የዮሐንስ ወንጌል ክፍል 16 | የእግዚአብሔር ልጅ

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 22. 08. 2024
  • ታላቅነት ታላቁን ማወቅና ማሳወቅ ነው። ስኬት የተወለዱበትን ዓላማ አንጠፍጥፎ ፈጽሞ ማለፍ ነው። መጥምቁ ዮሐንስ በዚህ የታደለ ሰው ነበር። ቅዱስ ቃሉ "ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም … " እንዲል፣ ከመለኮት ውጪ ወልድን በሚገባ ያወቀ ሰው ቢኖር መጥምቁ ዮሐንስ ነበር። ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ዘላለማዊ ምሥጢር ነው። እግዚአብሔር ይህን ምሥጢር ለሰው ልጆች ብሎም ለፍጥረት ሁሉ ሊገልጠው ፈለገ። በዚህ የመገለጥና የመግለጥ ረድፍ ቀዳማይ ተሰላፊ መጥምቁ ዮሐንስ ነበር።
    ቀደም ሲል "የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ" ብሎ ያስተዋወቀንን ኢየሱስን ዝቅ ብሎ "የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ መስክሪያለሁ" በማለት የእግዚአብሄር በግ የሆነው፣ የእግዚአብሄር ልጅ መሆኑን ያረጋግጥልናል።
    በዘላለም ዘመናት ውስጥ ከአብ ጋር የመንፈስ ቅዱስ ተካፋይ የሆነው ወልድ በሥጋ ፍጹም ሰው ሆኖ፣ ወደ ምድር መጥቶ በዮሐንስ እጅ በዮርዳኖስ ወንዝ በውሃ ከተጠመቀ በኋላ ሰማያት ተከፍተው መንፈስ ቅዱስ በአካል ሲወርድበትና ሲያድርበት የምናየው በዚህ መልኩ ላመኑበት ሥጋ ለባሾች ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ የሚያጠምቅ እሱ መሆኑን ለማሳየት ነው። ባጭር ቃል መጥምቁ ዮሐንስ በውሃ ያጠመቀው ሰዎችን በመንፈስ ቅዱስ የሚያጠምቀውን መጥምቁ ኢየሱስን ነበር።

Komentáře • 52

  • @salameskyes7240
    @salameskyes7240 Před 11 měsíci

    አሜን መንፈሱን ይሙላብን ለመንኩ በኢየሱስ ስም❤🙌🙏

  • @Hassan-ry4ye
    @Hassan-ry4ye Před rokem

    ጌታ ይባርክህ ወንጌላዊ ያረድ

  • @sergutmengistu944
    @sergutmengistu944 Před rokem

    አሜንንን አሜንንን አሜንንን ጌታ ኢየሱስ አብዝቶ ይባርክህ ያሬዱ ተባረክልኝ 🙏🙏🙏

  • @habtamusium8646
    @habtamusium8646 Před rokem

    ጌታ አገልግሎትህን አብዝቶ ይባርክ

  • @habtamusium8646
    @habtamusium8646 Před rokem

    አሜን ! ገና ኢየሱስን ለማወቅ ክርስቲያኖች ትጋትን እንጨምር እንጂ አውቀነዋል ካልን ራሳችንን እናስታለን ፡፡ ቆላ ምዕ 2 ፡1-7

  • @meseretlata253
    @meseretlata253 Před rokem

    አሜን ❤

  • @tsegamuzollo1720
    @tsegamuzollo1720 Před rokem

    Geta Yebarekeh Wendeme W. Yared. Bruk Neh.

  • @jerusalemtermeer5982
    @jerusalemtermeer5982 Před rokem

    Hallelujah amen amen ❤❤❤❤❤❤❤God bless you our brother we love too🙏🏽🙏🏽🙏🏽🙏🏽

  • @gizawwoldemariam6605
    @gizawwoldemariam6605 Před rokem

    Thank you 🙏🏾. Bless you.

