኝ ዶክተር!በተቻለኝ መጠን በአቶ ጌታችው ኃይሌ በትርጉም የተፃፈውን ለማንበብ ሞክሪያለሁ አንድም መንፈሳዊ ይዘት የሌለው መንፈሳዊነት የማይሸት ታምር አልባ ሆኖ ነው ያገኘሁት። ዶክተር እግዝአብሔር አምላክ ፀጋውን ያብዛልሽ!

  • @habeshaviews2114
    @habeshaviews2114 Před 5 měsíci +1

    God bless you! Dr. Meskem

  • @yohanneshaileselassie7284
    @yohanneshaileselassie7284 Před 5 měsíci +14

    በበኩሌ ከፍተኛ ግንዛቤ ነው ያገኘሁት ቸር አሰምተሽናልና የእግዚአብሔር ጥበቃ የክርስቶስ ቸርነት የመንፈስቅዱስ ፀጋ አይለይ።

  • @TsehayErifo
    @TsehayErifo Před 5 měsíci +1

    ቃለ ህይወት ያሰማልን መስኪ እናመሰግናለን ❤❤❤❤❤❤❤

  • @kalkal5842
    @kalkal5842 Před 5 měsíci +1

    እናመሰግናለን ዶ/ር እግዚአብሔር አብዝቶ ጥበቡን ይግለጥልሽ❤❤❤

  • @tezerashalemu6312
    @tezerashalemu6312 Před 5 měsíci +1

    እህታችን ውድና እንቁ የሆኑ አባቶቻችንን እነ አለቃ አያሌው ታምሩን እያነሳሽ የተደበቀውን ምስጥር እየገለጥሽ እግዚአብሔር አምላክ ባንች ላይ እዲሮ ስላስተማርሽን እናመሰግናለን

  • @user-mf8re2dk4r
    @user-mf8re2dk4r Před 5 měsíci +2

    ቃለህወት ያሠማልን አፄ ዘራይቆብ ምነው የአሁን ግዜ መሪ ቢሆን ኢትዮጵያ ም ቅድስት ቤተክርስትያንም ይፀዳነበር ህዝቦቿም በዘር አይተራመሡም ነበር እግዚአብሔር እደነዝህ አይነት ጀግና ንጉስ ለሀገራችን ቤተክርስትያንም በጣም ያስፈልጋታል እህቴ ደፋር ጀግና እዳች አይነቷን ትናፍቃለች ሀገሬ።

  • @lidiyat
    @lidiyat Před 5 měsíci +1

    እግዚአብሔር ይባርክሽ ዶክተር እናመሰግናለን

  • @BereketBaley-zf5lr
    @BereketBaley-zf5lr Před 5 měsíci +1

    እግዚአብሔር ይባክሽ

  • @muluye333
    @muluye333 Před 5 měsíci +1

    ቃለ ህይወት ያሰማልን መምህርት

  • @fireayalew9663
    @fireayalew9663 Před 5 měsíci +1

    ቃለህይወት ያሰማልኝ ውድ ዶ/ ር ክብር ይስጥልኝ

  • @Eric_tmr
    @Eric_tmr Před 5 měsíci +5

    🙏

  • @Kushaitopia
    @Kushaitopia Před 5 měsíci +2

    Blessings Dr Meskerem, thank you for spreading knowledge

  • @antensaylakew970
    @antensaylakew970 Před 5 měsíci +7

    Meskiye💚💛❤️

  • @alemtsehaysesaysisay7144
    @alemtsehaysesaysisay7144 Před 5 měsíci +18

    እህታችን እንኳን በደህና መጣሽ ጌታ ይባርክሽ ዘርሽን ይብዛው መለአኩ ቅዱስ ዑራኤል ከዚህ በላይ እውቀትን ይጨምርልሽ ምእመናን እንኳን ለአባታችን ለአቡነ እስትንፋስ ክርስቶስ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ የአባቶቻችን ረዴት በረከታቸው ይደርብን አሜን ሀገራችን የአለም ጌታ ኢየሱስ ሰላም ያርግልን 🙏🙏🙏🙏🙏🙏

  • @user-hq7pz7zx1p
    @user-hq7pz7zx1p Před 5 měsíci +2

    በርቺልን እህታችን ከዚ በላይ ጸጋሽን ያብዛልሽ ።

  • @nathan_mamo
    @nathan_mamo Před 5 měsíci +1

    ዶክተር ከፈጣሪ የተላክሽልን የማንቂያ ደውላችን ነሽ ! ልብ ያለው ልብ ይበል ! እረኛ እንደሌለው በግ ተቅበዘበዝን : : እንንቃ እንመርምር መልካም እውቀት አርነት ታወጣለች !!!!!

