"መርጦ ማፍቀር የለም" ግርማ ተፈራ | "Merto Mafqer Yelem" Girma Tefera

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 12. 09. 2024
  • ይህንን ሙዚቃ የስልክ ጥሪ ማሳመሪያዎ ለማድረግ shorturl.at/mlY74 ይህንን ሊንክ ይጫኑ
    "መርጦ ማፍቀር የለም" የተሰኘውን ሙዚቃ ከድንቁ አርቲስት ግርማ ተፈራ አልበም, "ግን የት ሓገር" ይዘንላችሁ ተገኝተናል
    From Girma Tefera's new album "Gin Yet Hager", we bring you "Merto Mafqer Yelem".
    --------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
    አይኔ ድንገት ሰርቆ አይንሽን ያየውና
    ሰው ያስታውሰኛል እንደገና
    ልቤ ካዳፈንኩት እሳት እየጫረ
    ከገጽሽ ያነባት ጀማመረ
    እኔስ ምዬ ነበር ላላነሳት
    ምስሏን ባንቺ ገልጻው እንዴት ልርሳት
    የረሳኋት መስሎኝ አ… ሃ
    አንቺን በማግኘቴ አ…. ሃ
    በድንገት ወደሷ አ…. ሃ
    ይጓዛል ስሜቴ አ …..ሃ
    ልሰጥስ ወስኜ ልቤን ሳሰናዳ
    የሷን ምስል አየሁ ከገጽሽ ሰሌዳ
    በመልካምነትስ ልተውሽ ባልወድም
    ልለይስ የኔ አለም ልጎዳሽ አልፈቅድም
    መርጠው ባልመጡበት በእንግድነት አለም
    አያድርስ አይጣል ነው መርጦ ማፍቀር የለም
    አ…..ሄ አይረሳትም ኦሆ….. አይረሳትም
    አይኔ ድንገት ሰርቆ አይንሽን ያየውና
    ሰው ያስታውሰኛል እንደገና
    ልቤ አበቃ አከተመካለ በኋላ
    ስንቴ አመሳሰላት ካንቺ ጥላ
    እኔስ ምዬ ነበር ላላነሳት
    ምስሏን ባንቺ ገልጻ እንዴት ልርሳት
    ኣ ….. ልርሳት
    ትርፍ የታለ ውዴ አ….. ሃ
    ብሰጥሽ እራሴን አ …..ሃ
    የ ራቀን ፍለጋ አ….. ሃ
    አባከንኳት ነፍሴን አ ….. ሃ
    ልካስሽ ባልልም ለዋልስው ውለታ
    ይቅርታ ከልቤ ለነፈግኩሽ ደስታ
    በመልካምነትስ ልተውሽ ባልወድም
    ልለይሽ የኔ አለም ልጎዳሽ አልፈቅድም
    መርጠው ባልመጡበት በእንግድነት አለም
    አያድርስ አይጣል ነው መርጦ ማፍቀር የለም
    አሄ ….. አይረሳትም ኦሆ ….. አይረሳትም
    --------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
    ግጥም :- ናትናኤል ግርማቸው
    ዜማ :- ዮሴፍ በቀለ
    ሲኒማቶገራፈር፦ዮናስ ወርቁ
    ዳይሬክቶር፦ ፍጹም ካሳሁን
    ካሜራ ፦ እዝራ ያሬድ
    ኤዲተር ፦ሄኖክ ጀርጀራ
    ሙዚቃ ቅንብር፦ አቤል ጳውሎስ
    ማስተሪንግ ፦አበጋዝ ኪብረዎወርቅ
    አልቶ ሳክስ ፦ዶ/ር ዶኖቫን
    ሊድ ጊታር ፦ ስብሃት እንዳለ
    ቤዝ ጊታር ፦ አቤል ጳውሎስ
    ድሮን ፦ሙሉአለም ጉደታ
    ሎኬሽን ማናጀር ፦ፕሮሞተር ቤቲ ሃዋሳ
    ሎኬሽን፦ ሃዋሳ ፤ወንዶ ገነት፤ ዱራሜ፤ሰሮ ቢራ፤ አ’አ እንጦጦ ኩሪፍቱ ሪዞርት
    ተዋንያን፦ ሰዪፈሚካኤል ተስፋዬ እና ኢየሩሳሌም ገበየሁ(ጄሪ)
    --------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
    ምንም አይነት ቪዲዮ እንዳያመልጥዎ ሰብስክራይብ ያድርጉ እና ማሳወቂያዎችን ያብሩ 🔔
    Subscribe and turn on notifications 🔔 so you don't miss any videos
    ይህን ሊንክ በመጠቀም ሰዋሰው መተግበሪያን ያገኙታል | Use this link to get Sewasew Multimedia
    onelink.to/ymaahn
    ከእኛ ጋር ጊዜዎን ይቆዩ | Stay Connected with us
    Facebook : / sewasewmultimedia
    Instagram : / sewasewmultimedia
    Linkedin : / sewasew-multimedia
    Twitter : / sewasewmmedia
    Tiktok : / sewasewmultimediaet
    CZcams : / @sewasewmultimedia
    Telegram : t.me/sewasewmu...
    #girmatefera #girmateferakassa #ginyethager #mertomefqeryelem #newalbum #sewasew #multimedia #music #creativity #ignitingcreativity #creativeeconomy #sewasewmultimedia #ethiopianmusic #ethiopianmusicapp #Ethiopian #Ethiopians #ethiopia #habesha #ethiopian #addisababa #ethio #africa #habeshabeauty #oromiffa #oromobeauty #oromo #ethiopianmusic #african #ethiopianmusician #ethiopianmusicapp #ethiopianmusicians #ethiopianmusicvideos #ethiopianartist #ethiopianartists #artist #artistic #christmas #holiday #holidaymusic #holidaygifts #sewasewgifts #sewasewresleases #relseased #newmusic2023 #newmusic2022
    Unauthorized use, distribution, and re-upload of this content is strictly prohibited
    Copyright 2023, ©Sewasew Multimedia. All rights reserved.

