ክነቢል ቁሬሺ ጋር የተደረገ ቃለመጠይቅ እና የክርስቲያኖች እጅ ማጠር

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 25. 05. 2024
  • • አሏህን ስፈልግ ኢየሱስን አገኘሁት ...
    መልካም ዜና
    የምስራች፣ የምስራች፣ የምስራች! የምስራች ማለት መልካም ዜና ማለት ነው። የእግዚአብሔር ቃል ደጋግሞ የሚነግረን ይሄ መልካም ዜና ምንድነው? ዛሬ፣ በእግዚአብሔር ረዳትነት፣ በእግዚአብሔር ቃል ላይ ስለተጠቀሰው ስለዚህ መልካም ዜና እንነጋገራለን። ነገር ግን ስለ መልካሙ ዜና ከመነጋገራች በፊት ስለ መጥፎው ዜና ማስታወስ አለብን።
    ምንድነው መጥፎው ዜና? በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ከፈጠረ በኋላ አዳምንና ሔዋንን በምድራዊዋ ገነት ውስጥ እንዳስቀመጣቸው ታስታውሳላችሁ። እግዚአብሄር እንዲያውቁት፣ እንዲወዱት፣ እንዲታዘዙት እና ለዘላለም እንዲያከብሩት ፈጥሯቸዋል። ይሁን እንጂ እግዚአብሔር እነሱን ለመፈተን አዳምን እንዲህ አለው፡-
    “በገነት ካለው ከዛፉ ፍሬ ብሉ፥ ነገር ግን እንዳትሞቱ በገነት መካከል ካለው ከዛፉ ፍሬ አትብሉ አትንኩትም።”
    መጥፎው ዜና አዳምና ሔዋን እባቡን ማለትም ከተከለከለው ዛፍ ፍሬ እንዲበሉ የፈተናቸውን ዲያብሎስን ማዳመጣቸው ነው። የአዳምና የሔዋን ኃጢአት እነርሱንና ዘሮቻቸውን ሁሉ በመበከል በዓለም ላይ ችግርንና ሞትን አመጣ። ብዙ ጊዜ እንደምንሰማው፡ "ወረርሽኝ መነሻው ላይ ብቻ አይወሰንም!" የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል መጥፎ ዜና ይነግረናል፡-
    “ለሰዎችም አንድ ጊዜ መሞት ከእርሱ በኋላም ፍርድ እንደ ተመደበባቸው፥...
    እነሆ፥ ጌታ በሁሉ ላይ እንዲፈርድ፥ በኃጢአተኝነትም ስላደረጉት ስለ ኃጢአተኛ ሥራቸው ሁሉ ዓመፀኞችም ኃጢአተኞች በእርሱ ላይ ስለ ተናገሩ ስለ ጭከና ነገር ሁሉ ኃጢአተኞችን ሁሉ እንዲወቅስ ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጥቶአል ብሎ ለእነዚህ ደግሞ ትንቢት ተናገረ።” (ዕብራውያን 9፥27 ይሁዳ 1፥15)
    ስለዚህ፣ መጥፎው ዜና ሁላችንም ኃጢአተኞች ነን እናም የእግዚአብሔርን የጽድቅ ፍርድ መጋፈጥ አለብን! ይሁን እንጂ፣ መልካሙ ዜና (የምስራቹ) በዚያው በገነት ውስጥ፣ በምረቱ ባለጠጋ የሆነው እግዚአብሔር፣ አንድ ቀን ከድንግል የሚወለድን ኃጢአት የሌለበትን ሰው ወደ አለም እንደሚልክ ማስታወቁ ነው። ይህ ቅዱስ ሰው፣ ይህ ጻድቅ አዳኝ፣ ለአዳምና ለዘሮቹ ሁሉ ኃጢአት ለመክፈል ራሱን መስዋእት አድርጎ ይሞት ነበር። ለኛ የሚገባን የኃጢአት ቅጣት በዚህ ኃጢአት በሌለበት አዳኝ ላይ ይወድቃል። አዳምና ሔዋን ኃጢአት በሠሩበት ቀን እግዚአብሔር የሰበከው ወንጌል (የምስራች) ይህ ነው። እግዚአብሔር የዚህን አዳኝ መምጣት ለማወጅ ብዙ ሰዎችን ተጠቅሟል፣ እንዲሁም መሲህ ይባላል። እያንዳንዱ የእግዚአብሔር ነቢያት ስለ መሲሑ አንድ ነገር አውጀዋል፣ ስለዚህም እርሱ ሲመጣ እግዚአብሔር የሾመው እርሱ መሆኑን ሁሉም ይገነዘባል። ለምሳሌ ያህል፣ ከመሲሑ መምጣት ሰባት መቶ ዓመታት ቀደም ብሎ የነበረው ነቢዩ ኢሳይያስ፣ መሲሑ እንዴት እንደሚወለድ ተንብዮአል። "ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው።"( ማቴ. 1:23፤ ኢሳ. 7:14 ) ሚክያስ የተባለ ነቢይ ደግሞ መሲሁ ከሰማይ መጥቶ በቤተልሄም መንደር በምድር ላይ እንደሚወለድ ትንቢት ተናግሯል። በትክክል መሲሑ የተወለደበት ቦታ ይህ ነበር። ሆኖም ሚክያስ ይህን ትንቢት የተናገረው መሲሑ ከመወለዱ ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት ነው። ነገር ግን ነቢያት የመሲሑን መወለድ ብቻ አላወጁም። በተጨማሪም መሲሁ በኃጢአተኞች ምትክ መከራ እንደሚደርስበትና እንደሚምት ትንቢት ተናግረዋል። ለምሳሌ ነቢዩ ዳዊት ሰዎች መሲሑን እንደሚንቁት፣ እንደሚያሰቃዩት፣ እጁንና እግሩን እንደሚወጉ እና እንደሚገድሉት ጽፏል። ዳዊት የመሲሑን ሞት ማወጅ ብቻ ሳይሆን፣ እግዚአብሔር መሲሁን ከሞት እንደሚያስነሳውም ተንብዮአል፤ ይህም እግዚአብሔር የአዳምን ልጆች ከኃጢአት ቅጣት ለማዳን የላከው አንድና ብቸኛ አዳኝ መሆኑን አረጋግጣል።
