ታላቁ ተጋድሎ ፩ኛ ትምህርት፡ ከጦርነቶች ሁሉ ጀርባ ያለው ጦርነት

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 29. 08. 2024
  • የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት ዐበይት ጭብጥ ምንድን ነው?” ተብለው ቢጠየቁ መልስዎ ምን ይሆናል?
    የሱስ?
    የደኅንነት እቅድ?
    መስቀሉ?
    ሦስቱም በትክክል መልስ መሆን ይችላሉ።
    ሆኖም እነዚህ ሦስት ወሳኝ ርዕሰ ጉዳዮች ሁሉን አቀፍ በሆነ አንድ ሀሳብ ይበልጥ ተገልፀው እናገኛቸዋለን ።
    ይህ ሀሳብ(ጭብጥ) ከዘፍጥረት አንስቶ እስከ ራእይ ባሉት የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክቶች በስፋት ናኝቷል፤ ከጦርነቶች ሁሉ ጀርባ፥ ከክፋቶች ሁሉ ኋላ ያለ ታላቅ ጦርነት--ታላቅ ተጋድሎ !
    ይህ ጦርነት የተጀመረው በሰማይ እንደሆነ መፅሀፍ ቅዱሳችን ይነግረናል::
     ከዚያ ጉዳዩ ወደ ምድር ቀጠለ
     በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠሩ
     በነጻነት የመወሰን ሙሉ ፈቃድ የነበራቸው ፍጡራን የዚህ ክፋት ተሳታፊዎች ሆኑ።
    ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
    ሰማይን በመሰለ ቅዱስና ንጹሕ ቦታ እንዴት ጦርነት ሊነሳ ቻለ? (ራዕይ 12፡7)
     የዚህ ጦርነት መሪ ተዋናዮች እነማን ናቸው? (ራዕይ 12፡7)
    የዚህ ጦርነት አካል አለመሆን እንችላለን?
     ስለ ሉሲፈር ዓመጽ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? (ሕዝቅኤል 28፡12-15፤ ኢሳይያስ 14፡12-14)?
    የሉሲፈር የጦር ስትራቴጂ ምንድነው? (ዮሐንስ 8፡44፤ ራዕይ 12፡4፣9)
    እግዚአብሔር ሁሉን ማድረግ የሚችል አምላክ ነው፤ ሰይጣንም ሆነ የእርሱ ተባባሪ አጋንንቶች ከኃያሉ አምላክ ጋር በምንም ሊወዳደሩ አይችሉም፤ ይህ ከሆነ ታዲያ እግዚአብሔር ለምንድነው የኃይል እርምጃ ያልወሰደባቸው? (ዮሐንስ 3፡16፤ 1ኛ ዮሐንስ 4፡8)
     ፍቅር የምርጫ ነጻነትን ሁልጊዜ ያከብራል፤ በፍቅር ውስጥ ግዴታ የለም፤ ግን ለዚህ ጦርነት የፍቅር መንገድ አዋጪ ነው? (ዘፍጥረት 2፡15-17፤ ዘጸአት 32፡26፤ ኢያሱ 24፡15፤ 1ኛ ነገሥት 18፡20-21)
     ስለዚህ ውዝግብ ማወቅ ለግል ሕይወቴ ምን ይጠቅመኛል?
    እነዚህና መሠል ተያያዥ ሀሳቦች ከመፅሀፍ ቅዱስ አንፃር በጥልቀት የተዳሰሱበትን የመፅሀፍ ቅዱስ ጥናት እንድትመለከቱ ለሌሎችም እንድታጋሩ እንጋብዛችኋለን !
    #greatcontroversy #biblestudy #amharicbibleteaching #amharicbiblestudy #hopechannelethiopia
    #sabbathlesson

Komentáře • 2

  • @muluneshashro4316
    @muluneshashro4316 Před 2 měsíci

    አሜን እግዚአብሔር ይባርካችሁ🙏

  • @giziew
    @giziew  Před měsícem

    ለ1ኛው ትምህርት እንዲረዳ የተዘጋጀው ይህ አንድ ገፅ የጥናት መምሪያ ትምህርቱን በግል ለማጥናትም ሆነ በቡድን ለመወያየት እንዲሁም ለማስጠናት የሚጠቅም ነው። የጥናት መምሪያው እዚህ ሊንክ ላይ ይገኛል፡ t.me/giziew7/112