Komentáře • 691

  • @user-qk7kq3gv9z
    @user-qk7kq3gv9z Před rokem +398

    ማነው እደኔ ገና ድምፁን ሲሰማው ደስስስ የሚለው ? ግርምሽዬ እንወደድሀለን!!!

  • @SeidAbebetelbo
    @SeidAbebetelbo Před 9 měsíci +37

    ማነው እደኔ ደጋግሞ ያዳመጠው እውነተኛ አፍቃሪዎች ❤

  • @eyueleshetu4768
    @eyueleshetu4768 Před rokem +170

    ግርማ ተፈራ
    የዘፋኝ ቀብራራ
    ቆሳስሎ ነበረ ጆሯችን በጊልዶ
    አሁን ተሺሎኛል እዉነት ምርጥዬ album ነው 🙏

    • @henatube7
      @henatube7 Před rokem +6

      ለካሙዙ ስትሉ ስም አትጥቀሱ እንደ ወንድም ሊሰማዉ ይችላል

    • @eyueleshetu4768
      @eyueleshetu4768 Před rokem +8

      እንዴ ታዲያ ይምከረዋ ተገደን አየተደፈርንኮ ነው

    • @endrisslamlethiopia1181
      @endrisslamlethiopia1181 Před rokem +2

      @@henatube7 👍

    • @ab-on1ev
      @ab-on1ev Před rokem +3

      i prefer 😂lelawn satneka madnq bichil

    • @henatube7
      @henatube7 Před rokem +3

      @@eyueleshetu4768 ምን ያርገዉ የእናት ሆድ ዥንጉርጉር ከሆነሳ ካሙዙ ኢትዮጵያ ዉስጥ አሉ ከተባሉ ከባድ ሙዚቀኞች ጋር ሚሰራ ነዉ ወንድሙ ጊልዶ ደግሞ ስለሙዚቃ ምንነት የማያቁ ትላንት የመጡ ጨቅላዎች በደፈናዉ ሚሰራ ነዉ ያዉ ምንም ማረግ አይቻልም

  • @abduyesuf2493
    @abduyesuf2493 Před rokem +230

    ከተለመደው የሀገራችን ሙዚቃወች ለየት ያለ እይታ ያለው አንደኛ ስራ ክሊፑ ደግሞ ከቦታ መረጣው ጀምሮ ሁሉም ነገር በጣም ነው የተመቸኝ 🥰🥰🥰🥰🥰🥰

  • @hiwotyoseph4325
    @hiwotyoseph4325 Před rokem +20

    መርጠው ካልመጡበት ከ'ንግድነት ዓለም :
    አያድርስ አይጣል ነው መርጦ ማፍቀር የለም ......
    ለእኔ የተዘፈነ እስክመስለኝ ደግመ ደጋግመ እየሰማዉነዉ😢😢😢👍👍👍good job girmesh