    ስለ መሲሁ መወለድ ብዙም ክርክር የለም፣ ነገር ግን ብዙዎች በሞቱና በትንሳኤው ይሰናከላሉ። ሰዎች የላከውን መሲህ ሲያዋርዱት እግዚአብሔር እንዴት ሊቆም እና ሊመለከት እንደሚችል አይገባቸውም። ብዙ ሰዎች ሊረዱት ያልቻሉት ነገር መሲሑ ለኃጢአታችን እንዲህ አይነት መከራ እንዲደርስበት ያቀደው እኛን የሚወደን አምላክ መሆኑን ነው። ነገር ግን ነቢያቱ እንዲህ ሲሉ አውጀዋል፡- “እግዚአብሔርም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።”
    - (ኢሳይያስ 53፥10)
    ነቢያትን እናምናለን? አዎ እናምናቸዋለን እንላለን። ነቢያትን በእርግጥ የምናምን ከሆነ የጻፉትንም ማመን አለብን። ነብያት የራሳቸውን ሃሳብ እንዳልተናገሩ ማስታወስ አለብን። እግዚአብሔር የሚናገሩትን በመንፈሳቸው ውስጥ አኖረ። እንግዲያውስ እነዚያን ነቢያት ለማመን ብንቃወም፣ ማንን ነው ምንቃወመው? የምንቃወመው እግዚአብሔርን ነው። ምክንያቱም ነቢያት መሲሁ ኃጢአትን ለማስወገድ መስዋዕት ሆኖ እንደሚሞት ትንቢት እንዲተነብዩ ያነሳሳው እርሱ ነውና።
    {የሚቀጥለው ማሊክ የሚባል ሰው የግል ምስክርነት ነው።} እዚህ ጋር ቆም ላድርገውና እንዴት በኢየሱስ ክርስቶስ አማኝ እንደሆንኩ ልንገራችሁ። በወጣትነቴ በቀን አምስት ጊዜ ለመጸለይ እና አመታዊ ጾምን ለመጾም ታማኝ ነበርኩ፣ ነገር ግን ከሞትኩ በኋላ ወዴት እንደምሄድ አላውቅም ነበር። ዙሪያዬ ያሉትን ሁሉ ጠየኩ፣ ሆኖም ግልጽ የሆነ መልስ አላገኘሁም። ወንጌልን (ኢንጂልን) ሳጠና ግን፣ ከሞቴ በኋላ ወዴት እንደምሄድ ማወቅ እንደምችል አወቅሁ፤ ምክንያቱም መሲሁ ኢየሱስ ራሱ በወንጌል እንዲህ ይላል፦ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም።” (ዮሐንስ 5፥24) እንዲሁም እንዲህ ብሏል፦ “ኢየሱስም፦ ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤” (ዮሐንስ 11፥25) ስለዚ፣ ራሴን ለማዳን ከራሴ ጥረት ንስሃ ገብቼ ነቢያት ሁሉ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ በስሙ የኃጢአቱን ስርየት ይቀበላል" ብለው ትንቢት በተናገሩለት መሲህ አመንኩኝ (ሐዋርያት 10፥43)። ተስፋዬን ሁሉ ወስጄ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ አስቀመጥኩት። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔር ለመንፈሴ ሰላም አምጥቶላታል። አሁን ህሊናዬ አይረበሽም። ኢየሱስ በመስቀል ላይ ከሰራው ሥራ የተነሳ የወደፊት እጣዬ በሚያስደንቅ ሁኔታ ብሩህ ነው። በሕይወቴ እንደ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር፣ አንዳንድ ጊዜ ችግር እና መከራ ያጋጥመኛል ምክንያቱም እምነቴ ከዘመዶቼ እና ከጓደኞቼ አስተያየት ስለሚለያይ፤ ግን ሰላም አለኝ። የእግዚአብሔር ሰላም ልቤንና አእምሮዬን ሞልቶታል። ይህን የሰጠኝ ኢየሱስም እንዲህ ይላል፦ “ዓለም ቢጠላችሁ ከእናንተ በፊት እኔን እንደ ጠላኝ እወቁ።” (ዮሐንስ 15፥18) “ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም።” (ዮሐንስ 14፥27) እና ወዳጆች ሆይ፣ ጌታ ለእኔ እና በእኔ ያደረገውን ለእያንዳንዳችሁ ሊያደርግ ይችላል። ካንተ ወይም ካንቺ አንድ ነገር ይጠይቃል፡-ሙሉ ልብህን እንድትሰጠው። ሙሉ ልብሽን እንድትሰጪው። የቀረውን እሱ ያደርገዋል። ጌታ ኢየሱስ ራሱ እንዲህ ብሏልና። "እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤" (ማቴ. 11:28-29)
    እግዚአብሔር ታላቁን ማዳኑን መቼም ቢሆን አይሸጥልህም ወይም አይሸጥልሽም። እንዲሁ ያለ ምንም ዋጋ (ከእናንተ ባልሆነ ዋጋ) በነጻ ሊሰጣችሁ ነው ሚፈልገው። መልካም ስራ፣ ፀሎት (ሶላት) እና ፆም በውስጣችሁ ጥሩ ስሜት ይሰጡ ይሆናል፣ ነገር ግን የእግዚአብሔርን ፅድቅ አያረኩም! ወደ እግዚአብሔር ገነት የምትገባበት/የምትገቢበት መንገድ አንድ ብቻ ነው።
    1.) በመጀመሪያ ኃጢአተኛ እንደሆንክና አምላክን ለማስደሰት የሚያስችል ኃይል እንደሌለህ መገንዘብ ይኖርብሃል።
    2.) ከዚያም ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝ እንደሆነ፣ ኃጢአትህን ለማስወገድ እግዚአብሔር በመስቀል ላይ እንዲሞት እንደ ላከውና እግዚአብሔር የዘለአለም ሕይወትን ይሰጥህ ዘንድ እንዳስነሳው ማመን አለብህ።
    የኦሮምኛውን ቻናሌን ለማግኘት ይህንን ተጫኑ👇
    / @dhugaanniboqachiisa
    አስተያየታችሁን በውስጥ ማድረስ የምትፈልጉ ይህንን የቴሌግራም ሊንክ ተጠቀሙ👇
    t.me/BibleAndMe
    Additional: - ewnetyasarfal123@gmail.com