  • @segidbrhane2738
    @segidbrhane2738 Před 10 měsíci

    ከሁሉ የሚበልጠውን እውቀት ኢየሱስንን ለማወቅና ለመጨበጥ ሌላውን እውቀት ሁሉ እንደ ጉድፍ (እንደ እበት) እቆጥራለሁኝ

  • @mimitube270
    @mimitube270 Před rokem

    Ameeeeeeeeeen 🙏💖

  • @tigestermayse8641
    @tigestermayse8641 Před rokem +3

    Amen Amen Amen ✅ 🙌 👏🏻

  • @Jesus_is_love7777
    @Jesus_is_love7777 Před rokem

    የኢየሱስ መንፈስ❤የጌታዬ መንፈስ❤ የአምላኬ መንፈስ❤ የንጉሴ መንፈስ❤ ሙላኝ ተቆጣጠረኝ ኢየሱስን ግለጥልኝ❤ ኢየሱስን በህይወቴ እንዳከብረው አግዘኝ❤😭 እንደ ፍቃዱ ብቻ እንድኖር እርዳኝ😢😢 ድካሜን ስህተቴን ስንፍናዬ አልማስተዋሌን ይቅር በል አሜን❤😢😢❤❤❤❤!
    በጌታ የተወደድክ ወንጌላዊ ያሬድ የእግዚአብሄር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ይባርክህ ጸጋው አትረፍርፎ ይስጥህ ብዙ ነው ያስተማርክን ክብር ለእግዚአብሄር ይሁን🙏

  • @alemtshaygetachew3493

    ዘመንህ ይባረክ

  • @user-ld7wg2tq5b
    @user-ld7wg2tq5b Před rokem +1

    ወንድመ ያረዶ ጌታ እየሱስ አሁንም አብዝቶ ጸጋውን ያብዛልክ እየሱስን ማወቅ ይሁንልን አመን

  • @sahaynesh7692
    @sahaynesh7692 Před rokem +2

    አሜን

  • @manal-jc777
    @manal-jc777 Před rokem

    ጌታ ዘመንህን ይባርክ ፀጋ ይብዛልህ እረጅም ዘመን የአንተን ትምህርቶች በተለያየ መንገድ ተጠቅመናል አሁን ደግመህ ሰፊ በሆነ መንገድ ስለመጣህልን ደስ ብሎኛል በጥልቀት ያየኻቸውን እይታዋች እያሳየኸን ስለሆነ ደግሞም በዚህ ዘመን የሁሉ ነገር መጠቅለያ የሆነውን ኢየሱስን መዕከል ያደረገ ዕውቀት በጣም ያስፈልገናል አዋ ተመልሰን ስለ ኢየሱስ ሀ ብለን መማር አለብን እና እኔ ሀ ጀምሬአለሁ እናም በዚህ ሐሳብ እንድትበዛ እፀልያለሁ ተባርከሐል❤

  • @temesgentantu5977
    @temesgentantu5977 Před rokem

    just woowww.......geta yibarkihhh

  • @yodittaressa3186
    @yodittaressa3186 Před rokem

    Amenn Geta Yebarkh!!

  • @selamselamawit467
    @selamselamawit467 Před rokem

    ተባረከ ተባፘክ ።

  • @shimelisabate8953
    @shimelisabate8953 Před rokem

    ተባረክ

  • @meseretlata253
    @meseretlata253 Před rokem

    ድንቅ መላእክት ነዉ ተባረክ
    (ኢየሱስን ማውቅ ። እግዚአብሔር አሁንም ኢየሱስ ክርስቶስን ይጋለጣልን🥰🥰🥰🙏🙏

  • @endunahi4546
    @endunahi4546 Před rokem

    Marvelous!

  • @tigestermayse8641
    @tigestermayse8641 Před rokem +1

    God bless you 😘 Thanks so much 😘 ✅ 🤝🏽 Lorde Best ✅ 😘 🤝🏽 👌 👍🏻 🎉🎉🎉

  • @eleniwoldetsadik5890
    @eleniwoldetsadik5890 Před rokem

    God bless you it was Amazing !!!