  • @michalwondwosen2279
    @michalwondwosen2279 Před rokem +13

    ይህ ስሜት በጣም ከባድ ነው የደረሰበት ያቀዋል

  • @dagiki2012
    @dagiki2012 Před rokem +151

    የምር ይሄን ዘፈን መስማት ማቆም አቅቶኛል 🥰

  • @nesredinmuhammed6000
    @nesredinmuhammed6000 Před rokem +16

    ግርምሽ ትለያለህ! የድሮውን የጥበብ ቃና በውብ ጥልቅ የተለየ ሀሳብና ይዘት ስላመጣህልን እውነትም የአባቱ ልጅ ነህ we feel proud 👍ይህ ዘፈን ነፍሴን ዘልቆ የሚነካው ለምን ይሆናል ? አረሳትም አዚየ ግን የት የሽ ?❤❤❤❤❤
    ትርፍ የታለ ውዴ ብሰጥሽ ራሴን
    የራቀን ፍለጋ ካባከንኳት ነፍሴን

  • @Fasiltessema-uy5kg
    @Fasiltessema-uy5kg Před rokem +8

    አቤት ድምፅ ግርምሽየ ትለያለህ ❤❤ መርጠዉ ባልመጡበት በእንግድነት አለም አያድርስ አይጣል ነው መርጦ ማፍቀር የለም ።😭😭 ስሜቱን የደረሰበት ሰው ያዉቀዋል

  • @linahailu1593
    @linahailu1593 Před rokem +28

    የውስጤን ስሜት የሚነግር ምርጥ አልበም ነዉ ደሞ በጣም የምወደው ዘፈን በክሊፕ ስላቀረብክ በጣም ነዉ የማመሰግንክ ሁሉም ስራዎችክ አይጠገቡም #1ኛ ናቸው ክበርልኝ🙌

    • @henatube7
      @henatube7 Před rokem +1

      ግርምሽ ትለያለህ እኮ ግርምሽ 🥰🥰🤩🤩🤩

  • @gelilatekle9168
    @gelilatekle9168 Před rokem +5

    ሁሌም ያንተ ስራ ቢደመጥ የማይሰለች ነው እውነት ማዳመጥ ማቆም አልቻልኩም ❤❤❤

  • @jamesabebe5909
    @jamesabebe5909 Před rokem +9

    ወይኔ ግርምሽ ድምፅህማ ገዳይ ነው ሰምቼ አልጣገብ አልኩኝ እረጅም እድሜ ከጤና ጋር ❤️🔥🙏

  • @tiztafikre5450
    @tiztafikre5450 Před rokem +19

    ከ 1000 ጊዜ በላይ ነው የሰማሁት ❤️

  • @mekonnenyohannesabera7444

    እግዚአብሔር ይመስገን በአሁን ሰዓት እጅግ በጣም በደስታ የተሞላ እጅግ በጣም ጥሩ የትዳር ህይወት ነው ያለኝ ነገር ግን ደራሲው ይሄን ዘፈን ግጥም ሲፅፍ ያለፍኩትን ታሪኪን በአጋጣሚ ነግሪዋለው ወይ እሱን እሚያቁ ሰዎች ነግረዉታል ያስባለኝ ድንቅ ውብ ኪክ የሆነ ስራ ነው ባንተ ላይ ስሰማው የእውነት በጣም ደስ ብሎኛል አመሰግናለው

  • @zeko-power
    @zeko-power Před rokem +29

    ጥበብ እንዲህ ጥበበኛ ስታገኝ ፍፁም
    ሃሴት ታረጋለች
    ሰላም ትሰጣለች
    መንፈስ ታድሳለች
    ምስጋና ለሁላችሁም ግርምሽ ፍቅር

  • @h.g3326
    @h.g3326 Před rokem +3

    ኡውፍ ከግር ጥፍሬ እስከራሴ ነዘረኝ ልቤ ምቱ ጨመረ ኡፍ ምን አይነት ያማረ ስራ ነው ግርማየ እናመሰግናለን 😭😭

  • @melakuendalie
    @melakuendalie Před rokem +6

    ህይወት ነው የሚዘራው። ሙዚቃን ምን እንደሆነ አውቀህ ነው የምትሰራው። ❤

  • @mulunehgirma4455
    @mulunehgirma4455 Před rokem +14

    ግርማ ተፈራ... an amazing and matured artist ... በቃ ከተዘፈነ ለዛሬም ለነገም አስቦ እንደዚህ መዝፈን ነው !!

