Tilahun Gessesse - Kome Limerkish | ቆሜ ልመርቅሽ - New Ethiopian Music 2021 (Official Video)

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 27. 08. 2024
  • Ethiopian Music : Tilahun Gessesse | ጥላሁን ገሰሰ - Kome Limerkish | ቆሜ ልመርቅሽ - New Ethiopian Music 2021 (Official Video)
    Subscribe: goo.gl/vdthqb
    Facebook : / hopemusicethiopia
    Instagram : / hope_music_ethiopia
    Twitter : / hopemusicent
    Google+ : plus.google.co...
    Get The Latest Brand New Ethiopian Musics and More Ethiopian Entertainment Videos by Subscribing Here: goo.gl/vdthqb
    #HopeMusic #EthiopianMusic #Ethiopia
    unauthorised use, distribution and re upload of this content is strictly prohibited
    Copyright ©2021 Hope Entertainment

Komentáře • 1,7K

  • @user-wv6bg7pz8u
    @user-wv6bg7pz8u Před 3 lety +927

    የድሮዋን ኢትዮጵያ የናፈቀ ?
    እንደኔ የሃገሩ ሰላም ያሳሰበው ላይክ ይግጨኝ!

    • @medihabesha1541
      @medihabesha1541 Před 3 lety +1

      😭እኔ😭

    • @nanidh5642
      @nanidh5642 Před 3 lety

      እኔ። ✋

    • @user-wj4bv8fe7o
      @user-wj4bv8fe7o Před 3 lety

      😹😹😹😹😂😂

    • @Iselassiei782
      @Iselassiei782 Před 3 lety +3

      አንድ ኢትዮጵያ . . . ዛሬም. . . ነገም . . . . ለዘለዓለም 💚💛❤

    • @meazagebrehiwot5600
      @meazagebrehiwot5600 Před 3 lety +6

      እኔ በጣም የድሮዋን ኢትዮጵያ ዘር ቀለም ሃይማኖት ሳንለይ ትምህርት ቤት ሄደን በሰላም እቤታችን የምንመለስበት ጎረቤት ልጁን ቤቱን አደራ ብሎ የሚሄድበት ግዜ ናፈቀኝ

  • @user-zq8df3is7w
    @user-zq8df3is7w Před 3 lety +395

    ቆሜ ልመርቅሽ …… ተቀበይኝ እማ
    ሕይወትን ​መርቀሽ …… ሰጥተሽኝ እኔማ
    ይህ ቀረኝ የምለው፣ …… የሚቆጨኝ በዓለም
    ኢትዮጵያ ዕድሜ ላንቺ፣ ያላየሁት የለም።
    አንገትሽ፣ ራስሽን፣ … ችሎ ልየውና
    ማግሥቱን ይውሰደኝ፣ አሥር ሞት ይምጣና።
    ጋሽ ጥላሁን ነፍስህን ይማረው

    • @Enkokelish
      @Enkokelish Před 3 lety +16

      ግንባር ቀደም በመሆን የምትሰጫቸው አስተያየቶች, ድፍረትሽንና የአስተሳሰብ አመለካከቶችሽን ያመላክታሉ።
      ዛሬ ቢያንስ የጥልዬን የሙዚቃ የግጥም ስንኞች ጊዜ በመውሰድ ፊደልና ሀረግን በጥንቃቄ በማቅረብሸ ከወዲሁ እሰየው ለማለት ነው።
      የፎቶ ምስልሽን ብቻ በማገናዘብ አንች በማለቴ ይቅርታ፤
      መልካም ጊዜ

    • @zenagech447
      @zenagech447 Před 3 lety +5

      በምጀመርያ ይምተጠቃማው ፎቶ የራሷ አይደላም ከሷ ጥሮ አስተያየት ማየት ከችድ ወስጥ መርፍይ አንደማገንት ነው

    • @oromiyabirthoromo1916
      @oromiyabirthoromo1916 Před 3 lety +2

      ❤🌳❤👈💪💪💪💪💪 forever tlahun and O blood oromo

    • @tigistashenafi276
      @tigistashenafi276 Před 3 lety +3

      @@oromiyabirthoromo1916 Are you talking about "oromo blood" ምናምን ? Are you thirsty ? You and your people slaughting people everywhere not enough that for you? You know what soon or later you and your people will pay that back.

    • @tigistashenafi276
      @tigistashenafi276 Před 3 lety

      @@user-xx9eo1cn3m I don't think you got my point? 🤔😇😇Never mind .

  • @mulualemfetene7441
    @mulualemfetene7441 Před 3 lety +211

    ብሔራዊ መዝሙር ሊሆን የሚገባው እጅግ ታላቅ የጥበብ ውጤት ።

    • @juliobela5846
      @juliobela5846 Před 3 lety

      ሀገር ፃታ የለውም ምን አይነት ደደብ ሰው ነው ሰውዬው

    • @esmaelsalih2045
      @esmaelsalih2045 Před 3 lety

      Lkhalk

    • @badruareb3738
      @badruareb3738 Před 3 lety +1

      @@juliobela5846 Tasastekal hager bizu gize be set new mixeraw iski Andi boota minaw behrawi mezmur layis be wondi new inde mixeraw bizu muzika lay be set new Innat ager adel mibalaw

    • @powerentertainment719
      @powerentertainment719 Před 2 lety +1

      @@juliobela5846 tebeda kante belay dedeb yet ale.

    • @juliobela5846
      @juliobela5846 Před 2 lety

      @@badruareb3738 አባት ራሽያ

  • @kefelegnteshome1631
    @kefelegnteshome1631 Před 2 lety +4

    ፈተናው አይለቅ የሚፈታተንሽ
    አንገትሽ ራስሽን ችሎ ልየውና
    ማግስቱን ይውሰደኝ
    አስር ሞት ይምጣና፡፡

  • @amansalomao3449
    @amansalomao3449 Před 3 lety +1027

    First viewer from Asmara, Eritrea 🇪🇷. Much love to our Ethiopian brothers and sisters. Much love ❤️

    • @forwaliya1754
      @forwaliya1754 Před 3 lety +10

      congra!!! is it now allowed to hear amharic music???

    • @mirrijacob7533
      @mirrijacob7533 Před 3 lety +9

      @@forwaliya1754 no. They sensor everything in eritrea. Only eri tv is allowed.

    • @mirrijacob7533
      @mirrijacob7533 Před 3 lety +8

      @@forwaliya1754 he is not from Asmara . He is living outside eritrea. Everyone is in house arrest in eritrea. You can't go out.

    • @tilahunsalas8144
      @tilahunsalas8144 Před 3 lety +25

      We love you too our Eritrean brother! One blood!

    • @adonaydimartini6130
      @adonaydimartini6130 Před 3 lety +2

      @@forwaliya1754 why not

  • @lijalemdcsa
    @lijalemdcsa Před 2 lety +21

    " ...ፀሎትሽ ይሰማ አምላክ ይለመነሽ ፣
    ፈተናው አይለቅ የሚፈታተንሽ ..."