Komentáře • 122

  • @ewnetyasarfal
    @ewnetyasarfal  Před měsícem +23

    አብራችሁኝ ማገልገል የምትፈልጉ ይህንን የቴሌግራም ሊንክ በመንካት አናግሩኝ። ተባረኩ!
    t.me/BibleAndMe

    • @betiadis
      @betiadis Před měsícem

      አለን ጌታ በረዳን መጠን 🙏

  • @noorwaga4502
    @noorwaga4502 Před měsícem +11

    ነቢል የወንጌል አርበኛ። እግዚአብሔር አንተን ተጠቅሞ ብዙዎች የምስራቹን አሰምቷል ❤❤❤

  • @tayechefo6312
    @tayechefo6312 Před měsícem +11

    የምትሰራው ሥራ ድንቅ ነው ። እግዚአብሔር ይባርክህ ። ግንዛቤ ስለጎደላቸው ሰዎች ልብህ አይዘን፤ ብዙ ሰዎች ደግሞ ይረዱሃልና። አንተ ትክክል ነህ፤ እኛም ከጎንህ እንቆማለን።

  • @meaza5096
    @meaza5096 Před měsícem +10

    የኔ ወንድም አንተ ብቻ በረታ አምላኬም እንደ ባለ ጠግነቱ መጠን በክብር በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሞላባችኋል

  • @wegenshekura9771
    @wegenshekura9771 Před měsícem +14

    ወንድሜ በእውነት እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክህ ለምትሰራው ስራ እጅግ እኮራለው እኔም አስገባለው አንተ ጀግና ነህ ወንድሜ በአስተሳሰብ ልጅ የሆኑትን አስተያየት እየተመለከትክ አትዘን ደግሞ እግዚአብሔር የሰጠህን ይህን ታላቅ ስራ በብርቱ እንድትሰራ አደራ እልሀለው ጌታ ካንተ ጋር ነው።

    • @ewnetyasarfal
      @ewnetyasarfal  Před měsícem +1

      አሜን! በጣም አመሰግናለው🙏🥰

  • @eteneshkassa2558
    @eteneshkassa2558 Před měsícem +8

    ተባረክ

  • @tigimotigimo9572
    @tigimotigimo9572 Před 9 dny

    በጣም የምፈልገው መረዳት ነው ወድማችንን የለወጠ የእግዚአብሔር ቃል የኛንም ቤተሰብ እህትወድሞቻችንን ይለውጥልን

  • @gospelteam526
    @gospelteam526 Před měsícem +7

    በምታቀርባቸው ነገሮች ብዙ ተጠቅሜአለሁ አብሬህ ለመስራት ዝግጁ ነኝ

    • @ewnetyasarfal
      @ewnetyasarfal  Před měsícem +2

      አመሰግናለው። የቴሌግራም ሊንኩን ነክተህ በውስጥ አናግረኝ። ተባረክ!

  • @user-vc8uj8qn4j
    @user-vc8uj8qn4j Před měsícem +3

    ቀጥልበት እንደዚህ አይነት ምስክርነት አስፈላጊ ነው ሰዎች ከጨለማ መውጣት አለባቸው ጌታን ተቀብሎ ❤❤

  • @ayniaaynia9036
    @ayniaaynia9036 Před měsícem +3

    እግዚአብሔር አምላክ በነገር ሁሉ መከናወንን ይስጠህ ወንድም አለም በኛ በጨለምተኛ አስተሳሰብ አገልግሎትህን አትሰላች ሰጪዎች እንድንሆን እግዚአብሔር ይዘርጋ በሰጠን እንድንሰጥ ይርዳን

  • @selameshete3967
    @selameshete3967 Před 29 dny +4

    በርታ ወንድሜ ጌታ ከአንተ ጋር ነው !!
    እኔም ቀኝ እጄን ሰጥቼሀለሁ !!

  • @grace4mankind467
    @grace4mankind467 Před 6 dny

    ወንድሜ ጌታን እንድታው የረዳህ መንፈቅድስ የተባረከ ይሁን። በርታ ጌታ ይረዳሃል።የጠራህንና እራሱን የገለፀልህ የታመነ ነውና ይረዳሃል በርታ ወንድሜ።