  • @user-ig2rz7to8f
    @user-ig2rz7to8f Před 4 měsíci +1

    የትውልዶች ታሪክ ሲነዛነዙ መዋል ማደር ለአንቺ ለራስሽ አይጠቅምሽም እንኳን ለሰሚው ሰው ካመነ ይድናል ካላመነ አሁን ተፈርዶበታል ሁሉ ከእርሱ በእርሱ ለእርሱ ነው በማንም ላይ የተንጠለጠለ ክርስትና የለም የማዕዘኑ እራስ ክርስቶስ ነው በክርስቶስ ጤናማ ትምህርት ሲኖር ሄዶ ይጋጠማል አለቀ።

  • @samsonabraha9536
    @samsonabraha9536 Před 5 měsíci +1

    ዳ/ር ትክክል ደቂቆቹ በዛን ሰሐት ያሴሩት ሴራ ዉጤት ነዉ አሁን እኛ ያለንበት :አሁን የማረብሹት የደቂቆቹ እፉኝት ልጆች ናቸዉ !!! ሕዝባችን ስለተኛ ያዉም የሚሰራዉን ሴራ በይፋ እያየዉ ነዉ : እንዳንች ያለ 10 አስተማሪ ያስፈልጋል : ወይም አንች 10 ስተምሪ: በርች 🙏🙏🙏💚💛❤👍👍👍

  • @maneaylegne3354
    @maneaylegne3354 Před 5 měsíci +1

    ዶ/ር እናመሰግናለን

  • @muluyeasegahegn487
    @muluyeasegahegn487 Před 5 měsíci +3

    በርቺ!
    כל הכבוד!

  • @qorontosmedia
    @qorontosmedia Před 5 měsíci +2

    ሠላም ዶክተር መስከረም እንኳን ደህና መጣሽ በጣም ጥሩ፣ ጥልቅ ሀሳብ የያዘ በዕውቀት ላይ የተመሰርተ ትንታኔ እና ማብራሪያ ጋር በማስረጃ የተደገፈ መሆኑ በጣም ጥሩን ግንዛቤ የሚፈጥር ነው። እግዚአብሄር አመላክ በዕድሜ በጸጋ ይጠብቅሽ ፣ ከነ ቤተሰብሽ ሠላም እግዚአብሄር ይብዛልሽ ። በሌላ ሠራ እስካግኝሽ ሠላም እንሰንብት አሚን!

  • @geletawaka
    @geletawaka Před 5 měsíci +3

    መስከረም እግዚአብሔር ይባርክሽ መልስ መመለስሽ ጥሩ ነው ልቦናቸውን ከፍተው ማዳመጥ ካልቻሉ ምንም ዋጋ የለውም

  • @FitsumTesfaye-si7sc
    @FitsumTesfaye-si7sc Před 5 měsíci +3

    ❤❤❤ እናመሰግናለን እህታችን!

  • @adanewoldemariam3630
    @adanewoldemariam3630 Před 5 měsíci +1

    እናመሰግናለን እህታችን

  • @Helenita27
    @Helenita27 Před 5 měsíci +3

    ዶክተር ፈጣሪ እድሜና ጤና ይስጥሽ❤ ይሔ ትውልድ በዘረኝነት የበሰበሰ የማያነብ ነጭ አምላኪ ትውልድ አክቲቪስትና ዘረኛን ብቻ ሚከተል ትውልድ ስለበዛ ሀሰተኛን እንደ ፃድቅ ሚያይ ትውልድ በዛ የፕሮቴስታንት ዘማሪ ፊልም እሰራለሁ ስትል ነበር ስለ ደቂቀ ስጢፋ የዛኔ ነው በጣም የገባኝ ከመናፍቃን ጋር ያላቸውን ዝምድና

  • @user-oh9vv8fb4z
    @user-oh9vv8fb4z Před 5 měsíci +1

    ትምህርትሽ ከማር ይጣፍጣል እግዛብሄር ይስጥልኝ

  • @melkamumitkue2990
    @melkamumitkue2990 Před 5 měsíci +1

    በእውነት ዶክተር ቃለ ህይወት ያሰማልኝ የአገልግሎ ዘመንሽን መንፈስ ቅዱስ ይባርክልሽ

  • @birukadane8022
    @birukadane8022 Před 5 měsíci +1

    እናመሰግናለን እውነታው ይሄው ነው

  • @tsionpetros4979
    @tsionpetros4979 Před 5 měsíci +1

    ቃለ ህይወት ያሰማልን እህታችን! ከማስረጃ ጋር የተደገፈ እውነተኛ ትምህርት ስላካፈልሽን በርቺ❤❤❤

  • @user-kx5ox4lh1q
    @user-kx5ox4lh1q Před 5 měsíci +2

    God bless you and your families

  • @user-cc2we2bl9c
    @user-cc2we2bl9c Před 5 měsíci +2

    Let God Bless you and your family. Keep searching the truth. God is with the truth. Your explanation flash light of wisdom for those who want to know the truth and encouraging them to examine doctrines thoroughly and spiritually.