  • @user-bo5th7ne3f
    @user-bo5th7ne3f Před 2 lety +14

    ጥልዬ እኔ በተቻለኝ ሀገሬ ኢትዮጵያ አንገቷ እራሷን ችሎ እንዲቆም ለማድረግ እሰራለሁ!!! ኢትዮጵያዬ መተኪያ የሌለሽ ሀገራችን ክፉሽን ያስቀረው። አሜን

  • @unknownboy4587
    @unknownboy4587 Před 3 lety +20

    የዉስጥን ሀገራዊ ፍቅር ፈንቅሎ የሚያወጣ ድንቅ ጥዑም ዜማ። ይህ ዘፈን ብሄራዊ መዝሙር ቢሆን እንዴት ደስ እንደሚል። ክብር ስሙ ከመቃብር ከፍ ላለሁ ሁላችንም ለምንወደዉ ጥላሁን ገሠሠ ይሁን።

  • @petrosmono
    @petrosmono Před 3 lety +54

    ለአንቺ የማይተኙ የማይንቀላፉ
    ብን ይበሉ እንደ ጉም ከምድረገፅ ይጥፉ 🔥🔥🔥
    ኢትዬጲያዬ 💚💛❤️

  • @yeabtazreact
    @yeabtazreact Před 3 lety +192

    ቃል የለኝም የኔ ንጉስ በቃ ቃል የለኝም ተውኝ 😭😭😭😭🙏🙏🙏❤️❤️❤️ የድሮዋ ኢትዮጵያ የት ሄደች እባካቹ ከዚህ ነች በሉኝ

    • @mow0wmo408
      @mow0wmo408 Před 3 lety +1

      አይዞን😭😭😭😥እርስ በርስ ተባላን😢😢😢💞💋

    • @Abe8803
      @Abe8803 Před 3 lety +1

      ምን እንደምል አላውቅም ጥሌ አባታችን አሁን የደረስንበትን ብታይ ምን ያህል ታዝን ነበር ሳታይ ማለፍህ እግዚአብሔር ይወድሀል ነፍስህን ይማርልን ፈጣሪ 🙏🙏🙏

    • @edtad9549
      @edtad9549 Před 3 lety

      I feel the same way brother!

    • @ethiopialove9780
      @ethiopialove9780 Před 3 lety

      😭😭😭😭😭

    • @tsiyonfantu6819
      @tsiyonfantu6819 Před 3 lety

      Entsley ye tile amlak alee

  • @mac-cyber
    @mac-cyber Před 3 lety +1

    በህይወት ስትኖር ስለህዝብህ ስለሀገርህ በመድረክ ላይ በፍቅርህ እያለቀስክ ብዙዎቻችንን ሀገር ምን ያህል ክብር እንደሆነ ያስተማርከን፣ ላገርህ የተመኘኸውን የሚቀጥለው ትውልድ እንዲያውቀው እስከመጨረሻው የህይወትህ ትንፋሽ በዜማ ያወረስከን፣ ታላቁ የኢትዮጵያ የሙዚቃ ንጉስ፣ ስጋህ ተለይቶናል ስራህ ግን ፣ ያላፈቀረን እንዲያፈቅር፣ የተጣላን እንዲታረቅ፣ የናፈቀን እንዲገናኝ ፣ ያዘነውን የተጎዳውን እንዲበረታ፣ ያጣን እንዲያገኝ በዜማዎችህ ልዪ የሆንከው ጥልዬ፣ ለኛ አልሞትክም በዜማዎችህ ከኛ ጋር ዘመን እስከ ዘመን ትኖራለህ።
    ማክ

  • @Meaziye
    @Meaziye Před 3 lety +36

    ሞቶ መኖር እንዳንተ ነው ጋሸ ጥላሁን። ነፍስህን ይማርልን።

  • @mnaddismereja
    @mnaddismereja Před 3 lety +296

    የትልቁች ትልቅ ድንቅ ትውልድ በነጥሌ ዘመን ተወልዶ ኖሮ የሞተ ምነኛ ታደለ በሞትም እንቀና ጀምር ሀገራችን ወደቀድሞ ሀያልነቷ ትመለስ ዘንድ ሁላችንም በየሀይማኖታችን እንፀልይ፡፡
    ኢትዮጵያ ፀሎትሽ ይሰማ ♥♥♥

    • @edtad9549
      @edtad9549 Před 3 lety +1

      Truly said, all I hope for is to be back to those good old days!

    • @shegerketema6622
      @shegerketema6622 Před 3 lety

      RASESHN CHELSH AWRI

    • @juliobela5846
      @juliobela5846 Před 3 lety

      ጅል የሆነ ሰውዬ ቲሽ 🤦‍♀️

    • @abukred5630
      @abukred5630 Před 2 lety

      Ketselotim betechemari yegna astewatso akm ysetal

  • @habhailu3312
    @habhailu3312 Před 3 lety +49

    እንዴት መታደል ነው በዚህ ጊዜ ይሄን የከበረ ድምፅ መስማት .....አወይ ቢኖር

    • @kardon4996
      @kardon4996 Před 3 lety +1

      Dimtsu Eko trwedadari yelewim yigermegnal

    • @juliobela5846
      @juliobela5846 Před 3 lety

      ሀገር ፃታ የለውም ምን አይነት ደደብ ሰው ነው ሰውዬው

    • @powerentertainment719
      @powerentertainment719 Před 3 lety

      @@juliobela5846 shele zim bel

    • @habeshawit2008
      @habeshawit2008 Před 3 měsíci

      O yeah. በስጋ ቢለየንም በድምጹ እና በስራዎቹ ህያው ነው. Respect Gash Tilahun💚💛❤️

  • @peace4all178
    @peace4all178 Před 3 lety +251

    Guys, I’m crying listening to this amazing music. Ebakih Egziabhere hoy yikir belen. Thanks Dr. Tilahun Gessese.

  • @lomiyoutube7599
    @lomiyoutube7599 Před 2 lety +15

    ሰምቼ የማልጠግበዉ እንባ ይቀድመኛል ኡፍ እምዬ ኢትዮጲያ ሰላምሽ ይብዛ 😢😢
    ስም ከመቃብር በላይ ነዉ አርቲስት ጥላሁን ገሰሰ የምወድህ ነፍስ ይማር 😢😢😢💔

  • @hiwetwebtaye3662
    @hiwetwebtaye3662 Před 3 lety +37

    ኢትዮጵያዬ ላንቺ የማይተኙ የማያንቀላፉ
    ብን ይበሉ እንደጉም ከምድረ ገፅ ይጥፉ👌አሜን
    ነብስ ይማር ዶ/ር ጥላሁን ገሰሰ 😥

    • @juliobela5846
      @juliobela5846 Před 3 lety

      ሀገር ፃታ የለውም ምን አይነት ደደብ ሰው ነው ሰውዬው

    • @hiwetwebtaye3662
      @hiwetwebtaye3662 Před 2 lety

      ሀገር በእናት ትመሰላለች!! እናት ደሞ እናት ናት ገባክ💚💛❤

    • @kor405
      @kor405 Před 2 měsíci

      Amen !!!
      ❤❤❤

  • @roba-raze6029
    @roba-raze6029 Před 3 lety +160

    የኔ አባት ነፍስህን ይማርልን ሁሌም እንወድሀለን🥲🥲

  • @abiybekele1131
    @abiybekele1131 Před 3 lety +9

    ጥሌ አንተ ምተህም አትሞትም ምክንያቱም አንተ የኢትዮጵያ ንጉስ ሰለሆንክ እግዚአብሄር ነፍስህን በገነት ያኑረው 🙏🙌🙌👌👍👏👏👏

  • @Rihu1000
    @Rihu1000 Před 3 lety +79

    SOMETHING STUCK IN MY THROAT AND CAN'T STOP CRYING WHEN I LISTEN THIS SONG OH.....
    MAY ALLAAH PROTECT OUR BELOVED COUNTRY "EMA EMA ETHIOPIA"