  • @hiwimillyman3681
    @hiwimillyman3681 Před rokem +8

    ጥበብን ለጥበበኞች።
    እንዴት ደስ የሚል ሙዚቃ።
    አዛዛም👏👏👏ግርምሽ መልካም እድል💗

  • @destakebede3953
    @destakebede3953 Před rokem +2

    የእውነት አንተ ባትደርስልን ምን ይውጠን ነበረ 🥰 Big respect 🙏 ረጅም እድሜ ከጤና ጋር ተመኘሁ 🙏🙏🙏

  • @solomonsolomon6619
    @solomonsolomon6619 Před rokem +16

    የአባቱ ልጅ ጥበብ ለካ አንዳንዴ ጥበበኛን ትወልዳለች ምርጥ ስራዎች ።

  • @seidneju
    @seidneju Před rokem +3

    ከ ሙዚቃው ጀርባ ያሉት ሰዎችን እናመሰግናለን ምርጥ lyrics ምርጥ film production. ምርጥ ምርጥ ምርጥ.....

  • @blackhabeshawit5954
    @blackhabeshawit5954 Před rokem +7

    Omg በቀን ስንት ግዜ እንደምሰማው ❤💝💝ግርምሽ ተባረክ 👌አቤት ድምፅ ❤ሁሌም ዉብ 💝

  • @romhaalene496
    @romhaalene496 Před rokem +5

    ግርምሽ ብራቮ የሚገርም ጥበብ እና ጉልበት ነው በርታልን። 🙋‍♂️🙋‍♂️🙋‍♂️👏👏👏

  • @dado36914
    @dado36914 Před rokem +6

    ግርምሽ ከቃላት በላይ የሆነ ምርጥ ስራ ነው እናመሰግናለን

  • @IAm-yc9ku
    @IAm-yc9ku Před rokem +4

    በጣም ሚገርም ሙዚቃ ነው ስንቴ ደጋግሜ እንደሰማሁት ግርምሽ በጣም ምርጥ ስራ
    አመሠግናለሁ

  • @saramotbaynor4380
    @saramotbaynor4380 Před rokem +5

    ግርምሽዪ ትዝታዬ ወንድሜ ውነትም መርጦ ማፍቀር የለም ልክ ብለሀል 👍

  • @adonaydimartini6130
    @adonaydimartini6130 Před rokem +13

    በቀን 5/6 ግዜ እሰማለው ይሄ ዘፈን በቃ ምርጥ ነው በተለይ ክሊፑ በስማም ያሳብዳል ማርያምን

  • @hayathayat9049
    @hayathayat9049 Před rokem +11

    በዚህ ኑሮ ትዝታ ተጨምሮ 💔💔💔

  • @yaredethio2200
    @yaredethio2200 Před 9 měsíci

    በዘመኑ ቅራቅምቦ ዘፈን ስልችት፣ግፍግፍ ብለን የሐገራችን ሙዚቃ በቃ ሞተ ተቀበረ ብለን እናዝንና ዳግም ደግሞ እንዲህ ያለ ዜማና የአንተን የመሰለ መረዋ ጽምጽ ዳግም በጆሯችን ሲንቅረቆር የምር ተስፋ ከመቁረጥ ይታደገናል።
    ግርምሽ ድምጽ ብቻ ሳይሆን ሰው ወዳድ መልካም ስብእናን የታዱድክ ምርጥ ሰው ኑርልን

  • @Misgemarkose
    @Misgemarkose Před rokem +26

    ከሰው ቤት የምትሰቃየው እህቶቼ የዕረፍት እንጄራ የነፃነት ኖሮ ይስጣቸው

  • @abaysisay8921
    @abaysisay8921 Před rokem +24

    የሁሌም ❤ምርጥ ❤ኢትዮጵያዊ ❤አርቲስት !!!