  • @glorypicturesofficial
    @glorypicturesofficial Před měsícem +2

    አባተ የምታመልከው አምላክ ይርዳክ ፀጋውንም ያብዛልክ

  • @MesfinBelay-pl7cg
    @MesfinBelay-pl7cg Před 5 dny +1

    እግዚአብሔር ዘመናችሁን ይባርክ ልብ ክፉ አይንካችሁ

  • @user-cr5dv4vz3t
    @user-cr5dv4vz3t Před měsícem +3

    በርታ እግዚያብሄር እኛንም ይርዳን ያንተንም ልብ እግዚያብሄር ያጽና ❤❤❤

  • @shalumiki-sd6cy
    @shalumiki-sd6cy Před 24 dny +1

    የኔ ወንድም በፀሎትና በገንዘብ ግዴታ ነው
    የኛ የክርስቲያን አንዱ አገልግሎት ነው

  • @abebaseyiume8949
    @abebaseyiume8949 Před měsícem +3

    ተባረኩልን ወንድሞች

  • @keeletatbeandeken2919
    @keeletatbeandeken2919 Před měsícem +2

    አይዞህ ጌታ ቅን የሆኑ ሰዎችን ይሰጥሀል ልብህ አይውረድ ብዙ አይነት ኮሜንት ስለሚኖር አታዳምጥ አልፈህ ሂድ ጌታ ካንተ ጋር አለ ተባረክ ደግሞ አገልግሎት ልዩ ልዩ ነው በመስጠት የሚያገለግሉ ደግሞ በማስተማር የሚያገለግሉ ደግሞ አሉ በአንተ በጣም ተጠቅመናል ተባረክ

  • @Kidest-ow3bw
    @Kidest-ow3bw Před 23 dny +2

    በርታልን

  • @behailuasgdom1101
    @behailuasgdom1101 Před měsícem +2

    መሰጠትን የመሰለ የሚያስደስት ነገር አለ ግን ???? ኖሮኝ ስሰጥ እንዴት ደስ እንደሚለኝ መፍትሔ ሆኖ መገኘት በእግዚአብሔር መመረጥ ነው

  • @user-mo6vs4sk3v
    @user-mo6vs4sk3v Před měsícem +5

    እኔ ስላልተመቸኝ ነዉ ከጥቅት ወራት ቦሀላ አግዛለዉ ስጅመር የጠየከዉ ብር አይባልም ተባረክ

    • @ewnetyasarfal
      @ewnetyasarfal  Před měsícem

      አመሰግናለው🙏 ተባረኪ🥰

  • @WizJanbo
    @WizJanbo Před měsícem +2

    ወንድሜ በርታልን

  • @saraaemedin1457
    @saraaemedin1457 Před 16 dny +2

    ወንድሜ በርታ በርታ ከጕንህ ነኝ

  • @meseretbekele9832
    @meseretbekele9832 Před 29 dny +2

    እግዚአብሔር ይባርክ ወንድም መሐመድ ላናግርክ ነበር ግን በቴሌግራም እንዴት ላናግርክ

  • @mesfinberise3977
    @mesfinberise3977 Před měsícem +1

    ወንድሜ እግዚአብሔር ባንተ እየሠራ ያለው ለማበረታታትና ከጎንህ በገንዘብ ሞቆም እንደኔ እንደ ትልቅ መልካም አጋጣሚ እንጂ እንደ ከባድ ሸክም የሚቆጥሩ የወንጌል እውነት አልገባቸውም እላለሁ። እኔ ቃል የሚገባው ከሰውነቴ ውጭ ያለውን ገንዘበን ብቻ አይሆን ዘመኔንና ሕይወቴንም ለመሠዋት ጭምር ቢሆንና ጌታየ ብቀበለኝ እንደት ያለ ታላቅ ክብር እንደሆነ ይሰማኛል እመኛለሁምም። ባደረገልኝምም

  • @merontefera8566
    @merontefera8566 Před měsícem +1

    አይዞህ እግዚአብሔር አምላክ ይረዳናል

  • @SerkalemAbebe-cd5qc
    @SerkalemAbebe-cd5qc Před 13 dny

    እግዚአብሔር አምላክ ይባርክህ

  • @abyssiniakitchen4217
    @abyssiniakitchen4217 Před 28 dny +2

    Tebarek wendeme enem lemageze desetegna negn ❤

  • @ethiopiantiktok2761
    @ethiopiantiktok2761 Před měsícem +1

    ነቢል ወንድማችን ነፍስህ በገነት ትረፍ

    • @ewnetyasarfal
      @ewnetyasarfal  Před měsícem +9

      አሜን። ግን በገነት ማረፉን ምድር ላይ ሆኖ ስላረጋገጠ የእኛ ምኞት አያስፈልገውም፣ ትክክለኛ አባባል አይደለም።🥰

    • @merontefera8566
      @merontefera8566 Před měsícem +1

      ገብቷል

    • @glorypicturesofficial
      @glorypicturesofficial Před měsícem

      ስለ ራስህ ብትጨነቅ ይሻልሃል ወንደማችን በምድር ላይ ሆኖ በገነት የምኖር ምርጥ የእግዚአብሔር ልጅነው። የአገልጋዮችን ልብ የምነካ አረመነያዊ ንግግር ባትናገሩ ጥሩ ነው።አመሰግናለሁ።

    • @alyayasenshewmolo3632
      @alyayasenshewmolo3632 Před 27 dny

      ​@@ewnetyasarfalትክክለኛ ሙስሊም ወይም ስለእስልምና ጠንቅ ቆ የሚያውቅ ሙስሊም በፉፁም ክርስትያን አይሆንም ለምን ብትል ኢየሱስ እኔን ሰይሆን እግዝሃቤርን ነው አምልኩ ያላው እኛ ሙስሊሞች የእያሱስን አምላክ አላህን ነው ምናመልካው ። ❤❤❤

  • @user-kq3oe5db5g
    @user-kq3oe5db5g Před 2 dny +1

    ሰል ምታቅርበው ብድዮ እናመሰግናልን❤❤❤❤❤❤

  • @AldaKassa
    @AldaKassa Před měsícem +3

    Tebarkhe

  • @user-ij2sd3sg9x
    @user-ij2sd3sg9x Před 11 dny

    አመስግናለው ❤

  • @kenaskids4126
    @kenaskids4126 Před měsícem +1

    God bless you!!!