  • @getugebere2410
    @getugebere2410 Před 3 lety +17

    አውሮፕላን መጣ እየገሰገሰ ከዘፈን አንደኛ ጥላሁን ገሰሰ 😭😭😭😭😭😭😭😭ነብስህን በአጸደ ገነት ያኑርልኝ እንወድሃለን

  • @user-ny7qm3xn1d
    @user-ny7qm3xn1d Před 3 lety +66

    ጥልዬ ይህንን ጉድ ስላልዬህ ታድለሃል በመድረክ በአይኖችህ ስሟን ስትጠራ እንባህ በመታው ሲፈስ እኮ የ90 ትውልዶች በሽጉጥ በቀስት. እየተገደልን ነው ኢትዮጵያ ስላልን ብቻ 😭😭 ኢትዮጵያ ታላቅ ነበረች ትልቅም ትሆናለች

    • @kardon4996
      @kardon4996 Před 3 lety

      Esunis man yaredew meselesh !!!.....enesu Eko nachew ........
      Demo yaswerut were girim yemil new .........
      Gin bezegenut Kuna yibal yele.........

  • @justflight88
    @justflight88 Před 3 lety +46

    Full love to Emma Ethiopia ❤️🥺 IAM from Sudan and I love Ethiopia ❤️ I reject the war any where and I hate politics

  • @hamudhassen9481
    @hamudhassen9481 Před 2 lety +6

    😭😭😭💚💛❤🇪🇹🇪🇹🇪🇹 እምዬ ኢትዮጵያ ፈጣሪ መከራሽን በቃ ይበለሽ!!

  • @burteethiopia6018
    @burteethiopia6018 Před 3 lety +44

    ኢትዮጵያ ዬ ሰላምሽ ይብዛ የድሮዋ ኢትዮጵያ ን ማየት እንዴት እንደ ናፈቀኝ 😭😭😭💔💔💔

    • @juliobela5846
      @juliobela5846 Před 3 lety

      ሀገር ፃታ የለውም ምን አይነት ደደብ ሰው ነው ሰውዬው

    • @burteethiopia6018
      @burteethiopia6018 Před 3 lety

      @@juliobela5846 ደደብ እራስህ ሳጋጤ

  • @90smusic52
    @90smusic52 Před 3 lety +25

    ጋሽ ጥልየ የሙዚቃው ንጉስ ሁሌም በልባችን ነህ መቸም አንረሳህም ትናፍቀናለህ ነፍስህን በአፀደ ገነት ያኑራት ነፍስ ይማር❤❤❤❤❤

  • @user-nl3pv4rn9r
    @user-nl3pv4rn9r Před 3 lety +6

    አንገትሽ ራስሽን ችሎ ልየውና ማግስቱን ይውሰደኝ አስር ሞት ይምጣና..... 😢
    ክቡር ዶክተር አርቲስት ጥላሁን ገሰሰ ስላንተ ቃል የለኝም ብቻ ሁሌም ስራህ ከመቃብር በላይ ነው ልባችን ውስጥ ታትሞ ይኖራል። አሁንስ ምናለ ቀና ብለህ እማማን ብታያት 💚💛❤️😭

    • @juliobela5846
      @juliobela5846 Před 3 lety

      ሀገር ፃታ የለውም ምን አይነት ደደብ ሰው ነው ሰውዬው

    • @powerentertainment719
      @powerentertainment719 Před 3 lety

      @@juliobela5846 አንች ሹጥ አውቀሽ ሞተሻል።

    • @user-nl3pv4rn9r
      @user-nl3pv4rn9r Před 3 lety

      @@juliobela5846 ቱ ስግጥና

  • @yeshi7143
    @yeshi7143 Před 3 lety +7

    በናተ ዘመን ቀረ የሙዚቃዉ ቃና የሰዉ ፍቅር መከባበር እረ ስንቱ ነብስህን ይማረዉ 💔💔🖤🖤😭😭😭

  • @abushgurmu4006
    @abushgurmu4006 Před 3 lety +11

    ትውልድ የሚያንፅ የዘመናት የጥበብ ምግብ የሆነ ስራ ግሩም ድንቅ።እባካችሁ የኔ ዘመን ትውልዶች የታላላቅ አባቶቻችንን ጥበብ አትግደሉ።

  • @tsedeymengesha3794
    @tsedeymengesha3794 Před 3 lety +20

    ታላቁ ሰው! ለውዲቷ ኢትዮጵያ ዘመን በማይሽረው መረዋ አንደበትህ የዘመርክላት፣ ያለቀስክላት፡ ከአልፈትህም በኋ የምትወደድ የኢትዮጵያ ልጅ ሁሌም እናከብርሃለን። RIP

  • @user-zx3og9jd5s
    @user-zx3og9jd5s Před 3 lety +12

    አፈሩን ገለባ ያርግልህ አባቴ🇪🇹❤🇪🇹 እማማ ኢትዮጵያ ሰላምሽ ይብዛ 😭

  • @massymebrate3475
    @massymebrate3475 Před 3 lety +9

    ሀገሬ አምናለው ይህን ቀን አልፎ እንደ ተርት ተርት እንደ ሚወራ 😥😥😭😭ኢትዮጵያ ጠላቶትሽ ወደ መቃበር ይወርዱ ሀገሬ ከፍ በይ ❤😍

  • @mimitsige2783
    @mimitsige2783 Před 3 lety +33

    "ቆሜ ልመርቅሽ"አዎ መርቁልን የቀድሞ ፍቅራችን ይመለስልን !!🙏💚💛💓

    • @juliobela5846
      @juliobela5846 Před 3 lety

      ሀገር ፃታ የለውም ምን አይነት ደደብ ሰው ነው ሰውዬው

    • @YahyaAmbaye
      @YahyaAmbaye Před 6 měsíci

      የደደቦች መሪ ብትባል ይመጥንሀል? ሀገር ሁሌም በእናት ነው የምትመሰለው ሀገር እናትም ናት ይግባህ በጥብጠው ብግቱህም የምገባህ አይነት ሰው እንዳልሆንክ ከኮመንትህ መረዳት ይቻላል ምሳሌ ልስጥህ አሜሪካ ኢራንን አስጠነቀቀች ኢትዮጵያ ቡናዋን ለዓለም ገበያ አቀረበች ራሽያ ዩክሬንን በሚሳኤል መታች ነው እንጂ በተቃራኒ ጾታ የምጠራ ሀገር የለም አሜርካ ኢራንን አስጠነቀቀ ስባል ሰምተህ ከሆነ ከሰው ጋር ሳይሆን አንተ የሰይጣን የቅርብ ጎደኛ ነህ ማለት ነው ደግሞም ነህ ስለ ኢትዮጵያ እንድህ ስወደስ አወዳሹን ደደብ ብለህ መሳደብህ አንተን ነው ድድብናህንና ድንቁርናህን ያሳየብህ እንድየው ባገኝህ ነበር ለግዜው ይበቃሀል