  • @zenatube4351
    @zenatube4351 Před rokem +4

    ከወደቀው ዘመን ከጊልዶ መንፈስ ዬገላገልከን ግርምሽዬ እናመሰግናለን

  • @ሰሚር
    @ሰሚር Před rokem +28

    ጥንቅቅ ያለ ስራ ግርምሽ ሁሌም ወደላይ ከፍፍ እያለ እሚመጣ ትልቅ ዘፋኝ

  • @hazyldada1918
    @hazyldada1918 Před rokem +10

    ሲገርም ግጥሙን ማን እንደጻፈው ሳላነብ የ ናትናኤል ግርማቸው እንደሆነ እርግጠኛ ነበርኩ nateyeee 🥰🥰

  • @haimedawit2939
    @haimedawit2939 Před rokem +2

    የሰውልጅን የህይወት ፈተና የፍቅር ገጠመኝ በግጥምና በዜማ ሲቀርብ

  • @user-wk7zq6fr6q
    @user-wk7zq6fr6q Před rokem +25

    ተመስገን ነው አንተ መጣህልን🙏😘 በጊልዶ ሙዚቃዎች ጆሮችን ተበላሽቶ ነበር 😳😛😂

  • @saritube4327
    @saritube4327 Před rokem +9

    ልብን የሚሰርስር አንደኛ የሆነ ምርጥ ስራ ነው

  • @nebeyuworku1795
    @nebeyuworku1795 Před rokem +14

    ለጆሮ የሚጥም ምርጥ ሙዚቃ!
    የአባቱን ተፈራ ካሳ ዙፋን ተረክቦ ዘመን የማይሽራቸው ዜማዎች እያስደመጠን ይገኛል።።

  • @edenabebe751
    @edenabebe751 Před rokem +4

    ግርምዬ ምርጥ ስራ እረጅም ዕድሜ ከጤና ይስጥህ

  • @kaleabeniemayehu2708
    @kaleabeniemayehu2708 Před rokem +1

    ምን ያክል ጀግና እንደሆንክ ግን ታውቃለህ?!💚🧡❤

  • @selamleethiopia4985
    @selamleethiopia4985 Před rokem +2

    ግርምዬ በየጊዜው እያስደመምከን ነው፣ ሁሌም ወደ ከፍታው ማማ ከፍፍፍፍፍፍ በል።

  • @miyadodo2238
    @miyadodo2238 Před rokem +3

    ይሄን ዘፈን የ መጀመሪያ ፍቅረኛዬ ጋብዞኝ ቀን በቀን መስማት ሆኖል ስራዬ😢😢😢😢እኔም ግን አረሳውትም😢😢😢💔

  • @henatube7
    @henatube7 Před rokem +19

    እንዴት ብወደዉ ነዉ ዘፈኑን ለ20ጊዜ የሰማሁት አረ ትለያለህ ንጉሱ

  • @sisayg5357
    @sisayg5357 Před rokem +14

    መርጠው ካልመጡበት ከእንግድነት ዓለም :
    አያድርስ አይጣል ነው መርጦ ማፍቀር የለም ::😱
    Nice Music ✌️

    • @wasihunali2356
      @wasihunali2356 Před rokem +1

      መርጠው ካልመጡበት ከ'ንግድነት ዓለም፡
      አያድርስ አይጣል ነው መርጦ ማፍቀር የለም::😊😊

  • @rastamulugeta8806
    @rastamulugeta8806 Před rokem +4

    ግርምሽ አገር ወዳድ ጀግና ትችላለህ።አገራችንን ስላም ያርግልን።

  • @loveandunity901
    @loveandunity901 Před rokem +9

    ሸጋ ስራ! እንኳን ደህና መጣህ ግርምሽ። ሰላም፣ፍቅር፣አንድነት ለውዷ ሐገሬ ኢትዮጽያ አሜን።

  • @helenyohannescoljo9277
    @helenyohannescoljo9277 Před rokem +5

    ግርሚሽ አንደኛ መልካም እድል አሪፍ ስራ እንወድሀለን እናከብርሀለን እድሜ ከጤና ይስጥልን🙏👍👍👍👍👌😍😍

  • @efilata6385
    @efilata6385 Před rokem +4

    በየሱስስስስስስ ስም ከስንት አመት በኋላ ትሩጉም ያለው ዘፈን ጆሮዬ ሰማ መንፈሴ ታደሰ

  • @derejegashaw724
    @derejegashaw724 Před rokem +4

    ግርምሽ በጣም የተደከመበት ምርጥ ስራ ነው♥

  • @kalkidantsegaye7336
    @kalkidantsegaye7336 Před rokem +7

    አንደኛ ነው ጥሩ ግጥም ከ ድምፅ wow 🥰🥰

  • @emebityaregale6193
    @emebityaregale6193 Před rokem +4

    ግርምሽየ የኛ ምርጥ እረጅም እድሜና ጤናውን እግዚአብሔር አብዝቶ ይስጥልን

  • @edilawitwblaye1702
    @edilawitwblaye1702 Před rokem +7

    የማላውቀው ሰው ነው እሚናፍቀኝ ዘፈኑን ስሰማ 🤔🤔🤔

  • @dagmawimesfin4687
    @dagmawimesfin4687 Před rokem +25

    What a music from our humble Ethiopian musician Girma Tefera Kassa. Pure and lovely Ethipoian colour of sound. I liked it a lot. Long live dear. Respect !

  • @user-ie7jd2fk5e
    @user-ie7jd2fk5e Před rokem +2

    የሚገርም ድምፅ በቃ ቃል የለኝም ትችላለህ ❤❤❤

  • @demeaddisu3686
    @demeaddisu3686 Před rokem +1

    ደግመህ ደጋግመህ የምታዳምጠው ምርጥ ስራ .
    Long time ago I have got a chance to listen to his music in person, back home .