  • @MarthaTegenewNigiru
    @MarthaTegenewNigiru Před měsícem

    እግዚአብሄር ይባርክህ ።
    እግዛብሄር ከአንተ ጋር ይሁን ።

  • @user-gl6oe3tw1l
    @user-gl6oe3tw1l Před 26 dny

    Teberek❤❤

  • @eteneshkassa2558
    @eteneshkassa2558 Před měsícem +2

    እግዚኣብሔር ስራ ይስጠኝ እኔ እረዳለው ያላቹ ስጡ እባካቹ

    • @ewnetyasarfal
      @ewnetyasarfal  Před měsícem

      አመሰግናለው። ተባረኪ!🙏🥰

  • @SagaleeLabsii
    @SagaleeLabsii Před měsícem

    Tebarek lemitseraw siraa

  • @user-tc2bm7ph7x
    @user-tc2bm7ph7x Před 9 dny

    አደሰንኝ ተምችቶኝል በረታ እንራደለን አካውንቶ የታለ

  • @user-wn2yq9qe8w
    @user-wn2yq9qe8w Před měsícem +1

    Egziabher yakbrligh MN libelk ke ewket manesm hone lela emnet teketay yehonu slemichlu adera bertaligh e wendme tsegah ybzaln🎉🎉

  • @Furious-ev5kn
    @Furious-ev5kn Před 25 dny

    I've always been thinking about someone translating David wood' , Nabeel' and also some debates from speakers corner involving BOB, your doing great job keep up the good work...….
    And also I think you should handle some comments in a smooth way...
    Colossians 3:8
    "But now you must put them all away: anger, wrath, malice, slander, and obscene talk from your mouth."

  • @Tylery-vu4kn
    @Tylery-vu4kn Před měsícem

    ❤❤❤❤❤❤❤

  • @EdenSamuel-ks7qf
    @EdenSamuel-ks7qf Před 13 dny

    Wendeme geta yibarkeh gen ene gena temari negn ena be genzeb ledegfeh balchelem etseliyilehalehu geta yirdah❤

    • @ewnetyasarfal
      @ewnetyasarfal  Před 13 dny

      አሜን!! እናንተ ከተማራችሁበትና ለጓደኞቻችሁ share ካደረጋችሁ በቂ ነው። ተባረኪ!!!

  • @melkamuyosef9509
    @melkamuyosef9509 Před měsícem +1

    Geta yiredegn wondime ye akimen eredalew berta❤❤❤

    • @ewnetyasarfal
      @ewnetyasarfal  Před měsícem

      አመሰግናለው🙏። ተባረክ🥰

  • @ETHIO-M1
    @ETHIO-M1 Před 29 dny +1

    🥰

  • @yacobkebede7052
    @yacobkebede7052 Před měsícem +3

    ሰርተሀል ስለዚ የሰራሰው መጠየቅመብላት ግድይለሀል ሳታገለግል አምጡ አላልክም እኔ ኦርቶዶክ ነኝ

  • @user-qn7mm4ls7r
    @user-qn7mm4ls7r Před měsícem +1

    እኔም ወንድሜአግዝካለው አንተ በርታ

    • @ewnetyasarfal
      @ewnetyasarfal  Před měsícem

      እሺ። አመስገናለው!🙏

    • @user-qn7mm4ls7r
      @user-qn7mm4ls7r Před měsícem

      @@ewnetyasarfal ቴሌግራም አልጠቀምምበምንድነው ልልክል ምችለው

    • @ewnetyasarfal
      @ewnetyasarfal  Před měsícem

      ቴሌግራም አውርደሽ በዛ ብታናግሪኝ ጥሩ ነው። የባንክ ቁጥር እዚህ ጋር መለጠፍ ስለማልችል ነው።

    • @user-qn7mm4ls7r
      @user-qn7mm4ls7r Před měsícem

      @@ewnetyasarfal ስልክ ቁጥር መላክ አትችልም በኢሞ አወራካለው ቴሌግራም በራሴ ምክንያት መጠቀም አልፈልግም

    • @ewnetyasarfal
      @ewnetyasarfal  Před měsícem +1

      ስልክ ቁጥር ከላኩማ ምን ቀረኝ😁
      ለማንኛውም ምላሰብሽ ብቻ ከልብ አመሰግናለው። ተባረኪ!!!!🙏

  • @danilee2569
    @danilee2569 Před měsícem +4

    1🎉

    • @ewnetyasarfal
      @ewnetyasarfal  Před měsícem +2

      ፍጥነት ጠላው😁🥰🥰 1ኛ🎉

    • @danilee2569
      @danilee2569 Před měsícem +2

      በርታ ወንድሜ ጌታ ካንተ ጋር ነው​@@ewnetyasarfal

    • @user-rj1go6zw6e
      @user-rj1go6zw6e Před měsícem

      ​@@ewnetyasarfalትክክል 👍ዋናው መረዳትህ ነው። ❤❤😂

  • @melakuwendimu9633
    @melakuwendimu9633 Před měsícem +1

    አካውንቱ የት አለ ?

    • @ewnetyasarfal
      @ewnetyasarfal  Před měsícem

      የቴሌግራም ሊንኩን ነክተህ አናግረኝ። አመሰግናለው!!!

  • @user-rj1go6zw6e
    @user-rj1go6zw6e Před měsícem +4

    ያ አስተያየቱን የሰጠው ሰው በፊጹም ክርስትያን ነው ብዬ አላስብም ከሆነም ይህ ሰው የታወቀ የክርስቶ ተቃዋም ሰው ይሆናል። ለምን ብኖረኝ ስለኢየሱስ የሚያወራው ያለኝን ሙሉ አልሰጥም 😭!ገንዘቡን የሚሰጠው ማን ነው!? እሱ አይደለም ወይ? bro አንተ ብቻ ለነዝያ እያልክ አግልግሎትህን እጅግ በጣም ኢጨመርክ ስለክርስቶስ አውራ!!መቸም ወንገል አሸናፊ ነው።የትኛውንም የአለም ቅራቅምቦ አትስማ። የሴማዩ የምድሩ አምላክ የአግልግሎት ዘመንህን ሁሉ ይባርክህ❤!ለክርስቶስ ያለህ ፍቅር መቸም አያቋርጥም ቀጥልበት!!❤❤🎉🎉