  • @travelhabesha
    @travelhabesha Před 3 lety +23

    Tilahun will forever be a Legend!!! የኢትዮጵያ እና የጥላሁን አድናቂዎች እስቲ እንያችሁ!! 🇪🇹 👍🏾

  • @hinahina4144
    @hinahina4144 Před 2 lety +5

    ሰም ከመቃብር በላይ ሲዉል እዲህ ነዉ ብሄራዊ መዝሙር መሆን የነበርበት ምርጥ ሰሜትን የሚሰጥ ዘፈን ነዉ የእዉነት በተለይ ባለንበት ሆኔታ ሲታይ😭😭 ጥሌ ነብሰህን ይማርልን

  • @jegnaserawit4477
    @jegnaserawit4477 Před 2 lety +7

    ምን ያለ ግጥምመሬት የማይወድቅ ውድ ኢትዮጵያችንን የሚገልጥ ግሩም ውብ ዝማሬ!!!!!!!!!!!!!

  • @orionentertainment6157
    @orionentertainment6157 Před 3 lety +44

    ክቡር ዶክተር አርቲስት ጥላሁን እናመሰግናለን ከልብ እንወድሃለን ነብስህን በገነት ያኑርልን

  • @ethiopianpoliticsaddisababa

    ባንዲራው ግን ኢትዮጵያን አይወክልም ኮከቡ የህውሃት ነው ጥሌ ኢሄን ባንዲራ አፈልግም
    ንፁውን የእምዬን ኢትዮጵያ 💚💛❤️
    ምርጥ ሙዚቃ 👏👏

    • @Sofi-ks3zo
      @Sofi-ks3zo Před 3 lety +1

      የበሰበሰ ዳይሬክተር ነው በሌላ ሰው ዘፈን ቢሆን እሽ በጥሌ ዘፈን ይሄ አይገባውም

    • @mohammedmowlidabdulahi3627
      @mohammedmowlidabdulahi3627 Před 3 lety +1

      Lenfah ye shrmuta lij ..ena ye derg bandir feleka

    • @suzanasiraj
      @suzanasiraj Před 3 lety +1

      This is not what we should be focusing on right now. It really doesn’t matter which flag as long as we have the same love for our country 🇪🇹

    • @ETBeMore
      @ETBeMore Před 3 lety

      Well said!! It doesn't represent TILAHUN

    • @ETBeMore
      @ETBeMore Před 3 lety

      @@suzanasiraj It matters for some.

  • @binipunk4212
    @binipunk4212 Před 3 lety +3

    ቆሜ ልመርቅሽ …… ተቀበይኝ እማ
    ሕይወትን ​መርቀሽ …… ሰጥተሽኝ እኔማ
    ይህ ቀረኝ የምለው፣ …… የሚቆጨኝ በዓለም
    ኢትዮጵያ ዕድሜ ላንቺ፣ ያላየሁት የለም።
    አንገትሽ፣ ራስሽን፣ … ችሎ ልየውና
    ማግሥቱን ይውሰደኝ፣ አሥር ሞት ይምጣና።

  • @jegnaserawit4477
    @jegnaserawit4477 Před 2 lety +10

    ይህ ነዉ ምስክርነት ለውድ ኢትዮጵያችን ታላቅነት !!!!!!!

  • @videoroom485
    @videoroom485 Před 3 lety +15

    Ethiopia is the cradle of humankind. The first homo sapiens emigrated from the territory of your country. In this sense, we are all Ethiopians.
    . . .
    ቆሜ ልመርቅሽ ... ተቀበይኝ እማ፣
    ሕይወትን መርቀሽ ሰጥተሽኝ እኔማ፤
    ይህ ቀረኝ የምለው የሚቆጨኝ በዓለም፣
    ኢትዮጵያ እድሜ ላንቺ ያላየሁት የለም፤
    አንገትሽ ራስሽን ችሎ ልየውና፣
    ማግስቱን ይወስደኝ አስር ሞት ይምጣና፤
    . . .
    ትንቢትሽ ይፈጸም ከመሬት ጠብ አይበል፣
    ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ ገድልሽ ይንበልበል፤
    ሰንደቅሽ ከፍ ይበል ይቁም ለዘለዓለም፣
    ሰላም ጥጋብ ደስታ ይታይብሽ ዓለም፤
    . . .
    እማማ .. ሴራው ይክሸፍበት .. እማማ .. የመታብሽ አድማ፣
    እማማ .. እጁን ሳር ያድርገው ጉልበቱን ቄጠማ፤
    እማማ .. ካቀባበለብሽ .. እማማ .. ብረት ከደገነ፣
    እማማ .. አምላክ ያግዝልሽ ላንቺ እየወገነ፤
    . . .
    ጸሎትሽ ይሰማ ... አምላክ ይለመንሽ፣
    ፈተናው አይለቅ የሚፈታተንሽ፤
    አንገትሽ ራስሽን ችሎ ልየውና፣
    ማግስቱን ይወስደኝ አስር ሞት ይምጣና፤
    . . .
    በሰው ሃገር ምድር ለተበተኑት፣
    ለልጆችሽ ሁኚ ዞሮ መግቢያ ቤት፤
    በዓለም አደባባይ ከመንግስታት ደጅ፣
    ሞልቶሽ ተርፎሽ እንጂ ጎሎብሽ አትሂጂ፤
    . . .
    እማማ .. ጎተራሽ አይጉደል .. እማማ .. አይድረቅ ሌማትሽ፤
    እማማ .. ከክፉ ሰውሮ ያድንሽ እምነትሽ፤
    እማማ .. ላንቺ የማይተኙ .. እማማ .. የማያንቀላፉ፣
    እማማ .. ብን ይበሉ እንደ ጉም ከምድረ ገጽ ይጥፉ፤
    እማማ .. ካረግንልሽ በላይ .. እማማ .. የምትሆኚልን፣
    እማማ .. መጠሪያ እናታችን አንቺው ቆዪልን . . .።