  • @hanatadesetadese7831
    @hanatadesetadese7831 Před rokem +2

    ገና ድምፅህን ስሰማ ውስጤ እንዴት እደሚደስት እድሜና ጤናውን ይስጥህ

  • @tiztafikre5450
    @tiztafikre5450 Před rokem +5

    ቃላት አይገልፀውም አልበሙን 🙏❤️❤️❤️

  • @tsega9141
    @tsega9141 Před rokem +217

    አላውቅም ባውቅም ማወቄን ለራሴ አልነግረውም ዛሬም ለምን በመሳዮችህ ውስጥ እንደምፈልግህ ለምን እንደምጨነቅልህ እረፍት አልባ ጥያቄ መልስ አልባ እውነታ በፈላጊዬ ላይ ሁሉ አንተን መፈለጌ የግል ሳይኖረኝ የግላችንን እምመኘው ድካሜም ብርታቴም ሆነህ ለቀረበኝ ሁሉ ሰነፍ ሆንኩኝ እውነት ነው መርጦ ማፍቀር የለም ሳልፈልግ ሳላስብ ለጎዳሁት ልቦች ሁሉ ልከኛ ዘፈን ሰውንና ፍቅርን ማልጠላ አብዝቼ ግን እምሸሽና ምፈራ አርገህ ሰራኸኝ ፍርሀቴና እዝነቴ ነገም እሚኖር ሆኖ ይቀጥላል ግርምሽዬ ልከኛ ዘፈን 🙏🙏🙏

    • @lalalie7280
      @lalalie7280 Před rokem +8

      ብሶትሽ ነው የገለፀልሽ ውዴ

    • @mubarakmuzi1178
      @mubarakmuzi1178 Před rokem +2

      ምናልባት ስተቱ ባኔ ናው ብላሽ አስባሽ ታውቃላሽ የራቃሽ ሰው ብችም ጥፌት ሆና ባራሱ ሪቆሻል የላፋውን እየሳብሽ ማብሳልሳሉ ዋጋ የላው አይማስላኝም ልብሽን ክፋች እህቴ 🎉

    • @user-hn8ef7lg5w
      @user-hn8ef7lg5w Před rokem +9

      ለሚገባው ሰው ብቻ ነው ልብን መስጠት እህቴ በትዝታ መአበል መጓዙ ልክ አይደለም ለራስም አንድ እድል ሰቶ ሌላን ሰው መልመድ ከቁስሉ መዳን ይሆናል ልብሽን ክፈቺ ለሚገባው ሰው

    • @asnakesorsanataniya351
      @asnakesorsanataniya351 Před rokem +2

      Tadelo ewnate

    • @RomiTube-j5ji
      @RomiTube-j5ji Před rokem +8

      በዚህ ልክ ሰው አለ ብዬ አላስብም ነበር እራሴን ተመልክቸ ሁሉንም ዘወር ብዬ ሳጣ ይገርመኝ ነበር ለካ በብዙወች ጋ ተቀምጧል ፍቅር አሁንም ነገም አለ ችግሩ እንዲያ የሚወደዱ ሰወች ቢያውቁት ምናለ😢

  • @tiztafikre5450
    @tiztafikre5450 Před rokem +11

    ድምፅ💯❤️
    ግጥም💯❤️
    ቅንብር💯❤️
    ዜማ💯❤️
    ሙሉ አልበሙ ❤️💯

  • @emubilal3143
    @emubilal3143 Před rokem +1

    ክሊፑን ስሰማ ልጅ ወልዳ በህክምና ስህተት ለሞተችዉ ልጁ የተዘፈነ መስሎኝ ነበር🥺ጊርማ ተፈራ የሁልጊዜ ምርጫዬ ስወደዉ♥️

  • @Mychannel-tk5kl
    @Mychannel-tk5kl Před rokem +2

    ንደጠበኩህ ግሩም ስራህን በምስምቴ ደስ ብሎኛል ❤❤❤ ታሪክ ያለው ስራ 👏🏾👏🏾👏🏾👏🏾👏🏾legend

  • @promoterbetty
    @promoterbetty Před rokem +7

    በአንተ ስራ መሳተፌ ዕድለኛ ነኝ❤

    • @surakeneni1310
      @surakeneni1310 Před rokem

      ወንዱ ሞደል / አፍቃሪዉ ሁነሽ የሰራሽው አንቺ ነሽ??🤔🤔

  • @user-nc4ww5ck5f
    @user-nc4ww5ck5f Před rokem +1

    ምንም ቃላት የለኝም ምክንያቱም በጣም ስለምወድህና ስለማደንቅህ👌🧡

  • @alemtube12
    @alemtube12 Před rokem +6

    እረሳሁት ብየ ሳስብ ግርምሺ የምር ትለያለህ በዚህ ዲምፅ ቀሪ ዘመንህን ብትዘምርበት እረጂም እዲሜ ከጤናጋር🙏🙏

  • @BiniElec2029
    @BiniElec2029 Před rokem +3

    ግርምዬ በጣም አንደኛ ምን ላድርግህ
    ግጥም ዜማ ድምፅ ልዩ ነው

  • @markos7615
    @markos7615 Před rokem +4

    እናመሰግናለን !""መርጦ ማፍቀር "" እንደማይችል ሁሉ "መርጦ ማልቀስ ባይኖር""