  • @user-is5np9bi7h
    @user-is5np9bi7h Před 25 dny

    አጋንንት ነው ቃል ጠቅሶ የቸርነት መንገድ የተቃወመክ ቢሆን ም አትፍራ ጌታ ካንተጋር ነው

  • @dabalohorro3448
    @dabalohorro3448 Před měsícem +2

    Berta wendime yezen sew video betechale mexen aqerbelen

  • @AmanuelGadisa-kv8pl
    @AmanuelGadisa-kv8pl Před 29 dny

    La Muslimoche eysus ysflgal😊tbarek bzu antbkalen kante more &more bzu sewoch alu gbzelan pls tabarek

  • @formula9034
    @formula9034 Před měsícem +1

    Lemin tisadebaleh ?

  • @trhaskafel6109
    @trhaskafel6109 Před 28 dny

    MLH ????? WENGEL MESBEK DEMO BETELEY LE MISLIM bcha bcha edu enji GENZEB mestet ke medan ga mnm aydelem ❤❤❤❤❤❤❤❤
    BCHA LE GETA TAMAN HUNU

  • @eteneshkassa2558
    @eteneshkassa2558 Před měsícem +1

    ለዛውም 5 ሺ ብር ነው ሁለት መቶ ይሮ ነው ነው በዶለር ነው አምስት ሺህ?

    • @biruktemesgen-ll1pe
      @biruktemesgen-ll1pe Před měsícem +1

      በኢቲዮጵያ 5000 ሺ ብር ነዉ❤

    • @Hope_chura
      @Hope_chura Před měsícem

      ኣንተ የሱዳን ዩሮ ነዉ እንዴ የምታዉቀዉ😂

  • @ishakibrahim3234
    @ishakibrahim3234 Před 29 dny

    ለማኝ ሼም የለህም ለምን tiktok ላይቭ አትገባም

  • @GaromaKenate
    @GaromaKenate Před 2 dny

    አር ተወዉ ባክ አሰናካይ በሞላበት ምድር ዉስጥ እንደምንኖር የታወቀ ነዉ !ምን አልባትም የግንዛበ እጥረትም ልሆን ይችላል //አግልግሎት ይቀጥላል

  • @freweynimebratu6870
    @freweynimebratu6870 Před měsícem

    Mayetachen , like maderegachen eco esu erasu eredata nw gene bethi dereja meteyeku shemoniu ok

    • @ewnetyasarfal
      @ewnetyasarfal  Před měsícem +1

      ምንም ሼም የለውም። ባይሆን ሼም ሊይዝህ የሚገባው አንተ ነህ። በስንት ጊዜ አንዴ ስትጠየቅ አትቆናቆን። በገንዘብህ አገልግል ነው የተባልከው። አንተ like እና share ባታደርግና ወደዚህ ቻናልም ዝር ባትል ደስ ይለኛል። ቢያንስ ከአንድ ቪድዮዬ ተጠቅመሃል ለሱ ብትከፍል ምናለበት። ሁለተኛ ወደዚህ ቻናል እንዳትመጣ block አድርጌ እንዳላሰናብትህ አርፈህ ተቀመጥ።

    • @user-rj1go6zw6e
      @user-rj1go6zw6e Před měsícem

      man eya ale lemin tayaleh man iya ale?? tew enji niketih iskemech new koy? lemin sile kiristos yemiyaworutin tikawomaleh kaltemecheh tew atiya! ❌degmo kiristian aydelehim bithon noro enem edegifahalew birr kelelegn betselot agizalehu bileh taskemitaleh!!😏❌❌❌

    • @user-di9hr9fv2x
      @user-di9hr9fv2x Před 23 dny

      ​@@ewnetyasarfal😳😳😳🙊🙊🙊

  • @dabalohorro3448
    @dabalohorro3448 Před měsícem +1

    Negative comments atey

  • @yasirmisganaw6833
    @yasirmisganaw6833 Před měsícem

    መልካም ፍቃድህ ከሆነ ላግዝህ እፈልጋለሁ በትርጉም ስራዎችህ በደንብ ትቀጥልበት ዘንድ ለግዜው የሀይማኖት ልዩነታችን ወደ ጎን እንበለውና

  • @user-zq5ko7oc7r
    @user-zq5ko7oc7r Před 27 dny

    awo. atlemin. dgmo. atsadebu. eyslk mehayem. eyalk tsasebalk. duma. nh

    • @ewnetyasarfal
      @ewnetyasarfal  Před 27 dny

      አመሰግናለው። እኔም መጠየቄን እቀጥላለው፣ እናንተም ፊታችሁ መጥቆሩንና ቀንድ ማብቀሉን ትቀጥላላችሁ።
      “መቶ ግርፋት በሰነፍ ጠልቆ ከሚገባ ይልቅ ተግሣጽ በአስተዋይ ሰው ጠልቆ ወደ ልቡ ይገባል።”
      - ምሳሌ 17፥10
      “ሰነፍን በሙቀጫ ውስጥ ከእህል ጋር በዘነዘና ብትወቅጠው፥ ስንፍናው ከእርሱ አይርቅም።”
      - ምሳሌ 27፥22

  • @rabiyaabudushur1273
    @rabiyaabudushur1273 Před 26 dny

    Enat bentwhs whsetamohs😜

  • @tsedekeyalew1825
    @tsedekeyalew1825 Před 27 dny

    Barta wndmchn igzhbhr yxbqih xru nger iysxkn nw

  • @user-md6ni8zn4j
    @user-md6ni8zn4j Před měsícem

    በተሃድሶ ድርጅት መልከም ሰራ ይሰራል እንዴ አንዴ ኮ ፀድቃችዋል ለዛ ነው
    ሰለ ት/ቱ ግን አናመሰግናለን ለጠቅላላ እውቀት ጥሩ ነው በጣም ጠቅሞኛል