  • @lidiyarashad3097
    @lidiyarashad3097 Před rokem +1

    ሀሌ ሉያ !! ጸጋ የበዛለት የእግዚአብሔር ሰው 🙏🔥♥️

  • @eyobelbuta9718
    @eyobelbuta9718 Před rokem

    God Bless u

  • @merongetu-fh3ec
    @merongetu-fh3ec Před rokem

    አስደናቂ ነው ያሬዶዬ ተባረክልን ሰላምህ

    • @merongetu-fh3ec
      @merongetu-fh3ec Před rokem

      ሰላምህ ይብዛ ደግሞም እናመሠግንሀለን ለዚ ጣፋጭ አጉአጊ ትምህርትህ ፡፡

  • @mekedesmezmur4057
    @mekedesmezmur4057 Před rokem

    ውንጌላዊ ያሬድ ግዜህን በትጋትና በታማኝነት ስጥተህ ስለ ምታገለግለን እግዚአብሔር ከነ ቤተስብህ ይባርክህ።
    "እየሱስ ክርስቶስን ማወቅ ማለት እግዚአብሔርን ማወቅ ማለት ነው " አሜን አሜን!!
    Thank you so much 🙏!!

  • @salsawisahle8569
    @salsawisahle8569 Před rokem

    አዎ !! ....ክርስቶስ ማወቅ ከዕውቀት ሁሉ ቁንጫ ነው። አሜን

  • @tigestermayse8641
    @tigestermayse8641 Před rokem +1

    Tabareke 🇪🇹 ❤

  • @biniamalemayehu4418
    @biniamalemayehu4418 Před rokem

    እንወድካለን ተባረክ ! ንፁ ወንጌል

  • @Sunem7
    @Sunem7 Před rokem

    አሜን ጌታ ሆይ ይበልጥ እናውቅህ ዘንድ እርዳን 🙏 Brother Yared you are so blessed ❤🙏

  • @segidbrhane2738
    @segidbrhane2738 Před 10 měsíci

    ኢየሱስን፡ስናውቅ የእግዚያንሄርን የዘለአለም፡ሚስጥር እናውቃለን!!! የእግዚያብሄር ሚስጥር አንድ ነው እሱም ኢየሱስ፡ነው!

  • @zivaasayhn30
    @zivaasayhn30 Před rokem

    תבורך

  • @Aki-rl2wz
    @Aki-rl2wz Před rokem

    I love every single of your teaching more grace Yared . ❤🙌🙌

  • @segidbrhane2738
    @segidbrhane2738 Před 10 měsíci

    ኢየሱስን ማወቅ የእውቀት አውራና ቁንጮ ነው!

  • @segidbrhane2738
    @segidbrhane2738 Před 10 měsíci

    ከሴት የተወለደ እንደ ዮሃንስ ታላቅ ነቢይ ፊተኛ ነቢ የተባለት፡ምክንያት ኢየሱስን በማወቅ በሚገባ በሙላት ስለኢየሱስ በመመስከሩ ነው። ምስክርነቱም አስገራሚና ትልቁ ምስክር ተብሎ ይታወቃል!!
    በቤተክርስቲያን ባለን ድርሻ ትልቁ ቁምነገር ትልቅ ነገር መስራት አይደለም፡ነገር ግን የተፈጠርንበትን የተሰራንበትን የተጠራንበትንን ምክንያት በሙላት መኖር ስንችል ነው!!

  • @segidbrhane2738
    @segidbrhane2738 Před 10 měsíci

    ቲዎፋኒ- የእግዚያብሄር መገለጥ ማለት ሲሆን

  • @segidbrhane2738
    @segidbrhane2738 Před 10 měsíci

    ዮሃንስ ያጠመቀውና ያስተዋወቀው መጥምቁን ኢየሱስን ነው- ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ የሚያጠምቕ እሱ ነው!!

  • @sergutmengistu944
    @sergutmengistu944 Před rokem

    እጅግ የተወደድህ ውድ ወንድሜ ያሬዱ እንዴት ነህ???