  • @salitahabtemariam2914
    @salitahabtemariam2914 Před rokem +4

    Voice 100
    Video 100
    All I like it keep it up 🇪🇷 😌 👌 😏 😉 👏 🇪🇹

  • @bineluda7558
    @bineluda7558 Před rokem

    ሁሌም ታስገርመኛለህ ግርምሽ ስራዎችህ በጣም ምርጥና ስሜትን የሚገዙ ቢሰሙ የማይሰለቹ ናቸው
    እንዲህ ያለ ሙዚቃ ስንሰማ ነው በሙዚቃችን ተስፋ እንዳንቆርጥ የሚያረገን

  • @helentadese3555
    @helentadese3555 Před rokem

    ግርምሽ ድንቅ ድምፅ እማይጠፋ ድምፅ ጤና ናና እድሜ ይስጥልኝ ደም በጣም ነው እማከብርህ እምወድህ ወድምህም ያተን ፈለግ ይዙአል በጣም ደስ ይላል ኑሩልኝ❤❤❤

  • @robanegera9232
    @robanegera9232 Před rokem +3

    ለዚህ እኮ ነው የምወድህ ግርምሽ!!!
    #My_All_Time_Favourite

  • @bineluda7558
    @bineluda7558 Před rokem

    ሁሌም ታስገርመኛለህ ግርምሽ ይዘሀቸው የምትመጣው ስራዎች ምርጥ የሚለው ቃላት ሁሎ ያንሳቸዋል

  • @user-qr7zd8vl1v
    @user-qr7zd8vl1v Před rokem +2

    እሚገርም ድምፅ ቦታው በቃ ይለያል ግርምሽዬ እናመሠግናለን ዋው ነው 👌👌👌👌

  • @tsigeredaamsalu476
    @tsigeredaamsalu476 Před rokem +1

    ምርጥ ሙዚቃ ሁሌም አንደኛ ግርምሽ እጀራ ይውጣልህ ሁሌም አድናቂህ ነኝ

  • @KidusTinsu-hy9ck
    @KidusTinsu-hy9ck Před 10 měsíci

    በሙዚቃ ተስፋ አስቆርጠውን ነበረ 😏የግርምሽ አይነት ዘመን ተሻጋሪ ሙዚቃዎችን ሚሰጡንን አይተን ተስፋችን ለምልሟል ገራሚ ስራ ነው በርታ ግርምሽዬ ❤❤❤

  • @tesfayeyimer4920
    @tesfayeyimer4920 Před rokem +1

    ይኸ ሙዚቃ ለኔ ነው የተዘፈነው በቃ የራሴ በጣም እምወዳት ልጂ ነበረች ተለያይተናል አሁን ሌላ ህይወት ብጀምርም ግን አልቻልኩም

  • @samridesta5080
    @samridesta5080 Před 9 měsíci

    ግርምሽ በጣም ምርጥ ቆንጆ ስራ ነዉ❤❤❤❤❤ ሰምቼ የማልጠግበዉ ስራ ነዉ በቃ ባጠቃላይ በጣም ወድጄዋለሁ❤❤❤❤❤❤

  • @banchifakhoury7895
    @banchifakhoury7895 Před rokem +3

    ግርማሸ እንዉዳህ አለን ፍጣሪ እረዠም እድሜ ከጤና ጋር ይስጣህ🙏🙏🥰❤

  • @abebagadisa9024
    @abebagadisa9024 Před rokem +2

    በጣም ደስ የሚል ዘፈን ነው። ግርምሽ እወድሀለው።😍😍

  • @rihanamohammed8904
    @rihanamohammed8904 Před rokem

    ግርምዬ ምንም የማይወጣለት የሙዚቃ ስራ ነው ያበረከታችሁልን። ለዚህ ስራ የደከሙ ሁሉ ምስጋና ይገባቸዋል።

  • @asterasefa7912
    @asterasefa7912 Před rokem

    በጣም እናመሰግናለን እንጀራ እንጀራ እሚል ሙዜቃ ነው 20ግዜ በላይ ይሆናል የሰማሆት ግን አልጠገብኩትም

  • @dailyshow9389
    @dailyshow9389 Před rokem +1

    ግርምሽ ምርጥ ስራ ነው የሰጠኸን!❤❤❤

  • @patricelumumba8683
    @patricelumumba8683 Před rokem +1

    አባቱም ቀላል ዘፋኝ አልነበረም እኮ!ለማንኛውም ጣዕም ያለው ዘፈን ነው።በርታ!!