  • @dawitejoberg1224
    @dawitejoberg1224 Před 3 lety +54

    ጥልዬ!!!! 😭😭😭 ሞት የት አባቱ። ባንተ ተሸነፈ !!!! ኖረክ አልፈህ አሁንም አገርህን የምታወድስ ምርጥ ኢትዮጵያዊ ጀግና።

  • @deutschland6890
    @deutschland6890 Před 2 lety +6

    ቅኔ የሆነች ሀገር እኮ ነው ያለችን!! Thank you lord that I am Ethiopian

  • @adetube1290
    @adetube1290 Před 3 lety +5

    ቆሜ ልመርቅሽ …… ተቀበይኝ እማ
    ሕይወትን መርቀሽ …… ሰጥተሽኝ እኔማ
    ይህ ቀረኝ የምለው፣ …… የሚቆጨኝ በዓለም
    ኢትዮጵያ ዕድሜ ላንቺ፣ ያላየሁት የለም።
    አንገትሽ፣ ራስሽን፣ … ችሎ ልየውና
    ማግሥቱን ይውሰደኝ፣ አሥር ሞት ይምጣና።
    ትንቢትሽ ይፈፀም ከመሪት ጠብ አይበል
    ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ ገድልሽ ይንደልድል
    ሰንደቅሽ ከፍ በል ይቁም ለዘላለም
    ሰለም ደስታ ጥጋብ ይታብሽ ባለም
    ሴራው ይክሸፍበት
    እማማ
    የመታብሽ አድማ :
    እማማ
    እጁን ሳር ያድርገው
    እማማ
    ጉልበቱን ቄጤማ::
    እማማ
    ካቀባበለብሽ
    እማማ
    ብረት ከደገነ :
    አምላክ ያግዝልሽ ላንቺ እየወገነ
    ፀሎሽ ይሰማ አምላክ ይለመንሽ
    ፈተናው አይለቅ የሚፈታተንሽ
    አንገትሽን እራስሽ ችሎ ልየው እና
    ማግስቱን ይውሰደኝ አስር ሞት ይምጣና
    በሰው ሃገር ምድር ለተበተኑት
    ለልጆችሽ ሁኚ ዞሮ በግቢያ ቤት
    ካለም አደባባ ከመንግስታት ደጂ
    ሞልቶሽ ተርፎሽ እንጂ
    ጎሎብሽ አትሂጂ
    እማማ
    ጎተራው አይጉደል አይድርቅ ሌማትሽ
    ከክፉ ሰውሮ ያድንሽ እምነትሽ
    እማማ
    ለአንቺ የማይተኙ
    እማማ
    የማይንቀላፉ
    እማማ
    ብን ይበሉ እንደ ጉም ከምድረገፅ ይጥፉ
    እማማ
    ካረግንልሽ በላይ
    እማማ
    የምትሆኝልን
    መጠሪያ እናታችን አንች ቆልን

  • @gedionmelese1081
    @gedionmelese1081 Před 3 lety +87

    I was smiling, same time crying. This feeling is miracle !💚💛❤🇪🇹✊

  • @yifruhailu5268
    @yifruhailu5268 Před 3 lety +133

    The love and respect we Ethiopians have for our Eritrean brothers is beyond description.I personally, have never been disconnected from the people I love. My dearest friends since undergraduate school,(beginning in 1972) Bereket Goitom, Tekeste Gebremegus and of course Berhane Teklehaimanot, also affectionately known as Gucci, kept the candle of my wonderful memories of the beautiful cities of Asmara and Massawa. I love everything about Eritrea,the people and their incredible kindness is contagious, their personality captivating and their beautiful music is mesmerizing .No amount of false propaganda by our commons enemies will ever build a barrier between these two wonderful countries. The best is yet to come, we will see these two nations. flourish together and emerge as symbols of brotherhood, with peace, prosperity and incredible economic success.
    May God continue blessing both Ethiopia and Eritrea for a thousand years to come.

    • @addisneger1356
      @addisneger1356 Před 3 lety +6

      እህህ መልካሙን ግዜ አጣነዉ ።ይብላኝ ለነጣጠሉን ።ለዘረኞቹ መኖር ደጉ ።ሰላሙን አምጥቶ የተሻለ ሂወት ያኑረን ።🇪🇷🇪🇹

    • @lizjhones9455
      @lizjhones9455 Před 3 lety

      Amen

    • @TheAfroSonic
      @TheAfroSonic Před 3 lety

      Very True. I was fortunate to visit Asmara/Massawa with my kids earlier this year before COVID. Beautiful country, amazing people and we are glad the journey towards prosperity and peace have started between Ethiopia and Eritrea.

    • @kardon4996
      @kardon4996 Před 3 lety

      Ertrawiyan abeshoch nachew poletica lela hizb lela.........

  • @EMM2024-1
    @EMM2024-1 Před 2 lety +3

    ይህን ሙዚቃ ማዳመጥ ከጄመርሁ አንዴ ብቻ ሰምቼው አይበቃኝም፣ ምን አልባትም አስር ጊዜ ሪዋይንድ እያደረግሁ ደጋግሜ እሰማዋለሁ። የአንድ ሙሉ አልበም ያህል ይመስለኛል። ሙዚቃው የተደበላለቀ ስሜት ይፈጥርብኛል።

  • @wintalyrics1226
    @wintalyrics1226 Před 3 lety +37

    After hearing this music i think there is no one who wanna leave his country ethiopia🇪🇹🇪🇹🇪🇹

  • @ethioaddis5766
    @ethioaddis5766 Před 3 lety +4

    ተአምር ነው!! ጥሌ ስለሞቱም ስለኢትዮጵያም እንዲ መሆን የተነበየበት ድንቅ ስራ ነው!!

  • @ethiotiktok5203
    @ethiotiktok5203 Před 3 lety +50

    ሙዚቃ ትን ቢላት ጥልዬ ድረስ አለች አሉ ጥሌ ዘመን አይሽሬው የ ጥበብ አለቃ🙌

    • @helina3753
      @helina3753 Před 3 lety

      😄😄😄😄😄🤣🤣🤣🤣🤣🤣😃🙌🏽🙌🏽🙌🏽🙌🏽🙌🏽🙌🏽

  • @girmat.kassie260
    @girmat.kassie260 Před 3 lety +11

    ጥላሁን ገሰሰም እኛም እኩል ኢትዮጲያዊ እንባላለን። ነፍስህን በአፀደ ገነት ያኑርልን!!

  • @fikiryashenifal7116
    @fikiryashenifal7116 Před 3 lety +1

    Egziyabeher nebsikin begenet yanurew ye Ethiopia tila neke. Tilahun gessesse ante hulem be Ethiopiyanochi libi wisti tinoraleki 💚💛❤️😭🙏💪

  • @ethiokalkidanyenazretlejii7741

    ጥልዬ አንተ የጥበብ ንጉስ ነብስህን በገነት ያኑረው ኢትዮጵያዬ ነህ እኮ ያም ጥግ ድረስ

  • @BefiYad
    @BefiYad Před 3 lety +14

    ጥልዬ ሀገራችን አንገቷን እንደደፋች ነው እንኳን ኖረህ ያላየሀት 😥 አንተስ 10 ሞቱን ባንዱ ቀደምከው የኔ ጀግና ነብስህን በአፀደ ገነት ያኑርልን 🙏🙏😘😥 እማማ

    • @juliobela5846
      @juliobela5846 Před 3 lety

      ሀገር ፃታ የለውም ምን አይነት ደደብ ሰው ነው ሰውዬው

  • @teddyatsede6011
    @teddyatsede6011 Před 8 měsíci +2

    ታላቁ የኢትዮጵያ ልጅ ብርቅዬው ጥላሁን ገሰሰ እምዬ ኢትዮጵያን የምትወድ ጀግና የህዝብ ልጅ ለሀገርህ ለህዝብህ ያለህ ፍቅር ታላቅ ነው በልባችን ሰሌዳ የክብር ቦታ አለህ ነፍስህ በፃዲቁ ኖህ በአብርሃም በይስሀቅ በያዕቆብ አጠገብ ትረፍ ጥልዬዬዬዬዬዬዬ በትንሹ እድሜዬ ባላወቅህም በስራህ በሀገር ፍቅርህ በልቤ ትኖራለህ ጥልዬዬዬዬዬዬዬዬዬ❤❤❤❤❤

