ተለቀቀ || የጽድቅ ልብሴ..U/A/F/G/C New Gospel song yetsidk libse 2024/2016 || ሰርዴስ Worship New Mezmur

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 22. 08. 2024
  • የተለያዩ መንፈሳዊ ዝማሬዎች በሚለቀቁበት ጊዜ ወዲያውኑ እንዲደርስዎ ቻናሉን ሰብስክራይብ እንዲሁም የደውል ምልክቷን ይጫኑ
    እንደሚታረድ በግ እንደሞኝ ዝም ያልከው
    ሲሳለቁብህም አፍህን ያልከፈትከው
    የደም ላብ ያላበህ ሁሉን የታገስከው
    ከህመምህ ይልቅ ፍቅር በልጦብህ ነው../2*/
    ደምግባት ያጣኸው
    የህማም ሰው ሆነህ ደዌንም ያወከው
    ክብርህን የተውከው
    ያለበደል ኃጢአት የሆንከው
    ለእኔ ነው........./3*/
    የተዋረድከው
    ከሰው ተራ ወጥተህ ራስህን ባዶ አድርገህ
    አይተው እንዳይወዱህ የባሪያ መልክ ያለህ
    ሆነህ ሕይወት ሰጠሀት ለአንዲቱዋ ነፍሴ
    አብ ፊት መታያዬ አንተ የጽድቅ ልብሴ../2*/
    ደምግባት ያጣኸው
    የህማም ሰው ሆነህ ደዌንም ያወከው
    ክብርህን የተውከው
    ያለበደል ኃጢአት የሆንከው
    ለእኔ ነው........./3*/
    የተዋረድከው
    በእኔ ቦታ አንተ ሆነህልኝ
    መርገሜን ከእኔ አርቀህልኝ
    ይኸው ዛሬ ላንተ... ዘምራለሁ
    ማዳንህን ዘወትር...አወራለሁ
    በፊትህም ነፍሴን...አፈሳለሁ
    ለዘላለም ስምህን...እባርካለሁ
    ክበር ክበር እልሀለሁ../2*/
    ንገስ ንገስ እልሀለሁ../2*/

Komentáře • 85