  • @segedumengistie1009
    @segedumengistie1009 Před 5 měsíci +2

    እናመሰግናለን እህታችን። ጤና እና ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን። በስራሽ ትውልድን እና የ ኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን እየታደግሽ ስለሆነ ፤ ብርታቱን ጥናቱን ይስጥሽ።

  • @yeqedusantube6529
    @yeqedusantube6529 Před 5 měsíci +5

    Dr You are a true Christian, keep revealing the truth

  • @kidestwselasi
    @kidestwselasi Před měsícem

    እናመሠግናለን ዶ/ር እውቅና ሰጠች አይነት ንግግር ከአንዳንድ ሰው ሰማሁ እና የዮዲት ጉዲትን ታሪክ ይሻሩታ ክህደት የጀመረበትን ዘመን ይነግሩናል መልሰው ከወዴት ነው ይሉናል እኔ የሚገርመኝ አንድ ቦታላይ ቆመን መተማመን ላቃተን ነው የማዝነው በርቺልን

  • @Agenda-2016
    @Agenda-2016 Před 5 měsíci +3

    ዶክተር እግዚአብሔር ይባርክሽ። የእውነት ድምፅ በመሆን እነዚህን አውቆ አበዶች፥ በጨለማ የሚዳክሩትን ግፈኞች በማጋለጥሽ እንወድሻለን። መፅሀፍሽንም በደንብ ተሰንዶ ለትውልድ ማሰተላለፍ አለብን። አሁን በአገራችንና በቅድስት ቤተክርስቲያናችን ላይ እየሆነ ያለው ግፍና መከራ እንድንረዳ ይጠቅማል። Mussolini, አባ እስጢፋ፤ አብይ፥ ዳንኤል ክብረት ፤ ጌታቸው ረዳ፥ አቶ ሰረቀብርሃን together come to mind.

  • @user-bt9wm6dn9s
    @user-bt9wm6dn9s Před 5 měsíci +2

    በተተነተነ ማስረጃ እያመሳከርሽ ግልፅ ማድረግሽ በራሱ የእውነት ሰው መሆንሽን ያረጋግጣል።
    ጀግኒት🙏🏿 በርቺ✊🏿
    ደሞ አትጥፊ 👈🏿 ቶሎ ቶሎ ፖስቺ🙏🏿

  • @alehegnbitew1803
    @alehegnbitew1803 Před 5 měsíci +1

    Let our God bless you. W have learnt a lot. Wish you long age. I always proud of you as I was your student.

  • @user-bl7so7kx8h
    @user-bl7so7kx8h Před 4 měsíci

    እግዚዖ መሃረነ ክርስቶስ ? የስው አ ልቦና ? እባክህ ጌታ ሆይ በምህረትህ ጎብኘን ?????

  • @aberashregassa2584
    @aberashregassa2584 Před 5 měsíci +1

    በርቺልን መስኪዬ እናመሰግናለን

  • @hassenoumer8936
    @hassenoumer8936 Před 5 měsíci +9

    ዶከተርዬ እግዚአብሔር ይባርክሽ እኔ ጴንጤ ነኝ ሆኖም ግን ስለ ደቂቀ እስጢፋኖስ ብዙጊዜ ቸርች ውስጥ ሲነገር እሰማለሁ ግን ሙሉ መረጃ እንደሌላቸው ያሳብቅባቸዋል ሁለተኛ ኦርቶዶክስን በመጥላት ነው ስለሆነም ጥሩ መረጃነው ያወጣሽው እናመሰግናለን

    • @ethioboys10
      @ethioboys10 Před 5 měsíci

      ወንድም ወይም እህት ! እያንዳንዷን ትምህርቷን አዳምጥ ደቂቀ እስጢፋኖስ የሚለው መይሐፍ ይነበብ ከተቻለ ሌላዎቹ ሁለቱ መጽሐፍ ቢኖረዎት ይጠቅማል ። እኔ ደቂቀ ስጢፋኖስን ስጦታ መስጠት እችላለው። በተረፈ በፕሮቴስታንት ውስጥ ያለውም ውሸት ትንሽም ቢሆን ፍንጭ ማግኘትህ እና መባነንህ መልካም ነው ሌለውንም ለመረዳት ይቀላል።

  • @salamrita2646
    @salamrita2646 Před 5 měsíci +1

    እናመሰግናለን ዶክተር ❤

  • @epheramwondmu3601
    @epheramwondmu3601 Před měsícem +1

    ሼር ላይክ ሼር ሼር አድርጉ ትውልድ አትርፋ ይህ አይከብድም ሼር ሼር ሼር❤❤❤❤

  • @YoniMan-iu8ro
    @YoniMan-iu8ro Před 5 měsíci +1

    ዶ/ር እስቲ ሀሌታ ሚድያ ለሚያወሩት ወሬ አንዳንድ ነገር በያቸው ። ግዜ ካለሸ !!