  • @meklitsime664
    @meklitsime664 Před 3 lety +4

    ይሄን ሙዚቃ ደጋግሜ ሰማሁት የምር ምንም ልረካ አልቻልኩም የምር ባዳመጥኩት ቁጥር እንባዬ ይወርዳል። ብሄራዊ መዝሙር እራሱ ቢሆን አይቆጭም የኢትዮጵያዬ

  • @kalkidantilahun9828
    @kalkidantilahun9828 Před 3 lety +58

    Dad no word you describe your patriotism god i am crying inside and outside😥😥😥😥✊

    • @solomonkoreb8786
      @solomonkoreb8786 Před 3 lety +3

      You should feel proud

    • @mesyazu
      @mesyazu Před 3 lety +2

      Be strong my dear ❤️ and proud ! Rest in peace legend 💓❤️

    • @dawitsolomon4067
      @dawitsolomon4067 Před 3 lety +2

      Let his majical voice be a comfort to you, Tialhuns' daughter, Kalkidan.

    • @dawitsolomon4067
      @dawitsolomon4067 Před 3 lety +2

      Let his majical voice be a comfort to you, Tialhuns' daughter, Kalkidan.

    • @juliobela5846
      @juliobela5846 Před 3 lety

      ሀገር ፃታ የለውም ምን አይነት ደደብ ሰው ነው ሰውዬው

  • @kng4900
    @kng4900 Před 3 lety +14

    ዶ/ር ጥላሁን እናመሰግናለን ነፍስህ በሰላም ትረፍ ኢትዮጵያ ለዘለዓለም በክብር ትኑርልን

  • @blenbalagerua4801
    @blenbalagerua4801 Před 3 lety +35

    አፈሩን ገላባ ያርግልክ የናንተ ዘመን ምንኛ መልካም ነበር አሁን አዋቂውም አላዋቂውም ዘረኛ ሆኖ እርስ በርሳችን ፍቅር አጣን

  • @user-tw6dh6mh8s
    @user-tw6dh6mh8s Před 3 lety +1

    ሀገሬ እወድሻለሁ የጣለሽ ይጠላ ሁሌም ሰላምሽን ያብዛልን አሁን የማብላጫሽ ጊዜ ነው ካፍ በይልን የአለም ንግሥት 🇪🇹🇪🇹👑👸

  • @user-ui2fc4vn1e
    @user-ui2fc4vn1e Před 3 lety +3

    ጥልዬ ለኢትዮጲያ እንዳዜምክላት ህይወትህ አለፈ እግዚአብሔር ነብስህን በገነት ያኑረው 💚💛❤️🙏🏽 አይጥልዬ ምነው ዛሬ በህይወት በኖርክ እና ጠላቶዎችህ ሜዳ ላይ ሲደባለሉ ባየሀቸው ኖሮ ምንኛ ደስ ይለን ነበር

  • @munmuh100
    @munmuh100 Před 3 lety +43

    This music made me fall in love with my country, ETHIOPIA.🇪🇹🇪🇹🇪🇹

    • @juliobela5846
      @juliobela5846 Před 3 lety

      ሀገር ፃታ የለውም ምን አይነት ደደብ ሰው ነው ሰውዬው

    • @biniamgjormai
      @biniamgjormai Před 2 lety +1

      I have the same filing 🇪🇷🇨🇬🇪🇷

    • @blovechanale2931
      @blovechanale2931 Před 2 lety

      This music made me fall in love with my cauntry ETHIOPIA 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

  • @zenebeyacob3956
    @zenebeyacob3956 Před 2 lety +5

    ይህ ግጥምና ዜማ በበ1980ዎቹ ተጽፎና ተዘፍኖ እንዴት የዛሬውን የወያኔ ሴራ እየተናገረ እንዳለ ሳስብ አድናቆቴ ከፍ ያለ ነው፡፡ ዘመን ተሸግሮ ዛሬም እንባዬን ያመጣል፡፡

  • @solomonseid4557
    @solomonseid4557 Před 3 lety +1

    በእውነት በህይወት ያለክ ያህል ነው የተሠማኝ ይህን አልበም የሰሩ ባለሙያዎች ፈጣሪ እድሜ ይስጣችሁ ደሞ ገቢውም ለሀገር ገበታ መሆኑ ልዩ ነው ጋሽ ጥሌ የህዝብ ልጅ ነው ስም ከመቃብር በላይ ይውላል ነብስ ይማር ፈጣሪ
    ሌላው ደግሞ የሆነ አደባባይ ላይ ሀውልት ልሰራለት ይገባል ከ ቦብ ማርሌይ እሱ ይቀርበናል የኛ የሆነውን ማክበር ስለማንወድ ነው እንጅ

  • @user-sh9et7zr7i
    @user-sh9et7zr7i Před 3 lety +16

    እምዬ ኢትዮጵያ በክፉ የሚያሽ አይነ ስውር ይሁን እማማዬ በሰላም ለዘላለም ኑሪ

  • @ezrateshome730
    @ezrateshome730 Před 3 lety +21

    ዘፈንን ዘፋኙ ሲዘፍነው እንዴት ደስ ይላል
    ጋሽ ጥሌ እንወድሃለን

  • @teyentadmassu1212
    @teyentadmassu1212 Před 3 lety +1

    ጥልዬ ❤️ እያለቀስኩ ነው የሰማሁ 😭ሀገሬ ኢትዮጵያዬ ኑሪልኝ ሰላምሽ ይብዛልኝ እምዬ ሀገሬ ዞሬ መግቢያየዬ🇪🇹🇪🇹🇪🇹❤️

  • @abdulkadirmohammed3510
    @abdulkadirmohammed3510 Před 2 lety +21

    Tilahun is a treasure, a gift, and a shining star to Ethiopia! The timing of this music is perfect, I’m sure lots of people will cry listening to his voice. May he Rest In Peace!

  • @alhmdlheforeverything6685
    @alhmdlheforeverything6685 Před 3 lety +21

    The one and only Ethiopian music legend Tilahun Gessese🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

  • @Eleanor0516
    @Eleanor0516 Před 3 lety +5

    ይህ ቀረኝ የምለው የሚቆጨኝ የለም
    ኢትዮጵያ እድሜ ላንች ያላየሁት የለም 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
    Emama

    • @juliobela5846
      @juliobela5846 Před 3 lety

      ሀገር ፃታ የለውም ምን አይነት ደደብ ሰው ነው ሰውዬው

    • @Eleanor0516
      @Eleanor0516 Před 3 lety

      @@juliobela5846 what?