  • @biniamalemayehu4418
    @biniamalemayehu4418 Před rokem

    ደግሞ ሀገር ቤት በተመለስህ ጊዜ በገነት ቤተክርስትያን አማኑኤል ቶታል አጥቢያ ድንገት ሳልፍ የአንተ ምስል ያለበት የሦስት ቀን ኮንፍረስ በተዘጋጀ ጊዜ የእሮብ ቀን ጌታ እረድቶኝ ተካፈልኩ። በአካልም ለመጀመሪያ ጊዜ አየሁ፤ ደስ ብሎኛል።

  • @kindenehnadew9916
    @kindenehnadew9916 Před rokem

    ሰላም ላንተ ይሁን ወንድሜ ወንጌላዊ ያሬድ ስሜ ክንዴነህ ናደው ይባላል ጌታ ፈቅዶ ያንተን ትምህርት ሙሉ በሙሉ ማለት ይቻላል እየተከታተልኩ ነው አሁን የዩሐንስን ወንጌል ትምህርት ጨምሮ::
    ዛሬ ልጠይቅህ የፈለኩኝ እባክህ ይህ በእብራይስጡ: በግርኩ ፣እያልክ የምታጣቅሰው መድሀፍ አለ ወይስ ከምን ነው? እባክህ መጽሐፍ ካለ ይህንን መጽሐፍ በለኝና እገዛዋለሁ ካልሆነም ምንጩን ንገረኝና እኔም ልጠቀም አገልጋይ ስለሆንኩኝ ይበልጥ ለማወቅ ይረዳኛል
    ጌታ ይባርክህ የምወድህ ያንተው ተማሪ

  • @yttube143
    @yttube143 Před rokem

    ሰላም ላንተ ይሁን ወንድሜ ሁሌም መርሐግብርህን እከታተላለው ተባረክ ጌታ ዘመንህን ይባርክ። # አንድ ጥያቄ ነበረኝ ማብራርያ ፈልጌ ነው። መዝሙር 139:16 ላይ ያለውን ቃል ነው። ቃሉን የተረዳውት ስለ እኔ ቀድሞ በመጽሐፍ እንደተጻፈ ሲሆን ጅማሪዬም ሆነ ፍጻሜዬ እንደተጻፈ ነው። ስለዚህ እንደ ፊልም ጽሁፍ ተዋኞች ነን ማለት ነው??? መልስህን እጠብቃለሁ ተባረክ።

  • @segidbrhane2738
    @segidbrhane2738 Před 10 měsíci

    እናንተ አታውቁትም እኔም አላውቀውም ነበር ግን ሰማይ ተከፍቶ መንፈስ ቅዱስ ሲወርድበት የምታየውና የሚኖርበት እሱ ነው አለኝ። የእግዚያብሄር ፍቃድ መንፈሱ በሰው፡ውስጥ እንዲኖር፡ነው- ሰውን፡ማደሪያ መኖሪያ ማድረግ ነው!!!!

  • @ameleworkjemberehabte

    እንደምን ከረምክ እጅግ የተከበርክ ወንድም ያሬድ ።በትምህርቶችህ እጅግ እየተጠምኩ ነዉ በብዙ ተባረክ።አንድ ጥያቄ አለኝ በዮሐንስ ወንጌል ቁጥር 16 ትምህርት ላይ ዮሐንስ ከአብ ቀጥሎ ወልድን ያወቀ ሠዉ ነዉ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት አልክ እና ጥያቄ ጫረብኝ እየሱስ ክርስቶስ ከአብ ጋር ወደዚህ ምድር ሠው ሆኖ ከመምጣቱ በፊት ከአብ ጋር አልነበር እነዴ? በአብ በዘላለም አቀዱ ማለት በዘመን ፍጻሜ በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል የሚለዉን ሀሳብ ጋር ብትችል ብታብራራልኝ ደስ ይለኛል ተባረክ።

  • @fevenyemane2346
    @fevenyemane2346 Před 11 měsíci

    ወንድሜ ያሬድ እድሜህ ይርዘም አንድ ጥያቄ አለኝ መንፍስ ቅዱስን መሞላታችንን እንዴት እናውቃለን ?

  • @habtamusium8646
    @habtamusium8646 Před rokem

    ወንድሜ ያሬድ መጥመቁ ዩሀንስ ኤልያስ አይደለሁም ያለበት ምክንያት ራሱን ዝቅ ዝቅ ላማድረግ ይሆንን ? ኤልያስ ነኝ ካላቸው በትንቢት ሲጠባበቁት ስለነበር የተለየ ከበሬታን እንዳይሰጡት ምናልባት ይሆን ብዬ ነው ፡፡ ተባረክ !

  • @milliongelan3490
    @milliongelan3490 Před rokem

    ተባረክ