    • @ewnetyasarfal
      @ewnetyasarfal  Před měsícem +3

      መንግስተ ሰማይ ለመግቢያ ጉቦ ካልሆነ አትሰጪም ማለት ነው? የተጠየቀው ትጸድቁ ዘንድ በሚል አይደለም። የተጠየቁት የጸደቁት ናቸው።
      እኔም ስለሰማሽና ስለተጠቀምሽ አመሰግናለው።

    • @user-rj1go6zw6e
      @user-rj1go6zw6e Před měsícem

      መጽሐፍቅዱስ አታነብም እሱ ነው ችግሩ። በክርስቶስ ጸድቀናል! አንተ በክርስቶስ ካልጸደክ ለምን አሁኑኑ የጽድቅ መንገዱን መፈለግ አለብህ እሺ bro! 😊

  • @Firew_Rahmet
    @Firew_Rahmet Před měsícem

    መሀይም😥😥😥 ወዮ😮😮

  • @user-xp7lc1me2u
    @user-xp7lc1me2u Před měsícem

    ehe saw ewunat kehona betam tesasetowal kehak mengad weda hushat,godana new yehedahu kkkkkkkkk kebrhan weda,chelama bicha alah weda tefetarabat emnat yimalsahu alah bekibr kemimalakbat weda chifara danse hushat yehushat tirikt hule wedamisabakbat bicha yesazinal alah yidraselat

    • @user-rj1go6zw6e
      @user-rj1go6zw6e Před měsícem +2

      እሱን ያዳነው ጌታ ለናንተም ይድረስ! የዘላለም ህይወት አግኝቷል። ምክንያቱም ህይወት ኤራሱ ክርስቶስ ነው። አንድ ነገር ማስታወስ ይገባችኋል ለምን ሰው ከክርስትና ወይንም ከሌላ ሀይማኖት ወደእስልምና መቶ አይመሰክርም ሙሐመድ እውነተኛ ነብይ ነው፣ በእስልምና ህይወት አለ፣ትክክለኛ ወዘተ እያለ?? አያችሁ ሰው እያዬ ወደብርሃን እንጂ ወደጨለማ መሄድ መቸም አይፈለግም። ክርስቶስ አይናችሁን ይክፈት። እንወዳቹኋለን ❤

    • @tesfasibatu-bj5mm
      @tesfasibatu-bj5mm Před měsícem

      ከእየሱስ ወደት ይከዳል እርሱ የዘላለም
      የህይወት ቃል አለዉ,ሙስልሞች አሁን ለግዘዉ ህዝቡን ለመያዝ እዉነተኛወን ጌታ ይሸፊኑታል እንጅ ገታ እየሱስ የወስዳቸዋል ከጨለማዉ አሰራር❤❤❤❤❤❤አንተም ጨምሮ,

  • @KeyredinMuhammedKeyredin
    @KeyredinMuhammedKeyredin Před měsícem

    ከሞት ረሱን የላደና እየሱስ አንተንም አየድንህምና ሞት ሰይቀድምህ ወደ አለህ ተመለስ። ሰው የሰቀለው የሰቀየው አምለክ? ወይጨለምተኝነት!! እኛ ምናመልከው አሏህ ከእንደዚህ አይነት ጎዶሎነት የጠረ ነው። ሰታዝን ምታደርገቸው ዱአዎች(ዝክሮች) ብዙ ነቸው። በንግጊሩ ብዙ ውሸቶች ተደምጣወል በአምስት አመቴ ቁርአንን በቀለ መየዝ ችዬ ነበር፣ቤተሰቦቼ የቁረይሽ ዘር ነቸው ሌላም

    • @ewnetyasarfal
      @ewnetyasarfal  Před měsícem +2

      ኢሳይያስ 53
      ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
      ¹ የሰማነውን ነገር ማን አምኖአል? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገልጦአል?
      ² በፊቱ እንደ ቡቃያ ከደረቅም መሬት እንደ ሥር አድጎአል፤ መልክና ውበት የለውም፥ ባየነውም ጊዜ እንወድደው ዘንድ ደም ግባት የለውም።
      ³ የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው፤ ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም።
      ⁴ በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው።
      ⁵ እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።
      ⁶ እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ።
      ⁷ ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም።
      ⁸ በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ፤ ስለ ሕዝቤ ኃጢአት ተመትቶ ከሕያዋን ምድር እንደ ተወገደ ከትውልዱ ማን አስተዋለ?
      ⁹ ከክፉዎችም ጋር መቃብሩን አደረጉ፥ ከባለጠጎችም ጋር በሞቱ፤ ሆኖም ግፍን አላደረገም ነበር፥ በአፉም ተንኮል አልተገኘበትም ነበር።
      ¹⁰ እግዚአብሔርም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።
      ¹¹ ከነፍሱ ድካም ብርሃን ያያል ደስም ይለዋል፤ ጻድቅ ባሪያዬም በእውቀቱ ብዙ ሰዎችን ያጸድቃል፥ ኃጢአታቸውን ይሸከማል።
      ¹² ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፥ ከኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል፤ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአልና፥ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአልና እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፥ ስለ ዓመፀኞችም ማለደ።

    • @user-rj1go6zw6e
      @user-rj1go6zw6e Před měsícem +1

      መቸም ድንቁርናችሁ እንደቀጠለ ነው 😂😂።ነገ አንተም መተህ ስትመሰክር ያንተን እስማለሁ! እንደአንተ ያሉ ናቸወ እውነቱ ስገባቸው የምመጡት። ኢየሱስ አይናችሁን ይክፈት ❤🎉

    • @tesfasibatu-bj5mm
      @tesfasibatu-bj5mm Před měsícem

      ሞቶ የተነሳ ከእየሱስ ዉጭ ማን አለ,ሞሀመድ ዋሽተዋል በእዉነት ጃነም ነዉ ያለዉ.እና አምልጥ ወንድሜ እየሱስ ያድናል ነፃ ያወጣሀል,