  • @thomasfeleke9851
    @thomasfeleke9851 Před 2 lety +3

    ምስጋና ፣ ፍቅር ፣ ተስፋ እና ጀግንነት አጠቃሎ የያዘ ተሻጋሪ ስራ ነው ጥበብ ቦታዋ ላይ ሳትዛነፍ ቁልጭ ብላለች💙💛💖

  • @tigesttadesse2362
    @tigesttadesse2362 Před 2 lety +1

    ኢትዩጵያዬዬዬዬዬዬዬዬዬ እንዴት እንደምወድሽ ሀገሬ ቆሜ ሁሌ ነው የምፀልይልሽ 😭💚💛❤️ ትንሳኤሽን እናያለን

  • @dawityewhalashet3746
    @dawityewhalashet3746 Před 3 lety +9

    ስምህ ሁልም ከመቃብር በላይ ነው እንወድሀለን ነብስህን ይማርልን ❤😭😭😭

  • @lijmicofficialfaf334
    @lijmicofficialfaf334 Před 3 lety +124

    Tile u r legend.

  • @sipara8333
    @sipara8333 Před 3 lety +2

    ጋሸ ኡፍ የምር እያለቀስኩ ነው የሰማሁት የእውነተኛ የሀገር ፍቅር ድምፅህ ላይ ያበራል ፈጣሪ ነብስህን ይማረው በቀኙ ያሳርፍህ❤❤❤❤❤😭😭😭😭😭

  • @qsoundmuzics160
    @qsoundmuzics160 Před 3 lety +1

    oh tilahun rest in peace ethiopian good father king of music

  • @sisay1183
    @sisay1183 Před 3 lety +6

    የብሔራዊ መዝሙራችን ቢሆን ደስ ይሉኛል።

  • @shewa2351
    @shewa2351 Před 3 lety +21

    ይህን ኮሜንት የምታነቡ ሁሉ ፈጣሪ አገራችንን እና ህዝቦቹዋን ጠብቅልን በሉ 👐🙏

  • @hazalaklo6639
    @hazalaklo6639 Před 3 lety +2

    ባሁኑ ስአት ሁሉም እራስ ወዳድ ነው እግዚያብሄር ቅድስት ሀገራችንን ጠብቅልን።

  • @Bwoldemichael
    @Bwoldemichael Před 2 lety +2

    The most beautiful and touching pictures ❤❤❤

  • @birukalemu1954
    @birukalemu1954 Před 3 lety +44

    ጥልዬ ማንም አንተን ሚተካ የለም ወደፊትም አይኖርም ለሀገርህ ያለህ ጥልቅ ስሜት

  • @aylembinte2439
    @aylembinte2439 Před 3 lety +5

    ኢትዮጵያ እንደ ጥላሁን የሚወድሽ ይብዛልሽ
    መልካም
    ይሰማብሽ
    የትወልድ አገሬ ወድሻለሁ

  • @benyamkebede1168
    @benyamkebede1168 Před 3 lety +1

    Tilahun Gessesse the one the only one no replacement !

  • @zinashethiopia502
    @zinashethiopia502 Před rokem +1

    ሀገሬ ሰላምሽ የሚመለስበት ልጆችሽ ከስደት የሚርቁበት ዘመን ናፈቀኝ ከማልቀስና ከመፀለይ ውጪ ምንም ላረግልሽ አልችልም ሙዚቃውን ስሰማው ከፋኝ ጥሌ እንኳን አላየህ ደግ ጊዜዋን ብቻ ፈጣሪ አሳይቶህ ዛሬ ባንዲራዋን መያዝ ኢትዮጵያ ማለት ወንጀል የሆነበት ጊዜ አላየህም

  • @yenebeteseb-3147
    @yenebeteseb-3147 Před 3 lety +25

    ሰላም ላገራችን
    Peace for Ethiopia ..💚💚💛💛❤️❤️
    RIP the great Dr Tilahun.

  • @ethiohabesha7069
    @ethiohabesha7069 Před 3 lety +2

    አይ ጋሽ ጥሌ እንኳንም ይህን አሁን ያለንበትን ጊዜ ሳታይ በሰላሙ ጊዜ ተሰናበትክ አባቴ😭😭😭 የምታነባላት ሀገርህ ዛሬ ላይ እንዲ በውስጧ በበቀሉ አሜኬላዎች ህዝቦቿ እረፍት አጥተው ቀን በቀን ሲደሙ ብታይ ምን ያህል ልብህ ይደማ ነበር ነፍስህ በሰላም ትረፍ ሁሌም የኢትዮጵያ ንጉስ ሆነህ ትኖራለህ🙏🙏🙏😍😍😍💚💛❤

  • @tidwuhamarkeshaw3732
    @tidwuhamarkeshaw3732 Před 3 lety +1

    ብዙዎች ድርሰትን ያዜማሉ፤ ጋሽ ጥላሁን ግን ስሜቱን በራሱ መንፈስ ይዘፍናል፡፡ እሱ ግን ስንኝ ሳይሆን፣ ህልሙን ያለኮመፖዚተር ያዜማል፡፡ መሳሪዎቹን ብታወጡም፣ የእርሱ ሙዚቃ ሙሉ ነው፡፡ በህይወት ካለነው የበለጠ፣ አንተ ባለራዕይ አልፈህም የሀገራችን ሃብት ነህ፡፡ ሀገርህ እና ዘርህ ይባረክ፡፡

  • @beakaltilahungessesse5759
    @beakaltilahungessesse5759 Před 3 lety +34

    I don't have a word l love it I wish you could be here my beloved dad

    • @yerasew1
      @yerasew1 Před 3 lety +2

      ክቡር ጋሽ ጥላሁን በሁላችንም በአዲሱም በቆየውም ትውልድ ልብ ውስጥ የታተመ ነው። አይዞህ አይክፋህ ለዘላለም የማይረሳ በሰው ልጆች ሁሉ ሲወደስ ይኖራልና። በርግጥ እንደልጅ አባትህ በህይወት አብሮ ቢኖር ምንኛ እጅግ ደስ የሚል ነበር፤ በተለይ የዝናውን ሃያልነት በአካል የወቅቱ አጋጣሚ ያሳምርለት ነበር። በሌላ በኩል ድግሞ እግዚአብሔር ይወደዋል፣ ምክንያቱም እንዲህ ከልቡ በእምባ ስቅስቅ ብሎ የሚያለቅስላት እናቱ ኢትዮጵያ ዛሬ ላይ ያለችበትን ሁኔታ በአይኑ ቢያይ እጅግ ይከፋው ነበር፣ ውስጡን በጣም ያመው ነበርና።
      ክቡር ጋሸ ጥላሁን ገሰሰ ነፍስህን በአፀደ ገነት ያኑራት ለዘላለም።
      ጥላሁን ገሰሰ አንተ የፍቅር ንጉስ
      እንኳንም አላየህ የኢትዮጵያን መዳጎስ
      እንኳንም አልሰማህ የናትክን መንኳሰስ
      አንተ ያለቅስክላት ቀድሞ ገብቶህ ቢሆንስ
      ፈጣሪ ይወድሀል እንኳንም አላየህ
      የርሷን መፈራረስ!
      ኡፍ በአካል ባላቅህም የአንተን ሁሉንም ስራዎችህን ስሰማ ራሴን መቆጣጠር አልችልም በደስታም ሆነ በማልቀስ። ኢትዮጵያዊነትን ለኛ ለከንቱዎች ለማስተማር ቢሆን ምናለበት በህይወት አሁን አብረህ ከኛ ጋር በኖርክ እላለው፣ ከዛ ውጭ ግን እንኳንም አላየህ የአሁኑን።

    • @earthenquake6672
      @earthenquake6672 Před 3 lety +2

      You need to thank God for being this huge Hero's son!I remember how i felt sad for not attending his funeral!