    • @elsaawoke9853
      @elsaawoke9853 Před rokem

      Wendemus bihon???mesay tefera???andegnoch nachew .

  • @ሳንታየገብርኤልልጅነኝ

    ግርምሽዬ በጣም ነዉ የምወድክ በጣም እናመሰግናለን የልቤን ነው አዳምጠክ የዘፈንከው አንጀቴን አርሰከዋልትዝታዬ ቢመለስም

  • @fikerfekadu
    @fikerfekadu Před rokem +1

    OMG ቦታ አመራረጥ የቀረፃ ጥበብ የታየበት ምርጥ ስራ ❤️🔥👌

  • @user-ik8du3zp1f
    @user-ik8du3zp1f Před rokem +1

    ዋውው ግርምሽዬ በጣም አሪፍ ስራ ነው ትልቅ ሰው እንወድኃለን😍😍😍😍

  • @kalkidanabebeA-yl4xo
    @kalkidanabebeA-yl4xo Před 11 měsíci +2

    በህይወት ያጣትን ልጁን በፍቅር ዜማ ያስታወሰበት ድንቅ ቅንብር

  • @TidnzbcvnGhdjfjdzg
    @TidnzbcvnGhdjfjdzg Před 2 měsíci

    ይሄንን ዘፈን ስሰማው አላውቅምደስ የሚል ስሜት ይሰማኛል

  • @haregwoinkassahun4010

    ዋው ድምፅ አንደኛ ግጥም ዜማ የማይሰለች ሙዚቃ👌👌👌

  • @danielg.162
    @danielg.162 Před rokem

    🎤🎤🎤🎧🎧💯🔉🔉🎵🎵🎶🎶💯🎼🎹🎼🎼💯 አመሰግናለሁ አቶ ግርማ ተፈራ ካሳ ኣድናቂህ ነኝ

  • @hannakidane6918
    @hannakidane6918 Před rokem +5

    He is a best and talented singer! He also have amazing voice 👌🏽Well done Girma Tefera 👋

  • @sebleshiferaw5576
    @sebleshiferaw5576 Před rokem +9

    እራሱን የቻለ ሙሉ፣ውብ ድርሰት፤ በምርጥ ኢትዮጵያዊ ከለር ያለው ሙዚቀኛ!🤭🥰🥰

  • @nesanetfikru817
    @nesanetfikru817 Před rokem +5

    ግርማ ተፈራ ካሳ ምርጥ ዘፈን 👌👌😍👍😍👍

  • @habtammekuriaw6656
    @habtammekuriaw6656 Před rokem

    waw ጥሩ ማእዛ ያለው ሙዚክ፣ትለያለህ ግርምሽ እድሜ ከሙሉ ጤና ጋር ይስጥልን!!

  • @zolaab968
    @zolaab968 Před rokem +2

    ያልተለመደ እና የሚያምር ስራ ነው ግርምየ!!!

  • @eyobkassahun6813
    @eyobkassahun6813 Před rokem

    ❤❤❤🎉🎉🎉❤❤❤ የዘፈኑ ስሜን ያማል መርጦ ማፍቀር የለም ፍቅር እኮ አያል ነው ከውስጥ የሚመነጭ ነው ግርምሽ በጣም ነው ምወድህ😊

  • @hagereethiopia1735
    @hagereethiopia1735 Před měsícem

    Love your work man,please make us more music like this one.especially when driving I prefer to listen to your works.long life man🎉🎉🎉🎉🎉🎉

  • @ruhamaabebaw2257
    @ruhamaabebaw2257 Před rokem +1

    ግርማ ሞገስ ያለው ድምጽ ቆንጆ ዘፈን wwww🙏

  • @simegngirma2657
    @simegngirma2657 Před rokem

    ግርምሽዬ የኔ ምርጥ ስንት ጊዜ እንዳዳመጥኩት ትችላለህ

  • @nobayi9173
    @nobayi9173 Před rokem +3

    ለእኔ የተዘፈነ እስክመስለኝ ደግመ ደጋግመ እየሰማዉነዉ አመሰግናለዉ ግርምሽ የጥበብ ሰዉ!