  • @ZeenahZeenah-zv8uq
    @ZeenahZeenah-zv8uq Před 28 dny

    ኢየሱስ አለይ ሰለም ነብይ ነዉ ጌታ አይደለም ሚበለ ሚጣጣ እንዴት ጌታ ይሆነል አይናቹ ተጨፍኖበቹወል እንጂ እዉነቱን ተቁተለቹ ሲጀመር ኢየሱስ አልሞታም አላህ ወደሰመይ አንስቶታል በቦታዉም ሌለን ሰዉ አመሰለለቸዉ ወይም እሱን የገደሉ መስሎወቸዉ ሌለዉን ገደሉ እስልምነን በደብ ሰትራደ ቁራንን ሰታቅ ከድክ አላህ አሁንም ወደ እስልምና ይመልስክ ኡሸት አትቅጣፉ ከእስልምነ ወታክ ምን አይነት ጨለመ ሂወትናዉ ምትኖራዉ አኡዝቢላህ

    • @mintemolla158
      @mintemolla158 Před 24 dny

      እሱ ሙሀመድ በቁርሀን ያለ አንዳች ምስክር የነገረህ ነገር ነው !! መርሳት የሌለብህ ኢየሱስ በምድር በነበረበት ወቅት ፍፁም ሰው ፍፁም አምላክ ነበር !! አንተም በሰውነቱ ያደረጋቸውን ነገሮች በመናገርህ አልተሳሳትክም ነገር ግን የመለኮት ባህሪዎችን አይተህ ሰምተህ ግን ባላየ ማለፍ በጣም ከባድ አጢያት ነው !!! አጢያትን ይቅር ሲል አምልኮ እና ስግደት ሲቀበል የዘለአለም ህይወትን ሲጥና ብዙ የመለኮት ባህሪዎችን መካድ መቅጠፍ ነው !!!

    • @mintemolla158
      @mintemolla158 Před 24 dny

      ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረበት ስዓት ፍፁም ሰው ፍፁም አምላክ ነበር !! አንተም በሰውነት ባህሪው የተናገረከው ነገር ልክ ነው ነገር ግን የመለኮት ባህሪውንም እንዲው መናገር አለብህ ለምሳሌ አጢያትን ይቅር ሲል አምልኮና ስግደት ሲቀበል የዘለአለም ህይወትን ሲሰጥ ....ወ ዘ ተ እነዚህን ነገሮች መካድ ደግሞ በጣም አጢያተኛ ያደርግሀል !!!

  • @henokkifle4533
    @henokkifle4533 Před měsícem

    እንዴ ሙልጭ አድርገህ እየተሳደብክ ነው እኮ ታውቆሃል ??

    • @ewnetyasarfal
      @ewnetyasarfal  Před měsícem

      ከተሳደብኩ ይቅርታ! የተሳደብኩ ግን አልመሰለኝም። ድርጊቱን የምገልጽበት ሌላ ቃል ስላጣሁ ነው። ሌባን ሌባ፣ ጠማማን ጠማማ፣ ጨለምተኛን ጨለምተኛ ማለት ስድብ አይመስለኝም። እንደዚህ አይነት ሰዎች የወንጌል እንቅፋት ናቸው። እንቅፋት የሚለው አሁን ስድብ አይደለም። ምክንያቱም እንደ እነሱ አስተያየት ቢሆን አገልግሎቴን አቁሜ ልቀር ነበር። ምክንያቱም ራሴን መቻል ስላለብኝና እንደ እነሱ አባባል መለመን ስለሌለብኝ። ባይሆን ላላደረኩት ስም በመስጠት ለማኝ ያሉኝ እነሱ ናቸው፣ ስለ እነሱስ ምን ትላለህ? ምን ትያለሽ?

  • @peac93
    @peac93 Před měsícem

    ውሸት እያቀረብክ ደሞ ብር ትጠይቃለህ ? ክርስትና እውነት ነው ማይመስል ነገር አታቅርብ ! በውሸት አማኙን አታታል!

    • @ewnetyasarfal
      @ewnetyasarfal  Před měsícem

      ማን ልበል?

    • @masara7252
      @masara7252 Před měsícem

      Ayezoshe galat 😂😂😂

    • @Hope_chura
      @Hope_chura Před měsícem +1

      የመሀመድ ስም ካልተጠራ ኣሆንላቹዉ መሀመድ በጀነት 72ሚስት ኣግብትዋል ኣሉ 😂

    • @ZeenahZeenah-zv8uq
      @ZeenahZeenah-zv8uq Před 28 dny

      @@Hope_chura አልሃምዱሊላህ ሙስሊም አድርገክ ስለፈጣርከኝ ወደፊትም ሙስሊም አድርገክ ግደለኝ የራቢ ጨለመ ለተገረደበት ሁሉ ከጨለመ አዉጣዉ አታ የወደድከዉን ብቻና ብቻነዉ እስለም ምታደርገዉ እኛ አልሃምዱሊላህ ግግም ብለን ወተት ጥቁር ነዉ አንልም በይሆን ወተት ነጭ እንደሆነዉ ምነምናዉ

    • @Hope_chura
      @Hope_chura Před 27 dny

      @@ZeenahZeenah-zv8uq 😂😂ሴት ነሽ በሴትነትሽ መከበረን የሌለበት ሃይማኖት ኣልሃድሊላህ ምናምን ትያለሽ እንዴ😂ጋሽ ማሜ ሴቶች እርሻ ናቸዉ እረሱዋቸዉ ብልዋል ይሄ ማረስ የማይደክመዉ ሰዉየ😂

  • @Firew_Rahmet
    @Firew_Rahmet Před měsícem

    ቆሻሻ😥😥😥 አይባልም