    • @Nani-pq6ff
      @Nani-pq6ff Před 3 lety +1

      Gash tilahun is everywhere ! , He is in ethiopians heart

    • @beakaltilahungessesse5759
      @beakaltilahungessesse5759 Před 3 lety

      Thank you for all comments

  • @almazkebebew3234
    @almazkebebew3234 Před 3 lety +11

    በበኩሌ ከልቤ ቆሜ ላመስግናችሁ እወዳለሁ ጥላሁን ገሰሰ አሁንም በህይወት እንዳለ ነዉ የምቆጥረዉ ይህ አልበም እንዲወጣና እና ቁምነገር ላይ እንዲዉል ላደረጋችሁ ሁሉ ክብር ይገባችኋል እናንተ የሀገር ኩራት ናችሁ እግዚአብሄር አብዝቶ ይባርካችሁ

    • @juliobela5846
      @juliobela5846 Před 3 lety

      ሀገር ፃታ የለውም ምን አይነት ደደብ ሰው ነው ሰውዬው

  • @nhialreathnyuon8029
    @nhialreathnyuon8029 Před 2 lety

    Tilahun was very great Ethiopia pioneer
    Praise his greatness.
    His memory still a live.

  • @habeshawit2008
    @habeshawit2008 Před 3 měsíci +1

    የእናት ኢትዮጵያ ዕንቁ ጥላሁን ገሠሠ💚💛❤️ respect. በእውነት "ጥላሁን አልሞተም" ማለት ይሄ ነው

  • @ITSNOTME260
    @ITSNOTME260 Před 3 lety +4

    እግዚአብሔር የባረከን አጥንታችን
    ያጠነከረን እግዚአብሔር ክብር ይግባወና በሱ ነው ያለነው ያለሱ ማንም የለንም። አዋ ማንም የለም ።

  • @ariftube7703
    @ariftube7703 Před 3 lety +18

    I am crying listening this music 😢 it tells every thing ! Rest in peace the legend!! ላንቺ የማይተኙ የማያንቀላፉ..........

  • @joyo1198
    @joyo1198 Před 3 lety +1

    Yemere eyalekesku nw yayehut..🥺🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ...."ማግስቱ ን ይውሰደኝ አስር ሞት ይምጣና"....teleyae antes teleyaleh🙏🙏😍 neguse ne le zelalem😍

  • @hanitakele5305
    @hanitakele5305 Před 3 lety +1

    #ቆሜ #ልመርቅሽ
    ቆሜ ልመርቅሽ፤ ተቀበይኝ’እማ
    ህይወትን መርቀሽ፤ ሰጥተሽኝ እኔማ
    ይህ ቀረኝ የምለው የሚቆጨኝ በዓለም
    ኢትዮጵያ እድሜ ለአንቺ ያላየሁት የለም
    አንገትሽ ራስሽን ችሎ ልየውና
    ማግስቱን ይውሰደኝ አስር ሞት ይምጣና
    💚💛❤️
    ትንብቲሽ ይፈፀም ከመሬት ጠብ አይበል
    ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ ገድልሽ ይንበልበል
    ሰንደቅሽ ከፍ ይበል ይቁም ለዘለአለም
    ሰላም ጥጋብ ደስታ ይታይብሽ በአለም
    💚💛❤️
    እማ እማ ሴራዉ ይክሸፍበት እማ እማ የመታብሽ አድማ
    እማ እማ እጁን ሳር ያድርገዉ ጉልበቱን ቄጠማ
    እማ እማ ካቀባበለብሽ እማ እማ ብረት ከደገነ
    እማ እማ አምላክ ያግዝልሽ ለአንቺ እየወገነ
    💚💛❤️
    ፀሎትሽ ይሰማ አምላክ ይለመንሽ
    ፈተናዉ አይለቅ የሚፈታተንሽ
    አንገትሽ እራሥሽን ችሎ ልየዉና
    ማግስቱን ይዉሰደኝ አስር ሞት ይምጣና
    💚💛❤️
    በሰዉ ሀገር ምድር ለተበተኑት
    ለልጆችሽ ሁኚ ዞሮ መግቢያ ቤት
    በአለም አደባባይ ከመንግስታት ደጅ
    ሞልቶሽ ተርፎሽ እንጂ ጎሎብሽ አቲጂ
    💚💛❤️
    እማ እማጎተራሽ አይጉደል እማ እማ አይድረቅ ሌማትሽ
    እማ እማ ከክፉ ሰዉሮ ያድንሽ እምነትሽ
    እማ እማ ላንቺ የማይተኙ እማ እማ የማያንቀላፉ
    እማ እማ ብን ይበሉ ይዉደቁ ከምድረ ገፅ ይጥፉ
    እማ እማ ከአረግንልሽ በላይ እማ እማ የምትሆኝልን
    እማ እማ መጠሪያ እናታችን አንቺዉ ቆይልን
    💚💛❤️
    ክቡር ዶክተር አርቲስት ጥላሁን ገሰሰ 😭🙏💛

  • @osmanabdulaziz7395
    @osmanabdulaziz7395 Před 3 lety +8

    የጥላሁን ገሰሰ ኢትዩጵያ የኛ ኢትዩጵያ ❤️🇪🇹❤️

  • @ednachannel5463
    @ednachannel5463 Před 2 lety +4

    It's so sweet and beautiful Ethiopiaye,telie the clip is amazing😘😘😘😘💚💛💗

  • @mataliba8814
    @mataliba8814 Před 3 lety +2

    ሀገሬ የኔ እናት
    ሲርበኝ የምታጎርሽኝ
    ሲርበኝ ሳትሳሺ የምትመግቢኝ
    ሲበርደኝ የምታሞቂኝ
    ሄደሽ የማትሄጂ ሁሌም ከጎኔ ሁነሽ
    ማንም አይንካብኝ ያለአንቺ ባዶ ነኝ

  • @darieselamtibor9020
    @darieselamtibor9020 Před 8 měsíci +2

    ኢትዮጵያን በልኩዋ የገለፀ ... ድንቅ ግጥም ያየህይራድ አላምረው !!!! ....እድሜው ከ ስልሳ በታች ሰው መድረክ ላይ እንኩዋ ባይዘፍነው !!!!

    • @darieselamtibor9020
      @darieselamtibor9020 Před 8 měsíci

      በአለም አደባባይ በመንግስታት ደጅ ;;ሞልቶ ተርፎሽ እንጂ ጎሎብሽ አትሂጂ ::

    • @yayehyiradalamerew1419
      @yayehyiradalamerew1419 Před 3 měsíci

      ስለ ሰማችሁት እድለኛ ነኝ. ያየህይራድ

  • @abebaallwe6984
    @abebaallwe6984 Před 3 lety +3

    ጥልዬ ነብስህን በገነት ያኑረው ዘፈኖችህ ከትዉልድ ትውልድ እየተደመጡ ዘላለም ስራዎችህንጨ እናስታውስሀለን