  • @endalkachewlakew1866
    @endalkachewlakew1866 Před 5 měsíci +4

    ዶ/ር እግዚአብሔር የገለጸልሽን እውቀት ስላካፈልሽን ቃለ ህይወት ያሰማልን። ቀሪው ዘመንሽ የተባረከ ይሁን።

  • @user-gg4hq5uq4e
    @user-gg4hq5uq4e Před 5 měsíci +1

    ኑሪልን::

  • @user-vs6ef4vd4k
    @user-vs6ef4vd4k Před 5 měsíci +10

    የእውቀት ማህደራችን ሐኪማችን እንኩዋን ደህና መጣሽልኝ ረጅም እድሜ ከጤና ይስጥልን ❤️🙏

  • @AncientEthiopia1279
    @AncientEthiopia1279 Před 5 měsíci

    እግዚአብሔር ይስጥልን ይጠብቅልን

  • @AmelonZewdu
    @AmelonZewdu Před měsícem

    በእውነት አንቺ እንዳልሺው መልአኩ እውነቱን ገልጦልሻል።

  • @tsedenaynessibu3006
    @tsedenaynessibu3006 Před 5 měsíci +1

    ትክክል ነው የኢትዬጵያን ታሪክ ለማጥፊት ብዙ ጠላት አላት ምክናያቱም እግዚአብሔርን በትክክል አምና ሳትበረዝ መኖሯ ለሰይጣን አስተሳሰብ ለሚከተሉት ሁሉ ጥላት ነች እና!!! በቅኚ ግዛትም ለመያዝ ሳይችሉ ስለቀሩ ዛሬ የኞ ዘመን ሰወች ምንም አይነት እውቀት ሳይኖረን የ
    ምእራባዊያን ታሪክ በነሱ ቋንቋ አንብበን እናቃለን የሚሉና በገንዘብ የተገዙ ናቸው:: ሆኖም ቃል ኪዳን አለን እግዚአብሔርም ብዙ ጥሩ እውቀት ያላቸውን እያስነሳልን ( አንች አንዷ ነሺ) ትምህርቱን እያስተማራችሁን ነው:: የጠባብ የዘረኚነት በሺታ ይዟን ወደሰይጣን እየመራን ነው:: እባካችሁ የኞ ዘመን ሕዝብ እንማር እንወቅ ለመናገርና ለመቃወም ከመነሳታችን በፊት እንማር!!!! ትንሺ እውቀት ለብዙ ጥፋት ያጋልጠናልና:: ይህ ነው አሁን ለመጣብን ችግር ሐገራችንን ሐይማኖታችንን አንበጥብጥ:: ሁላችንም እዚህ ለዘለአለም አንኖርም ለነፍስም ለስጋም እንኑር!! መቸ ነው የምንነቃው:: እግዚአብሔር ን እንፍራ የሱ አማኞች ከሆንን🙏

  • @fitsumbereket7392
    @fitsumbereket7392 Před 5 měsíci +3

    Welcome!

  • @mekdesworku4765
    @mekdesworku4765 Před 5 měsíci

    እህታችን፣ መ ም ሕራችን ፣ውዲቷ፣ ዶክተር መስከረም ደቺሳ፣ ወቅታዊ አንገብጋቢ፣ ተዳፍኖ የኖረውን አገራ ችንን ሃይማኖታችንን የሚቦረቡረውን ነቀርሳ እየመረመርሽ ውስጡን ስላሳወቅሽን የኛ መድኃኒ ዓለም መድኃኒቱን ይግለጽልን፣ አንቺንም ይጠብቅሽ፣ የራቀውን አቅርቦ፣ የተከደነውን ገልፆ ያሳይሽ፣፣ በርቺልን። የቤተክርስቲያናችን መ ም ህራንና ካህናት፣በገንዘብ ፍቅር ተጠምደውብናል።

  • @haimanotneguse2208
    @haimanotneguse2208 Před 5 měsíci +1

    ተባረኪ ያለኝን ብዥታ መስመር እንዲይዝ አድርገሽኛል ቃለሂወት ያሰማልኝ ።❤

  • @BH-xl1mo
    @BH-xl1mo Před 5 měsíci +8

    የዘር በሽታ ያለበትን ሰው አክሞ ለማዳን በጣም ከባድ ነው:: እግዚአብሔር መድሀኒቱን ይግለፅልን

  • @tamene1525
    @tamene1525 Před 5 měsíci +2

    💚💚💚💛💛💛❤❤❤